“የሳጥናኤል ሳል ኢትዮጵያ” የህይወት ዛፍ” “ገነት” “ኢትዮጵያ” የሚል ርዕስ ያለውና በጋዜጠኛና ደራሲ ፍሰሓ ያዜ ካሳ የተጻፈው መጽሃፍ በያዝነው ሳምንት በገበያ ላይ ውሎ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ መጽሃፉ የዓለም ሃያላን አገራትና መሪዎቻቸው በህብረት ሆነው በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩበትን ምክንያትና ዋነኛ ግባቸውን የሚተነትን ነው ያለው ደራሲው፤ 376 ገጾች እንዳሉትና በ80 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝም ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛና ደራሲ ፍሰሐ ያዜ ካሳ ከዚህ ቀደም “የኢትዮጵያ የ5ሺህ ዓመት ታሪክ፣ ከኖህ እስከ ኢህአዴግ”፣ “ካልተዘመረለት እያሱ እስከተዘመረለት ኢህአዴግ” እንዲሁም “እኔና ቹ” የተሰኙ ሦስት መጽሃፍትን ለአንባቢያን አድርሷል፡፡

   ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ጣይቱ የባህል ማዕከል ያዘጋጀው “መንገድ” የተሰኘ የስነጽሁፍ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ በአዲስ አበባው አክሱም ሆቴል ትልቁ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ የስነጽሁፍ ዝግጅት ላይ የተመረጡ ግጥሞች፣ ወጎች፣ የፍቅር ደብዳቤና አጭር ልቦለድ የሚቀርብ ሲሆን ባለሙያዎችም በአገራችን ወቅታዊ የስነ ግጥም እንቅስቃሴ ዙሪያ ሙያዊ አስተያየት እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ የሥነጽሁፍ ቤተሰቦች የጥበብ ድግሱን በነጻ እንዲታደሙት አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ጣይቱ የባህል ማዕከል፤ የአገሪቱን የስነጽሁፍ እድገት ማገዝ፣ ጥበብን ከጥበብ ወዳጆች ጋር ማገናኘት፣ ወጣት ጠቢባንን ማበረታታትና አንጋፋ የጥበብ ሰዎችን ማክበርና መዘከርን አላማው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, 26 May 2015 08:43

“ዙቤይዳ”

     3ኛው ዕትም ሊወጣ ነው ተባለ

     በደራሲ አሌክስ አብርሃም ተፅፎ በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው “ዙቤይዳ” የተሰኘው የአጭር ልብወለዶች መድበል የመጀመሪያና ሁለተኛ ዕትሞች ተሸጠው ማለቃቸው ተገለፀ፡፡ ሦስተኛው እትምም ከነገ በስቲያ ለገበያ እንደሚበቃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መፅሐፉ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዌብ ሳይት አማካኝነት እንደሚሸጥም ደራሲው ጠቁሟል፡፡ 22 ታሪኮች የተካተቱበት መጽሐፉ፤ በ59 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

አሌክስ አብርሃም ከዚህ ቀደም “ዶ/ር አሸብርና ሌሎችም” የተባለ የአጭር ልቦለዶች መድበልና “እናት ፍቅር ሃገር” የተሰኘ የግጥም መፅሃፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

    የ73ቱ ዓመቱን የዕድሜ ባለፀጋ የዶክተር ተስፋፅዮን ደለለ ግለ-ታሪክ የሚያስነብበው “ከሚሽግዳ እስከ ዓለም ዳርቻ (ሕይወቴ ትምህርት ቤቴ)” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ ግለ-ታሪኩን የፃፉት ራሳቸው ዶ/ር ተስፋጽዮን ሲሆኑ የአርትኦት ሥራውን ያከናወነው ገጣሚ ወንድዬ ዓሊ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የፖፑሌሽን ሚዲያ ሴንተር የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ “ይህ መጽሐፍ እግዚአብሔር በዶ/ር ተስፋፅዮን ህይወት ውስጥ ያደረገውን በጐ ነገር እንድታውቁ የሚረዳችሁ ብቻ ሳይሆን “‹በእኔ የህይወት ጉዞ የታየ ትርጉም ያለው ድርሻ ምንድን ነበር” ብላችሁ እንድትጠይቁ ያደርጋችኋል… ሁሉም ሊያነበው የሚገባ ቁምነገር የያዘ መጽሐፍ” ብለውታል፡፡

የመፅሐፉ አርታዒ ገጣሚ ወንድዬ አሊ በበኩሉ፤ “አተራረኩ ሲበዛ ተፈጥሮአዊ ከመሆኑ የተነሳ የጋሽ ተስፋን ረቂቅ ኩል መኳኳል፣ እንሶስላ ማሞቅ አላስፈለገኝም፤ በርኖስ ላይ ካቦርታ መደረብ ነውና፡፡” ሲል አስተያየቱን ገልጿል፡፡ በ10 ምዕራፎችና በ284 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ80 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

Tuesday, 26 May 2015 08:36

አዲስ ፍኖት

(ካለፈው የቀጠለ)

   ፍቅሯ ስላልወጣልኝ በአቋሜ ልፀና አልቻልኩም።

ሌላ ጊዜ ጥቂት ቆይታ ደግሞ “ለጥፋቴ ይቅርታ ጠይቄ የለ? … ግንኙነታችንን ብንቀጥልና ባሌ ብትሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ እንዲህ የምጠይቅህ ለሌላ ሳይሆን ስለምትወደኝ ነው፡፡”

ፍቅር እንደገና!

*         *         *

ላንቺ፡-

ስሜቴን መካድ እችላለሁ?! … በስሜት የመኖር እንጂ ስሜት የመካድ ተሰጥኦ የለኝም፡፡ ግልጽ ነው፡፡ … ወድጄያለሁ! …. ወድጄና ፈቅጄ ተንበርክኬያለሁ። በእርግጥ እስከ ምን እንደምድህ አላውቅም። ብዙ በመዳህ ጉልበትና ልቤ የተላጠበትን ዘመን አልረሳሁም፡፡ ቁስሉ አሁንም ልቤ ላይ ይሰማኛል። እና ከእንግዲህ ብዙ የመዳህ አቅም ያለኝ አይመስኝም፡፡ አቅሜን ጨርሰሽዋል ሊያ!! ጨ… ር…. ሰ….ሽ…ዋ….ል!!

እወድሻለሁ ወድሻለሁ እወድሻለሁ እወድሻለሁ እወድሻለሁ

ልክድሽ አልችልም …

መዝሙሬ ነበርሽ፡፡ ቋንቋዬም ነበርሽ፡፡ የምዘምረው ስላንቺ ነበር፡፡ የምግባባው ባንቺ ነበር። መልኬን አውቆ፣ ስምሽን የማያውቅ ጥቂት ነበር፡፡ ባልንጀሮቼ ጓደኛችን ነው ብለው እንጀራ ሲያጎርሱኝ፤ እኔ ካንቺ ጋር የምናብ እንጀራ እቆርስ ነበር፡፡ በፍቅር የወዛ፣ በክብር የራሰ እንጀራ ስታጎርሺኝ አልም ነበር። በእርግጥም ህልም ነበር፡፡

ጓደኛ ሁነን ብለው ይመጣሉ፡፡ ስለአንቺ ወዳጅነት ተሰብከው ይመለሳሉ፡፡ ወዳጅነቴን ፈልገው ስለ ወዳጄ ይጠመቃሉ፡፡ ሊያ ልክ ነሽ፤ ክፉ ነበርኩ፡፡ አንቺን እንጂ ሌሎችን አላይም ነበር። አንቺን ለማጽናት ለሌሎች የታወርኩ ክፉ ነበርኩ፡፡ አይኔም ልቤም የተከፈተው ላንቺ ብቻ ነበር፡፡ …

እዘፍንሽ ነበር ሊያ!

