የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የታላቁን የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላን ህልፈተ ህይወት በማስመልከት ባወጣው መግለጫ፤ የማንዴላን የነፃነት ትግል እንዲሁም የሰብአዊነትና ዴሞክራሲያዊ መርሆዎች ለፍትሀዊ የትግል ስልት አጋዥ መርህ አድርጐ እንደሚጠቀምባቸው ገለፀ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ፤ በሰላማዊ ትግል አፓርታይድን ታግሎ በማሸነፍ በዘር ከፋፍሎ ሲገዛቸው የነበረውን ሥርዓት አስወግዶ፣ የጥቁር መሪ ፋና ወጊ በመሆን አለምን ማስደመሙንና ህልፈቱም እንዳሳዘነው ፓርቲው በአፅንኦት ገልጿል፡፡

“የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግልና ተጋድሎ ሲታሰብ፤ ከኔልሰን ማንዴላ የህይወት ታሪክ ተለይቶ የሚታይ አይደለም” ያለው ኢዴፓ መግለጫ፤ ታላቁ መሪ ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ የሰላም፣ የአንድነትና የመቻቻል ፖለቲካን የመሰረተ ከመሆኑም በተጨማሪ ጥቁርና ነጭን ያስተሳሰረ ፓርቲና መንግስት በመመስረት፣ አለምን ያስደመመ ታላቅ ታጋይ እንደነበረ አውስቶ፤ በውሻና በአውሬ እያሳደደ በጥይት ይገድላቸው የነበረውን ዘረኛ መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመግታት ብቀላን ያቆመ፣ በአፍሪካ የእርቅ፣ የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህልን የመሰረተ ታላቅ መሪ ነው ሲል ፓርቲው አሞካሽቷል፡፡

ማንዴላ ከነፃነትም በኋላ የተከተላቸው የዴሞክራሲ ምስረታ ሂደቶችና የዜጐች መብት አከባበር መርህ፤ በአለም ላይ ለሚኖሩ መሪዎችና ባለስልጣናት ትልቅ አስተማሪ መሆኑን የገለፀው ኢዴፓ፤ ህዝብን በግድ በመግዛት ሀገር ማስተዳደር የማይቻል መሆኑንም በግልፅ አሳይቷል ብሏል፤ በመግለጫው፡፡ በሚከተላቸው የነፃነት የትግል ጐዳናዎች፣ የማንዴላን የመቻቻል፣ የይቅር ባይነት እና የፅናት መርሆዎች፤ የትግል አጋዥ መርህ አድርጐ እንደሚጠቀምባቸው የጠቆመው ኢዴፓ፤ በኔልሰን ማንዴላ ህልፈተ - ህይወት በጥልቅ ማዘኑን ገልፆ፤ ለመላው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

Published in ዜና
  • ሶስት የኮንስትራክሽን ባለሃብቶችን ጨምሮ 6 ባለሃብቶች ይከሰሳሉ

ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ በሙስና ተጠርጥረው ከሌሎች ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ጋር በቁጥጥር ስር በዋሉትና፣ በሶስት መዝገቦች ክስ በተመሰረተባቸው፣ በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መልስ እየተጠበቀ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ስድስት ከፍተኛ ባለሀብቶች ክስ እንደሚመሰረትባቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡

የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት፤ ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ አቶ መላኩ በሚኒስትር ማዕረግ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል መሆናቸውን ተከትሎ፣ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የየትኛው ፍ/ቤት ነው በሚለው ላይ የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት፣ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ስር ላለው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ትእዛዝ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ከፍ/ቤቱ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ ህዳር 23 ቀን 2006 በመሰብሰብ ጉዳዩን የተመለከተው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ፤የደረሰበትን ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረቡን ለፍ/ቤቱ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ በዚህም መሰረት ከትላንት በስቲያ የዋለው ችሎት፤ አጣሪ ጉባኤው የደረሰበትን ውሳኔ በመመርመር፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህገመንግስቱ አንቀፅ 83፣ ምክር ቤቱ በ30 ቀን ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት የሚለውን በማስታወስ፤ በእስር ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ሁኔታ ከግምት በማስገባት በቀጣይ ቀጠሮ ምላሹን ያሳውቅ ብሏል፡፡ መዝገቡንም ለታህሳስ 22 ቀን 2006 ቀጥሯል፡፡

በተያያዘ ዜና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሶስት ባለሃብቶችን ጨምሮ፣ ከጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ 6 ባለሃብቶች እንደሚከሰሱ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ለህንፃ ግንባታ የሚውል የኮንስትራክሽን ቁሳቁስ ከውጭ አገር እንዲያስገቡ አስፈቅደዋል የተባሉት ባለ ሃብቶች፤ ከቀረጥ ነፃ ያስገቡትን ቁሳቁስ ለሌላ ሰው በመሸጥ፣ አላግባብ ጥቅም አግኝተዋል ተብለው እንደሚከሰሱ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ከጉምሩክ ሃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ያለ ሙሉ የቀረጥ ክፍያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገብተዋል ከሚለው ሁለተኛ ክስ በተጨማሪ፣ የሌሎች ባለ ሃብቶችን ጉዳይ በማስፈፀም ጥቅም ለማግኘት ከባለስልጣናት ጋር ተደራድረዋል የሚል ክስ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡ ካሁን ቀደም በሙስና ወንጀል የተከሰሱና ክስ የተቋረጠላቸው ሰዎች በምስክርነት እንደሚቀርቡም እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Published in ዜና

በቢሾፍቱ ከተማ ቢሾፍቱ ሀይቅ ዳርቻ ላይ የተገነባው “ፒራሚድ” ሆቴልና ሪዞርት ዛሬ ይመረቃል፡፡ 85 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሪዞርቱ፤ ለግንባታ አምስት አመታትን የወሰደ ሲሆን ደረጃቸውን የጠበቁና ምቹ የመኝታ ክፍሎች፣ የህፃናት መጫወቻ፣ ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሾች፣ ስፓ፣ ባርና ሬስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳ እና ላውንጅ እንዳሉት ታውቋል፡፡ ለ200 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል የተባለው ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት፤ ከፍተኛ የመንግስት ባስልጣናት፣ ባለሀብቶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ተመርቆ ስራ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞርት በቢሾፍቱ መሀል ከተማ ፒራሚድ የተሰኘ እህት ሆቴል አለውም ተብሏል፡፡

Published in ዜና

• “ታክሲዎች ወደ ውስጥ የማይገቡት አቤቱታ ስለበዛ ነው”

• ከሳውዲ ተመላሾች በታክሲ ላይ ስርቆት ተቸግረዋል ተባለ

ወደ አሮጌው ጉምሩክ እየገቡ ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎችን ሲያስተናግዱ የነበሩ ሚኒባስ ታክሲዎች፤ ከስደት ተመላሾች ባቀረቡት አቤቱታ ወደ ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸው ተገለፀ፡፡ ሚኒባሶቹ ኤርፖርትም ሆነ የድሮው ጉምሩክ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የገለፁት የጉምሩክ ፖሊሶች፤ አንዳንድ የሳኡዲ ተመላሾች በታክሲዎች በሚፈፀሙ ስርቆቶች እንደተቸገሩ አቤቱታ በማቅረባቸው፣ መንግስት የመደባቸው ኮድ 3 ሚኒባሶች ብቻ ገብተው እንዲጭኑ መወሰኑንና ሚኒባስ ታክሲዎቹ ውጭ ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ “ከኤርፖርት አውቶቢስ ተራ” የሚል ታፔላ የለጠፈው የታክሲ ሹፌሩ ዳንኤል ይፍሩ፤ ስራቸውን የሚሰሩት በማህበር ተደራጅተውና በታፔላ በመሆኑ ሌቦችን ለመቆጣጠር አመቺ እንደሆነ ገልፆ፤ ብቻ “ሁሉንም ገብታችሁ አትጫኑ” ተብሎ መከልከሉ ተገቢ እንዳልሆነና ተመላሾችን ለከፋ እንዳሉት የሚያጋልጥ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ሌላው የዚሁ መስመር ሹፌር አድማሱ ሰጠኝ በበኩሉ፤ ከሶስት ቀን በፊት ተሳፋሪ ረስታ የወረደችውን ሻንጣ ለማህበሩ በማስረከብ ለባለቤቷ መሰጠቱን አስታውሶ፤ ከዚህ በፊትም እቃ ጥላ የወረደች የሳኡዲ ተመላሽ ለተቆጣጣሪ የማህበር አባላት ተናግራ፣ በተሳፈረችበት ሰዓት መሰረት ዕቃዋ ተገኝቷል ብሏል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ስራችን በህጉ መሰረት የሚከናወን በመሆኑ ነው ያለው አድማሱ፤ እንደውም ከግቢው ውጪ የሚጭኑ ታክሲዎች ሌብነትን ያስፋፋሉ ብሏል፡፡ ከሳውዲ የተመለሱ ዜጎች በበኩላቸው፤ ታክሲዎች ወደ ውስጥ ባለመግባታቸው ለተጨማሪ ወጪና እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

Published in ዜና

“ወሬኛም ያውራ ሃሜት ይደርድር
እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር
ሊያፈርስ አስቦ የሸረበውን
ተክቦ ሆኗል የሚያገኘው…”

ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!)
ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡
እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡   እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)  
እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ  በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!)
እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም - “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…)
እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!)
እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ - ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ - “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም  የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!)  በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡

ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!

