በሰዓሊ ደረጀ ደምሴ የተዘጋጀው “ዑደት” የተሰኘ የስዕል አውደርዕይ የፊታችን ማክሰኞ ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል በብሄራዊ ሙዚየም ይከፈታል፡፡ ኑቢያ አርት ስቱዲዮ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአውደርዕዩ የሚቀርቡት ስዕሎች የምንኖርበት አካባቢ በማንነት፣ በባህል እና በአኗኗር ላይ ያለውን ተፅዕኖ ያንፀባርቃሉ። “ዑደት” የስዕል አውደርዕይ ለተከታታይ ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ሰአሊው በበርካታ የስዕል ስራዎቹ እንደሚታወቅ ተገልጿል።

የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት የተዘጋጀለት የኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ ሁለተኛ ዙር “የተሰጥኦ ውድድር” መጀመሩ ተገለፀ፡፡ የኮካ ኮላ ብራንድ ማኔጀር አቶ ምስክር ሙሉጌታ ባለፈው ሐሙስ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ እንደተናገሩት፤ ውድድሩ ከ13-29 አመት እድሜ ያላቸውን የሚያሳትፍ ሲሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በዘጠኝ የአገሪቱ ከተሞች ያሉ ባለ ተሰጥኦዎች ይወዳደሩበታል፡፡ “ተተኪን ፍለጋ” በሚል መርህ የሚካሄደው የኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ የተሰጥኦ ውድድር፣ በድምፅና በቡድን ውዝዋዜ ዘርፍ የሚካሄድ ሲሆን ለአሸናፊዎቹ የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት ያከፋፍላል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የተሰጥኦ ውድድር ከአይጃ ኢንተርቴይመንት ጋር በኦሮሚያ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ለ10 ወራት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ለአምስት ወራት እንደሚዘልቅ ተገልጿል፡፡

“...ማንኛዋም እናት አደጋ ውስጥ እንዳለች ማሰብ ያስፈልጋል...” “...ከተወሰኑ አመታት በፊት ነው ...ወሬው በአዲስ አበባ ከተማ የተሰማው፡፡ በጊዜው በመገናኛ ብዙሀንም ተደምጦአል... ሲሉ አንድ ተሳታፊያችን የሚከተለውን መልእክት አድርሰውናል፡፡” “...ሁኔታው ያጋጠመው ምናልባትም የዛሬ 15/ አመት ገደማ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዲት እናት በምጥ ተይዛ በየሆስፒታሉ ስትሄድ ...አልጋ የለንም ...አልጋ የለንም የሚል ምላሽ ታገኛለች፡፡ ከዚያም በስተመጨረሻ በሄደችበት ሆስፒታል አልጋ የለም ተብላ ወደመኪናው ስትመለስ በድንገት የሆነ ነገር ከሰውነቷ ዱብ ይላል፡፡ ለካንስ ልጁዋ ሊወለድ ደርሶ ኖሮአል፡፡ በዚህ ሳቢያም ብዙ ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በእርግጥ ዛሬ ...ዛሬ ሁኔታዎች ተሻሽለዋል ቢባልም አልፎ አልፎ ግን ችግር ሊኖር ይችላልና እስኪ አነጋግራችሁ መልስ ስጡን...” ያሉን አቶ ወንድአጥር ማስረሻ ከአዳማ ናቸው። የዚህ አምድ አዘጋጅም በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመገኘት የእናቶችን የሪፈራል አሰራር በመመልከት ለአንባቢ ብላለች፡፡በጋንዲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደረጀ አለማየሁ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጥ/ እናቶች በምጥ ሰአት ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ ተቀባይነት የማይኖራቸው ምን ሲጎድል ነው? መ/ በመሰረተ ሀሳቡ አንዲት ሴት ምጥ ይዞአት ለመውለድ ወደ ሆስፒታል ስትመጣ መመ ለስ የለባትም፡፡ አገልግሎቱን ማግኘት ይገባታል፡፡ በእርግጥ የማዋለድ አገልግሎቱ የሚሰ ጥባቸው ጤና ተቋማት ደረጃ ይለያያል፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጥባቸውም ቦታዎች በመጀመሪያ ሆስፒታሎች ከዚያም ጤና ጣብያዎች እንዲሁም ከጤና ጣቢያም በታች እስከ ጤና ኬላ ድረስ ያሉ ተቋማት በተመሳሳይ ደረጃ የማዋለድ ስራውን አይሰሩም፡፡ ነገር ግን የምጡን አመጣጥና የእናትየውን ጤንነት እየተከታተሉ ጤና ኬላዎች ወደ ጤና ጣቢያ ጤና ጣቢያዎች ደግሞ ወደሆስፒታል ሪፈር እንዲያደርጉ አሰራሩ ይፈቅዳል፡፡ አንዲት እናት በጤና ጣቢያ ለመውለድ ከምትቸገርባቸው ምክንያቶች... ምጡ በትክክለኛው መንገድ ካልመጣ፣ የጽንሱ አቀማመጥ ትክክል ካልሆነ፣ ደም በጣም እየፈሰሳት ከሆነ እና ሌሎች የጤና ችግሮች ካሉ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ካጋጠሙ ጤና ጣቢያዎች ወደሆስፒታል ለተሻለ አገልግሎት ሊልኩ ይችላሉ፡፡ ሆስፒታሎች የተላኩላቸውን እናቶች ተቀብለው የማዋለድ አገልግሎቱን መስጠት ይጠበቅ ባቸዋል እንጂ በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ከአንዱ ሆስፒታል ወደሌላው ሆስፒታል መላክ የለባቸ ውም፡፡ በሆስፒታል ማንኛውንም እርዳታ ሊሰጥ የሚችል የሰው ኃይል ማለትም ከእስፔሻል ሐኪም ጀምሮ እስከ ሚድዋይፍ ድረስ መኖር አለበት፡፡ በሆስፒታል የደም ባንክ አገልግሎት አለ፡፡ በሆስፒታል የኦፕራሲዮን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በሆስፒታል በቂ አልጋዎች ወላድ እናቶችን መጠበቅ አለባቸው፡፡ ጥ/ ከመሰረተ ሀሳብነት ደረጃ ባለፈ ተግባራዊነቱ ምን ይመስላል? መ/ በአዲስ አበባ ባሉ ሆስፒታሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ብዙ ጊዜ አልጋዎች እየሞሉ ምጥ የያዛቸው እናቶች ከሆስፒታል ወደ ሆስፒታል የሚላኩበት አሰራር አለ፡፡ ኦፕራሲዮን የሚያደርግ ሐኪም የለም ወይንም ኦፕራሲዮን የሚሰራበት እቃ የለንም በሚል እናቶች ወደሌላ ሆስፒታል የሚላኩበት አጋጣሚም ይስተዋላል። ከዚህም በተጨማሪ ውሀ የለም ወይንም መብራት የለም የሚሉ ምክንያቶችም የሚሰጡ አይጠፉም፡፡ በተለይ በጋንዲ ሆስፒታል አብዛኛው የሪፈራል ምክንያት የአልጋ ጥበት ነው፡፡ በሆስፒታሉ በቀን ከ25-30/ እናቶች የማዋለድ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ከዚህ በላይ ግን በቀን እስከ 40 ወይንም ከዚያ በላይ እናቶች ቢመጡ ለማዋለድ የሚያስችል አቅም ስለማይኖር በየቀኑ ከአምስት እስከ ሰባት የሚሆኑ እናቶች በየቀኑ ወደሌላ ሆስፒታል ሪፈር ሊባሉ ይችላሉ፡፡ ጥ/ ምጥ የያዛትን ሴት ሪፈር ለማለት የምጡ ደረጃ ወይንም የሴትየዋ አቅም የሚለካበት አሰራር አለ? መ/ በጋንዲ ሆስፒታል በጭራሽ ሪፈር የማይባሉ እናቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ... በምጥ ሰአት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ያለባት ከሆነ፣ ቀደም ሲል ሁለት ጊዜ በኦፕራሲዮን የተገላገለች ከሆነች፣ የማህጸን መከፈት ደረጃው ስምንት ሴንቲ ሜትር እና ከዚያ በላይ ከሆነ፣ ልጁ በከፍተኛ ሁኔታ መታፈን ያለበት ከሆነ እና ሕይወቱን ሊያሳጣው ይችላል ተብሎ ከታመነ፣ የጽንሱ አቀማመጥ በአግድም በመሳሰለው ሁኔታ ካለ እናትየው ሪፈር አትደረግም፡፡ ከላይ ከተጠቀሱትና መሰል ምክንያቶች ውጭ ግን ምጡ አሳሳቢ ወይንም አስቸጋሪ ካልሆነና ጊዜ የሚሰጥ ከሆነ አልጋ ከሌለ ሪፈር ይባላሉ፡፡ ማንኛዋም እናት ሪፈር ከመባልዋ በፊት ግን በሐኪም ታይታ እና ተመዝግቦ ነው ውሳኔው የሚሰጠው፡፡ ጥ/ ምጥ የያዛት ሴት ወደሌላ ሆስፒታል ሪፈር ስትባል ልትሄድ የምትችልበት ሆስፒታል ይነገራታል? ወይንስ እራስዋ ፈልጋ እንድትሄድ ነው የሚደረገው? መ/ ይህ አገልግሎት አሁን በተጀመረው አሰራር ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ጤና ጥበቃና አዲስ አበባ ጤና ቢሮ አንድ ላይ በመሆን የአሰራር መረብ ዘርግተዋል፡፡ በዚህ አደረጃጀትም እያንዳንዱ ሆስፒታል በስሩ ከስምንት እስከ አስራ አንድ የሚደርሱ ጤና ተቋማት ተደልድለውለታል፡፡ ለምሳሌም ጋንዲ ሆስፒታል በስሩ አስራ አንድ ጤና ጣቢያዎች አሉ፡፡ እነዚህ አስራ አንድ ጤና ጣብያዎች ምጥ የያዛቸውን ሴቶች ሪፈር የሚያደርጉት በቀጥታ ለጋንዲ ሆስፒታል እንጂ ለሌላ ሆስፒታል አይደለም። በዚሁ መንገድ ሁሉም የጤና ጣብያዎች ሪፈር የሚያደርጉት ለተመደቡበት ሆስፒታል ብቻ ነው። ስለዚህ አሁን በተጀመረው አሰራር ኮማንድ ፖስት፣ ጤና ጣቢ ያዎቹና ሆስፒታሎቹ በመናበብ የሚሰሩበት ነው፡፡ በየሆስፒታሉም ላይዘን ኦፊስ የሚባል ቢሮ ስለተቋቋመ በዚህ የተመደበው ኦፊሰር ከሌላ ሆስፒታል የላይዘን ኦፊሰር ጋራ የስልክ ግንኙነት በማድረግ አልጋ የት እንዳለ በማመቻቸት አገልግሎቱን ወደሚያገኙበት ተቋም እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡ የእናቶች ተገቢውን የጤና አገልግሎት የማግኘት አሰራር የመንግስትም ከፍተኛ ትኩረት ስለሆነ ሆስፒታሎችን እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የጤና ተቋማትን በአስፈላጊው ደረጃ እያሟሉና የተሻለ አሰራር እየዘረጉ ስለሆነ አሁን የተሻለ አሰራር ይታያል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የእናቶች ሪፈራል አሰራር በአብዛኛው ከጋዲ መታሰቢያ ሆስፒታል አሰራር ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ዶ/ር አብዱርቃድር መሐመድ ሰይድ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜዲንል ዳይሬክተር የሚከተለውን ብለዋል፡፡ “...በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስር ስምንት የሚሆኑ ጤና ጣቢያዎች ተመድበዋል፡፡ ከእነዚህ ጤናጣቢያዎች ጋር ሆስፒሉ በቅርብ እየተገናኘ የሚገጥሙዋቸውን ችግሮች በመወያየት የሚፈታበት አሰራር ተዘርግቶአል። በተለይም ምጥ የያዛቸው ሴቶችን በሚመለከት ሂደቱ እንዴት እንደነበርና ያጋጠመውን ችግር በመለየት በጤና ጣብያዎቹ ሊፈታ የማይችል ከሆነ በአገናኝ ባለሙያዎች አማካኝነት በመነጋገር ወደ ጥቁር አንበሳ እንዲመጡ እና አስፈላጊው ሕክምና ተደርጎላቸው እንዲወልዱ ይደረጋል። ማንኛዋም እናት አደጋ ውስጥ እንዳለች ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ምጡ ችግር አለበት የለበትም ወይንም በዚህ ጊዜ ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ በድንገት ሊፈጠር የሚችለውን ነገር አስቀድሞ መገመትም የሚያስቸግርበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ እናቶች ምጥ ይዞአቸው ወደሕክምና ተቋም ከደረሱ ጀምሮ ሁሉም ቦታ ትኩረት እንዲያገኙ ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አልጋ የማይኖር ከሆነ እና ችግሩ ብዙም አሳሳቢ ካልሆነ በአገናኝ መኮንኖቹ አማካኝነት በመነጋገር ወደሌላ ሆስፒ ታል የምንልክበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ አጠቃላይ የሪፈራል አሰራሩን በሚመለከት ብዙ የተሻሻለ ነገር ያለ ሲሆን ገና ብዙ መስተካከል ያለበት ነገር እንደሚኖር እናምናለን፡፡