እዘምርሽ ነበር!

ወጌ ነበርሽ ሊያ!

እተርክሽ ነበር!

ሁሉ እንዳይሆን ሊሆን …

ግን ህይወት በተዓምር ጢቅ ያለች ናት፡፡ በህይወት ለመቆየት ስል የጣመነ ስጋዬንና የዛለች ነፍሴን ይዤ ከሸሸሁ፤ ፍቅሬን አፈር አልብሰሽ ካዳፈንኩ በኋላ፤ ይሄው ትንሳኤ መጥቷል፡፡

ፍቅሬ አላዛርን ሆኗል፡፡ አፈሩን አራግፎ ሲንቀሳቀስም ይታየኛል፡፡

ግን እፈራለሁ፡፡ …

እፈራለሁ ሊያ …

እፈራለሁ …

እፈራለሁ …

እባብ ያየ በልጥ አበረየ አይነት፡፡

ትላንት የቆሰለ ዛሬ ይደነብራል አይነት፡፡

ነገ ከወደቅክ መቼም አትራመድ አይነት፡፡

እፈራለሁ …

እፈራለሁ ሊያ …

ስወድ በሙሉ ልብ ነው፡፡ ስወድ እስከ ጥግ ነው፡፡ እንደ ፊኛ … እንደ ባሉን ልቤ ውጥር ብላ፡፡ … ውስጧን ፍቅር ሞልቷት፡፡ እና ፊኛ ወይም ባሉን በትንሽ ስንጥር ይተነፈስ የለ? … ሙሽሽ ጥፍት ይል የለ … እንደዛው ህልውናዬን አጣለሁ፡፡ የኑሮ ምህዋሬ ይበዛል፡፡ እሸነቆራለሁ፤ እጎድላለሁም፡፡

ያኔም የሆንኩት እንደዝዚህ ነው፡፡

ለምን እንደሆነ እንጃ አሁንም እፈራለሁ። ውሸት በላዬ ላይ ሲኖር የማልችለውን ያህል መዋሸትም አልችልም፤ እመኝኝ ተመልሼ መዳፍሽ ውስጥ ገብቻለሁ፡፡ እኔ እርግብ ነኝ፡፡ … ወደ ከፍታ ልታበሪኝ ነው? … ጨፍልቀሽ ልትገይኝም ትችያለሽ!

የምለምንሽ እንድታኖሪኝ ነው፡፡

እና ደግሞ ናፍቄሻለሁ …

ንፍቅ!

ለአንባቢ፡-

የኔና የሊያ ፍቅር ከትቢያ ተነስቶ አቧራውን ገፈፈ፡፡ “ተሀድሶ” አካሄድን፡፡ ፍቅር ብቻ ሣይሆን ማንነታችንም ተሀድሶ ያካሄደ ይመስል እንደ ቸኮሌት ጣፋጭ የሆነ ግዜ ማሳለፍ ጀመርን፡፡ ዘመኑ ራሱ ዘመነ ተሀድሶ (Renaissance period) መሰለኝ፡፡ ይሄ ያለፈ ዘመን በየት በየት ዞሮ መጣ ባካችሁ?! … የፍቅር የማንነትና ተሀድሶን በአንድ ረድፍ ተሰልፎ ያየሁ ያህል ተሰማኝ፡፡ እና ደስ አለኝ፡፡ ደስታ ውድ በሆነበት አገር በደስታ መኖር ከጥቂት ዕድለኞች ውስጥ እንደ አንዱ የሚያስቀጥር መሆኑን አመንኩ። ቀንና ሌሊቱን የላቀ ደስታ ሀሰሳ መንቀሳቀስ ጀመርኩ። የንጉሥ (አፄ ቴዎድሮስ) ሚስት ተዋበች፤ ንጉሱን “ታጠቅ” ብላ እንዳነሳሳችሁና አባ ታጠቅ የሚለው ተቀጽላ መለያቸውና መጠሪያቸው እንደሆነ ሁሉ፤ እኔንም ታጠቅ የምትለኝ ሴት ያለች መሰለኝ፡፡ ስሜን ጠርታ ታጠቅ ስትለኝ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ እናም ለዚህም ደስታ ተሰማኝ፡፡ ከደስታ ወደ ደስታ መሻገር እጣፈንታዬ ወይም ዕድሌ መሰለ።

ይህን ያጣው ስንቱ ነው? ቁጥሩን መዘርዘሩ አድካሚና አሰልቺ ነው፡፡ ጥቂት የማይባል “በርካታ” በሚል ቃል የሚገለጽ መሆኑ ግን ዕውነት ነው፡፡ መቼም ሀገሪቱ ደስታ (እና ሣቅ) እንደ አልማዝ ውድ የሆነባትና ደስተኞች እንደ ጁፒተር የማይሰፍሩባት እንደሆነች ማወቅ ለኢትዮጵያዊያን የጥበብ መጀመሪያ ነው፡፡

እኔ ግን በየመዓልቱ ደስታን እንደ አስቤዛ ለመሸመት የታደለና በየሌሊቱ ሳቅ እንደ ሪችት መተኮስ የቻለ ዜጋ ሆንኩ፡፡ ሊያ የደስታዬ (እና የፍንደቃዬ)፤ የሣቄ እና (መፍነክነክያየ) ምንጭ ሆነች፡፡ የሣቅና የፈሽታ፤ የደስታና የሀሴት ወላድ! …

“ቀንና ሌሊቱን የላቀ ደስታ ሀሰሳ መንቀሳቀስ ጀመርኩ” ብዬ ነበር፡፡ ይሄ እውነት ነው፡፡

እንቅስቃሴውን የጀመርኩት ደግሞ ሊያን ለማስደሰት በመትጋት ነው፡፡ ስሜቷንና ፍላጎቷን ማጥናት ጀመርኩ፡፡ ትንሽ ነገር የሚያስደስታት (በደስታ ጣሪያ የሚያስነካት) እና ትንሽ ነገር የሚያስከፋት (በሀዘን ትቢያ የሚያለብሳት) ሴት መሆኗን አወቅሁ፡፡

እና እጠነቀቅላት ጀመር፡፡

በስሌት ወደ መኖርና በስልት ወደ መቅረብ ገባሁ፡፡ በመጨረሻም ስልቱና ስሌቱ ውጤታማ ሆነው አገኘሁ፡፡ እናም ተደሰትኩ፡፡

*   *   *

የፍቅራችን መደርጀትና መበጀት ምክንያቱ የኔ ጥረት ብቻ አልነበረም፡፡ ሊያም አለችበት፡፡ እንዲያውም የአንበሳውን ድርሻ የምትወስደው እሷ ናት፡፡ ባህሪዋን ለማረም ተግታለች፡፡ ጊዜ ልትሰጠኝና ልታስደስተኝ ጥራለች፡፡ ካለፈው ግንኙነታችን (ታሪካችን) ልምድ ሳትቀስም የቀረች አትመስልም። “አንድ ድንጋይ ሁለቴ ከመታህ ድንጋዩ አንተ ነህ።” የምለውን አባባል ምንነትና ትርጉም የተረዳች መስላለች፡፡ “ምንትስ በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይገባም፡፡” ከሚለው አባባልም ትምህርት ወስዳለች፡፡

ለማንኛውም አብረው እንዳደጉ ሁለት የልብ ወዳጆች ለኔ ምቹ ሆና አግኝቻታለሁ፡፡ ውበትና ልስላሴ በቸረው ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ እንደመቀመጥ ወይም በኮንፈርት ተጠቅልሎ እንደመተኛት ምቾት ስጥታኛለች፡፡

አንዳንዴ ሳስበው ሊያን የሆነ መልአክ ለየት ያለ ሀሳብ ይዞ ከሰማይ በመውረድ አስተምሮ የለወጣት እንጂ በራሷ ጊዜ አገናዝባ የተለወጠች አይመስለኝም። እንዲህ ዓይነት ለውጥ በተለየ የመንፈስ ጫናና በልዩ መልዓክ እርዳታ ካልሆነ በስተቀር እውን የሚሆን አይመስልም፡፡

ሰው በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲህ ይለወጣል?! ይህ ትንግርት ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ፤ እባብም ዘንዶ የመሆን ዕድል አለው፡፡ እንዲህ ከሆነ፤ አይጥም ዝሆን የመሆን ተስፋ አላት፡፡ እንዲህ ከሆነ፤ ዝንጀሮም ሰው ለመሆን ቅርብ ነው፡፡ (አጋጣሚውን ካገኙ ማለቴ ነው፡፡ እንደዚያ፡፡ ወይም እንደዚያ የመሰለ ነገር!)