ኤልያስ

ሌሎች ባጨሱት ከ600ሺ በላይ ሰዎች በየዓመቱ ይሞታሉ
በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ አጫሾች አሉ
ኢትዮጵያ ሲጋራ ማጨስን በተመለከተ አዲስ አዋጅ ልታፀድቅ ነው

በዓለማችን ከሲጋራ ማጨስ ጋር በተያያዘ በየዕለቱ 13 ሺህ ሰዎች እንደሚሞቱ አንድ መረጃ ይፋ አደረገ፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ ያደረገው ይኸው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በዓለም ላይ 1.3 ቢሊዮን የሚሆኑ ሲጋራ አጫሾች የሚገኙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላዩ የዓለም ህዝብ ብዛት 1/5ኛው ማለት ነው፡፡
በመላው ዓለም ላይ በትምባሆ ምክንያት በየዓመቱ 6 ሚሊዮን ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህም ማለት በየስድስት ሰከንዱ አንድ ሰው በትምባሆ ሣቢያ ህይወቱን ያጣል ማለት ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የሚሞቱት ሲጋራን በቀጥታ በማጨሳቸው ሣቢያ ሲሆን 600ሺ የሚሆኑት ደግሞ ትምባሆን በቀጥታ የማያጨሱ ነገር ግን በሁለተኛ ወገን አጫሽነት (Second hand smoking) ምክንያት የሚሞቱ መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 ዓ.ም የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ባለስልጣን መ/ቤቱ ይፋ ያደረገው መረጃ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ አጫሾች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የሴት አጫሾች ቁጥር ከ1 በመቶ አይበልጥም፡፡
ሰሞኑን በግዮን ሆቴል በተካሄደ አውደ ጥናት ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ እንደተናገሩት፤ ሲጋራ ማጨስ አንድ ሰው በህይወት ከሚቆይበት ጊዜ ከ10 ዓመት የበለጠ ዕድሜ ሊቀንስበት ይችላል፡፡ በዓለማችን ከሚከሰቱ 10 የአዋቂ ሰዎች ሞት መካከል አንዱ ከሲጋራ ማጨስ ጋር በተያያዙ ችግሮች የሚከሰቱ እንደሆኑ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በአገራችንም ከሲጋራ ማጨስ ጋር በተያያዙ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች እየጨመሩ መጥተዋል ብለዋል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ፤ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የአጫሽ ቁጥር ያላት አገር መሆኗን አመልክቶ የአጫሽ ዜጐቿ ቁጥር ግን የመጨመር አዝማሚያ ይታይበታል ብሏል፡፡
በዓለማችን እጅግ በርካታ ሰዎች የሚያጨሱባት አገር ቻይና መሆኗን ያመላከተው መረጃው፤ 1.3 ቢሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ ወደ 550 ሚሊዮን የሚጠጋው ከሲጋራ ጢስ ጋር ለተያያዙ የጤና ችግሮች ተጋላጭ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
“ያለፈቃዳቸው እንዲያጨሱ” በመገደዳቸው ምክንያት በየዓመቱ ህይወታቸውን ከሚያጡት 600ሺ የዓለም ህዝቦች መካከል አብዛኛዎቹ ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ አጫሾች ሲጋራ በሚያጨሱበት ወቅት ከሣንባቸው የሚወጣውን ወይንም በቀጥታ ከሲጋራው የሚለቀቀውን ጢስ እንዲቀበሉት ወይንም እንዲተነፍሱት ይገደዳሉ፡፡ ይህም በአጫሹ ቤተሰቦች ላይ ጉዳቱ እንዲጐላ ያደርገዋል ይላል-መረጃው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት የተለያዩ ጥናቶችን ዋቢ አድርጐ እንደገለፀው፤ ሲጋራ በሚጨስበት አካባቢ ያሉ ሰዎች ከዋናው አጫሽ በአማካይ ከ15-30% የሚሆነውን ድርሻ ወደ ሣንባቸው ያስገባሉ፡፡
ይህንን በቀላሉ ለማስረዳትም በአካባቢያችን ከተጨሱ 10 ሲጋራዎች መካከል አንድ ተኩል የሚሆነውን ያለፍላጐታችን እንድናጤስ እንገደዳለን ማለት ነው፡፡ ከ85% በላይ የሚሆነው የሲጋራ ጢስ ለዓይን በማይታይና ምንም አይነት ሽታ በሌለው ጋዝ መልክ ወደ ሣንባችን የሚገባ ሲሆን ጢሱ ካርቦንሞኖክሳይድና ሃይድሮጂን ሲያናይድን የመሳሰሉ መርዛማ ጋዞችን ይይዛል፡፡
ሌሎች ሰዎች ያጨሱትን ሲጋራ ወደ ሣንባቸው በማስገባታቸው ሣቢያ ለጉዳት የሚዳረጉ ሁለተኛ ወገን አጫሾች ለሣንባ ካንሰር፣ ለልብ ህመም፣ ለአስም በሽታ፣ ለማስታወስና የመረዳት ችሎታ መቀነስ፣ የፅንስ ማስወረድና ደካማ ለሆነ የደም ዝውውር እንደሚጋለጡም ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።
ሲጋራ ማጨስ በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚያስከትለው የጤና ችግር እጅግ የከፋ መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ጢሱ በፅንሱ ላይ እጅግ የከፋ የጤና ችግር ከማስከተሉም በላይ ዝቀተኛ ክብደት እንዲኖረውና ፅንሱ ያለጊዜው እንዲወለድ ሊያደርገውም እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ ለማርገዝ የሚፈልጉ ሴቶች ሲጋራ ማጨሳቸውን ወይንም ለሁለተኛ አጫሽነት የመጋለጥ ዕድላቸውን በእጅጉ ሊቀንሱ ወይንም ሊያስቀሩ ይገባል ያለው ሪፖርቱ፤ የሲጋራው ጢስ የማርገዝ ብቃታቸውን ሊቀንሰው አሊያም ሊያስቀረው ይችላል ብሏል፡፡
በግዮን ሆቴል በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት ዶ/ር አበባየሁ አሰፋ እንደገለፁት፤ በሲጋራ ማጨስ ሣቢያ የሚከሰተውን የጤና ችግርና እየጨመረ የሄደውን የአጫሾች ሞት ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ጥረት አጋዥ የሆነ 38 አንቀፆች ያሉት ስምምነት በ177 አገራት መፈረሙን ዶክተሩ ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ካልፈረሙ ስድስት የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ገልፀዋል፡፡ በሲጋራ ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሣደግና ለማስተማር የሚያስችሉ አዳዲስ ደንቦችና መመሪያዎች ለማፅደቅ በሂደት ላይ እንደሆነችም ተናግረዋል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያፀድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ መመሪያና ደንብ፤ ህዝብ በተሰበሰበባቸው ሥፍራዎች፣ በሆስፒታሎች፣ በአውቶቡሶችና የህዝብ ማጓጓዣ ትራንስፖርቶች ላይ ሲጋራ ማጨስን የሚከለክል ሲሆን በሆቴሎችና በመዝናኛ ሥፍራዎች ሲጋራ ለማጨስ የሚያስችሉ የተከለሉ ሥፍራዎች የማዘጋጀት ግዴታም የሚጥል እንደሆነ ታውቋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ከበደ ወርቁ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን በቅርቡ አፅድቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በሲጋራ ማጨስ ሣቢያ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል ዋነኞቹ የልብ ህመም፣ የደም ግፊት መጨመር፣ ካንሰር፣ የአይን ሞራ ግርዶሽ፣ የጥርስ መበስበስ፣ የቆዳ መጨማደድ፣ የጨጓራ ቁስለት፣ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ፣ የመሥራት አቅም መዳከም እና የራስ ፀጉር መመለጥ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ከሲጋራ አጫሾች ጋር አብረው በመኖር ወይንም ሲጋራ በብዛት በሚጨስባቸው አካባቢዎች ላይ በመሆን የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ደግሞ የመተንፈሻ አካላት ህመም፣ ለደም መርጋት ችግሮች መጋለጥ፣ በሣንባ ካንሰር መያዝ፣ አስም፣ የዓይን የማየት ችሎታ መዳከም የልብ ህመምና የማስታወስ ብቃት መቀነስ ችግሮች ተዘውትረው መታየታቸውን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
በሲጋራ ማጨስ ሣቢያ የሚከሰቱትን የጤና ችግሮች ለማስወገድ አገሮች እንደየአገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ ህጐችንና መመሪያዎችን እያወጡ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የዓለም አገራት መካከል ጥቂቶቹን መጥቀስ ቢያስፈልግ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እንግሊዝና ሆላንድ ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ሥፍራዎች፣ በባቡር ጣቢያዎች፣ በአውቶቡስ መጠበቂያ ሥፍራዎች፣ በሲኒማና ቲያትር አዳራሾች፣ በሆስፒታሎችና በሕክምና ተቋማት እንዲሁም የተከለለ የሲጋራ ማጨሻ ሥፍራ በሌለባቸው ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ሲጋራ ማጨስ በህግ እንዲያስቀጣ ደንግገዋል። ይህንን መሰል ህጐች ህዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ እንዳይጨስ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም በየመኖሪያ ቤቱና በየመንገዱ ላይ ሲጋራ በማጨስ በሁለተኛ ወገን አጫሽነት የሚቆጠሩ ዜጐችን በሲጋራ ሣቢያ ከሚመጣ ችግር ሊታደጉ አይችሉም የሚሉ ወገኖች ሌላ መፍትሄ ይሰነዝራሉ፡፡ በግዮን ሆቴል በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ፤ ይህንን ችግር ለማስወገድ በሲጋራ ላይ የሚጣሉ ታክሶችን ከፍ በማድረግ፣ አጫሾች ሲጋራ የመግዛት አቅማቸውን ማዳከሙ የተሻለ አማራጭ እንደሚሆንና በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት አበክሮ እንዲያስብበት ተጠቁሟል፡፡

Published in ዋናው ጤና
Saturday, 07 December 2013 13:17

በፈጣሪ ዙርያ ሙግት!