Published in ላንተና ላንቺ
Saturday, 28 December 2013 10:18

ሐረር ቢራን ማን ያድነዋል?

             በፕሪሚዬር ሊግ ምስራቅ ኢትዮጵያን በመወከል ብቸኛው የሆነው ሐረር ቢራ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት በማጣት፤ በአደረጃጀት ችግሮች ህልውናው አደጋ ውስጥ ነው፡፡ በችግሮች እንደተውተበተበ ፕሪሚዬር ሊግን ሲሳተፍ ሁለተኛ የውድድር ዘመኑ ነው፡፡ የውድድር ዘመኑ ሳይጋመስ ሐረር ቢራ መፍረስ ፤ መገለልና መሸጥ የተጋረጡበት ሶስት አደጋዎች ናቸው፡፡ ከ4 ዓመታት በፊት በሐረር ቢራ ክለብ በረዳት አሰልጣኝነት መስራት የጀመረው አሁን ዋና አሰልጣኝ የሆነው ሳምሶን አየለ ከስፖርት አድማስ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ክለቡን ከተጋረጠበት አደጋ ማዳን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ይገልፃል፡፡ሐረር ቢራ ካሉበት አሳሳቢ ችግሮች ጋር ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በሊጉ ሊቆይ የበቃው በተጨዋቾች ቁጭት እና መስዕዋትነት መሆኑን ሳምሶን ሲናገር፤ በሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ስለተነፈገው አጣብቂኙ ተፈጥሯል ብሏል፡፡ የምስራቅ ኢትዮጵያ ውክልናው ሐረር ቢራ የእግር ኳስ ክለብ በፕሪሚዬር ሊግ በቋሚነት በመሳተፍ እና ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ በመቅረብ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ ተጨዋቾች በማፍራት እና ምስራቅ ኢትዮጵያን በመወከል በአገሪቱ እግር ኳስ ጉልህ ሚና ነበረው፡፡ እነ ይድነቃቸው፤ ተከተል ኡርጌቾ የሚታወሱ የክለቡ የቀድሞ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

በክለቡ አሰልጣኝነት ከሰሩት መካከል ደግሞ እነወርቁ ደርገባ፤ እነ ወንድማኝ ከበደ እና እነ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ይጠቀሳሉ፡፡ ሐረር ቢራ በፕሪሚዬር ሊግ ነባር ክለብ ሆኖ መቆየቱ ብቻ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ በአንዳንድ የአገሪቱ ክልሎች ለምሳሌ በትግራይ እና አማራ ለክለቦቻቸው ከፍተኛ በጀት እያወጡ የሊጉን ተሳትፎ ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡ ምስራቅ ኢትዮጵያን በመወከል የፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊነቱ ሳያጣ መቆየቱ እንደአርዓያ ሊታይ ይገባው ነበር፡፡ እንደ ዋና አሰልጣኙ ሳምሶን አየለ ገለፃ ሐረር ቢራ ክለብን ከኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ማጣት የክልሉን እግር ኳስ ወደ ኋላ መጎተት ይሆናል ፡፡ በተለይ በክልሉ ወጣቶች ላይ ተስፋ መቁረጥ የሚያመጣ መሆኑ ያሳስበኛል ይላል፡፡ እንደ ሐረር አይነት ክለብ አሁን ባለበት የተዳከመ ሁኔታ ከሊጉ የሚወርድ ከሆነ ወደ ውድድር ለመመለስ ከባድ ፈተና ይሆናል ብሎ አሰልጣኝ ሳምሶን የተጋረጠውን አደጋ ያሳስባል፡፡ ማነው ባለቤቱ? ሐረር ቢራ የእግር ኳስ ክለብ በዋናነት ህልውናውን አደጋ ላይ የወደቀው ባለቤት በማጣቱ ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የክለቡ ባለቤት እና አስተዳደሪ የነበረው የሐረር ቢራ ፋብሪካ ለታዋቂው የአውሮፓ ቢራ ጠባቂ ኩባንያ ሄኒከን ከተሸጠ በኋላ የተከሰተ ነው፡፡ ሄኒከን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ትልልቅ የስፖርት ውድድሮችን በስፖንሰርሺፕ በመደገፍ የሚታወቅ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ላለፉት ሁለት ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ 24 ሚሊዮን ብርም ከፍሏል፡፡

የሆላንዱ ቢራ ጠባቂ ኩባንያ በፖሊሲው የእግር ኳስ ክለብ ይዞ ለመቀጠል አለመፈለጉ ክለቡን ለችግር ያጋለጠ አቅጣጫ ነው፡፡ ሐረር ቢራ ክለብ ላለፉት ሁለት አመት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለቤት የሌለው ሆኗል፡፡ ከሄኒከን በፊት የእግር ኳስ ክለቡ በባለቤትነት ያስተዳደር የነበረው በመንግስት ስር የነበረው የሐረር ቢራ ፋብሪካ ነው፡፡ ያኔ የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ የነበሩት እና አሁን የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጁነዲን ባሻ የክለቡ የበላይ ጠባቂ ነበሩ፡፡ አቶ ጁነዲን በሚያደርጉት የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ የክለቡ አስተዳደር በመልካም ሁኔታ ላይ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ክለቡ ከሰራተኛ በሚወጣለት መዋጮ ፋብሪካውንና ከተማውን ወክሎ ሲወዳደር ቆይቷል፡፡ የሐረር ነዋሪዎች እና የፋብሪካው ሰራተኞች ክለቡን ለመደገፍ ብዙ ርቀት ሁሉ ተጉዘዋል፡፡ በሄኒከን ባለቤትነት ፋብሪካው ከተያዘ በኋላ ሃላፊዎች ሰራተኛውን ሰብስበው ፖሊሲያችን ስለማይፈቅድ ክለቡን በባለቤትነት አናስተዳድርም ብለው አሳወቁ፡፡ ከዚያን ግዜ ወዲህ ክለቡ በችግሮች ውስጥ ገብቷል፡፡ ክለቡ ሐረርን አይወክልም የሚል ሙግት ነበር፡፡ አሁን ባለው የቡድን ስብስብ ሁለት የሐረር ልጆች ቋሚ ተሰላፊዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ 8 ተጨዋቾች ከክልሉ የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ዋና አሰልጣኝ ሳምሶን የፋብሪካው ማኔጅመንት ክለቡን አዳክሞ እና አፍርሶ ፖሊሲውን መተግበር አልነበረበትም ይላል፡፡ ከክለቡ ትልቅ ታሪክ አንፃር በነበረበት የአደራጀጀት ሁኔታ እና የተሟላ የፕሪሚዬር ሊግአቅም በመመለስ ለሌላ ባለቤት ማዛወር እንደሚገባ ይመክራል፡፡ ህልውናውን ያሳጡት ሌሎች ችግሮች ባለፉት ሁለት ዓመታት የሐረር ቢራ ክለብ በቂ የአስተዳደር መዋቅር ሳይኖረው ቆይቷል፡፡