መሶብና ወሰከንቢያ ሆነናል፡፡ ማናችን መሶብ ማናችን ወስከንቢያ (ማን ከላይ ማን ከታች) እንደሆንን እርግጠኛ መሆን ባይቻልም፤ ገጥመናል፡፡

እሷ ግጣሟን አግኝታለች፡፡

እኔም ግጣሜን አግኝቻለሁ፡፡

ላንቺ፡-

አሁን ፍርሃት የለብኝም፡፡

አሁን ስጋት የለብኝም፡፡

አልበሳጭም፡፡

አልናደድም፡፡

ብስጭትና ንዴትን እንደ በግ ቆዳ ከልቤ ላይ ገፍፌ ገንዳ ውስጥ ጥያለሁ፡፡ ተስፋ መቁረጥን ገርዤ ወደ ተስፋ ለውጨዋለሁ፡፡ ጨለምተኝነትን ገንዤ ቀብሬዋለሁ፡፡ የፊቴ ሰሌዳ ላይ ደስታ ቦግ ብሎ ይታያል፤ ተስፈኝነት በደማቁ ተጽፎ ይነበባል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው ባንቺ ምክንያት ነው፡፡

ወደ ህይወት መልሰሽኛል ሊያ! …

ኑሮን አስጀምረሽኛል!

ከደስታ ጋር ጉንጭ ለጉንጭ አሳስመሽኛል ሊያ!…

በተስፋ የታጨቀና ኃይል የተሞላ ወጣት አድርገሽኛል! …

አንቺ ባትደርሽልኝ ፍጻሜዬ ይሆን ነበር፡፡

ህይወት እንደሞት አስጠልታኝ ነበር፡፡

ሞት እንደ ገነት ናፍቆኝ ነበር፡፡

ግን ተመስገን፤ ሁሉ ባንቺ ተቀለበሰ፡፡

ለአንባቢ፡-

“ጨምሯል ፍቅር ጨምሯል፡፡

ጨምሯል ፍቅር ጨምሯል፡፡” እያሉ ወዳጆቹ የሚያንጎራጉሩለትና እሱ ራሱም መልሶ የሚያንጎራጉር ሰው ሆንኩ፡፡ መዋቅራችን ግዝፈቱ እንደ ዝሆን፤ ቁመቱ እንደ ግመል ሆነ፡፡

ፍቅራችን ከኛም አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ፤ ሌሎችንም የሚማርክና የሚያስቀና ሆነ፡፡ ከአዲስ አበባ ህዝብ  አንድ ሶስተኛው አጀብ ሲልልን፤ ሩቡ ሲቀናብን፤ ኩርማኑ ሲደሰትልን፤ የተቀረው ሲያደንቀን ከረመ፡፡

ላንቺ፡-

ብስል ትመስይኝ ነበር፡፡ ለካ ጥሬ ነሽ፡፡ ይሄንን በመሰለ ዓረፍተ ነገር በመጀመሬ አዝናለሁ፡፡ ግን ምርጫ የለኝም፡፡ እውነቱ እንደታሸ ሎሚ መፍረጥ አለበት። እውነታን በእውነትነቱ መቀበል ምርጫ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው፡፡ ስለዚህ ስሜቴን ልደብቅሽ አይገባም፡፡ በግልጽ እኮንንሻለሁ፡፡ “ወጉ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” ማለት ያንቺ ፈንታ ነው። ለእግዜርም ሆነ ለሰው ኩነኔ ከመሳቢያ ውስጥ የሚሳብበት ጊዜ አለ፡፡

ይሄው ላንቺም እጄ ከመሳብያው እጀታ ላይ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሷል፡፡ ኩነኔን ለመታጠቅ አጥብቀሽ ተሰናጂ፡፡

ግን ምን ነው?

ምን ነው ሊያ? …

ነገሮች የሚገባት ሴት ናት ብዬ ስመሰክር፤ አስተዋይ ናት ብዬ አታሞ ሳስመታ፤ አዋቂ ነች ብዬ እምቢልታ ሳስነፋ፤ ትረዳኛለች ብዬ ከበሮ ስደልቅ … ምነው ሊያ?!

በተራ ወሬ ሰው ይዘጋል?! … በተራ ወሬ! እኔማ ወደ ኋላ ሄጄ ሳስብ ገርሞኝም አላባራ አለ፡፡ “እኔነቴን አልተቀበለችም ነበር ማለት ነው? “አልኩ፡፡

በማንነቷ የማታፍር፣ ኮርታ የምታስኮራኝ እንቁዬ ናት ብዬ ስተማመንብሽ መርጬ ባላመጣሁት ማንነት ስትርቂኝ ደነቀኝ፡፡

ለማንኛውም የኔ እምነት እንዲህ ነው፤ ከምንም ነገር በላይና ከምንም ነገር በፊት እኔ ሰው ነኝ፡፡ የምኮራውም ሆነ ልኮፈስ የምችለው በሰውነቴ ነው። በሌላ በኩል ልወገዝም ልጠላም የሚገባው ሰው ከመሆኔ ጋር የማይመጣጠን ማንነት ይዤ ብሆን ነው፡፡ እኔ ግን ሰው ከመሆን የማስቀድመው ምንም ነገር የለም፡፡

እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወራሽ ነበርኩ። ኃይማኖቴ ከቤተሰቦቼ የተወረሰ ነው፡፡ ብሄሬ ከቤተሰቦቼ የተወሰደ ነው፡፡ እነዚህን በራሴ ፈቃድ ላናገኛቸውምሆነ፤ ልፍቃቸው አልችልም፡፡

ለማንኛውም አንቺ የተከፋሽብኝና የዘጋሽኝ እኔ ልመርጥ በማልችለው ማንነቴ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ ከኔ ይልቅ አንቺን አንገት ወደ ማስደፋት ያዘነብላል፡፡

ለአንባቢ፡-

ከጉራጌ ማህበረሰብ ጀገር የሚባለው ጎሳ አባል ነኝ። በዚህ ጎሳዬ ምክንያት ገጠር ጥዬው የመጣሁ የመሰለኝ ግን የተከተለኝ ስያሜ ሰለባ ነኝ፡፡

በሰባት ቤት ጉራጌ ጅግሮ የሚታወቁት በተለየ ጉዳይ ነው፡፡ ደስ የሚል አይደለም፡፡ ግን እጠቅሰዋለሁ ማህበረሰቡ ጅግሮች ቡዳዎች ናቸው ብሎ ያምናል። እንደ ጅብ ሰው ይበላሉ፡፡ ጅብ ሆነው ሌሊት ሌሊት ይንቀሳቀሳሉ ወዘተ እየተባለ ይወራል፡፡ ይሄን ስም ገጠር ትቸው መጥቻለሁ ብዬ አምን ነበር፡፡ ነገር ግን እዚህ አዲስ አበባ የሚያውቁኝ (በጅግሮነቴ) ሰዎች ነበሩና “ቡዳነቴ” አልተረሳም፡፡

ሊያ ይህን ሰማች እና እንዳይበላይ ብላ ሸሸች። አዘንኩ!