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ “የአየር ሰዓት” አግኝተው የመወያያ ርዕስ ጉዳይ ከሆኑት ውስጥ ስለ ፈጣሪ የተወራው ጊዜ ተወዳዳሪ ያለው አይመስለኝም፡፡ የሰው ልጅ ጥንታዊ ጽሑፎች በአብዛኛው የሚተርኳቸው ታሪካች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈጣሪን የመመለከት አንቀጾች የያዙ ናቸው፡፡ ከቻይና እስከ አሜሪካ @ከእንግሊዝ እስከ ደቡብ አፍሪካ ዓለምን በዓራቱም አቅጣጫ ብናካልላት ይኸው ጉዳይ ገዥ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለጊዜው ስሙን በውል ባላስታውሰውም “ፈጣሪ ባይኖር እንኳን እንፈጥረው ዘንድ ግድ ነበር” ያለ ፈላስፋ መኖሩን አስታውሳለሁ፡፡
በፍልስፍና ሙያ ውስጥ በጣም በአወዛጋቢነታቸው ከሚታወቁት ርዕስ ጉዳዮች ውስጥ የፈጣሪ አለመኖር ለማስረገጥ የሚቀርቡ ሙግቶች አንዱ ነው፡፡ የፈጣሪን መኖር በምክንያት ለመግለጽ የማይፈልጉ እንዳሉ ሁሉ’ፈጣሪን መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም፡፡ ፈጣሪን በእምነት የመቀበል ያህል የሚቀል መንገድ ያለ አይመስኝም በአምክንዮ እና በተጠየቅ ፈጣሪን መፈለግ እንደኔ እንደኔ ቢወጡት በማያልቅ አቀበት መንገድ መጓዝ ማለት ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን አብዛኞቹ የምናውቃቸው ፈላስፎች በሚጣፍጥና በሚያማልል መልኩ ግዳጃቸውን ተወጥተዋል ማለት እንችላለን፡፡ የቻልነውን ያህል ለዛሬ ንባባችን የሚሆነን መረጥ መረጥ እያደረግን እንመለከታለን፡፡
ስለ ፈጣሪ መኖር የሚሞግቱ ፈላስፎች በአብዛኛው በአራት ምድብ እየተከፈሉ ትንታኔ ይሰጥባቸዋል፡፡ የCosmological Argument’የTeloogical Argument እና ሌሎች ሙግቶች በመባል ይታወቃሉ (አንዳንዴ moral arguments እንደ አምስተኛ ምድብ ይቀርባል)፡፡
አንደኛ ተፈጥሮን በመመርመር የሚገኝ ማስረጃ የፈፊሪን ኀላዌ ለመመስከር ሲያገልግል Cosmological Argument ይባላል፡፡ የቶማስ አኩናስ “አምስቱ መንገዶች” እየተባሉ የሚታወቁለት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ያረቀቃቸው ሙግቶች እንደ መስፈርት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ቶማስ አኩናስ አርስጣጣሊስን ፍልስፍና በመጠቀም ክርስትናን በፍልስፍና ለማደርጀት ከታተሩ የመካከለኛው ዘመን ፈላስፎች የሚመደብ ሲሆን@ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ማዕረግ የተሰጠው ፈላስፋ ነው። እርሱ ያቀረባቸው የሙግት ፍሬ ሐሳሶች በአጭሩ እንደዚህ ይቀመጣሉ፡-
ሀ. ብዙው ፍጥረት መነሻ /አስገኝ አለው፡፡
ለ. እራሱን በራሱ ያስገኘ ማንም የለም፡፡
ሐ. የእያንዳንድ አስገኝ ሌላ አስገኝ አለው ሁልቆ መሳፍርት አስገኝ ግን ሊኖር አይችልም
መ. ለሁሉም ነገር አንድ መነሻ የሚሆን@ የራሱ አስገኝ እራሱ የሆነ አለ ማለት ነው፡፡
ሠ. ይህም ለኀላዌ ምክንያት የማያሻው የራሱ አስገኝ እራሱ የሆነው በብዙዎቻችን ዘንድ “ፈጣሪ” የምንለው ነው፡፡
ይህ የሙግት ዘርፍ የተፈጥሮን የመጀመሪያ መነሻ በመመርመር የፈጣሪ ኀልውና ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረት ነው እናም የፍጥረት ሁሉ መነሻ ምንድን ነው? ብሎ ይጠይቃል፡፡ መቼም እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ ፈጣሪ እራሱ ሊሆን አይችልም። ስለሆነም እያንዳንዱ ፍጡር እራሱን ካልፈጠረና የመገኛ ምክንያቶች ደግሞ ቆጥረን የማንዘልቃቸው ካልሆኑ @ለሁሉም ነገር መነሻ የሚሆን@ የራሱ ፈጣሪ እራሱ የሆነ አካል እነዚህን ሁሉ ተፈጥሮዎች አስገኝቷል ማለት ነው ይሉናል፣ በዚህ ሙግት ዘርፍ የሚገኙት ፈላስፎች፡፡
ሁለተኛ፡-ይህኛው ዘርፍ ደግሞ ኀላዌያዊ  (Ontological Argument) ሙግት እየተባለ ይጠራል፡፡ በዚህ የሙግት ቡድን ውስጥ ሌሎች ፈላስፎች ተጠቃሽ ቢሆኑም እንደ አውራ የሚቆጠረው ፈላስፋ Anselm የተባለው የመካከለኛው ዘመን እየተባለ በታሪክ የሚታወቀው ዘመን ይኖር የነበረ የቤተ ክርስትያን አባት ነው (የቅድስና ማዕረግ የሰጠው ፈላስፋ ነው)፡፡
አንሳለም ያቀረባቸው ሙግቶች ባጭሩ ይህንን ይመስላሉ፡-
ሀ. ትልልቅ ነገሮች ማሰብ እንችላለን፡፡
ለ. ትልልቅ ነገሮችን እንድናስብ የሚያደርግን ደግሞ ከሁሉም ትልቅ የሆነ ሌሎችን የምናወዳድርበት የትልቅነት መለኪያ የሚሆነን ሌላ ነገር አለ ማለት ነው፡፡
ሐ. ከሁሉም ትልቅ የሆነና የትልቅነት መለኪያ የሚሆነን ነገር ደግሞ በሐሳቦችን እንድናስበው የፈቀደልን በአካልም ስላለ ነው ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የትልቆች ሁሉ ትልቅ መሆን የሚችል ደግሞ ፈጣሪ የሆነ ብቻ ነው፡፡
መ. ስለዚህ ፈጣሪ አለ /ህልው ነው/ ማለት ነው።
ይህ የሙግት ዘርፍ “ትልቅ ነገር” የምንለው ሐሳብ ማሰብ መቻላችን ብቻ ታላቅ ፈጣሪ መኖሩን ያመላክታል የሚል እንድምታ ያዘለ ነው፡፡ አዕምሯችን ትልቅ የሚባል ሐሳብ ማሰብ መቻሉ የፈጣን መኖር ያመለክተናል፡፡ ከእርሱ በላይ ሌላ ትልቅ ማሰብ የማንችልበት ደረጃ ስንደርስ እርሱ ፈጣሪያችንን ይመስላል ማለት ነው፡፡
ሶስተኛ፡- ይህኛው የሙግት ዘርፍ ደግሞ ከስነ-ውበት አንጻር መከራከሪያውን ያቀርባል፡፡ ሰዓትን ለምሳሌ ብንወስድ በጣም ውብ ሆኖ የተለያዩ ጥቃቅን የሚመስሉ አካላትን ይዞ ተሰርቶ የራሱ ትልቅ ግልጋሎት ይሰጣል፡፡ ይህ ዓለም/ዩኒቨርስ በጣም ውብ ሆና መሰራቱ@ አንድ በጣም በማስዋብ የተካነ ጥበበኛ ፈጣሪ መኖሩን ያመለክተናል፣ ይላል የዚህ ሙግት ፍሬ ሐሳብ፡፡ በዘመናዊ ሳይንስ ግኝታቸው ዓለም አንቱ ያላቸው ሳይንቲስቶች ይህንን የሙግት ዘርፍ ተቀላቅለዋል@ እነ ኒውተንን መጥቀስ ይቻላል። ይህ የተፈጥሮን ውበት በመመርመር የማቀርብ ሙግት /Telogical Argument/ ይባላል።
አራተኛ፡-ሌሎች ሙግቶችን ያቀረቡ ፈላስሮች፡፡
ሀ. ስፒነዛ (Spinoza):-በጣም ጥቅል ሐሳቦችን አንስቶ የፈጣሪን መኖር የሚተርክልን ይህ ፈላስፋ እንዲ ይላል፡- “ፈጣሪ ማለት ሁሉንም ነገር ነው@ፈጣሪ ማለት እራሱ ዩኒቨርስ ነው፡፡ በኛ አና በፈጣሪ መካከል ሩቅ የሆነ ልዩነት መፈጠር የለበትም@ቅርባችን እንደ ሆነ አድርገን ማሰብ አለብን፡፡” ስፒነዛ የሃይማኖት ልዩነት እንዳይከሰት የሚጠነቀቅ ይመስላል@ “የኔ የተሻለ አምላክ ነው” “አይ የተሻለ የኔ አምላክ ነው” እያልን ሽኩቻ ውስጥ እንዳንገባ የሚያሳስብ ይመስላል፡፡ ሁላችንንም ሰማየ ሰማያት ዩኒቨርስ ላይ ይሰቅለንና አንድ መሆናችንን አጥብቆ ይነግረናል፡፡ “እኛ ሁላችንም የዩኒቨርስ ወሳኝ አካላት ነን /one Substance/@ስለሆነም የፈጣሪም አካል ነን ማለት ነው፡፡” ይለናል ስፒነዛ፡፡ ሁላችንም አንድ የምንሆነው የፈጣሪ ወሳኝ ክፍሎች በመሆናችን ነው እንደ ማለት ነው ጉዳዩ፡፡
ለ. ሔግል(HEGEL):-እኛ በተፈጥሯችን በእራሱ ብቻ የመንፈስ መገለጫዎች ነን@ መንፈስ በኛ ውስጥ ይሰራል፤ እንዲያም ሲል ደግሞ የሚፈልገውን ግብ በእኛ ላይ ይፈጽማል፡፡ የስፒነዛን ዩኒቨርስ ሐሳብ ሔግል ወደ መንፈስነት ያረቅቀዋል@ልቅ የአንድ እግር ኳስ ቡድን መንፈስ ብንወስድና ደጋፊው ሁሉ በአንድ ላይ እስቴዲየም ውስጥ በአንድ ቋንቋ ሲደግፈው የምናየው ትስስር ወደ ዩኒቨርስነት ብናሳድገው’መንፈስ የምንለው ሐሳብ ይገለጽልናል። ስለዚህ ሆላችንም የመንፈስ ማደሪያዎች’ነን ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈስ ደግሞ የፈጣሪን መኖር የሚያረጋግጥልን በቂ ማስረጃችን ነው፡፡
ሐ. ኪርጋድ (Kierkegaard):- ኪርጋድ የምክንያትን ውስንነት/አቅም ማነስ መነሻ በማድረግ ሙግቱን ያቀርባል፡፡ “እና ይሄ አመከንዮ (Reason) እየተምታታበት ሊያውቀው ያልቻለው ነገር መንግድ ነው? ለአመክንዮ አስጨናቂ የሆነው ይህ ጉዳይ (ሰውን እስከ ምናውቀው ድረስ) ሰው አይደለም@ ያው ፈጣሪ ማለታችን ነው፡፡ ፈጣሪን የማስተዋወቅ ጉዳይ በአምክንዮዊነት የማቻል አይደለም፡፡ ፈጣሪ የለም ካልን@ ላለመኖሩ ማስረገጫ ማቅረብ አይቻለንም፡፡ አለ ካልን ደግሞ ማስረገጫ መፈለጉ ጅልነት ነው፡፡ ኪርጋድ ፈጣሪን ለመረዳት መሞከር ከባድ ጉዳይ መሆኑን ብቻ ሳይሆን@ ፈጣሪን መረዳት አለብን ብለን ማመናችንንም ይቃወማል፡፡
መ. ካንት (Kant):- ሶስቱን ዋና ዋና የሙግት ዘርፎችን (የCosmological argument’ የOntological Argument እና የTelological Argument) አጥብቆ የሚተቸው ካንት@”በአመክኗዊ መሰረት ላይ ሆኖ ፈጣሪን መኖር ማስረገጥ ለማንኛውም የሞራል ሰው አስፈላጊ ነው” ይለናል፡፡ በአምክንዮ ይጀምረውና በሞራል ይደመድመዋል ካንት@ ስለ ሆነው የሞራል ማስረገጫ (a moral proof) እየተባለ ይጠራል።” ጥበብ/ቅንነት ውለታው እንዲመለስለትና ክፋትም የእጁን እንዲያገኝ አንድ ሁሉን አወቅ’ሁሉን ማድረግ የሚችል የሁሉ ዳኛ ፈጣሪ መኖር ግድ ነው፡፡ የፈጣሪን መኖር ሳናረጋግጥ ስለ ፍትህና ስለ ግብረገብነት ማውራታችን መሰረት የለሽ /እናም የእንቧይ ካብ/ ይሆንብናል” የለናል ካንት፡፡
ሁሉም የቀረቡት ሙግቶች የተለያዩ ትችቶች የሚሰነዘርባቸው ስለሆነ አንድ ምርጥ የምንለው የሙግት ዘርፍ ለመምረጥ እንቸገራለን፡፡ አዕምሮን ለማሰራትና ሐሳባችንን የረቀቀ ለማድረግ ሁሉንም የሙግት ዘርፎች በጥንቃቄ መመልከቱ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የሃገራችን ታዋቂ ትንቢተኛ እና “ፈላስፋ” ሼህ ሁሴን ጅብሪል በዘመናቸው ሰነዘሩት የሚባል ሐሳብ የርዕሰ ጉዳያችንን ጠጣርነት የሚያመለክት ስለመሰለኝ ልጠቅሰው ወደድኩ፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፡- በሃይማኖት ጉዳይ ግራ የተጋቡ ሰዎች ሰብሰብ ይሉና ሼህ ሁሴንን ፍርድ ጠየቋቸው “እንዴው ይኸው ሃየማኖት እኛ ነን ገነት የምንገባ ይላል@ ያኛውም ደግሞ በበኩሉ ገነትን የምንወርሳት እኛ ነን ይላል@ ትክክለኛው የትኛው ነው? አሏቸው አሉ፡፡ ሼህ ሁሴንመ ሲመልሱ “ተውት ባካችሁ ከሁለት አንዱን የሲኦል እሳት አመድ ያስበላዋል” አሉ ይባላል። ፍርድ የአንድ የፈጣሪ ሐብት ነውና እኛ በእርሱ ስልጣን ጥልቅ እንበል የሚሉ ይመስላሉ፡፡ እንደ ስፒነዛ የመለያየትን ነገር ለሚኮንኑ ተሟጋቾች፣ ተጨማሪ የሐሳብ ማደርጃ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