ክለቡ በእግር ኳስ ፌደሬሽን የመወዳደርያ ደንብ አንድ የሊግ ክለብ ሊያሟላ የሚገባውን አደረጃጀት አያሟላም፡፡ ክለቡ በፕሪሚዬር ሊግ ሲወዳደር የክለቡ ስራ አስኪያጅ፤ የቡድን መሪ፤ ገንዘብ ያዥ እና ዋና ፀሃፊ አንድ ግለሰብ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የ15 የስራ ሃላፊነቶች ተገቢው ሰው ሳይመደብላቸው እየተሰራ መቆየቱ ይገርማል፡፡ የ2006 የውድድር ዘመን ሲጀመር ክለቡ ከ12 በላይ ወሳኝ ተጨዋቾችን በዝውውር ገበያው ያለአግባብ ማጣት ግድ ሆኖበታል፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ባፈረሱት ኮንትራት ተመላሽ የሆነ 1.5 ሚሊዮን ብር ለተተኪ ተጨዋቾች ግዢ ከሚሆን ይልቅ ገቢ የሆነው ለፋብሪካው ነው፡፡ የክለቡ ካምፕ ብዙ ነገር ያልተሟላለት፤ ተገቢውን ድጋፍ ለተጨዋቾች የማይሰጥ ነው፡፡ የክለቡ ተጨዋቾች በአንድ ወቅት አንሶላ አጥተው ማልያቸውን እያነጠፉ ተኝተዋል፡፡ በካምፑ ለእረፍት መዝናኛ የሚሆናቸው ቴሌቭዥን እንኳን የላቸውም፡፡ የምግብ አቅርቦቱም የተሟላ አይደለም፡፡ ክለቡ በቂ አስተዳደር ስራ ስለማያከናወን በፕሪሚዬር ሊጉ ካሉ ክለቦች በመላው አገሪቱ ብዙ ርቀቶችን ምቹ ባልሆኑ የትራንስፖርት ሁኔታዎች በመጓጓዝ እየሰራ መቆየቱ ለመጎዳቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ ግልፅ አይደለም እንጂ ክለቡ ከፋብሪካው በዓመት እስከ 10 ሚሊዮን ብር በጀት ቢኖረውም ባለው የአስተዳደር ችግር አይጠቀምበትም፡፡ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለና የተሟጠጠው ትግስቱ የሐረር ቢራ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ከ1977 ጀምሮ እስከ 1990 ዓም በታዋቂው የእርሻ ሰብል ክለብ ተጨዋች ነበር፡፡

ከእርሻ ሰብል ከለቀቀ በኋላ ወደ ስልጠናው የገባው በታዳጊ እና ወጣቶች ፕሮጀክት ያሉ ቡድኖችን በማሰልጠን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ባህርዳር ከነማ እና አልሜዳ ጨርቃጨርቅ የተባሉ የብሄራዊ ሊግ ክለቦችን በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ልምድ አለው፡፡ አሰልጣኝ ሳምሶን ሐረር ቢራ ክለብን የተቀላቀለው በ2004 ዓ.ም ላይ የክለቡ አሰልጣኝ ለሆነው ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ረዳት ሆኖ ነበር፡፡ በ2005 ዓ.ም የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተቀጠረ በኋላ እነሆ ሁለተኛ የውድድር ዘመኑን ከክለቡ ጋር በፕሪሚዬር ሊግ እያሳለፈ ነው፡፡ አሁን ግን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ትእግስቱ አልቋል፤ በመጭው የጥር ወር ክለቡ በአፋጣኝ በሊጉ ተፎካካሪ ሆኖ የሚቀጥልበትን ሁኔታ ካልፈጠረ፤ በዝውውር ገበያው ቢያንስ 5 ተጨዋቾች ካልገዛ ሃለፊነቱን በገዛ ፍቃዴ ለመልቀቅ ወስኛለሁ ብሏል፡፡ መጨረሻው ምን ይሆናል? ባለፉት 20 ዓመታት የኢትዮጵያ ክለቦች ከፍተኛ ውድድር በሆነው ፕሪሚዬር ሊግ በቋሚ ተሳታፊነት ሲወዳደር ነበር፡፡ በ2001 ዓም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን ሆኖ በ2002 ዓም በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌደሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣርያ ተሳትፎ ነበረው፡፡ ክለቡን ለመግዛት ሐረር ከነማ፤ ድሬዳዋ ከነማ፤ ባህርዳር ከነማ፤ መተሃራ ስኳር ፍላጎት ነበራቸው፡፡ እሰከ 20 ሚሊዮን ብር ሊያወጣ ይችላል፡፡ ግን በተሟላ አደረጃጀት እና በጠንካራ ስብስብ ላይ አለመገኘቱ ይህ አይነቱን የባለቤትነት ሽያጭ ለማድረግ አይመችም፡፡

አትሌት ቀነኒሣ በቀለ ከ2 ሳምንት በኋላ በስኮትላንድ ኤደንብራ አገር አቋራጭ በታሪክ ለ6ኛ ጊዜ እንደሚሳተፍ ታወቀ፡፡ በጭቃማና አስቸጋሪ መሮጫው በሚለየው ኤደንብራ አገር አቋራጭ በ4 ኪሎ ሜትር ውድድር ከ2006 እ.ኤአ ጀምሮ ሲሳተፍ በዚሁ ለ3 ዓመታት አከታትሎ ያሸነፈው አትሌቱ በ2010 እ.ኤ.አ 2ኛ እንዲሁም ባለፈው ዓመት 11ኛ ደረጃ ነበረው፡፡ የዘንድሮው ተሳትፎ ወደ አሸናፊነቱ ለመመለስ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በዓለም አገር አቋራጭ ውድድሮች በከፍተኛ ውጤት የሚመራው ቀነኒሣ፤ በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር 4ኪሎ ሜትርና በ12 ኪሎ ሜትር ረዥም ርቀት ውድድሮች11 የወርቅ ሜዳልያዎች መሰብሰቡ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል በ2014 የለንደን ማራቶን አዘጋጆች የዓለም ሪከርድ ባለቤት የሆነውን ኬንያዊውን ዊልሰን ኪፕሳንግ፣ እንግሊዛዊውን ሞ ፋራህና ቀነኒሣን የማገናኘት ዕቅድ አላቸው ፡፡ ከሞ ፋራህ ይልቅ የማራቶን ክብረወሰንን ለመስበር እድሉ ለቀነኒሳ በቀለ እንደሆነም ይገለፃል፡፡ የማራቶን ሪከርድ በዊልሰን ኪፕሳንግ 2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ23 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ የተያዘ ነው፡፡ ቀነኒሣ ወደ ማራቶን ፊቱን እንዳዞረ ዋናው ፍላጎቱ በ2016 እኤአ ላይ በሪዮዲጄኔሮ በሚደረገው 31ኛው ኦሎምፒያድ በ34 ዓመቱ በመሳተፍ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት እንደሆነ በመግለፅ ነበር፡፡ በ2014 ወደ ማራቶን ሙሉ ለሙሉ ለመግባት እቅድ እንዳለው መናገሩም የሚታወስ ነው፡፡ ቀነኒሣ በቀለ ባለፉት 3 የውድድር ዘመናት ከነበረበት ጉዳት በተያያዘ ከውድድር እንደተገለለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ አሁን የዓለማችን የምንጊዜም ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጭ ተብሎ የሚደነቀው ቀነኒሣ በቀለ የመጀመርያው ማራቶኑን የት ሊሮጥ ነው? እንዴት እየተዘጋጀ ነው ?ለተሳትፎ ስንት ይከፈለዋል? ምርጥ ሰዓት ያስመዘግባል ወይ? ሪከርድስ ሊሰብር ይችላል? በሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በአትሌቲክሱ ዓለም እያነጋገረ ነው፡፡ የ31 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሣ‹‹ ማራቶንን ከሮጥኩ ለማሸነፍ ነው፡፡ በመጥፎ ውጤት ልጀምር አልፈልግም፡፡ ብሎ ለአይኤኤኤፍ የተናገረ ሲሆን ‹‹ የመጀመርያው ማራቶኔን የት እንደምሮጥ አላውቀውም፡፡ በሩጫ ዘመኔ ያስመዘገብኳቸው ትልልቅ ታሪኮችን በሚመጥን ደረጃ መሮጥ ግን እፈልጋለሁ፡፡ እንዳለኝ ውጤታማነት በቂ የተሳትፎ ክፍያ የሚያቀርብልኝን እየጠበቅኩ ነው፡፡ ሁሉ እስኪሳካ ጉዳዩን ምስጥር ማድረግም ተገቢ ነው፡፡ ምርጫዬ ትልቅ ክብር እና ታሪክ ያለው፤ ምርጥ አትሌቶችን የሚያሳትፍ የማራቶን ውድድር ነው፡፡ በማይረባ የማራቶን ውድድር እና ጥሩ ገቢ በማይገኝበት ሁኔታ አጥንቴን አልሰነጥቅም›› በሚል ማብራራያም ሰጥቷል፡፡ ‹‹ፈጣን ሰዓት ለማስመዝገብ ስለምፈልግ በከፍተኛ ትኩረት ጠንካራ ዝግጅት እያደረግኩ ነኝ፡፡ 2፡03፤ 2፡05፤ 2፡06 እገባለሁ ብዬ ለመናገር አልችልም፡፡ ዋናው በቂ እና የተሟላ ዝግጅት ማድረግ ነው፡፡ ልምምዱ ፈታኝ ነው፡፡ ሁሉን ተቋቁሞ በስነልቦና ጠንካራ ሆኖ ራሴን በማነሳሳት ጥሩ ውጤት ለማምጣት ፍላጎት አለኝ፡፡›› ብሏል፡፡‹‹አንዳንድ ሯጮች ማራቶን ከ30 ኪሎሜትሮች በኋላ ፈታኝ ይሆናል ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከ35፤ ከ38 እና ከ40 ኪሎሜትሮች በኋላ ማራቶንን መሮጥ እንደሚከብድ ይገልፃሉ፡፡ የማራቶን ልምድ በእያንዳንዱ አትሌት ብቃት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ገልፆታል፡፡ ቀነኒሣ የማራቶን ልምምዱን ካለፈው ሁለት ወር ወዲህ እየሰራ ነው፡፡ ከባህር ጠለል በታች 2700 ሜትር ከፍታ ባላቸው ሱልልታ እና ሰንዳፋ፡፡ ለማራቶን መዘጋጀት ሲጀምር ከነበረው መደበኛ ልምምድ ባሻገር በሳምንት ፕሮግራሙ ላይ 3 ሰዓት ተጨማሪ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ በሳምንት 130 ኪሎሜትሮችን እየሮጠ ነው፡፡ ከተግባር ልምምዱ ባሻገር በማራቶን ውድድር የአሁን ዘመን አትሌቶች ያላቸውን ልምድ እና ውጤት የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ድረገፆችን እየተከታተለ ያጠናልም፡፡ ማናጀሩ የሆኑት ሆላንዳዊው ጆስ ሄርማንስ የመጀመርያ ማራቶኑን የት ሊሮጥ እንደሚችል፤ ስንት ሊከፈለው እንደሚገባ እና ከየትኞቹ አትሌቶች ጋር ሊፎካከር እንደሚችል በማጥናት መላው የዓለም አትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች ሁኔታውን በጉጉት እንዲጠባበቅ በሚያደርግ ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡ ከታላላቅ የማራቶን ውድድሮች ለቀነኒሣ በቀለ የመጀመርያ ማራቶን ተሳትፎ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው የለንደን ማራቶን ነው፡፡ የለንደን ማራቶን አዘጋጆች ለአትሌት ቀነኒሣ በቀለ ተሳትፎ ብቻ እሰከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ የመክፈል ፍላጎት እንዳላቸው ከተወራ ሰነባብቷል፡፡ ከ3 ወራት በፊት በቡፓ ግሬት ኖርዝ ራን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የመጀመርያ ግማሽ ማራቶኑን ሲያሸንፍ በመጨረሻዎቹ ሜትሮች ሞ ፋራህን ቀድሞ በመግባት ነበር፡፡ ውድድሩ ካለቀ በኋላ ሞ ፋራህ ለንደን እንገናኝ ብሎታል፡፡ የለንደን ማራቶን አዘጋጆች ሞ ፋራህ ከቀነኒሳ ጋር የመጀመርያ ማራቶኑን እንዲወዳደር እያግባቡ ናቸው ፡፡ ቀነኒሳ የመጀመርያ ማራቶኑን የት ሊሮጥ እንደሚችል በይፋ አልተናገረም፡፡ የኒውዮርክ ፤የሮተርዳምና የበርሊን ማራቶን አዘጋጆችም የቀነኒሣን ተሳትፎ ይፈልጋሉ፡፡ ራነርስ ዎርልድ በአትሌት ቀነኒሣ በቀለ የመጀመርያው ማራቶን ተሳትፎ ዙርያ በሰራው ትንተና ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ 05 ሰኮንዶች በማጠናቀቅ ሪከርድ ሊያስመዘግብ እንደሚችል ወይም 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ10 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ በማስመዝገብ መልካም አጀማመር ሊኖረው እንደሚችል ገምቷል፡፡