ማገናዘብ የምትችል ናት ብዬ አስብ ነበር፡፡ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የዘለቀው ትምህርቷ ከአሉባልታ እንድትፋታና ተጨባጭ እውነት ላይ ብቻ እንድታተኩር ያደርጋታል ብዬ አምን ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ 

ወሬውን በእርግጠኝነት አምና ወደእኔ መቅረብ ፈራች፡፡

በሆነው ሁሉ አዘንኩ፡፡

አንገቴን ደፍቼ አነባ ገባሁ፡፡

Published in ልብ-ወለድ

“በግጥሞቼ ፈገግ እላለሁ፤ በልቤ ግን ግፍን እያስታወስኩ አለቅሳለሁ”

   በዐሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍል ዘመን ላይ የሩሲያ መጽሔታዊ ሥላቅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ የመጽሔት ዝግጅት ክፍል ኃላፊ የነበረው ደግሞ ኢቫን ክሪሎቭ ነው፡፡ ካንቴሚር “በግጥሞቼ ፈገግ እላለሁ። በልቤ ግን ግፍን እያስታወስኩ አለቅሳለሁ” እንዳለው ክሪሎቭም የካንቴሚርን ይትበሃል ጠብቆ መጽሔት ያሳትም ነበር፡፡ ክሪሎቭ ተሣላቂ /ሣታየሪስት/ እና በጣም ርኅሩኅ /ሰብዓዊ/ ደራሲ እንደነበር ይነገርለታል፡፡

ክሪሎቭ “የደብዳቤው መንፈስ” በሚል ዓምዱ ቦሬይን የተባለው ጸሐፊ “እብደታቸውን ሳልመለከት ሰዎችን እወድዳቸዋለሁ” በሚል የጻፈውን ሐተታ በመጽሔቱ ላይ አሳትሞ ተደናቂነትን አግኝቷል፡፡

ኢቫን አንድሪየቪች ክሪሎቭ የተወለደው የካቲት 13 ቀን 1769 ሞስኮ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ብዙም ሀብት አልነበራቸውም፡፡ ወላጅ አባቱ አንድሪየቪች የጦር ሠራዊት መኮንን ነበር፡፡ በ1774 አንድሪየቪች ጡረታ ሲወጣ ኑሮን ለመቋቋም ሲል ከዋና ከተማው ከሞስኮ “ትቮር” ወደ ተባለች አነስተኛ ከተማ ሲሄድ ክሪሎቭም ቤተሰቦቹን ተከትሎ ወደዚያው ሄደ፡፡ ትቮር በዘመኑ የሳይንስና የባህል ማዕከል ስለነበረች ለወጣቱ ክሪሎቭ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረለት፡፡

ትቮር ከተማ የቴአትርና የሥነ ጽሑፍ ማዕከል ተቋቁሞ ትምህርት ለወጣቶች በሴሚናርና በውይይት ደረጃ ይሰጥ ነበር፡፡ ክሪሎቭም ወደ ማዕከሉ በመሄድ የሚሰጠውን ትምህርት በንቃት ተከታተለ። በተለያዩ ቴአትሮችና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ላይ የሚደረገው ውይይት፣ ክርክርና በዐውደ ጥናቱ ላይ የሚሰጠው የማጠቃለያ ሐሳብ ወይንም አስተያየት ለወጣቱ ክሪሎቭ በእጅጉ ጠቃሚ ነበር። በዚህ ዓይነት ቴአትርንና ሥነ ግጥምን ለማጣጣም በመቻሉ ለኪነጥበብ ከፍተኛ ፍቅር አደረበት። መምህራንና ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ውስጥ በሥላቅ ላይ ያተኮረ ድርሰት ሲያነብቡና ድራማም ሲያቀርቡ ክሪሎቭ በየጊዜው መንፈሱ ይመሰጥ ጀመር። በተለይ የገጣሚ ፌዎዶር ሞዴስቶቭን ግጥም ከሰማ በኋላ መላ ሕይወቱን በኪነጥበብ ዙሪያ ተሠልፎ ለመኖር ወሰነ፡፡ የሞዴስቶቭ ግጥም የሚከተለው ነው፡-

“ለመኖር ከፈለግህ በሰላም በርጋታ፣

ፈጣሪን ሳትሰለች አመስግን ጠዋት ማታ፣

ከመከራው ጉድጓድ ያወጣሃል ጌታ፡፡

ከክፉ አድራጊዎች ከየገበታቸው፣

እንዳትበላ ፍሬ ከጠረጴዛቸው፣

አብረህ እንዳትጓዝ በሰረገላቸው፡፡

ሰረገላቸውን እርሳው እንደ ሞተ፣

በእግርህ መንቀሳቀስ ይበጅሃል ለአንተ፡፡

ክፉ አድራጊዎቹ ጥሩ ወዳጅ መስለው፣

በውሸት ፈገግታ ልብህን አሙቀው፣

ያፈቀሩህ መስለው፣

መርዝ ያቀርቡልሀል በውሃ በርዘው፡፡

አንተም ምስኪኑ ሰው ያኔ ትወድቃለህ፣

ይህ ነው የእነርሱ ቅርስ የተላለፈልህ፡፡”

ለትቮር ነዋሪዎች በሴሚናር መልክ የሚተላለፈው የሥነጽሑፍ ትምህርት ታላቅ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ በሴሚናሩ ላይ በየጊዜው በግምት ስድስት መቶ ሰዎች ይሳተፉ ነበር፡፡ እናም ክሪሎቭም ወደ ሥነ ጽሑፍ ክበብ በየወቅቱ መሄዱና ትምህርቱን መከታተሉ ላያስገርም ይችላል፡፡ በ1779 ታዋቂ መኮንን የነበረው አባቱ ሲሞት የመኖር ተስፋ ፈጽሞ ራቀው፡፡ ነገር ግን ወላጅ እናቱ በጣም ጠንካራና ታታሪ ስለነበረች ልጅዋን በተሻለ መንገድ ለማሳደግ ስትል ወደ ፔተርቡርግ ይዛው ሄደችና የመንግሥት ሥራ አስቀጠረችው፡፡ ክሪሎቭ ፔተርቡርግ ከተማ እንደገባ “ኮፌይኒሱ” የተሰኘ ኮሜዲያዊ ኦፔራ አዘጋጀ፡፡ ቆይቶም በተረትና በኮሜዲ ላይ ያተኮረ ድርሰት በመጻፍ ታወቀ፡፡ ወደ ፔተርቡርግ በሄደበት ዓመት ላይ ሌላ የኮሜዲ ድረስት ጽፎ ለአንድ የመጽሐፍ ባለመደብር ሸጦ በአገኘው ገንዘብ የእነ ሞሌርን፣ የእነራሲንንና የእነ ቦሌይን መጻሕፍት ገዛ። ወዲያው “ፊሎሜላን” የተሰኘ ድርሰቱን አሳተመ፡፡

