ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
ባለፈው ሚያዝያ 2 መቅረብ የነበረበትና ታዳሚዎች በሥፍራው ከተገኙ በኋላ የተቋረጠው “ግጥም በጃዝ” በመጪው ረቡዕ እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀን ልናቀርብ ከተዘጋጀን በኋላ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተቆጣጣሪ አካል ፈቃድ የላቸውም በማለቱ ስለሌላቸው አያቀርቡም በሚል ለራስ ሆቴል ዝግጅቱ መቋረጡን ተናግረዋል፡፡ ረቡዕ…
Rate this item
(1 Vote)
አርቲስት ፍቃዱ አያሌው ባጋጠመው የነርቭ ህመም ወደ ታይላንድ ባንኮክ ሄዶ ህይወቱን የሚታደግ ህክምና እንዲያገኝ በህክምና ባለሙያዎች ተወሰነ፡፡ የሰዓሊው ጓደኖችና ወዳጅ ዘመዶች በውጭ አገር በሚያደርገው ህክምና ጥሪ ለማሰባሰብ እያስተባበሩ ናቸው፡፡ ሰዓሊ ፍቃዱ የነርቭ ህመሙ ለመታከም አዲስ አበባ ለሚገኘው የሚዮንግ ሰንግ ሆስፒታል…
Rate this item
(9 votes)
የኢትዮጵያ የዜማ አባት የሚባለው ቅዱስ ያሬድ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተዘከረ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስትያን፤ የዜማ አባቱ የተወለደበትን 1500ኛ የልደት በዓል ነገ ከረፋዱ አራት ሰዓት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አዲሱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ…
Rate this item
(0 votes)
በሻሸመኔ ከተማ ጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው ከ “አድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር 42ኛ ዝግጅቱን ነገ ከሰዓት በኋላ በከተማዋ ሁለገብ አዳራሽ እንደሚያቀርብ ገለፀ፡፡ በዚህ ጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ልምዳቸውን ለታዳሚዎች እንደሚያካፍሉ ማህበሩ አስታውቋል፡፡
Rate this item
(2 votes)
በጋዜጠኛና ደራሲ በኃይሉ ገብረእግዚአብሔር የተፃፈው “ኑሮና ፖለቲካ” የወጎች መጽሐፍ ሁለተኛ ቅጽ ለንባብ በቃ፡፡ አርባ ወጎችን የያዘው መፅሃፉ፤160 ገፆች ያሉት ሲሆን ለአገር ውስጥ 35 ብር፣ ለውጭ አገራት 15 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ በርካታ ወጎች የተካተቱበት የመጀመርያው ቅጽ አምና በታሕሳስ ወር መውጣቱ ይታወሳል፡፡
Rate this item
(5 votes)
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተለያዩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙርያ መጣጥፎች የሚያቀርብበት “የዳንኤል ዕይታዎች” የጡመራ መድረክ (Blog) የተመሠረተበት ሶስተኛ አመት ሚያዚያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄድ ፕሮግራም እንደሚከበር ተገለፀ፡፡ በዕለቱ በሚካሄደው…