Published in ህብረተሰብ

የጌራና የአስቦ፣ የአባ አቼ ዮኃንስ አፈታሪክ በመንዝ ጓሳ ኗሪዎች አንደበት

መንዝ ጌራ ወረዳ ዋና ከተማው መሃል ሜዳ ነው። በመንዝ ጌራ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራው መካከል አንድ ሎጅ ይገኛል፡፡ ሎጁ ከባህር ጠለል በላይ 3400 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ በጥብቅ ስፍራው ውስጥ ከባህር ጠለል በላይ እስከ 3700 ሜትር የሚደርሱ ከፍተኛ ቦታዎች አሉ፡፡
ወረዳውን በሰሜን ግሺ ራቢል፣ በምስራቅ ቀያ፣ በደቡብ አልፋ ምናር እና በምዕራብ ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡ ጓሳ ደጋ ላይ የሚበቅል ሳር ነው፡፡ ጥቅምትና ህዳር ጓሳ ሳሩ ደረቅ ይልና በየመሃከሉ አንገታቸውን አስግገው በበቀሉ ልዩ ልዩ አበቦች የቁንጅና ውድድር የሚደረግበት መድረክ ይመስላል፡፡ የትኛው ደራሲ ነበር “ሜዳው አልማዝ የተፈጨበት ይመስላል” ብሎ የፀሐዩንና የማለዳውን ጤዛ ነፀብራቃዊ ውህደት የገለፀው? አዎ በአሉ ግርማ ነው፡፡
ጠዋት መነሳት ከቻሉ እና ፀሐይ ስትፈነጥቅ ከደረሱ ይህን ውህደት ማየት ይቻላል፡፡ የዚህ ጥብቅ ስፍራ ስፋት 78.452 ኪ.ሜ ነው፡፡
አሁን የምንገኘው ከባህር ጠለል በላይ በ3508 ሜትር ላይ ባልተ ግራ ተብላ በምትጠራው ተራራ ከሎጁ አብሮን ከመጣው አስጐብኛችን ከአቶ የሺጥላ በየነ ጋር ነው፡፡ ከዚህ ከፍታ ላይ ሆኜ ቁልቁል ስመለከት አጣየ ከተማ ወለል ብላ ትታያለች። አይኔ አጣየ ከተማ ላይ ከማረፉ በፊት ያለው ሸንተረር ሰአሊ በቡርሹ የተጠበበበት ስዕል እንጅ በአይን እየታየ መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ ሸለቆውንና ተረተሩን ቁልቁል ለተመለከተው ዕውቅ ልብስ ሰፊ ተጨንቆና ተጠቦ የሰራው ሽብሽቦ ቀሚስ (ሽንሽን ቀሚስ) እንጅ እግዚአብሔር የፈጠረውና መሬት ላይ ያለ አይመስልም፡፡ እንዲያው አያድረገውና አንድ ድንጋይ (ናዳ) ቁልቁል ቢንከባለል ያለርጥር በደርግ አውሮፕላን ተደብድባ ተቃጥላ የነበረችውንና ተመልሳ የተሰራችው ባለ ሰማያዊ ቆርቆሮ ክዳኗ ብር ማርያም ዘብጥ ላይ ማረፉ አያጠራጥርም፡፡ ባልተ ግራ አፋፍ በስተግራ ባለችው ሸለቆ ውስጥ ደግሞ ጅብ ጠዋት ሶስት ሰአት ላይም ሊጨህባችሁ ይችላል፡፡
ወደጓሳው ልመለስና በውስጡ ዘጠኝ ቀበሌዎችን የያዘው መንዝ ጓሳ አንድ ቢሆንም በሁለት ክፍልና በሁለት ስም ይታወቃል፤ ጌራና አስቦ በመባል፡፡ ኗሪዎቹም የጌራና የአስቦ ዘር በመባል ይታወቃሉ። የዚህን አፈ ታሪክ አስጐብኛችን አቶ የሺጥላ አጫውተውኛል፡፡ እኔ ግን በምናብ ተጉዤ በጌራና አስቦ ዘመን፤ እነሱን አክዬ፣ እነሱን ሁኜ ልተርከው ወደድኩ፡፡ አፈታሪኩ ያለ፣ አሁንም የሚተረክ ነው፤ ምናባዊ ምልከታው ግን የእኔ ነው፡፡
ጌራ እና አስቦ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ ወደመንዝ ጓሳ የደረሱት ከጐንደር ተነስተው ነው ብለው ይጀምራሉ ኗሪዎቹ፡፡ ወንድማማቾቹ በጓሳው ውስጥ ውለው በማደር ከጫፍ ጫፍ ዞረው ተመለከቱት። ከዚህ ቦታ ውጪ ለከብቶቻቸው፤ ለልጆቻቸውና ለጠቅላላ ቤተሰቡ የተመቸ ቦታ እንደማያገኙ ላፍታ አልተጠራጠሩም፡፡ የቀራቸው ነገር ቢኖር የየግል ይዞታቸውን በርስትነት መከለል ብቻ ሆነ፡፡
ወንድማማቾቹ በጓሳው ትንሽ ከሰነባበቱ በኋላ የእንከፋፈል ጥያቄ ተነሳና “በየት በኩል ትፈልጋለህ? አንተ መጀመሪያ ምረጥ ኧረ በፍጹም!” በመባባል ሲገላገሉ ቆዩና ብዙ ጊዜ ወደ ስምምነት የሚያደርስ ገዥ ሃሳብ የሚያመጣው አስቦ እንዲህ የሚል ሃሳብ አቀረበ:- “ወንድማለም ጌራ የእናቴ ልጅ፣ ፈጣሪ ሳይለየን አብሮ እዚህ አድርሶናል፡፡ የእሱ ፈቃድም ሆነና እንዲህ ያለ ለመምረጥ የሚያዳግት ቦታ ገጠመን፡፡ እንዲያው ቸኮልክ ባትለኝ አንድ ሃሳብ ነበረኝ” አለ፡፡ ጌራም “አይ ወንድማለም ለልጆቻችን ቁርሾ ጥለን እንዳናልፍ ነው እንጅ እኔማ የአንተስ ጋሻ ጃግሬ ሆኘ ብኖር ምን ገዶኝ! በዚያ ላይ አንድያ ወንድሜ እኔን የሚጐዳ ነገር አታመጣ እስኪ ነገረኝ ልስማው” አለ፡፡
አስቦ በወንድሙ መልስ እጅጉን ደስ አለው። ጉሮሮውን ጠራረገናም፤ “አያ እንግዲያውስ ያሰብኩት እንዲህ ነው፡፡ አንተ ከደቡብ ጓሳ ጫፍ፣ እኔ ከሰሜን ጓሳ ጫፍ አዳራችንን እናድርግ፡፡ ተዚያ ሰማይ ያህያ ሆድ ሲመስል ፈረሶቻችንን ጭነን ልክ ፀሐይ በምስራቅ ተራሮች ጫፍ አንገቷን ብቅ ስታደርግ ፈረሶቻችን ላይ እንውጣ፡፡ አንተም ወደ ሰሜን እኔም ወደ ደቡብ ሽምጥ እየጋለብን እንገስግስና የተገናኘንበት ቦታ ድንበራችን ይሁን” በማለት ሃሳቡን አቀረበ፡፡ “ምን ገዶኝ፤ ማለፊያ” አለ ጌራ ነገር ሳያበዛ፡፡ ለህዳር ማሪያም ቀነ ቀጠሮ ተያዘ፡፡
በቃላቸውም መሰረት ወዲያው ጌራ ወደ ደቡብ፣ አስቦ ደግሞ ወደ ሰሜን ጫፍ በመሄድ ሰፈሩ፡፡ ለውድድሩ ዝግጅቱ ቀጠለ፡፡ ቅልብ ፈረሶቻቸውን ጓሳው ውስጥ ለቀቋቸው፡፡ ቀለብ የተስማማቸው ፈረሶችም ለጅብ እንኳ የማይቀመሱ ጥጋበኛ ቅልቦች ሆኑ፡፡ አልፎ አልፎ ለማሟሟቅ ሲወጡባቸው ልጓም የማይገታቸው፣ አለንጋ የማያርፍባቸው ሽምጥ ጋላቢዎች ሆኑ፡፡ ጌራና አስቦም በየአረፉበት ሆነው የሚጋልቡበትን መንገድ ሲያጤኑና ሲመረምሩ፣ ፈረሶቻቸውንም ገብስ ሲቀልቡ ሰነበቱ፡፡ ቀኑ ደረሰ። ጌራ ከደቡብ፣ አስቦ ከሰሜን ጫፍ ፈረሶቻቸውን ጐህ ሳይቀድ ጭነው፣ የፀሐይ መውጫ ላይ አይኖቻቸውን ተክለው መጠባበቅ ያዙ፡፡
ትልቅ ውድድር፣ ትልቅ ፉክክር እና የርስት ማስከበር ጉዳይ ቢሆንም ያለ ፊሽካ፣ ያለሩጫ ማስጀመሪያ ሽጉጥና ያለ መነሻ መስመር፣ ያለዳኛ በዕምነት ብቻ ዝም ብለው ፀሐይቱን መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ተፈጥሮ ኡደቱን አይስትምና ፀሐይዋ የእሳት አሎሎ መስላ በምስራቁ የተራራ እና የተራራ ጣብቅ መሃል ስትወጣ አስቦ በጥቁር ቦራ ፈረሱ፣ ጌራ በጥርኝ ፈረሱ ላይ ወጥተው መጋለብ ጀመሩ፡፡
ፈረሶቻቸው ቁጥቋጦውን፣ ጉድባውንና ጥሻውን እመር እያሉ ሲጋልቡ እርካቡ ላይ ቆመው ሰውነታቸውን ከፈረሶቻቸው ጋር ልክክ አድርገው ይሰፉታል፡፡ ገላጣና ሜዳ ሲያገኙ ደግሞ የሰው ዘር በማይታይበት በዚያ ዘመን ጠፈፍ ባለው የህዳር መሬት ላይ እንዲህ እያሉ ይፎክራሉ፡፡
የጥርኝ ጌታ ጌራ ቀጭኑ
ጉዳዩም አደል ጓሳና ደኑ
እንኳን በጥርኝ በልጓም ገብሱ
ድንበር አይቆምም ተኝቶ ነፍሱ፡፡ ሲል ጌራ፣ አስቦ ደግሞ በኪያ በኩል እንዲህ እያለ ይፎክራል፡፡
ቦራ ፈረሴ አትዘናጋ
ለዘሮቻችን ታሪክ ይወጋ
የጌራ ወንድም እልህ ያከሳው
በፈረሱ እግር ጓሳውን ወቃው፡፡