በ1788 ጠንካራና ታታሪ የነበረችው ወላጅ እናቱ ስለሞተችበት እንደገና ሕይወት ጨለመችበት፡፡ ግን የጨለመ ሕይወቱን ለማፍካት ሲል መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ ቆይቶ “ክሊዮፓትራ” እና “ፊሎሜላ” የተሰኙ ትራጄዲያዊ ቴአትሮችን ሠርቶ አቀረበ፡፡ በእነዚህ የኦፔራ ድርሰቶቹ አማካይነት በዘመኑ የነበሩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለተመልካቾቹ አሳይቷል፡፡ አቀራረቡ ፋርሳዊ ነበር፡፡ ፋርስ የቴአትር ሌላኛው የአቀራረብ ስልት ነው፡፡ በ1786 “ቤሽናያ ሴማያ” የተሰኘ ኦፔራ ደረሰ። በኦፔራው ትዕይንት የሱምቡር አያት፣ እናቱና እህቱ፣ ፓስታን የተባለውን ሰውዬ ያፈቀረች ልጁ ይታያሉ፡፡ ሁሉም ቆንጆ ልጃቸውን ስለአላፈቀረ ከፓስታን ገንዘብ ለመቀበል ይፈልጋሉ፡፡ ሱምቡር ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፡-

“ፓስታን ወርቅ ከአልሰጠኸኝ አንገትህን በሠይፍ ከልየ - እገድልሃለሁ” ይለዋል፡፡ በዚህም ንግግሩ ሴቶቹ በእጅጉ ይደሰታሉ፡፡ ሱምቡር ሐሳቡን እንዲህ እያለ በግጥም ፓስታንን ይሰድበዋል፡፡

“ጭንቅላት ባይኖርህ፣

ወርቅ ነው ካፖርትህ፣

አክብሮት ሳልሰጥህ፣

ስለዚህም ፈለግሁ ልዘባነንብህ፡፡

እኔ አለኝ መብቱ አንተን ለማንጓጠጥ፣

እንደልቤ ልዝለል እንደልቤ ልፍረጥ፡፡

እንዳላወራጭህ ቀንበር አሸክሜ፣

በካፖርትህ ብቻ እቀፈኝ ወንድሜ፡፡”

ሱምቡር አፉ እንደአመጣለት የሚናገርና ዓላማ ቢስ ሆኖ በተለምዶ የሚኖር ገጸባሕርይ ነው። ክሪሎቭ ከ1787 -1788  “ፊት  ለፊት” የሚል “ሪፍሞክራድ” “ሪፍሞህቫታ” ኮሜዲ አዘጋጀ። የኮሜዲው ይዘት የሚያተኩረው የሥነ ጽሑፍ ሥራው ተጻራሪው በነበረው ጸሐፌ ተውኔት ክንያዥኒን ላይ ነው። የክንያዥኒን ሚስት ደግሞ የጸሐፌ ተውኔቱ የሱማርኮቭ ልጅ ስትሆን በኮሜዲው ውስጥ የእርስዋን ባሕርይ የሚያንጻባርቅ ገቢር አለበት፡፡

የክሪሎቭ ኮሜዲያዊና ኮሚካዊ ኦፔራ ለሩሲያ ቴአትር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በሩሲያ የቴአትር ታሪክ ውስጥም የከበረ ቦታቸውን ለመያዝ የቻሉት የሙያውን ሳይንሳዊ አቅጣጫ ስላመለከቱ ነው። ለክሪሎቭ ዝና ከአተረፉለት ኮሜዲያዊ ሥራዎቹ ውስጥ ከ1798-800 የጻፋቸውና ለመድረክ ያበቃቸው “ቁንጥጫ” እና “ቀልዳቀልድ” የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

እነዚህ ቴአትሮች የተጻፉት ለአንድ የቤተሰብ አባላት ሲሆን “የቤተሰብ ቴአትሮች” ይሰኛሉ። እነዚህ ቴአትሮች ለብዙ ጊዜያት ያህል ቤት ለቤት ሲታዩ የቆዩበት ዋናው ምክንያት የቀዳማዊ ጴጥሮስ መንግሥት ወደ ሕዝባዊ መድረክ ቀርበው እንዳይይታዩ ስለከለከለ ነው፡፡ ሥራዎቹ ለመድረክ እንዳይበቁ በተከለከለበት ወቅት ክሪሎቭ ለኪየቭ ቅርብ በሆነችውና የመስፍኑ የሰርጌይ ኤፍ ጋሌዚን የገጠር መንደር /ግዛት/ በሆነችው ካዛን ውስጥ የቤተመጻሕፍት ሠራተኛ ሆኖ ሠርቷል፡፡ ልዑሉ የሊቮንያ ወታደራዊ ገዥ በነበረበት ወቅትም ልዩ ጸሐፊው ሆኖ አገልግሏል፡፡ ሃያ ሦስት ያህል ፋቡላዎችን (በእንስሳት ሕይወት ላይ የተመሠረቱ ድርሰቶችን) ደርሶዋል፡፡ ከ1812-1841 የንጉሣውያን ቤተ መጻሕፍት ኃላፊና የሩሲያ መጻሕፍት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እንዲሰራም ተሹሟል፡፡ ክሪሎቨን የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የክብር አባል አድርጐት ነበር። ሥራውን መዝኖም የወርቅ ሜዳልያ ሸልሞታል። በ1838 በንጉሣውያን ትእዛዝ በስሙ የተሰየመ ታላቅ ፌስቲቫል ተዘጋጅቶለታል፡፡ ከመሞቱ በፊት የሩሲያን ገበሬ ሕይወት የሚያንጸባርቁ ሥራዎች ሠርቶ 77 ሺህ ኮፒ የፋቡላ ድርሰቶች ተሸጠውለታል፡፡ የፋቡላ ድርሰቶቹ የኤዞፕንና የጂን ዶ. ላፎንቴንን ሥራዎች መነሻ አድርገው የተደረሱ ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሣ ክሪሎቭ “ታላቅ የሩሲያ ፋቡሊስት” እየተባለ ይወደሳል፡፡ የሩሲያ ቴአትር ተመራማሪዎች “ቀልዳቀልድ” የሚለው ሥራው የቀዳማዊ ጳውሎስን ዘመን ፍንትው አድርጐ ያመለክታል ይላሉ፡፡ ዲ.ኢ ዛቫሊሽን የተባለ ታኅሣሣዊ (ዴካብሪስት ወይንም ዲሴምበር 7) ይህንኑ አስመልክቶ በጻፈው ሐተታ፤ ቁንጥጫና ቀልዳቀልድ ቴአትሮች ከላይ ከመንግሥቱ “ቁንጮ እስከ ዝቅተኛው የመንግሥት ባለሥልጣን እና መጥፎ መካሮች ድረስ የነበረውን ድርጊትና ክፋት፣ እንዲሁም ጭካኔ በሥላቃዊ አቀራረብ የሚያመለክቱ ናቸው” ብሏል፡፡

እነዚህ ሥላቃዊ ኮሜዲዎች /ቁንጥጫና ቀልዳቀልድ/ በ1924 ማለት ከታላቁ የጥቅምት ሶሻሊስት አብዮት በኋላ በሌኒን ግራድ፣ በ1944 ደግሞ በፔትሮዛቮድ ቴአትር ቤቶች ለመታየት ችለዋል፡፡ ፔትሮዛቮድ በቀዳማዊ ጴጥሮስ ስም የሚጠራ የአንድ ፋብሪካ ቴአትር ቤት ነው፡፡ የዐሥራ ስምንተኛው መቶ ክፍለዘመን የሩሲያ ድራማ ተመራማሪ የነበረው ፒ.ኤች ቤርኮቭ ስለፀሐፌ - ተውኔቱ በሰጠው አስተያየት “ክሪሎቭ ከክላሲዝም ቴአትር ተነሥቶ የሩሲያን ሕዝባዊ ድራማ ቅርጽ ያስያዘና ከሕዝባዊው ዘፈን ተነሥቶ የቴያትርን መመሪያ ያፈለቀ ደራሲ ነው፡፡” ብሏል፡፡