Monday, 23 December 2013 11:31

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!
ነ.መ

ሙት - ዓመት በቃል አይገባም፡፡
ቢሆንም አሴ ቢሆንም፤
     በመንፈስ ፅናት ውስጥ‘ኮ
     በመንፈስ ጽዳት ውስጥ‘ኮ
        ጊዜም ቦታም ተነው ቢያልቁ፣ ድምፅ አለ ሩቅ እሚያግባባ!
     የሚናገር ልሣን አለ፣ ያገርን ፈገግታና ዕንባ!
       ነብስ - አጥንት ድረስ ዘልቆ፣ ዕውነቱ ሲያስቡት
     ቢያምም
     ባገር ነገር ሆድ - አይቆርጥም፣
     ተራቁታ ብናያት እንኳ፣ እርቃኗም የእኛ ነው
     ዛሬም!
አሴ!
አልበራ ባለው መብራትም፣ እኛ ተስፋችን
ይበራል
አላናግር ባለው ስልክም፣ እኛ ድምፃችን
ይሰማል
ባላደገ የዕድገት ቀንም፣ እኛ ቀናችን ይነጋል
ለተቀጨ ምኞት ሳይቀር፣ ራዕይ ወጌሻ ሆነናል
ተሰደው በተመለሱ፣ ብዙሃን ግፉዓን ዕድል
ሄደው ተሰደው በቀሩም፤ ብዙሃን መንገደኞች
ውል
ስለአገር መጮህ አይቀርም፣ በዕልቆ - መሣፍር
ምሬት ቃል
ስለዚህ ካለህበቱ፣ አሴ ዛሬም ፈገግ በል!
የልብን መሙላት ነው የሰው - ድል፣ አሴ ሰላም
እንባባል!!
በሳቅህ ቁጥር ነው ሀሳብህ፣ እንደ ኤርታሌ
እሚያቃጥል
በሳቅህ ቁጥር ነው ህልምህ፣ እንደተራራ
እሚሰቀል
በሳቅህ ቁጥር ነው ዓላማህ፣ እንደ ሊማሊሞ
እሚገዝፍ
በሳቅህ ቁጥር ነው አድማስ፣ እሚዳረስ ከፅንፍ
ፅንፍ
ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!...
ፈገግ በል አሴ፤ ፈገግ በል……

(ለአሰፋ ጐሣዬ 9ኛ ሙት ዓመት) ከመላው ቤተሰብና ከወዳጆቹ ታህሣሥ 11/ 2006 ዓ.ም

Published in የግጥም ጥግ
Monday, 23 December 2013 11:31

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!
ነ.መ

ሙት - ዓመት በቃል አይገባም፡፡
ቢሆንም አሴ ቢሆንም፤
     በመንፈስ ፅናት ውስጥ‘ኮ
     በመንፈስ ጽዳት ውስጥ‘ኮ
        ጊዜም ቦታም ተነው ቢያልቁ፣ ድምፅ አለ ሩቅ እሚያግባባ!
     የሚናገር ልሣን አለ፣ ያገርን ፈገግታና ዕንባ!
       ነብስ - አጥንት ድረስ ዘልቆ፣ ዕውነቱ ሲያስቡት
     ቢያምም
     ባገር ነገር ሆድ - አይቆርጥም፣
     ተራቁታ ብናያት እንኳ፣ እርቃኗም የእኛ ነው
     ዛሬም!
አሴ!
አልበራ ባለው መብራትም፣ እኛ ተስፋችን
ይበራል
አላናግር ባለው ስልክም፣ እኛ ድምፃችን
ይሰማል
ባላደገ የዕድገት ቀንም፣ እኛ ቀናችን ይነጋል
ለተቀጨ ምኞት ሳይቀር፣ ራዕይ ወጌሻ ሆነናል
ተሰደው በተመለሱ፣ ብዙሃን ግፉዓን ዕድል
ሄደው ተሰደው በቀሩም፤ ብዙሃን መንገደኞች
ውል
ስለአገር መጮህ አይቀርም፣ በዕልቆ - መሣፍር
ምሬት ቃል
ስለዚህ ካለህበቱ፣ አሴ ዛሬም ፈገግ በል!
የልብን መሙላት ነው የሰው - ድል፣ አሴ ሰላም
እንባባል!!
በሳቅህ ቁጥር ነው ሀሳብህ፣ እንደ ኤርታሌ
እሚያቃጥል
በሳቅህ ቁጥር ነው ህልምህ፣ እንደተራራ
እሚሰቀል
በሳቅህ ቁጥር ነው ዓላማህ፣ እንደ ሊማሊሞ
እሚገዝፍ
በሳቅህ ቁጥር ነው አድማስ፣ እሚዳረስ ከፅንፍ
ፅንፍ
ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!...
ፈገግ በል አሴ፤ ፈገግ በል……

(ለአሰፋ ጐሣዬ 9ኛ ሙት ዓመት) ከመላው ቤተሰብና ከወዳጆቹ ታህሣሥ 11/ 2006 ዓ.ም

Published in የግጥም ጥግ
Monday, 23 December 2013 10:24

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!

ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!
ነ.መ

ሙት - ዓመት በቃል አይገባም፡፡
ቢሆንም አሴ ቢሆንም፤
     በመንፈስ ፅናት ውስጥ‘ኮ
     በመንፈስ ጽዳት ውስጥ‘ኮ
        ጊዜም ቦታም ተነው ቢያልቁ፣ ድምፅ አለ ሩቅ እሚያግባባ!
     የሚናገር ልሣን አለ፣ ያገርን ፈገግታና ዕንባ!
       ነብስ - አጥንት ድረስ ዘልቆ፣ ዕውነቱ ሲያስቡት
     ቢያምም
     ባገር ነገር ሆድ - አይቆርጥም፣
     ተራቁታ ብናያት እንኳ፣ እርቃኗም የእኛ ነው
     ዛሬም!
አሴ!
አልበራ ባለው መብራትም፣ እኛ ተስፋችን
ይበራል
አላናግር ባለው ስልክም፣ እኛ ድምፃችን
ይሰማል
ባላደገ የዕድገት ቀንም፣ እኛ ቀናችን ይነጋል
ለተቀጨ ምኞት ሳይቀር፣ ራዕይ ወጌሻ ሆነናል
ተሰደው በተመለሱ፣ ብዙሃን ግፉዓን ዕድል
ሄደው ተሰደው በቀሩም፤ ብዙሃን መንገደኞች
ውል
ስለአገር መጮህ አይቀርም፣ በዕልቆ - መሣፍር
ምሬት ቃል
ስለዚህ ካለህበቱ፣ አሴ ዛሬም ፈገግ በል!
የልብን መሙላት ነው የሰው - ድል፣ አሴ ሰላም
እንባባል!!
በሳቅህ ቁጥር ነው ሀሳብህ፣ እንደ ኤርታሌ
እሚያቃጥል
በሳቅህ ቁጥር ነው ህልምህ፣ እንደተራራ
እሚሰቀል
በሳቅህ ቁጥር ነው ዓላማህ፣ እንደ ሊማሊሞ
እሚገዝፍ
በሳቅህ ቁጥር ነው አድማስ፣ እሚዳረስ ከፅንፍ
ፅንፍ
ብቻ አንድ ጊዜ ፈገግ በል!...
ፈገግ በል አሴ፤ ፈገግ በል……