እንዲህ እየፎከሩ ጌራና አስቦ መንገዱን እንደቋያ እሳት ለበለቡት፡፡ ጓሳው ላይ የረበበው አመዳይና ጤዛ እረግፎ፣ የፀሀይ ሙቀት ሰውነትን ለማፍታታት ሲደርስ ወንድማማቾቹ ከሁለቱ አቅጣጫ መተው ድጃ አፋፍ ላይ ተገናኙ፡፡ የፈረሶቻቸው አፍ ደም የተቀላቀለበት አረፋ ደፍቋል፡፡ ሁለቱም ከፈረሶቻቸው ጀርባ ላይ ተፈናጥረው እግራቸው መሬት ሲነካ አንድ ሆነ፤ ተቃቀፉና ተሳሳሙ፡፡ ፈረሶቹ ደግሞ አፍና አፋቸውን ገጥመው በትኩስ ትንፋሻቸው ተገፋፉና በፊት ቀኝ እግሮቻቸው መሬቱን ይፎግሩ ገቡ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌራ “የእናቴ ልጅ፣ ይኼ ነገር ከፈጣሪ ነው፤ የርስታችንን ድንበር ለይተው እንስሳቱ ምልክት አበጁበት” ሲለው አስቦ ፈገግ አለና መልሶ አቀፈው፡፡ ጓሳው ተለካ፣ ለካስ ቦራና የአስቦ ፈረስ አብተው ኖሮ የአስቦ ይዞታ ከጌራ ርስት በለጥ አለ፡፡ አሁንም ድረስ የአስቦ ጓሳ በለጥ፣ የጌራ ደግሞ አነስ ይላል፡፡ ከዚያም እስከ  ደርግ መምጣት (1966) ድረስ ለ400 መቶ አመታት የዘለቀውን የቄሮ ስርአት ሰሩ፡፡ ቄሮ የጋራ መተዳደሪያ/አስተዳደር ደንብ/ስርአት ማለት ነው (Communal management system)፡፡ ጓሳው በቄሮ ደንቡ መሰረት የሚጠበቀው እንደሚከተለው ነው፡፡ የዘጠኙ ቀበሌ ኗሪዎች በየአለቆቻቸው አማካኝነት ይቀሰቀሱና ጓሳውን ያስሳሉ፡፡ በጥብቅ ቦታው ላይ ጥፋት ሲያጠፋ የተገኘ ሰው፣ ቤቱ ውስጥ እንኳ የጓሳ ገመድ የተገኘበት ሰው ቅጣት ይጣልበታል፡፡ መቀጫዎቹም የእመጫት ነብር ቆዳ፣ የቀጨሞ ሙቁጫና የነሀስ ዘነዘና እንዲሁም አንድ ሺ ዳውላ ማሸሻ (በፍጹም አይገኝም) የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ደግሞ የማይሞከሩ ናቸውና ጥፋተኛው ከመቀጣት አይድንም፡፡ በአጭሩ ጓሳውን ያረሰ፣ ያጨደ፣ ያስጋጠ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ቅጣቱን ማቅረብም ስለማይችል ከብቶቹ ተወርሰው የሚበሉት በህዝቡ ይበላሉ፤ የማይበሉት ተሸጠው ለግብር መክፈያ ይሆናሉ፡፡ እህሉም ተቆልቶ ይበላበታል፡፡ በጋራ ስምምነት በተወሰኑ ጊዜያቶች ግን ጓሳውን መጠቀም ይችሉ ነበር - ለእንስሳት መኖነትና ለቤት ክዳን፡፡
እንግዲህ የመንዝ ጓሳ ሎጅ የሚገኘው በዚህ ጥብቅ ስፍራ ውስጥ ነው፡፡ የአካባቢው ልምላሜ፣ መልክአ ምድር፣ ሰው ሰራሽ ደን፣ በብዙ ቦታ የማይገኘው ጓሳ … ትንፋሽ ይሰርቃል፡፡ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ አነር፣ ስስ፣ ሚዳቋ፣ ልዩ ልዩ አእዋፍት ወዘተ. የአካባቢው መገለጫዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙ እንስሳት 26% ያህሉ እና 114 የአእዋፍት ዝርያዎች በዚህ ስፍራ የሚገኙ ናቸው፡፡ ሎጁ ከአዲስ አበባ በ265 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የተሟላ ኪችን፣ መኝታ ቤቶች፣ አልጋ፣ ሽንት ቤቶችና መታጠቢያ ቤቶች ያሉት ባለ ሳር ክዳን ቤት ነው፡፡ ሁሉም ነገር የባህላዊ ጥበብ እጅ እንዲያርፍበት ተደርጎ ተሰርቷል፡፡ የሎጁ ሰራተኞች ትሁቶች፤ ሽቁጥቁጦችና ታዛዦች ናቸው፡፡ ይህ ባለ አንድ ፎቅ ሎጅ ደረጃው እንኳ የተሰራው በአንድ ዋና አምድ ላይ በገመድ በተቋጠሩ ጣውላዎች ላይ ነው፡፡ አልጋዎቹና ወንበሮቹ የተሰሩበት ኢትዮጵያዊ ጥበባዊ ብልሃት ዘመናዊነትን ያስንቃል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ንብረትነቱ የዘጠኙ ቀበሌ ኗሪዎች መሆኑ ነው፡፡
ጓሳውን ለመጎብኘት ሲነሱ ከፈለጉ በእግርዎ፣ አለዚያ ሳይከራከሩ ሎጁ በተመነው ቋሚ ዋጋ በቅሎ መከራየት ይችላሉ፡፡ 30 ኪ.ሜ በሚሆነው የእግር ወይም የበቅሎ ጉዞ አፈ ታሪኩ ይተረካል፤ አእዋፋትና እንስሳት ይታያሉ፡፡ በዚያ ላይ ጓሳው የ26 ወንዞች መፍለቂያ ስለሆነ ጥርት ኩልል ያሉ ትንንሽ ወንዞችን ያቋርጣሉ፡፡
አፈታሪክ ሁለት
መንዝ ጓሳ ድሮ ድሮ የጤፍ አዝመራ የሚታፈስበት፣ መሬቱ የሰጡትን የሚያበቅል ነበር ይባላል፡፡ ይሁን እንጅ በአንድ መነኩሴ እርግማን ደረሰበት፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መሬቷ መነኩሴውን ሰማች መሰል ለገመች፡፡ አሁንም ከአቶ የሺጥላ የሰማሁትንና ከበራሪ ወረቀታቸው የተመለከትኩትን ከመነኩሴው የዘመን መንፈስ ተነስቼ፣ ከእነሱ ጋር ሆኜ ላውጋችሁ፡፡ በርግጥ አፈ ታሪኩ ስለሚጣፍጥ እንጂ ከ3200-3700 ሜትር የባህል ጠለል በላይ የሆነ ቦታ ጤፍ አብቅሎ ለማሳፈስ የመቻሉ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፡፡
ታሪኩ እንግዲህ እንደዚህ ነው (ምናባዊ እይታው የእኔ ነው) አባ አጬ ዮሀንስ የሚባሉ መነኩሴ ከግብጽ ምድር ተነስተው ፍርኩታ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ታዩ፡፡ በዚችው ቤተክርስቲያንም ማገልገል ጀመሩ፡፡ መነኮሰ ማለት ሞተ ማለት ነውና ለአለም የማይጓጉ፣ ለዕምነታቸው የቀኑ አባት ነበሩ ይባላል፡፡ በዚህ ቦታ ለህዝቡ ቃለ እግዚአብሔርን እያሰሙ፣ ልጆችን እያስተማሩ፣ በህዝቡ ተወደው ሲኖሩ አንድ ባልገመቱት ቀን ክስ ቀረበባቸው፡፡ በአለሙ ልብስ ያልታዩት፣ የነፍሳቸውን ልዕልና ሽተው ስጋቸውን ከላመ ከጣመ ምግብ አርቀው በጾም በጸሎት ይኖሩ የነበሩት አባት “ከሴት ደርሰዋል፤ እሷም እነሆ አርግዛለች፤ ይህ ጽንስም የእርስዎ ነው” ተባሉ፡፡ አልደነገጡም፤ ግን ከሳሾቻቸውን ተፀየፏቸው፡፡ የኖሩት በድንግልና በብህትውና ነውና፣ ምሳሌዎቻቸው ግብጻውያኑ የምንኩስናና የብህትውና ፋና ወጊዎች አባ ጳውሊና አባ እንጦንስ ነበሩና፣ ክሳቸውን ሲሰሙት ስለአለሙ ተንኮል ልባቸው በሀዘን በሀዘን ፍላጻ ተወጋ፡፡ በተንኮል ክሱን ለማቅረብ ወደቀረበችው ነፍሰጡር ሴትም ዘወር ብለው “አንቺ ሴት በዕውነት በሆድሽ ያለው ጽንስ የእኔ ነው ትያለሽን?” ብለው ጠየቋት፡፡ ሴቲቱም ደከም ባለ ድምጽ “ይሄ ልጅ ተወልዶ አባቴ ማነው ቢለኝ ምን እላለሁ ብዬ ሚስጥሩን አወጣሁት፤ አዎ! እርስዎ ያውቁ የለ” አለቻቸው፡፡ አባም “እንዲያ ከሆነ እስኪ ማይልኝ! ብትዋሽም ብዋሽም መልሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” አሏት፤ እሷም ተስማማች፡፡ “የተናገርኩት እውነት ካልሆነ ድንጋይ ያድርገኝ” በይ አሏት፡፡ እሷም “ይሄ ጽንስ የእርስዎ ካልሆነ ድ…” እንዳለች ወደ ድንጋይነት ተለወጠች፡፡ የተሰበሰው ህዝብ ላይ ድንጋጤ ወደቀበት፡፡ አባ ግን ድንገት ብድግ ብለው ወደበአታቸው ገቡ፡፡ ከማለዳ ጀምሮ ግን በዚያች ቤተክርስቲያን ደምጻቸው አልተሰማም-ጠፉ፡፡ ምድሪቱን ግን ረገሟት፡፡ “እህል አይብቀልብሽ፤ ውርጭና ብርድ ይስፈፍብሽ” ብለው፤ እንዳሉትም ሆነ፡፡
ህዝቡ በመሬቷ መለገምና በአየር ንብረቱ ተቀጣ፡፡ ተሰበሰበናም “ምን ይበጀን” ብሎ መከረ። በመጨረሻም ሽማግሌዎች ተመርጠው አባን እንዲፈልጓቸውና ከርግማኑ እንዲፈቷቸው ለመለመን ተስማሙ፡፡ ሽማግሌዎቹ አባ የተሰደዱበትን ሲያጠያይቁ ጎንደር ልዩ ስሙ በለሳ ወደተባለ ቦታ መሄዳቸውን ሰሙ፡፡ ወደ ቦታው ሲደርሱ ግን ካረፉ ብዙ ጊዜ እንደሆናቸው ሰሙ፡፡ በብዙ ድካምና ልፋትም አስከሬናቸው ያረፈበትን መቃብር አግኝተው አጽማቸውን በማውጣት ወደአገለገሉበት ቤተክርስትያን አምጥተው አሳረፉት፡፡ እንደድሮው ባይሆንም ትንሽ መሻሻል ታየ ይለናል አፈታሪኩ፡፡ ደስ አይልም!    

የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል   
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው

ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ እንደምታጧጡፍና በየጊዜው ወደተለያዩ አገራት ለሥራ ጉዳይ እንደምትመላለስ ብቻ ነው። ሥራዋ የግል ሚስጢሯ ብቻ ሆኖ እንዲኖር የምትፈልገው ህሊና (ስሟ ለዚህ ጽሑፍ የተቀየረ) ይህንን የእህቷን እምነት አጥብቃ ትፈልገዋለች። በተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ደንበኞቿ ጋር እየከረመች በመጣች ቁጥር ለእህቷ የተለያዩ ቸኮሌቶችና ስጦታዎችን እየያዘችላት መምጣቷ የእህቷን እምነት አጠናክሮላታል፡፡
እሷ “ቢዝነስ” ብላ የገባችበት ህይወት ገቢ፣ እህቷ ቀኑን ሙሉ ተገትራ ከምትውልበት ቡቲክ ገቢ ጋር ሊወዳደር እንደማይችል ስለሚገባት “ሥራውን” አጥብቃ መያዙን  ትፈልገዋለች፡፡ የንግድ ፍቃድ እድሣት፣ ቫት ምዝገባ፣ ሪሲት ማሽን፣ ቀረጥና ታክስ የሚሉ ዝባዝንኬዎች የሌሉበት፣ “ራስን እያስደሰቱ ሌሎችን በማዝናናት” በቀን የሚገኝ ረብጣ ብር ከቡቲኳ ወርሃዊ ገቢ በእጅጉ ይልቃል። ተፈጥሮ ያደላትን ውበትና ማራኪ ቁመናዋን ለገበያ እያቀረቡ በተሻለ ገንዘብ ለመሸጥና ጠቀም ያለ የኮሚሽን ገንዘብ ለመቀበል አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ደላላ ደንበኞች አሏት፡፡ ለዚህ ተግባር ብቻ የምትጠቀምበት የሞባይል ስልኳ ሲጮህ “ሥራ” እንደተገኘ እርግጠኛ ትሆናለች። ቅያሬ ልብሶችን የምትይዘበትና ሁሌም ለጉዞ ዝግጁ የምታደርገውን ቦርሣዋን አንጠልጥላ ውልቅ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሥራ የምትንቀሳቀሰው በደላሎቹ መኪና ነው። ደላላው እሷን ካለችበት ወስዶ ወደምትፈለግበት፣ ሥራዋን ስትጨርስ ደግሞ ወደነበረችበት የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የኮሚሽን ክፍያው እነዚህን አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡ ህሊና ይህንን ህይወት ላለፉት አራት አመታት ኖራበታለች። ከዚህ ህይወት ስለመውጣትና ቢዝነሱን ስለመተው ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡
ባላት ትርፍ ሰዓት ሁሉ ራሷን እጅግ አድርጋ መጠበቅ፣ ጂም መሥራት፣ ሳውና፣ ስቲምና ማሣጅ በየጊዜው መግባት ታዘወትራለች፡፡ ውበቷንና ጥሩ ቁመናዋን ጠብቃ ለማቆየት ማድረግ የሚገባትን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አትልም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አዱኛ ያበቃት እሱ በመሆኑ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ታምናለች፡፡ ይህ የህሊና ህይወት የብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ህይወት እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተጧጧፈ የመጣውን ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ የተቀላቀሉ የከተማችን ወጣት ሴቶች የትላልቅ ድርጅቶች ኤክስኪዩቲቭ ፀሐፊዎች፣ የሽያጭ ሰራተኞች፣ ሞዴሎች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የዩኒቨርስቲዎችና የኮሌጅ ተማሪዎችና ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ የሀብታም ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህን ወጣት ሴቶች ለወሲብ ሽያጭ “ሥራ” የሚያመቻቹና የማገናኘት ተግባሩን በቅልጥፍና የሚወጡ ፈረንጆች “ፒምፕ” የሚሏቸው አይነት ደላሎች በከተማችን እየተበራከቱ ነው፡፡ ደላሎቹ ራሳቸው በኔትዎርክ የተሣሰሩ፣ የራሳቸውን መኪና ይዘው የሚንቀሳቀሱ፣ በከተማው ውስጥ አሉ የተባሉ ሆቴል ቤቶችን፣ እንግዳ ማረፊያዎችን፣ መቃሚያ ቤቶችንና የመዝናኛ ሥፍራዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉ ናቸው፡፡