ድርሰቶቹ ፀረ - ፊውዳል አቋም ነበራቸው። እናም የሩሲያ ተራማጅ አስተሳሰብ ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ወደፊት እንዲራመድና ዕድገት እንዲያሳይ ሆነው የተጻፉ ናቸው። ኮሜዲዎቹ እስከ ቀዳማዊ ጴጥሮስ ዘመነ መንግሥት ድረስ በሞስኮ የነገሡት ነገሥታትን ያወግዛሉ፡፡ ምሳሌ የሚያደርጉትም ዛር /ንጉሠ ነገሥት/ ቫኩልን ነው። በቫኩል ዘመነ መንግሥት በሕዝብ ላይ የደረሰውን መከራና ችግር እንደ መስታወት ወለል አድርገው ያሳያሉ።

ክሪሎቭ የሕዝቡን ድህነትና የቫኩልን መንግሥት ጭካኔ “ቁንጥጫ” በተሰኘ ኮሜዲው አቅርቦታል፡፡ የቫኩል ሴት ልጅ እንዲህ ትላለች፡-

“አባባ ለምን ነው ሕዝቡ ተሰብስቦ፣

ስምህን የሚያጠፋው እየበላ ዳቦ፡፡”

አባትዋ ቫኩል ደግሞ እንዲህ ሲል ይመልስላታል፡-

“እጄ ዐመድ አፋሽ ነው ሐሜት ነው ቀለቤ፣

እንጀራ በአበላሁ ሕዝቦቼን ሰብስቤ

ዛሬ በጥጋቡ በደስታው ወራት፣

ሕዝቦቼ አነደዱኝ ጠበሱኝ እንደእሳት፡፡

የእኔን ታላቅነት ወደፊት ያያሉ፣

በችጋሩ ዘመን በቀጠና ወራት ስሜን እየጠሩ ያመሰግናሉ፡፡”

ክሪሎቭ በዚህ ዓይነት በዛሩ መንግሥት ዙሪያ ያሉ መሳፍንት፣ መኳንንትና ባላባቶች መልካም አስተሳሰብ የሌላቸው፣ አርቆ ማስተዋል የማይታይባቸው፣ ድድብና የበዛባቸው፣ ነባራዊውን እውነታ ለመገንዘብ የተሳናቸው መሆናቸውን በጥበቡ አድምቆ ያስረዳናል፡፡

“ከነገሥታቱና ከመሰሎቻቸው ይልቅ ድልድይ ሥር ተቀምጣ ኮፔክ የምትለምን አንዲት የጂፕሲ ሴት ከእነሱ ትበልጣለች፡፡ ምክንያቱም ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ በሩሲያና በዓለም ጭምር የሚሆነውን ስለምትተነብይ ነው” እናም “ከእነርሱ ጂፕሲይቱ ለማኝ መቶ ጊዜ ትበልጣለች፡፡” ይላል ክሪሎቭ፡፡

ክሪሎቭ “ቁንጥጫ” በተሰኘ ቴአትሩ ላይ፤

“ንጽሕና ከሌለ ይቆሽሻል ገላ

ከንፈር ከወፈረ

ጢም ከተከመረ

ይይዛል አተላ፣

ራስ ከቆሸሸ ያስጠላል ቁንዳላ፡፡

ነፋስ አያስጥልም የረዘመ አፍንጫ፣

የትም አያደርስም የዳክየ ሩጫ፡፡

አሁን በእኛ ዘመን አይ ጉድ አይ ጊዜ ብሎ እማያማርር፣

ከሴቶች ከወንዶች አለ ወይ ልመሥክር፡፡” ይላል፡፡

ክሪሎቭ “ሸሚዜ መሥክሪ” የሚል ባለ ሁለት ቤት ስንኝም አለው፡፡

“ሸሚዜ መሥክሪ ቅርብ ነሽ ለአካሌ፣

የተሳካ አይደለም የመኖር ዕድሌ፡፡”

ክሪሎቭ በሩሲያ የመጽሔት ሥላቅ ታላቅ ሥራ በመሥራቱ ስሙ ለሁልጊዜም ይጠቀሳል፡፡ ከ1769 -1774 የቢኮቭ ሥላቃዊ መጽሔት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ በኋላ እየቀነሰ ቢሄድም በ1780 “ምን አዲስ ነገር አለ?” በሚል በለዛ /ሒዩመር ላይ/ ያተኮሩ መጣጥፎችን ከነ ኖቪኮቭና ፎንቪዚን ጋር በማቅረብ የመጽሔቱን ተወዳጅነት ከፍ አድርጐታል፡፡

ማስታወሻ፡- በፅሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓ.ም በሙሉ እ.ኤ.አ ናቸው)

Published in ጥበብ

   ‹‹አብዮት፤ አበየ ፤እምቢ አለ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ነው›› የሚለው ዬኔታ ስብሀት፤ የመጀመሪያው አብዮተኛ ሰይጣን ዲያቢሎስ ነው ይላል፡፡ በእንግዳና ተቆርቋሪም ‹‹ጋዜጠኛ›› መሳይ አቀራረብ ‹‹በእውኑ እግዚአብሔር ከዚህ በገነት መካከል ከሚገኘው ፍሬ እንዳትበሉ አዝዟልን…›› በሚል ህልውናን ተፈታታኝ ጥያቄ አብዮቱን ያቀጣጠለባቸው ምስኪኖቹ አዳምና ሄዋን ግን ‹‹ሰው›› ነበሩ፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ የሚጀምረው ከውድቀት ነው፡፡ ‹‹ሰው አፈር ነው አሉ፤ ሰው አፈር ነወይ…አዬ ሰው አፈር ነወይ…›› ትላለች ሙሾ አውራጅ፡፡ አዎ እናቴ! ያውም ስድስት ክንድ መሬት ውስጥ ኩርምት ብሎ የሚረሳ ነዋ! አስከሬኑም ከሌሎች እንስሳት አንጻር ለመበላሸት ይቸኩላል፡፡ ‹‹የኔ ቢጤው›› ደግሞ ያውም ከስህተቱ የማይማር፤ታጥቦ ጭቃ! እንዴት ማለት መልካም…በዚያው በኦሪት አቀራረብ በሰዎች መካከል ጠብንና አለመተማመንን መዝራት ተለምዶ! ምነው…አይባልም! ነውር ነው! ፋሽን ሁኗላ! እናም በአለም ላይ የመጀመሪያው ቀጣፊና ዋሾ ሰውን አሳተ! ቃየን ተወለደ። ‹‹ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይመለስም›› የኦሪት ተረት ነች መሰለኝ፡፡ ሴጣን ዲያቢሎስ ዳግም በቃየን ልብ ቅናት ሆኖ ገብቶ አቤልን አስገደለ!