(ለአሰፋ ጐሣዬ 9ኛ ሙት ዓመት) ከመላው ቤተሰብና ከወዳጆቹ ታህሣሥ 11/ 2006 ዓ.ም

Published in የግጥም ጥግ
Monday, 23 December 2013 10:23

የሎተሪው እጣ

ኢቫን ዲሚትሪች፤ እራቱን በልቶ እንዳበቃ ሶፋው ላይ ተቀምጦ የዕለቱን ጋዜጣ ማንበብ ጀመረ፡፡ በዓመት 1200 ሩብል ደሞዝ የሚያገኘው ዲሚትሪች፤ከቤተሰቡ ጋር መካከለኛ ኑሮ የሚመራ ደስተኛ  አባወራ ነው፡፡
 “ዛሬ እርስት አድርጌው ጋዜጣውን አልተመለከትኩም” አለችው ሚስቱ፤እራት የበሉበትን ጠረጴዛ እያፀዳዳች “እስቲ የሎተሪ ዕጣ ዝርዝር ወጥቶ እንደሆነ ተመልከትልኝ”
“አዎ ወጥቷል” ከመቅፅበት መለሰላት፤ ኢቫን ዲሚትሪች “ግን ያንቺ ሎተሪ ጊዜው አላለፈበትም እንዴ?”
“በፍፁም፤ ማክሰኞ እኮ አይቼው ነበር”
“ቁጥሩ ስንት ነው?”
“የኮድ ቁጥሩ 9‚499፣ የእጣው ቁጥር ደግሞ 26”
“ደህና እንግዲህ፤ የኮዱንም የእጣውንም ቁጥር እናየዋለን”
ኢቫን ዲሚትሪች፤ በሎተሪ እድል የሚያምን ሰው አይደለም፡፡ ሎተሪም ገዝቶ፣ አሸናፊ የእጣ ቁጥሮችንም ተመልክቶ አያውቅም፡፡ አሁን ግን ሌላ የሚሰራው ነገር ስለሌለውና ጋዜጣውም ዓይኑ ስር ስለሆነ፣ ጣቱን አሸናፊ የእጣ ቁጥሮች ወደተደረደሩበት የጋዜጣው ረድፍ በመላክ መመልከት ጀመረ፡፡ የሎተሪ ዕድል ላይ ያለውን ጥርጣሬ የሚፈታተን በሚመስል መልኩ፣ ገና አንደኛውን  መስመር እንዳለፈ፣ 9‚499 የሚል ቁጥር ተመለከተ፡፡ ዓይኑን ፈጽሞ ማመን አቃተው። ጥርጣሬውን ለማጥራት ዳግም ጋዜጣው ላይ አፈጠጠ፡፡ የተለወጠ ነገር ግን የለም፡፡ 9‚499 - ይላል በሁለተኛ መስመር ላይ የሰፈረው  የኮድ ቁጥር፡፡ ከመቅፅበት ጋዜጣውን ጉልበቱ ላይ ቁጭ አደረገው፡፡ የተለያዩ ስሜቶች ተፈራረቁበት - ድንጋጤ፣ መገረም፣ መደነቅ፣ እና ደስታ፡፡ የፊቱ ገፅታ ላይ ጎልተው የሚታዩት ግን የግርምትና የድንጋጤ ስሜቶች ናቸው፡፡
 “ማሻ፤ ቁጥሩ ጋዜጣው ላይ ወጥቷል --- 9‚499 የሚለው” አለ፤ ኦና በሚመስል የተዋጠ ድምጽ፡፡  
ሚስቱ ግርምትና ድንጋጤ የወረሰውን ፊቱን ባትመለከት ኖሮ እየቀለደ መስሏት ነበር፡፡
“9‚499?” ጠየቀችው፤ በድንጋጤ ተውጣና የተጣጠፈውን የጠረጴዛ ልብስ ጠረጴዛው ላይ እየጣለች፡፡
“አዎ…አዎ….የምሬን ነው --- ጋዜጣው ላይ ወጥቷል!”
“የእጣው ቁጥርስ?”
“አዎ-- እሱም አለ…ግን ቆይ… ማለቴ ---ለማንኛውም የኮዱ ቁጥር አለ! ገባሽ--”
ኢቫን ዲሚትሪች፤ ለሚስቱ ምክንያት አልባ ፈገግታ ለገሳት - ልክ ህፃን ልጅ  አንፀባራቂ እቃ ሲያሳዩት እንደሚሆነው፡፡ እሷም አፀፋዋን በፈገግታ መለሰችለት፡፡ የኮዱን ቁጥር እንጂ የእጣውን ቁጥር አለመመልከቱ እምብዛም የቆረቆራት አትመስልም፡፡ ለነገሩ ራስን ባልተረጋገጠ የአዱኛ ተስፋ ማጓጓትና ማሰቃየት ሲጣፍጥ ለጉድ ነው ፤ በጣም ደስ ይላል!
ከረዥም ዝምታ በኋላ “የኮድ ቁጥሩ እኮ  የእኛ ነው--- ማንም የማይወስድብን” አለ ኢቫን ዲሚትሪች፤ “ስለዚህ ዕጣውን የምናሸንፍበት ዕድል አለን … ኮዱን ግን ወሰድነው!”
“በል አሁን --- የዕጣውን ቁጥር ተመልከት!”
“ትንሽ ቆዪ --- ለመበሳጨት የምን መጣደፍ ነው፡፡ የእኛ ቁጥር ከመጀመርያው ሁለተኛ መስመር ላይ ነው ያለው፡፡ እናም  ሽልማቱ 75ሺ ሩብል ነው፡፡ ይሄ ገንዘብ አይደለም ፡፡ ተዓምር ነው። የሃብት ተራራ! በደቂቃ ውስጥ ደግሞ ዝርዝሩን እንደገና እመለከተዋለሁ … 26 ነው አይደል? ግን የምር ቢደርሰንስ?”
ባልና ሚስቱ ሲሳሳቁ ቆዩና እርስ በእርስ መተያየት ጀመሩ - በዝምታ ተውጠው፡፡ የሎተሪ ዕድሉን እናሸንፋለን የሚለው ሃሳብ አቅላቸውን አስቷቸዋል፡፡ 75ሺ ሩብሉ ቢደርሳቸው--- ምን እንደሚሰሩበት፣ ምን እንደሚገዙበት፣ የት እንደሚጓዙበት… አላሰቡም፤ አላለሙም፡፡ እነሱ ማሰብና ማለም የቻሉት  9‚499 የሚለውን የኮድ ቁጥርና 75.000 ሩብሉን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ሎተሪውን ማሸነፍ ስለሚያጐናጽፋቸው ደስታ ትዝ አላላቸውም፡፡
ኢቫን ዲሚትሪች፤ ጋዜጣውን በእጁ እንደያዘ ከአንዱ ጥግ ወደ ሌላኛው ጥግ ብዙ ተመላለሰ። ከመጀመሪያው የድንጋጤ ስሜት ሲወጣ ነው ስለሎተሪው ገንዘብ ትንሽ ማሰብና ማለም የጀመረው፡፡
“ሎተሪውን ካሸነፍን…” አለ ለሚስቱ “በቃ…አዲስ ህይወት ነው የምንጀምረው፡፡ ሥር ነቀል ለውጥ ማለት ነው፡፡ በእርግጥ የሎተሪ ትኬቱ ያንቺ ነው፤ የእኔ ቢሆን ኖሮ ግን መጀመሪያ 25ሺውን ለሪል እስቴት አውለዋለሁ፡፡ 10ሺውን ደግሞ ለአስቸኳይ ወጪዎች… ለአዳዲስ የቤት ቁሳቁሶች… ለጉዞ… ለዕዳ መሸፈኛና ለመሳሰሉት፡፡ የቀረውን 40ሺ በቀጥታ ባንክ እከተውና ወለዱን መብላት!”
“አዎ፤ ሪል እስቴት ግሩም ሃሳብ ነው!” አለች ሚስቱ፤ ሶፋው ላይ እየተቀመጠችና እጆቿን ጭኖቿ ላይ እያሳረፈች፡፡ “ከቱላ ወይም ከኦርዮል ግዛቶች አንዱ ጋ ሊሆን ይችላል…በመጀመሪያ ደረጃ ግን እኛ የበጋ ቪላ አያስፈልገንም…እናም ቤቱ ሁሌም የገቢ ምንጭ ይሆናል ማለት ነው” ስትል ሚስቱ ማብራርያ ሰጠች፡፡
አሁን አዕምሮውን የሚያጨናነቁ ምናባዊ ምስሎች እየተግተለተሉ ይመጡበት ጀመር-ኢቫን ዲሚትሪች፡፡
እያንዳንዱ ምስል ደግሞ ከመጨረሻው የበለጠ የሞቀና የደመቀ፣ ቅንጡ ህይወትን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ በምናባዊ ምስሎቹ ሁሉ ራሱን በቅጡ ተመጋቢ፣ ጤናማና፣ የሰከነ አድርጐ ነው የሳለው። የወደፊቱን በአዱኛ የተሞላ ህይወት ሲያስብ ሞቅ አለው፤ ተኮሰም ሳያደርገው አልቀረም፡፡ በዚህ ህይወቱ …እንደ በረዶ የቀዘቀዘ  የበጋ ሾርባውን ካጣጣመ በኋላ፣ ከምንጩ አጠገብ እሚያቃጥለው አሸዋ ላይ ወይም እመናፈሻው ካለው የሎሚ ዛፉ ስር በጀርባው ይንጋለላል፡፡ አቤት ሲሞቅ! አቤት ሲያቃጥል! ... ትናንሽ ልጆቹ አጠገቡ እየዳሁ፣ አሸዋውን በጣታቸው ይቆፍራሉ፤ አሊያም ከሳሩ ላይ ቢራቢሮ እየያዙ  ይጫወታሉ፡፡ ትንሽ ደከም ሲለው--- ያለአንዳች ሃሳብ ጣፋጭ እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ዛሬ ቢሮ መሄድ ላያሰኘው ይችላል…ነገም ከነገወዲያም እንዲሁ ካላሰኘው ይቀራል፡፡ ዝም ብሎ መጋደምና መንጋለል ከሰለቸው ደግሞ የእንጉዳይ ማሳ ወዳለበት ጫካ ይሄዳል ወይም ገበሬዎች አሳ ሲያጠምዱ ቆሞ ይመለከታል፡፡ ፀሐይዋ መጥለቅ ስትጀምር፣ ፎጣና ሳሙናውን ይይዝና ወደ ገላ መታጠቢያው ያመራል፡፡ ዘና ብሎ ልብሱን ያወላልቅና እርቃን ደረቱን በእጁ ፈተግ ፈተግ ያደርጋል፤ ከዚያም ውሃው ውስጥ ይገባል። ገላውን ታጥቦ ሲያበቃ ደግሞ ሻይ በክሬም ይጠብቀዋል፡፡ መሸትሸት ሲል የእግር ጉዞ ያደርጋል ወይም ከጐረቤቶቹ ጋር ወግ ይጠርቃል …
ከሰጠመበት ምናባዊ ዓለም ድንገት ያነቃው የሚስቱ ንግግር ነበር፡፡
“አዎ፤ ሪል እስቴት መግዛት ግሩም ነው!” አለች፤ እንደሱ የሞቀና የደመቀ፣ ቅንጡ ህይወት ስታልም ቆይታ፡፡ በህልሞቿ እንደተደሰተች የፊቷ ገጽታ ይመሰክራል፡፡