ደላሎቹ ወደ እነዚህ ሥፍራ የሚመጡ አዳዲስ እንግዶችንና ነባር ደንበኞቻቸውን ለማጥመድና እንደ እንግዳው ፍላጐት የሚጠይቀውን ለማቅረብ ሁሌም ዝግጁ ናቸው፡፡ በአንዳንድ የከተማችን ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች ውስጥ የሚሰሩ እንግዳ ተቀባዮች፣ (receptionists) አስተናጋጆችና የትላልቅ ቪላ አከራዮች የኔትዎርኩ አባላት ናቸው፡፡ አዲስ እንግዳ የመምጣቱ ዜና እነዚህ ደላሎች ጆሮ ለመድረስ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይበቃሉ፡፡ ከዛም ደላሎቹ ሥራቸውን ይጀምራሉ። በእንግዳው መውጫና መግቢያ ላይ መረቡ ይዘረጋል። አብዛኛውን ጊዜ የደላሎቹ መረብ አሣውን ሣያጠምድ አይመለስም። ከልጃገረድ እስከ ቤት ልጅ፣ ከቤት ልጅ እስከ የቡና ቤት ሴት ድረስ እንግዳው የጠየቀው ይቀርብለታል። በዚሁ የሴት ድለላ ተግባር ላይ የተሰማሩ ደላላዎች እንደነገሩኝ፤ በአሁኑ ወቅት በከተማችን ለገበያ የሚቀርቡ ልጃገረድ ሴቶች እየተበራከቱ ነው። ሴቶቹ በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎም ከክፍለ ሃገር የሚመጡ ታዳጊ ልጆች የዚህ ድርጊት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ ከተለያዩ የአገራችን ክልሎች ይመጡ የነበሩት ታዳጊ ሴቶችም የእነዚህ ደላሎች ወጥመድ ውስጥ የሚገቡበት አጋጣሚ እንዳለ ይታወቃል፡፡
ልጃገረዶቹ ድንግልናቸውን በሽርፍራፊ ገንዘብ በደላላ ሸጠው ወዳሰቡበት ባህር ማዶ ይሻገራሉ፡፡ ይህ ወደ አረብ አገር ባቀኑ በርካታ ሴት እህቶቻችን ላይ ሲፈፀም የኖረ ሃቅ እንደሆነ ደላሎቹ ያለሀፍረት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ በተለያዩ ማባባያዎችና ጉትጐታዎች ከቤታቸው የሚወጡ ከየትምህርት ቤቱ የሚወሰዱ ታዳጊ ሴቶች፤ ድንግልናቸውን ከእነሱ በእድሜ እጅግ ለሚበልጣቸው (አንዳንዴም ለወጣት ሀብታም ነጋዴዎች) በ10ሺዎች በሚቆጠር ብር ይሸጣሉ፡፡ ይህ ተግባር በስፋት የሚከናወንባቸው ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች በተለይም ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉ ከተሞች (ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ሞጆና ናዝሬት… በብዛት ይጠቀሳሉ) በስፋት ይገኛሉ፡፡ በዚህ “የልጃገረዶች የድንግልና ግብይት” ውስጥ በብዛት ተሣታፊ የሚሆኑት የከተማችን ቱጃር ነጋዴዎችና አልፎ አልፎ ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡
ቀይ፣ ጠይም፣ ጠቆር ያለች፣ ረዥም፣ ቀጭን፣ ቁመናዋ ያማረ… እንደ እንግዳው ስሜትና ምርጫ ተፈላጊዋን በደቂቃዎች ውስጥ መኝታ ቤት ድረስ ማምጣት ለደላሎቹ አዳጋች ሥራ አይደለም። ከውጭ አገራት ከሚመጡና ይህንን አይነት አገልግሎት በስፋት ከሚጠይቁ የውጪ ዜጐች መካከል አብዛኛዎቹ አረቦች እንደሆኑ በስራው ላይ የተሰማሩ ደላሎች ይናገራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሱዳኖችም በብዛት እንደሚመጡ እነዚሁ ደላሎች ገልፀውልኛል። ለረዥም አመታት ውጪ ኖረው ወደ አገራቸው የተመለሱ ዳያስፖራዎች፣ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ዲፕሎማቶችና በተለያዩ ስብሰባዎችና ሥራ ሰበብ አሊያም ለጉብኝት የኢትዮጵያን ምድር የሚረግጡ የውጪ ዜጐች ሁሉ የዚህ “አገልግሎት” ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከተማችን የምታስተናግደው አለማቀፋዊ ስብሰባ በሚኖርበት ወቅት የደላሎቹ ወይም የግብይቱ ኔትወርክ ይጨናነቃል፡፡ የአብዛኛዎቹ “አገልግሎት” ፈላጊዎች ጥያቄም “ቆንጆ የቤት ልጅ እፈልጋለሁ” የሚል ነው፡፡ ጥያቄያቸውን በአግባቡ መመለስ የቻለ ዳጐስ ካለ ክፍያ በተጨማሪ ወፈር ያለ ጉርሻ ማግኘቱም እርግጥ ነው፡፡ “አንዳንድ ጊዜ “የቤት ልጆች” ከገበያ የሚጠፉበት ወቅት አለ። እንዳልኩሽ ስብሰባዎች በሚኖርበት ወቅት ገበያው ስለሚሟሟቅ የቤት ልጆች በጊዜ ያልቃሉ፡፡ ስለዚህ ያለን አማራጭ ብዙም ያልተጐሳቆሉ ሴተኛ አዳሪዎችን እየፈለግን በቤት ልጅ ታርጋ ለገበያ ማቅረብ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ ይባነንበታል፡፡ ሰዎቹ  የቤት ልጅና ሴተኛ አዳሪን የሚለዩበት የራሳቸው መንገድ አላቸው ብሎኛል ከገበያው ደላሎች አንዱ፡፡”
በከተማችን የተለያዩ ሥፍራዎች ቦሌ፣ ወሎ ሰፈር፣ ሳር ቤት፣ ሳሚት፣ መስቀል ፍላወርና መገናኛ አካባቢዎች የሚገኙ ቪላ ቤቶች ከነሙሉ የቤት ዕቃዎቻቸው ለቀናት፣ ለሳምንታትና ለወራት ከውጪ የሚመጡ እንግዶችን ይቀበላሉ፡፡ የእነዚህ ቤቶች የጥበቃ ሠራተኞች ከደላሎቹ ጋር በኔትዎርክ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለሴቶቹ የሚከፈለው ዋጋ እንደ እንግዳው አይነትና እንደ ሴቷ የማስተናገድ ብቃት እንደሚለያይ ደላላው ይናገራል፡፡ ሴቷ እንግዳው በፈለገው መንገድና ሁኔታ ልታስተናግደው (ያፈነገጠ የወሲብ ጥያቄን ያካትታል) ፈቃደኛ ከሆነች ክፍያዋ ከፍ ይላል፡፡ በአብዛኛው ግን ለውጪ አገር ዜጐች የሚቀርቡ ሴቶች ለአንድ ምሽት ከ300-400 ዶላር ክፍያን ይጠይቃሉ፡፡ የቆይታ ጊዜያቸው የሚራዘምና እነሱም የሚመቻቹ ከሆነ ግን ክፍያው እንደየሁኔታው ሊለዋወጥ ይችላል። ለሁለትና ለሶስት ቀናት በነበራቸው ቆይታ እጅግ ተደስተው ከዋናው ክፍያ ጋር ተጨማሪ ቲፕ (በገንዘብም በአይነትም) ለምሳሌ ላፕቶፕ፣ ካሜራ፣ አይፎንና መሰል ውድ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች በስጦታ ሰጥተዋቸው የሚሄዱም አሉ። ከዚህ ባስ ሲልም ወደ አገራቸው እስከ መውሰድ የሚደርሱም ይኖራሉ፡፡ በከተማዋ የሚገኙ ትላልቅ የመቃሚያ ቤቶችን እንደ እጁ መዳፍ አብጠርጥሮ እንደሚያውቃቸው የሚናገረውና በዚሁ ሴቶችን በመደለል “ቢዝነስ” ላይ የተሰማራው ሌላው የላዳ ታክሲ ሾፌሩ ታዲዮስ፤ በአሁኑ ወቅት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የምትገኝን “የቤት ልጅ” አንጠልጥሎ ለወሲብ ገበያ ማቅረብ ለእሱ እጅግ ቀላል ሥራ እንደሆነ ይናገራል፡፡