 ይህን መንገድ ገና በዘፍጥረት በኖሩ ሰዎች ላይ ስናየው ባይገርመንም አሁን ላይ ቆመን አወራረዱ ሰውን ምንኛ ከራሱ ጋር እንዳቆራረጠው ስናስተውል ግን ዘግናኝ ሆኖ ይገኛል፡፡ ማን ነበር ‹‹አላዋቂን ብታስደምም ተመራማሪን ታስቀይማለህ›› ያለው…እህ! ይኸዋ ያንኑ የቀድሞውን የኦሪት አልባስ ‹‹ሰው›› በልኩ እያስጠበበና እያስሰፋ ሲለብሰው ይኖራል፡፡ ታላቁ እስክንድር የአምላከ አማልእክቱ የዜዩስ ልጅ ነኝ፡ ፈረሴም እንዲሁ! አለ። ሸመጠጠ፡፡ በአፍ የተናፈሰ ገድሉ ገና በሩቁ የሰሙትን ሁሉ እያርበደበደ አለምን በሞላ ሊገዛ በቃ! ችግሩ በመጨረሻ የሚገዛው ግዛት ማለቁ ሲነገረው ስቅስቅ ብሎ ማልቀሱ ነው፡፡ ሰው ነዋ! አይረካም! ‹‹ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› እንዲል መጽሐፍ፡፡ ናፖሊዮን ቦናፖርት! ከአንድ ባታሊዮን ጦር አንድ ጋዜጠኛ የሚያስፈራው ንጉሥ ናፖሊዮን በወታደሮቹ መካከል በአጭር ቁመቱ እየተንጎራደደ የአንዱን ወታደር ስም ጠርቶ ‹‹ዤራርድ ቀና በል እንጂ!›› ይለዋል፡፡ አበቃ! ወታደሩ ሁሉ የኔንም ስም ያውቀዋል ብሎ ይደመድማል፡፡ የናፖሊዮን ጋዜጠኞችም ይህንኑ መሰል ወሬዎችን ሞቅ አድርገው ያራግባሉ፤በቃ በዚህ የተጠናና የተቀናበረ ያቀራረብ መልክም ናፖሊዮን በተጨናበረ አለማዊ ክብር ሽቅብ እየተመነደገ ፈረሱን ኮልኩሎ ይሸመጥጣል፤ሀገር ወዳዱ ምስኪን ዜጋ ለሀገር ሉአላዊነት ቢሆን ደግ፡ንጉሡ ጠብ ያለሽ በዳቦ እያለ አቧራ በሚያስነሳበት በየፍልሚያው ያለእዳው ነፍሱን ይገብራል። ለምን ቢል…ሀገር መክዳትን አይነት ከቀረው ዜጋ ጋር የሚያቃቅርና የሚያራርቅ በቀዬውና በየጎጡ የሚናፈስ ረቂቅ ወሬ ሴራ ይቀመርለታል! ካፍታ የማስታወቂያ ቆይታ በኋላ ይፈጠፈጣል! ከዚህ ይልቅስ የሂትለር ‹‹ወዳጅነትና እንክብካቤ›› ይምጣብኝ! ‹‹ያስጠራውህ ለስልጣኔ ስለምታሰጋኝ ልገድልህ ነው፤ ቢሆንም ግን ምንም ቢሆን ወዳጄ ነህና አንተ እንደማንኛውም ሰው አትሰናበትም፤እናም አይዞን! ቀብርህ በክብር የፊልድ ማርሻልነትህ ደረጃ በምናምን ሺህ ያህል መቶ ጄኔራሎች፣በምናምን ሺህ አለቃዎች ይከናወንልሀል። እንዴ ምን በወጣህ፤ወዳጄኮ ነህ! ህእ!›› ታዲያ  አሁንም ሚዲያ ነፍሴ የፊልድ ማርሻሉን እንቆቅልሽ የህልፈት ጉዳይ ትቶ ከአለም አንደኛ የሆነውን ጉደኛውን የቀብር ስርአቱን አግዝፎ ሲዘግብ ይገኛል። ምን ታመጣለህ አልክ….ልክ ነህ፡፡ አዎን ምንም አይባልም። ምንስ ሊባል ይችላልና…በአምባገነኖችና ክቡር እምክቡራኑ መዋእል ውስጥ አዲስ ነገር ነውን’ዴ ይኼ…ንጉስ ካሊጉላ ቢሰማ ግን ‹‹ሞት ራሱ ነው መሞት ያለበት›› ይልሀል፡፡

ማሪያን አንቶኔት፤ የትውልድ ሀገሯን ስዊዝን በስውር እየረዳች በሚዲያ ወከባዋ የፈረንሳይ አፍቃሪ ንግስት ነበረች፡፡ ጠኔ ሲያንገላታው የነበረው የሰፊው ህዝብ ሚዲያ በእንቁ እንደምትንቆጠቆጥ የደረሰባትና ያጋለጣት ጊዜ ግን የተገኘችው በእኩለ ሌሊት ወደ ሀገሯ ልትፈረጥጥ ስትሞክር ነበር፡፡ ድንበር ላይ፡፡ ጀንበር ስትፈነጥቅ አንገቷ እንደሚቀላ ስታውቀው በታሰረችበት ማቆያ ክፍል ውስጥ መአልቱን ጠጉሯ ጥጥ መስሎ ሸብቶ አደረ፡፡

ዘመናዊው የሚዲያ ጦስም ይህንኑ መንገድ ሲገፋበት እናያለን፡፡ ለከፍታም /ሽምጠጣ/ ለዝቅታም /ፍጥፈጣም። ከሽምጠጣ ብዙ ቀሽት ቀሽት የሆኑ የየዘመኑ የታሪክ ዝንጣፊ ድርሳናት አሉ፡፡ ግራ የሚያጋባው ፍጥፈጣ ከገጠማቸው መሀል ዝነኛ ዝነኛ የሆኑትን ለመጥቀስ ያህል ማይክል ጃክሰን ፆታው ‹ግራ› ነው፤ ቢል ክሊንተን ሞኒካን እነሆ በረከት አለ፤ ማራዶና ዕፀ ፋርስ አጤሰ፤ ከሀገራችን ደግሞ ቴዲ አፍሮ ጡት ላይ ፈረመ እና በእንትን ምክንያት ታረደን የጥላሁን ገሠሠን መጠቀስ ይቻላል፡፡ ‹‹የዜማው ንጉሥ!›› ጥላሁን አንድ ነገር ብቻ አለ…‹‹ሆድ ይፍጀው!›› … እሱኑ በዜማ ብናጅብለትስ… ‹‹አረ ተዉኝ፤ባትነኩኝ ምናለበት፤እባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት…››

ፈጥፋጮቹ ባቀራረበባቸው የሚከተሉት ጥበብም ለተፈጥፋጩ /ለሚጠመድበት/ ከዚያው ከኦሪቱ አዳምና ሄዋን ከገጠማቸው ፈተና/ ወጥመድ ጋር ተመሳሳይ ነው። ‹‹መልኩ ያማረ ለመብላትም የሚያጓጓ›› እንደነበረ ስለ በለስ ፍሬ ተፅፏል፡፡ ሰው አፈር ነውና፤ፍፁም አይደለምና ይስታል፡፡ ያኔ ፈጥፋጭ ከች ይላል፡፡ ዘመናዊው አለም ደግሞ ይህንን ሁናቴ ‹‹የአኪሌዝ ተረከዝ›› ይለዋል። አኪሌዝ ምንም ጦርና ቀስት እንዳይወጋው እናቱ እግሩን ይዛ ምትሀተኛ ውኃ ውስጥ /ቡሌት ፕሩፍ ነገር አይነት/ ነከረችው፡፡ ምን ዋጋ አለው፤ ሰው ፍፁም አይደለም አይደል…በእጇ የያዘችው መዳፏ የሸፈነው የተረከዙ ክፍል በዚያ ‹‹ተአምረኛ›› ውሃ አልተነከረም ኖሮ ለውድቀቱ ሰበብ ሆነ፡፡