ኢቫን ዲሚትሪች፤ የመከርን ዝናባማ ወቅትና ቀዝቃዛ ምሽቶች በምናቡ ይስል ገባ፡፡ በዚህ ወቅት በአትክልት መናፈሻውና በወንዙ ዳር ረዥም ጉዞ ያደርጋል፤ በደንብ እንዲቀዘቅዘው፡፡ ከዚያ ሲመለስ በትልቅ ብርጭቆ ቮድካ ይጐነጫል። ጨው የበዛበት እንጉዳይ ወይም ኩከምበር ይበላል፡፡ ከዚያ እንደገና ሌላ ቮድካ ይቀዳል… ልጆቹ ከጓሮ ካሮት ነቅለው አፈር አፈር እየሸተቱ ሲሮጡ ይመጣሉ፡፡ ወደ ኋላ ላይ ደግሞ ሶፋው ላይ በረዥሙ ተንፈላሶ በተንደላቀቀ ስሜት፣ በምስሎች የተሞላ መጽሔት ያገላብጣል፤ አሊያም ፊቱን ይሸፍንበታል፡፡ የካፖርቱን ቁልፎች ፈታቶም ራሱን ለእንቅልፍ ያዘጋጃል…
በመከር መገባደጃ ላይ የሚመጣውን የበጋ ወቅት ተከትሎ፣ ደመናማና ጭጋጋማ አየር ከተፍ ይላል፡፡ ቀንና ሌሊት ሲዘንብ ውሎ ሲዘንብ ያድራል፡፡ እርቃናቸውን የቆሙት ዛፎች፤ ከሰማይ የተቀበሉትን ዝናብ እንደ እንባ ያፈሱታል፡፡ ለቅሶ በሚመስል ዜማ፡፡ አየሩ ውርጭና ቅዝቃዜ የሞላው ነው፡፡ ውሾቹ፣ ፈረሶቹ፣ ዶሮዎቹ…ሁሉም በስብሰዋል፡፡ ሁሉም ገፅታቸው ጨፍግጓል። ሁሉም የፈዘዙ የደነገዙ ናቸው፡፡ የትም መሄጃ ሥፍራ የለም፡፡ ለቀናት ያህል ማንም ሰው ከቤቱ ንቅንቅ አይልም፡፡ እዚያው መንጐራደድ ብቻ! በመስኮት የጨፈገገውን አየር በደነዘዘ ስሜት እየተመለከቱ፡፡ አቤት ሲቀፍ!  
ኢቫን ዲሚትሪች፤ ቆም አለና ሚስቱን  ተመለከተ፤ “ማሻ፤ ውጭ አገር መሄድ አለብኝ …” በመከር  መገባደጃ ላይ ወደ አንዱ ውጭ አገር … ወይ ደቡብ ፈረንሳይ … ወይ ጣልያን አሊያም ህንድ መጓዝ… ምንኛ ግሩም እንደሆነ ማሰብ፤ ማሰላሰል ያዘ፡፡
“እኔም ራሴ  መሄድ አለብኝ!” አለች፤ ሚስቱ “ግን መጀመርያ የእጣውን ቁጥር ተመልከት!”
“ቆይ! … ቆይ! … ”
ወዲያው በክፍሉ ውስጥ እየተንጐራደደ ማሰብ ማሰላሰሉን ቀጠለ፡፡ ግን ሚስቱ ከምር አብራው ውጭ አገር ብትሄድስ? ይሄን ሀሳብ ጨርሶ አልወደደውም፡፡ መጓዝስ ለብቻ ነው- ሲል አስቧል፡፡ ወይ ደግሞ ከሰለጠነችና ጭንቀት ከማያቃት ዘመናዊት ሴት ጋር! ሚስቱ በጉዟቸው ስለ ልጆቻቸው እያሰበችና  እየለፈለፈች … በእያንዳንዷ ሰባራ ሳንቲም እየነተረከች እንደምታሰቃየው አልጠፋውም፡፡ ይሄ ደግሞ ሰላምና ነፃነትን ይነፍጋል፡፡ ሚስቱ ባቡር ውስጥ በበርካታ እሽግ ካርቶኖች፣ ቅርጫቶች፣ ቦርሳዎች … ተከብባ  ስትጓዝ በሃሳቡ ሳላት፡፡ በሆነ ባልሆነው ስትቃትት … ባቡሩ ራሴን አሳመመኝ እያለች ስትነዘንዘው … ብዙ ገንዘብ አጠፋሁ ብላ ስታማርር … ይሄ ሁሉ ታሰበውና ዘገነነው፡፡ በየጣቢያው የፈላ ውሃ እንዲሁም ዳቦና ቅቤ እያለቀበት ሲሰቃይ ---- እሷ ደግሞ እራት ውድ ነው ብላ ፆሟን ስታድር …
“ለምትከፍላት እያንዳንዷ ድምቡሎ ልትነዘንዘኝ እኮ ነው!” ሲል አሰበና፤ ሚስቱን ለአፍታ ቃኘት አደረጋት፡፡ “በእርግጥ የሎተሪ ትኬቱ ባለቤት እሷ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ግን የሷ ውጭ አገር መሄድ ፋይዳው ምንድነው? እዚያ ምን ጉዳይ አላት? ራሷን ሆቴል ውስጥ ከርችማ እኮ ነው የምትከርመው!  እኔን ደግሞ ከአጠገቧ ውልፊት እንደማታደርገኝ አውቃለሁ!”
በህይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ ስለሚስቱ ማርጀትና መገርጣት፣ እንዲሁም ስለራሱ ጐረምሳነት፣ ጤናማነትና ሌላ ሚስት ሊያገባ እንደሚችል በማሰብ ተጠመደ፡፡  
“ይሄ እንኳን ዝም ብሎ የጅል ሃሳብ ነው ...” አለ፤ ሌላ ሚስት የማግባቱን ጉዳይ፡፡ “ግን እሷ ለምንድነው ውጭ አገር መሄድ ያስፈለጋት? ቆይ እዛ መሄዷ ምን ይፈይድላታል? ብትሄድም እኮ ሁሉም አገር ለሷ አንድ ነው … የእኔን ሰላማዊ ጉዞ ከማስተጓጐል በቀር ምንም የምትሰራው የለም። በቃ እኔን የእሷ ጥገኛ ለማድረግ ነው! አዎ እንደማንኛዋም ተራ ተርታ ሴት፣ የሎተሪውን ገንዘብ በእጇ ካስገባች በኋላ ሳጥን ውስጥ ትከረችመዋለች፡፡ ከዚያስ? እኔን ለእያንዳንዷ ድምቡሎ እየነዘነዘች፣ ዘመዶቿን ትጠቅምበታለች!”
ኢቫን ዲሚትሪች፤ ወዲያው ስለ ዘመድ አዝማዶቿ ማሰላሰል ያዘ፡፡ እነዚያ መናጢ ወንድሞቿና እህቶቿ፤ እነዚያ ድሆች አክስቶቿና አጐቶቿ … ሎተሪ እንደደረሳት ሲሰሙ፣ እየተጓተቱ ይመጡና እንደ ለማኝ ማላዘናቸውን ይጀምራሉ፤ አንዳንዴም ራሳቸውን በይስሙላ ፈገግታ ሞልተው፣ የውሸት ውዳሴ ያወርዳሉ። እነዚህ  መናጢዎች! … በሃዘኔታ የሆነ ነገር ጣል ሲያደርጉላቸው! ሌላ ጨምሩ፤ ሌላ አምጡ ብለው ችክክ ይላሉ፡፡ አይሆንም ሲባሉ ደግሞ ስድብና እርግማናቸው አይጣል ነው፡፡
የራሱንም ዘመድ አዝማዶች አልዘነጋቸውም- ያውም ከእነ ፊት ገፅታቸው፡፡ በፊት ሁሉንም በቅን ልቦና ነበር የሚመለከታቸው፡፡ አሁን ግን በጣም አስጠሉት፤ ሲበዛ ቀፈፉት፡፡
“ቀበሮ ሁላ!” ሲል በጅምላ ወረፋቸው፡፡
የሚስቱም ገፅታ እንዲሁ ቀፋፊና አስጠሊታ ሆኖ ታየው፡፡ ድንገተኛ ቁጣ በልቡ ውስጥ ገነፈለ፤ በሚስቱ ላይ ያነጣጠረ! በክፋት ተሞልቶም እንዲህ ሲል አሰበ፤ “እሷ እኮ ስለ ገንዘብ አንዲት ነገር አታውቅም፡፡ ስለዚህ ቋጣሪ ናት፤ ስግብግብ! ሎተሪው ከደረሳት እኮ … 100 ሩብል ትወረውርልኝና አታስደርሰኝም … የቀረውን ትከረችመዋለች፡፡”
በዚህ መሃል ሚስቱን ቀና ብሎ ተመለከታት። አሁን ግን የይስሙላ ፈገግታ እንኳን ፊቱ ላይ አይታይበትም፡፡ ጥላቻ እንጂ፡፡ እሷም አየት አደረገችው - እንደሱው በጥላቻና በቁጣ እየገነፈለች፡፡ እሷም እንደ ባሏ በራሷ ምኞቶች፣ በራሷ ዕቅዶች፣ በራሷ ሃሳቦች… ስትብሰለሰል ነው የቆየችው፡፡ የባሏን ሃሳብና ምኞት ጠንቅቃ ተረድታለች፡፡ ሎተሪው ቢደርሳት መጀመርያ ሊነጥቃት የሚሞክረው ማን እንደሆነ አሳምራ ታውቃለች፡፡
“በሌሎች ሰዎች መስዋዕትነት የራስን የቅንጦት ህልም ማለም ግሩም ነገር ነው!” የሚል  መልዕክት ነው ዓይኗ ላይ የሚነበበው፡፡ “በፍፁም! … አታደርገውም! ቆሜ ነው ሞቼ!” አለች - ለራሷ፤ ባሏን እየተመለከተች፡፡ ኢቫን ዲሚትሪች ገፅታዋን በቅጡ አንብቦታል፡፡ ለዚህ ነው ደረቱ ሥር የጥላቻ ስሜት ዳግም መንፈራገጥ የጀመረው፡፡
ሚስቱን ለማብሸቅና ስሜቷን ለመጉዳት ክፉኛ ተጣደፈ፡፡ ከመቅፅበት የጋዜጣውን አራተኛ ገፅ ገለጠና በድል አድራጊነት ስሜት ጮክ ብሎ ማንበብ ጀመረ:-   
“ኮዱ 9,499 ነው፤ አሸናፊው የእጣ ቁጥር ግን 46 ነው! 26 አይደለም!”
ጥላቻና ተስፋ ከመቅፅበት ድራሻቸው ጠፋ፡፡ ለኢቫን ዲሚትሪችና ባለቤቱ፤ ቤታቸው ጠባብ፣ ጨለማ የወረሰውና ጣራው ዝቅ ያለ መሰላቸው። የበሉት እራትም የተስማማቸው አይመስልም፤ ሆዳቸው ውስጥ ተቀምጦ የከበዳቸው እንጂ! ምሽቱም የማይገፋና አሰልቺ ሆነባቸው፡፡
“አሁን ይሄ ምን ማለት ነው?” አለ ኢቫን ዲሚትሪች፤ በቁጣ ገንፍሎ፡፡ “የትም ቦታ አንድ እርምጃ ሲራመዱ ቁርጥራጭ ወረቀት፣ ትርፍራፊ ምግብ፣ የፍራፍሬ ልጣጭ ነው የሚገኘው፡፡ ክፍሉ ጨርሶ መጥረጊያ ነክቶት አያውቅም፡፡ ውጡ ውጡ እንጂ ተቀመጡ አያሰኝም፡፡ በቃ ነፍሴ ወደ መቀመቅ ትወርዳለች፡፡ ቀጥ ብዬ ሄጄ ራሴን የመጀመርያው ዛፍ ላይ እሰቅላለሁ!”   