“ሴቶቹ የብር ፍቅር ሊገላቸው ነው ዝም ብለሽ እኮ አንዳንድ ትላልቅ የቁንጅና ሣሎኖች፣ ካፌዎችና መዝናኛ ሥፍራዎች ብትሄጂ ሆን ብለው ለጠለፋ የሚወጡ የቤት ልጆችን ማግኘት ትችያለሽ፡፡ በየመቃሚያ ቤቱ ለዚሁ ተግባር የሚዞሩ ሴቶች ነፍ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ ፈላጊና ተፈላጊን ማገናኘት ነው ሥራችን። እነሱ ሲመቻቹ እኛም ይመቸናል” ይላል ታዲዮስ። በከተማዋ ካሉ ትላልቅ ሆቴሎች በአንዱ በእንግዳ ተቀባይነት የሚሰራው ፍፁም (ስሙ የተየቀረ) በሆቴሉ ውስጥ ከሚያርፉ እንግዶች አብዛኛዎቹ የተለያዩ አገር ዜጐች እንደሆኑ በመጠቆም፤ በሥራው ወቅት የሚያጋጥመውና እጅግ ያስመረረው ጉዳይ ግን የእነዚህን እንግዶች “ሴት አስምጣልን” ጥያቄ መመለስ እንደሆነ ይናገራል። የእንግዶቹን ጥያቄ መመለስ ካቃተው እንግዶቹ በአግባቡ እንዳልተስተናገዱ ለሆቴሎቹ ኃላፊዎች ከመናገር ወደ ኋላ እንደማይሉም ይገልፃል፡፡ ይህ እንዳይሆንም በእነ ታዲዮስ ኔትወርክ መታቀፍ ግድ ሆኖበታል፡፡ እንግዶቹ በዚህ ዓይነት መንገድ በከተማችን በሚጧጧፈው ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ውስጥ ተዋናይ ሆነው ቆይተው ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ወቅት ከአበሻ ውብ ቆነጃጅት ጋር የፈፀሙትን የወሲብ ገድል እንደ ፌስ ቡክ፣ ትዊተር ባሉ የማህበረሰብ ድረገፆች ላይ በማስፈር ለዓለም ያስኮመኩማሉ፡፡ ጐበዝ! ወዴት እየተጓዝን ይሆን? ምስጢሩም ቢገለጥ ዝምታውም ቢበቃ አይሻልም ትላላችሁ፡፡ ምንም ቢሆን መወያየቱ አይከፋም እላለሁ፡፡

Published in ህብረተሰብ
Saturday, 07 December 2013 13:08

የድሬዳዋ የጉዞ መደምደሚያ!

“ድሬ ወላድ-ነሽ፤ ሽለ-ሙቅ”

በሀይቅ ከተከበበችው ደብረዘይት ጀምሬ በአዳማ የአሸዋ እምብርት አቋርጬ፣ አዋሳ ገባሁ፡፡ ከዚያ ወደ ደብረ ብርሃን ዘለቅሁና ድሬ ላይ አረፍኩ። የማህበረሰብ አቀፍ የሆኑትን ዕድሮች ህበርታቸውን፣ የሸማቾች ማህበራትን አቅም፣ እናት አባታቸውን ያጡ ህፃናትና ጧሪ - አልባ አረጋውያን የሚረዱበትን መንገድ፣ አየሁ፡፡ የአካባቢያቸውን ህዝባዊ አቅም (Resource)  እንዴት ፈልፍለው፣ አደራጅተው የልማት አቅም እንደሚገነቡ አስተዋልኩ፡፡ ትምህርት ጤና፣ የከተማ ግብርና እንዴት ከህዝቡ ክንድ እንደሚበቅል ተማርኩ፡፡ እናቶች፣ ሴቶች የገዛ ኑሮዋቸውን ለማሻሻል በገዛ እጃቸው ሲፍጨረጨሩ ተመለከትኩ፡፡ ከብት ከማርባት፣ በከብት ተዋጽኦ እስከገመገልገልና ራሳቸውን እስከ መቻል፤ ብሎም ዘላቂ ህልውናቸውን ለማረጋገጥ ሲጣጣሩ አይቼ ተማረኩ፡፡  ወጣም ወረደም፤ ህዝብ በራሱ ሲተማመን እንደማየት አስደሳች ነገር የለም!! ህዝብን እንደመውደድ፣ በራሱ ሲተማመን እንደማየት አስደሳች ነገር የለም፡፡ ህዝብን መውደድ፣ ህዝብን ማመን፣ ራሱን እንዲችል የተቻለንን ሁሉ ማድረግ፤ ከማንኛውም ነገር የተሻለ ተጨባጭ ጉልበት ማፍራት ነው፡፡ በሀገር ላይ ለውጥ ማየትን አፈሩ ላይ ሆኖ መመስከር መታደል ይመስለኛል። የህዝብን ዕውነተኛ ኑሮ በማናቸውም አጋጣሚ ተጠግቶ ማስተዋል ቢያንስ ከሃሣዊ - አዋቂነትና ከአዛኝ ቅቤ አንጓች የይስሙላ ፕሮፖጋንዳ ያድናል፡፡
የእየሩሳሌም ህፃናትና ማሕበራዊ ልማት ድርጅት፤ በልማት ላይ ትኩረት አድርገው ለረዥም ጊዜ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና ካሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። ከላይ በተዘረዘሩት ፍሬ - ጉዳዮች ዙሪያ አያሌ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ሀገራችን ለሚቀራት ረጅም ጉዞ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ያደርጋልም፡፡
የድሬዳዋ ጉዞ ማስታወሻዬን በሚከተለው ግጥም ደምድሜ ወደ ባህርዳርና አውራ አምባ ጉዞዬን እቀጥላለሁ፡፡ (የፀጋዬ ገ/መድህንን “እንኳን ለዓመት ጉድ አበቃን” የሚለውን ግጥም በዚሁ እትም ገፅ 17 ይመልከቱ) “መጓዝ ማወቅ ነው” ይላሉ ፈረንጆች፡፡ ማሳወቅም ትልቅ ፀጋ ነው ብዬ ስለማምን፤ ያየሁትን፣ የሰማሁትን፣ ያጋጠመኝን ሁሉ ባመቸኝ ሰዋዊ መልኩ እነቁጣለሁ፡፡   
ድሬ ወላድ ነሽ፤ ሽለ-ሙቅ
ድሬ ወላድ የጭንቅ ቀን
ጐርፍ ምጥሽ፣ ፈውስሽ እርከን፤
ዥንጉርጉር የቀለም ድንኳን፣ ህብረ - ቀለም የፀባይ ዳስ
የፍቅር አዋይ፣ የውበት ዳንስ
የምድር ከለላ ዛፍ ጥላ
የሁሉ አገር፣ ሁለት ባላ፤
የድህነት የዕድገት - ማላ!
ድምር ፅዋ ድሬዳዋ፣
ድሬ የሳቅ ቀን ደመራ፣ ችግር - ፈዋሽ የለውጥ - ግት
የጐርፍ ሥጋት ምጥ እናት
ድሬዳዋ የአደጋ ሥር፣ የነግ-ተጓዥ የልባም-ቋት
የጫት አድባር የሰላም ጣት፣ የመፈቃቀር ቅን ጥለት፤
ጭንቅ - አምካኝ የመሬት ጽላት
ድሬዳዋ የፍቅር ርስት
የድንገቴ  ወዳጅ እንኳ፣ ዘላለም የሚያሽርብሽ
ገንደ - ደሀሽ ሜዳ ሁዳድ
ተቸጋሪሽ ዙሪያ መንገድ
ገንደ - ጋራሽ ተራራ አናት፣ ድሬ ፈትል የመላ-ምት
ድሬዳዋ ያገር እናት፡፡
ስሚኝ ድሬ…
የማይገታ ጐርፍ የለም፣ የማይታለፍ እንቅፋት
የማይሸኝም ቀን የለም፣ የማይሻር ያሰት - ሹመት!
የማይለማ ጪንጫ የለም፣ የማይከስም ሀሳዊ - ዕድገት!
ድሬ ጣሪ፣ ድሬ ኑሪ፣ ራስሽን ቻይ ድሬ ምሪ
ተራሮችሽን ተርትሪ፣ የጋራ ሰምበር ፍጠሪ
ድሬ፤ “ዛላ-አንበሳ” ያልሺው፣ ጐርፍ-ገድቡ ግንብሽ
በምጥ-ቀንሽ ያበጀሽው፣ ውድ ጋሻ ነው አጥርሽ!
ምራቅን ከንፈር ነው እሚያጥረው፣ በይ እርከንሽን አሳምሪ
ማዶ ለማዶ “ሞረሽ” በይ፣ በሞባይል ተጠራሪ
ህዝብ ነው ምንጊዜም ክንድሽ፣ እድርሽን አጠንክሪ፡፡
የከተማ አትክልትሽን፣ ወዶ - ልማትሽን ቀጥዪ
የቀን ሐራራሽን ሻሪ፣ ምስኪንሽን ውለሽ አውዪ!
ህዝብሽ ልብ ውስጥ ነው ተስፋሽ፣ ሲያምን የሚረታ እሱ ነው
በግድ የትም አይደረስ፣ በፍቅር ነው ሰው ዕድገቱ
ያንቺ መቀነት መጥበቅ ነው፣ ሀሞትሽ ነው መዳኒቱ
“ከቶም ያልተዋጉበት ቀንድ፣ ከጆሮ አንድ ነው” ይላሉ
ቅርስ-ቅሪትሽን ቀስቅሰሽ፣ አብስይው ይድረስ ለሁሉ!
ድሬ ወላድ ነሽ፣ ሽለ ሙቅ፤ የሚቀናብሽ ይጨነቅ
የማይመርቅሽ ይውደቅ፣ የክፉ - ቀን ጠርሽ ይራቅ!!
እና ድሬ፤ ሞትሽ ይሙት፤ መቀመቅ ይግባ ድህነት
የማይገታ ጐርፍ የለም፣ የማይታለፍ እንቅፋት
የማይሸኝ ቀን የለም፣ የማይሻር ባለ ሹመት …
ሳቂ ድሬ ጐርፍሽ ይድረቅ
ድሬ ቡሬ ያባድር ጨርቅ
ድሬ ፍቅር የአገር ደማቅ! ..
ድሬ ወላድ ነሽ፤ ሽለ-ሙቅ!
(ለድሬዳዋና ጐርፉን ለረታው ህዝብ)
ህዳር 26 -2006 ዓ.ም

Published in ባህል
Page 12 of 16