Published in ልብ-ወለድ

ስለነገርየው በማጥናት መተንተን አንድ ነገር ነው፡፡ “አናሊሲስ” ይባላል፡፡
የተጠናውን እና የተተነተነውን ነገር ወስዶ በሌላ የተጠና እና የተተነተነ ነገር ላይ መደመር ደግሞ ለላ ነገር ነው፡፡ መደመሩን “ሴንቴሲስ” ይሉታል፡፡
ለምሳሌ 1 + 1 = 2 “አንድ” ቁጥር ምንን እንዳሚወክል አናውቅም፡፡ “አንድ ሰው” ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ መንግስት---- አንድ ብርጭቆ አሊያም አንድ የሃሳብ ዘውግ ሊሆን ይችላል፡፡ ለአንድ ነገር መወከያ መጠን ገላጭ ነገር መሆኑን ብቻ ነው የምናውቀው፡፡ ምንነቱን እስካላወቅን ድረስ ከሌላ ምንነቱ ባልተተነተነ ነገር ላይ ወስደን ልንደምረው፣ ልንቀንሰው፣ ልናባዛው ወይንም ልናካፍለው እንችላለን፡፡
ነገር ግን የተተነተነ ሃሳብን ወስደን በሌላ በተተነተነ ሃሳብ ላይ የመደመሩን ፍቃድ ማነው የሰጠን? የሚለው ነው ጥያቄዬ፡፡ ወንድ ሲደመር ሴት…”ወንድ ሴት” ይፈጠራል ልንል አንችልም። የማይደመሩ ነገሮችን ከመደመር ብዙ የፅንሰ ሃሳብ መንጋደዶች ተፈጥረዋል፡፡ ለመደመር ብቁ የሚያደርጋቸው ነገር “ሎጂክ” ብቻ ሳይሆን “ምክንያታዊነትም” አንዱ  መመዘኛ መሆን አለበት፡፡
እኔም አንድን ነገር ልውሰድና…በመጠኑ በመተንተን ከሌላ ማንነቶች ጋር ለመስፋት ልሞክር፡፡ ሙከራዬ ልክ ሆኖም ይሁን ስህተት ስፌቱን የምትለብሱት እናንተ ብያኔ ትሰጣላችሁ፡፡ ለመተንተን የመረጥኩት ነገር በጣም ቀላል መሆን አለበት፡፡ ለሁላችንም ቅርብ እንዲሆን፡፡ በቀላሉ የሚገኝ…ተፈጥሮአዊ ነገር፡፡ ሁላችንንም ከተወለድን ጀምሮ ስለታደልነው እግሮቻችን ሊሆን ይችላል። ግን በተፈጥሮ ለሁላችንም የተሰጠን ነገር ከሆነ ደግሞ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ሳይሆን ጥናት መስራት የሚያስፈልገው በብዙሐኖቹ ላይ ነው፡፡ ያ ደግሞ በጣም ብዙ ጊዜ፣ ብዙ መረጃ ያስፈልገዋል፡፡ በእኔ አስተውሎት ብቻ ሊከናወን የሚችል አይሆንም፡፡
እንደ ኪንታሮት በሽታ የመሰለ ነገርንም አይደለም መመርመር የፈለግሁት፡፡ ጤነኝነትም በሽታም ከመሰለ ነገር ቢሆን እመርጣለሁ፡፡ ምክንያቴ ወደኋላ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ብዙ ሩቅ መሄድ አያሻኝም ምሳሌዬን አግኝቼዋለሁ፡፡ በወንዶች እራስ ላይ የሚገኝ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በሁሉም ወንዶች ላይ ግን አይደለም። በአንዳንዶች እንደ ውበት፣ በሌሎች ደግሞ መልክ አጥፊ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ ከቁርንድድ ፀጉር ባለቤቶቹ ይልቅ ለስለስ ያለ ፀጉር ባላቸው የሰው ዝርያዎች ላይ ይኼ ክስተት ይበዛል፡፡ አንዳንዶች “የምሁርነት” ምልክት ነው ይሉታል፡፡ ከሽበት ማብቀል ባልተናነሰ ነገርዬው በማህበረሰቡ ውስጥ ያስከብራል፡፡ ተቀማጭን አሽቆጥቁጦ ከወንበር ያስነሳል፡፡ የነገርየው ባለቤቶች ቆብ በነገርየው ላይ መድፋት ያዘወትራሉ፡፡ ማዕዘናም የራስ ቅል ባላቸው ላይ በብዛት አይታይም፡፡ ወይንም በማዕዘናም ራሶች ላይ ከመውጣቱ በፊት የራስ ቅላቸውን ቅርጽ ወደ እንቁላል ክብነት ይቀይረዋል፡፡
እስካሁን ግልፅ ካልሆነላችሁ ምናልባት የነገርየው ባለቤት ስለሆናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገርየው “በራ” ተብሎ ይጠራል፡፡ “ራሰ በራ” ደግሞ የነገርየው ባለቤት ነው፡፡ የሚገርመው ግን ስለ እዚህ ነገር ያገኘሁት ትንተና ከሁለት መስመሮች የረዘመ አይደለም፡፡ በተለይ ነገርየው በጤና እክል ወይንም በአደጋ ምክንያት የመጣ ካልሆነ፡፡ በዘር የሚወረስ ምክንያቱ ግልጽ ያልሆነ የፀጉር መብቀል መቆም ነው፡፡ ልክ ሽበት ማለት የፀጉር ቀለም የሚያመርቱት የቆዳ ስር ፒግመንቶች ቀለሙን ማምረት ሲያቆሙ የሚከሰት የዕድሜ ቁልቁለት ላይ በተፈጥሮ ሂደት የሚያጋጥም ጉዳይ እንደሆነው፡፡
ይህ የተፈጥሮ ገጽታ በሽታ አለመሆኑን ካረጋገጥን በኋላ፣ ወደ ተጨማሪ አስተውሎቶቻችን እንሻገር፡፡ በተወሰኑ የወንድ ዘር ግንድን ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን እያወቅንም…በተፈጥሮ ረገድ ሳይሆን እስካሁን ባስተዋልኩት አንፃር ድምሮቼን ለመስራት ልሞክር፡፡ ጽሑፌ ላይ ስነሳ የማይደመሩ ነገሮችን ከመደመር ነው የፅንሰ ሃሳብ መንጋደድ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አጉል እምነት እና አምልኮ የሚከሰቱት ብያለሁ፡፡
ምን ማለቴ እንደሆነ የበለጠ ልግለጽ፡፡ ለምሳሌ በአንድ የገጠር መንደር (ማህበረሰብ) ውስጥ የሚመለክ ዛፍ አለ እንበል፡፡ ዛፉ ትልቅ፣ ግንዶቹን ወደ ሰማይ፣ ስሮቹን ወደ አፈር ስር ሰድዶ ያጠነከረ አድባር ሊሆን ይችላል፤ በስፍራው ለሚኖሩ አምላኪዎቹ፡፡
እንግዲህ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች አሉ…አንድ ዛፍ አለ፡፡ ሁለት በነዋሪዎቹ አእምሮ ወይንም ነፍስ ውስጥ የፈጣሪ እውቀት እና ፍላጐት…ዛፉን የፍላጐታቸው መወከያ ወይንም የእውቀታቸው መጠቅለያ ተጠቅልሎ የሚገኝበት ቦታ ሲያደርጉት ተራው ዛፍ ወደ አድባርነት ደረጃ ከፍ ይላል። ሁለት የማይደመሩ ነገሮችን ደምረዋል የሚሉ የሎጂክ እና ምክንያታዊነት አምላኪዎች ቢኖሩም። እነሱም ከመደመር ነው እውቀታቸውን ያገኙት፡፡ እነሱም ሃሳባቸውን ከቁሳዊ እቃ ጋር ለማስተሳሰር የሚጠቀሙበት መንገድ አላቸው፡፡ የተፈጥሮን ሚስጢር ማወቂያ መንገድ ብለው ነው ይኸንን ምክንያታዊነታቸውን የሚጠሩት፡፡ ቅልብጭ ባለ ስያሜው ግን “ሳይንስ” ነው፡፡
ሳይንስ ለመባል አንድ ነገር መጀመሪያ በአስተውሎት ሊጤን ይገባል፡፡ ከማስተዋል እና ማጤኑ በኋላ…ስለነገርየው ያስተዋለው ሰው “መላ ምት” ይሰጥበታል፡፡ ከመላምቱ በኋላ ሦስተኛው እና ወሳኙ ደረጃ ይመጣል፡፡ መላ ምቱን ወደ ተጨባጭ የማይለዋወጥ እውነታ ለመቀላቀል በቤተሙከራ ተፈትኖ እውነትነቱ እና እምነትነቱ ይረጋገጣል፡፡
እኔ በመላጣ ላይ ለመምታት የሞከርኩት መላ…በመላምትነቱ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡ ወደ ቤተሙከራ ወስዶ ለማረጋገጥ ከዚህ የበለጠ ሙያ እና አቅም ይጠይቃል፡፡ እኔ የሌለኝ ነገር ነው፡፡ መላ ምቶች ለሳይንስ ከሚቀርቡት ይልቅ ለጥበብ የቀረበ ዝምድና አላቸው፡፡ ስለ ራሰ በራ የምለውን ከጥበብ በበለጠ እርግጠኝነት ኮስተር ብሎ መቀበል ሞኝነት ነው፡፡   
 መላምቴን የትም ቦታ መጀመር እችላለሁ። ራሰ በራዎች በአብዛኛው መሪዎች ናቸው ልል እችላለሁ፡፡ ራሰ በራ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመሪነት መድረክ ላይ ዋና ተጫዋች እንደነበረ ትዝ ይለኛል?..ሌላ ማን አለ?!...አፄ ምኒልክ ራሰ በራ አልነበሩም ለማለት ብችልም….ራሳቸው ሳይሸፈን ግልጽ ፎቶአቸውን ግን አይቼ አላውቅም፡፡ የአፄ ሃይለስላሴ ፀጉር ገባ ያለ ቢሆንም እስከመጨረሻው ደረጃ አልተመለጠም፡፡
ለመሆኑ የሀገር መሪ ሆኖ የተመለጠ ሰው ካለም ሀገሩን የመራው በጭንቅላቱ ነው ወይንስ በክንዱ…ሌኒን ራሰ በራ ነበረ፡፡ ብዙ ያነብብ እና ይጽፍ የነበረ ሰው ነው፡፡ ብዙ የሚያነብና እና ብዙ የሚጽፍ መሪ ነው የሚመለጠው ማለት ነው?
መሪ ስል በጥቅሉ ነው ወይንስ በተናጠል? ለምሳሌ ቬክስፒርም በዘመኑ የስነ ጽሑፍ ዘርፉ መሪ ነበር፡፡ ራሰ በራ ነው፡፡ ግን አንዱ የአእምሮዬ ጓዳ ደግሞ አንድ የታወቀ አሉባልታ ሹክ አለብኝ፡፡ የሼክስፒርን ቅኔዎች እና ቴአትሮች የደረሰው Sir frincis ነው የሚል አሉባልታ፡፡ ሼክስፒር ተመልጦ የሚያሳይ ፖርትሬት በብዙ አጋጣሚ አይቻለሁ፡፡ ራሰ በራው ሼክስፒር ሆኖ ግን በጥበቡ ግዛት መሪ ያደረገውን ሥራዎቹን የሰራለት ባለ ሙሉ ፀጉሩ “ሰር ፍራንሲስ ቤከን” ከሆነ ---- መመመለጥ መሪ ያደርጋል የሚለውን መላ ምቴን ቅዠት ያደርገዋል፡፡
በሼክስፒር ላይ የሚወራው አሉባልታ ወደ አንድ ጥርጣሬ መራኝ፡፡ ራሰ በራ ሌባ ሊሆን ይችላል ማለት ነው? ነገር ግን በህይወት ዘመኔ  ራስ በራ የሆነ አጭበርባሪ አይቼ አላውቅም፡፡ ታክሲ ለመያዝ ስጋፋ ከጐኔ ያለው ሰው ራሰ በራ ከሆነ ለኪሴ የማደርገውን ጥንቃቄ እቀንሳለሁ፡፡ ይህ የሚያሳየው ነገር አለ፡፡ ራሰ በራ ከተሞክሮ እድሜ ልኬን እንዳየሁት የተከበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ የረከሰ የኪስ አውላቂ ስራ አይሰሩም፡፡ ለአቅመ ራሰ በራነት ከደረሰው ይልቅ ድፍን ፀጉር ያለውን እና ወጣት የሆነውን ነው ኪሴ እንዳይገባ የምጠነቀቀው፡፡
እኔ ራሴ ፀጉረ ድፍን እና ወጣት ሆኜ ሳለሁ --- እኔን መሰል ወጣት መጠራጠሬ ምን የሚሉት ለ”መላ ምት” የማያመች ነገር ነው? “እኔ ወጣት ሆኜ ወጣቶች አልወድም/ሰይጣን ይመስሉኛል--- የዳቢሎስ ወንድም” የሚለው ይገልፀኝ ይሆን?
ለማንኛውም ራሰ በራ ኪስ አውላቂ ሊሆን አይችልም፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከሚመሩት ሰዎች ምን ያህሉ ራሰ በራ ናቸው። የተከበሩበትን ያህል ፀጉራቸው ገባ ያለ ይሆን? ፕሮፌሰር መስፍን ራሰ በራ ባለመሆናቸው ምክንያት ይሆን ብዙውን ጊዜ ፊታቸው ላይ የቁጣ ቅላፄ የሚነበበው?
ይሄንኑ የራስ በራ መላምቴን እያሰላስልኩ ጫማዬን የጠረገልኝ በፒያሳ የሚገኝ ሊስትሮ ራሰ በራ ነው፡፡ መነጽርም አድርጓል፡፡ ጫማዬን ጠርጐ፣ ክሬም ቀብቶ ያስከፈለኝ 8 ብር ነው፡፡ ነገር ግን የቀባልኝም ክሬም፣ ለመቀባት የወሰደበት ጊዜም ዘለቅ ያለ ነው፡፡ በጥራት ነው ስራውን የሰራው፡፡ በሊስትሮ ሙያ ላይ ለእኔ መሪ ነው፡፡ ገና ስራውን ከመጀመሩ በፊት እንኳን በደንብ አድርጐ ጫማዬን እንደሚያክምልኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ እንደጠበቅሁት ሆነ፡፡
ቅድም የፈጠርኩት መላምቴ ትክክል ሳይሆን አልቀረም መሰለኝ፡፡ ለምሳሌ ህመም ታምሜ አንድ ክሊኒክ ብሄድ እና ከጠረጴዛው ጀርባ ተቀምጦ ስለ ህመሜ ባህሪ የሚጠይቀኝ የህክምና ዶክተር ራሰ በራ ቢሆን … እርግጠኛ ነኝ ግማሽ ህመሜ ለቀቅ እንደሚያደርገኝ፡፡ ከወጣት እና መላጣ ካልሆነው ዶክተር የበለጠ ራሰ በራው እና ምራቁን ዋጥ ያደረገው ባለሞያ መፍትሄ እንደሚሰጠኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡
ሌላው በእይታ ካደረግሁት ጥናት የተገነዘብኩት ነገር … መለጥ ያሉ ሰዎች ወፈር ለማለትም የቀረቡ ናቸው፡፡ ወፈር ለማለት እና ቦርጭ ለማውጣት ቅርብ ናቸው፡፡
ደራሲዎችን በአይነ ህሊናዬ ደርድሬ … ይሄ በተለምዶ የሚደፉትን ቆብ በምኞት እጄ እየገለጥኩ አናታቸውን መረመርኳቸው፡፡ የሚገርመው (በተለይ በሐገራችን ላይ ያሉት) “ራስ ሙሉ” ናቸው፡፡ ከባህር ማዶ ያሉትም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ትያትር ፀሐፊዎች እና ገጣሚዎች ግን በተገላቢጦሽ ፀጉራቸው የገባ ብዙ አገኘሁ፡፡ የህዝቡን ሀላፊነት በራሳቸው ላይ ተሸክመው በመወጣት በኩል ትልቅ ሚና የተሸከሙት ደራሲዎች ናቸው ገጣሚዎች እና ትያትር ፀሐፊዎች …፡፡
እስካሁን በራሰ በራዎች መሪነት፣ አስተዋይነት፣ ምሑርነት ላይ ማረጋገጫ ለመስጠት ስባዝን ቆይቼ አሁን እጄን ልሰጥ አልችልም! … ከደራሲ ይበልጥ ገጣሚዎች ለህዝብ ሀላፊነት ይቀርባሉ ማለት ነው-እንደኔ መላምት፡፡
ማረጋገጫዬ አስተውሎቴ ብቻ ነው፡፡ ራሰ በራ የሆኑ የአእምሮ በሽተኞችም ብዙ አይቻለሁ። ከተራው የአእምሮ በሽተኛ ላቅ ያሉ ቢሆኑ ነው የሚል መላምት አለኝ፡፡ ራሰ በራ የሆነን በሽተኛ ፀጉረ ጨብራራ ከሆነው እኩልማ ልመዝነው አልችልም፡፡ በትምህርት ብዛት ካበደው ጋር በትምህርት እጦት ምክንያት ያበደውን እኩል ቦታ ላስቀምጠውም ህሊናዬ አይፈቅድም፡፡
በዝግመተ ለውጥ እይታም ራሰ-በራነትን ልመለከተው እችላለሁ፡፡ እነ ሉሲ እና አርዲ (በስዕል ባሳዩን መሰረት) ሰውነታቸው በፀጉር የተሸፈነ ዝንጀሮ ነው የሚመስሉት፡፡ ራሰ በራ በእነሱ የጦጣ ዘመን ላይ ያለ አይመስለኝም፡፡ በዝንጀሮዎች ዘንድ ራሰ በራ የሆነ አይታችሁ ታውቃላችሁ? … እኔ አላውቅም፡፡ በሰዎች ዘንድ ግን ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ብዙ አለ፡፡ ባይሆን ዝንጀሮዎች ሲመለጡ ደረታቸው አካባቢ ነው፡፡ ጭላዳ ዝንጀሮ ደረቱ ላይ አይደለ ራሰ-በራው ያለው፡፡
ስለዚህ ፀጉሩ ገባ ገባ ካለው ይልቅ ያላለው ወደ ዝንጀሮኛ ይቀርባል እንደኔ መላምት፡፡ ግን እኔም ፀጉራቸው ገባ ካላሉት መሀል የምመደብ ነኝ። እኔ ራሴ ወደ ዝንጀሮዎቹ ጐራ ሆኜ ነው እንዴ መሰሎቼን የምነቅፈው? “… እኔ ዝንጀሮ ሆኜ ዝንጀሮ አልወድም/ሰይጣን ይመስለኛል የዳቢሎስ ወንድም”
እዚህ ላይ ላብቃ፡፡ የማይደመሩ ነገሮችን ከመደመር ምን አይነት መላ ምቶች እንደሚገኙ ለማሳየት ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል፡፡    

Published in ጥበብ
Page 4 of 16