ዘመናዊው አለም መረጃን ለአይነተኛ አላማ ማስፈፀሚያነት ከማዋሉ ባሻገር እንደ ሸቀጥ መተዳደሪያ ማድረግን አጠናክሮ በገፋበት መጠን ደግሞ የሰብአዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ መውደቁን የምናስተውለው ወጣቷን ልዕልት ዲያናን ቀን ተሌት በመከታተል አሳድደው አሳድደው ከፍፃሜዋ አፋፍ ላይ ካደረሷት በኋላም፤ በፎቶግራፍ ጥበብ ሩሕዋን፣ የነፍስ ህቅታዋን በምስል ለማስቀረት ሲጋፉ መታየታቸው ነው - ፓፓራዚዎች። የሙያ ፍቅርም ሊሆን ይችላል በእርግጥ፡፡ መረጃን ፈጥኖ ማቀበል የሚበረታታ ሙያ መሆኑን ባንክድም፤ወደ ድሀዋ ጎጇችን ትውፊታዊና ባህላዊ መስተጋብር ስንመጣ ግን፤መቸም ወፍ እንደ ሀገሩ ይጮሀልና ‹‹ካፍ ከወጣ አፋፍ››፣ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› …ወዘተ በሚባልበትና መገናኛ ብዙኃን ያወሩት በፅኑ በሚታመንበት ማህበረሰብ መካከል የአንዳንድ አዕዋፍ የተኮረጁ ፉጨቶች /‹‹ፍጥፈጣዎች››/ የአንድ ወገን ዘገባዎች ጩኸት ‹‹ፍጥፈጣ›› በክቡሩ የሰው ልጅ ስብእና ላይ የሚያደርሱት የማይጠገን የመንፈስ ስብራት፤ በሰማዕታቱ የነፃነት ታጋዮች ክቡር ደም ህገ መንግስታዊ የዜግነት መብት በተጎናፀፈው ክቡር ዜጋ ላይ የሚፈጥሩት አሉታዊ አመለካከትና የሚያሳድሩት ማህበራዊ ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጽሙና ይስጠን! አሜን…

በዚህ አካሄድ ከቀጠልንና ምዕራባዊያንን የመኮረጅ ችሎታችን ረቀቅ እያለ ከመጣ’ኮ…ኦኦኦ! አደጋ ነው ወገን! የምር! አርቪንግ ዋላስ፤ መረጃ ያጣውን ተወዳጅ ጋዜጣ ላለመዝጋት ሲሉ ትኩስ/ያልተጣሩ/ለነጭ ባህልና አኗኗር የሚስማሙ የወንጀል ዜናዎችንና ራሱን ወንጀሉንም መስራት ስለጀመሩት የኤዲቶሪያል አባላት የፃፈውን መፅሀፉን ያስታውሷል፡፡ የሰው ልጅ ሆይ ወዴት እየሄድን ነው …በቅንነት ካየነውም ይህን መሰሉ በግለሰቦች ማንነትና ገመና ላይ ያነጣጠረ ክብረ ነክ የወሬ ማዕድ ለኢትዮጵያዊ ከሚሰጠው የሚዲያ /ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት ትሩፋቱ ይልቅ መከባበርን የሚያጎድለው፣እውነትን የሚያራቁተው፣ እርስ በእርስ መተማመንን የሚሸረሽረው፣ በገዛ ሀገር ላይ የሚያሳቅቀው፣ ጥርጣሬን የሚያነግሰውና ሰላማዊ ኑሮን የሚያሽቆለቁለው …ወዘተ ነገሩ የበዛ ይመስለናል፡፡ የእውነት፡፡ ‹‹አይነፋም!›› እንዲል ያራዳ ልጅ ሰሞንኛ ቋንቋ፡፡ ሌሎች የሚያስጨንቁ የሚያንገበግቡ አጀንዳዎች የሉንም ማለት ነውስ…ከነገረ ቀደምስ፣ ዋናው ግብ ማለት መረጃው በህግ አግባብ ከመዳኘቱ በፊት ለሚሊዮኖች ለማድረስ የመጣደፉስ አካሂያድ ነገር የምር በቃ አላማው ምንድን ነው ያሰኛልም’ኮ አንዳንዴ። በተለይ በተለይ ደግሞ የሌላኛው ፅንፍ /የተፈጥፋጩ እንበለው…/ የመደመጥ መብት (the right to be heard) ገና ባልተስተናገደበት ሁኔታ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ፡፡ ደርግ አንድን ዜጋ ከገደለ በኋላ ጉዳዩ ሲጣራና ዜጋው ንፁህ ሆኖ ሲገኝ ‹‹ለቤተሰቦቹ አብዮታዊ የይቅርታ ደብዳቤ ይፃፍላቸው!›› የምትል ብሂል ነበረችው አሉ፡፡ ቀልድ! (ጅብ ከሄደ ውሻ) የከበደ ሚካኤል ‹‹ጃፓን እንዴት ሰለጠነች››፣ የነጋድራስ ገብረህወት ባይከዳኝ ‹‹ህዝብና መንግስት አስተዳደር›› አይነት መጻህፍት፣ አስተሳሰቦችና አሳቢ አሰላሳዮች thinkers , visionaries ቢበረክቱላት ብለን የምንመኝላት፣ እትብታችን የተቀበረባት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ምድር ናት፡፡ እናም ኢትዮጵያ ሀገራችንም መቼም ቢሆን ልጆቿን በእኩል አይን ነው የምታየው ብለን ነው በፅኑ የምናምነው እንግዲህ እስካሁን፡፡ ክብር ለሰብአዊነትና እኩልነት ቅድሚያ ለሚሰጡ ‹‹ነፃ›› ሚዲያዎች ይሁን!

እግዚአብሔር ከሚፀየፋቸው ነገሮች አንዱ በወንድማማቾች መካከል ፀብን የሚዘራ ምላስን ነው ይላል ቅዱሱ መጽሀፍ፡፡ ዮሴፍ እግዚአብሔር የሰጠውን ራዕይ/ህልም ለመኖር ሲተጋ በጲጥፋራ እልፍኝ የደረሰበትን የ‹‹አስገድዶ መድፈር›› ውንጀላ በጋሻው ደሳለኝ በስብከቱ ሲተነትነው፤ ‹‹አድርጎት ቢሆን ኖሮ ጨርቁ /በንግስቲቱ ተበጭቆ ኤግዚቢት የሆነበት/ ከፊቱ ነበር የሚቀደደው፤ ውሸት የሆነ ነገር ሁሉ ከኋላ ነው የሚጎለጎለው…ዮሴፍ ንግሥቲቱ እጮሃለው ስትለው እግዚአብሔር ዘለአለም ከሚጮህብኝ እሷ አንድ ጊዜ ትጩህ ብሎ ፈቀደና ራሱን ለእስር፣ ለእግር ብረት ዳረገ›› ብሏል፡፡……ማንም ፍፁም አይደለም ማለቱስ አይደለም ወይ ክርስቶስ ‹‹በራስህ አይን ያለውን ግንድ ሳታወጣ፤በሰው አይን ያለውን ጉድፍ ላውጣ አትበል›› ወይም ‹‹ከናንተ ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋ ይወርውር›› ማለቱ…

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ዋዜማ አንድ አውሮጳዊ ጋዜጠኛ በድንገት ተነስቶ ‹‹በምድራችን ለሚከሰቱት ችግሮች ሁሉ መንስኤዎቹ አይሁዳዊያን ናቸው!›› አለ። በቃ! አይሁዳዊያን ‹‹ተፈጠፈጡ››! … ከአሰቃቂው የኦሽዊትዝ ካምፕ የሰቆቃ ህይወት ምስኪን ወላጅ እናት፣ አባቱንና ሁለት እህቶቹን አጥቶ ብቻውን በተአምር የተረፈው ኤሊ ዊዝል ‹‹ናይት›› በሚል ርዕስ የመከራ ዘመን ታሪኩን ባሰፈረበት መፅሀፉ፣የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ሆኖ መድረክ ላይ ሲቆም ፤የሰው ልጆችን ወደ ጥፋት በሚነዱ ድርጊቶች የተሰማሩ ሰዎች በህሊናቸው እንዲያመዛዝኑና ሰፋ አድርገውም እንዲያስተውሉ አበክሮ ሲገልጽ፤ በአለም ላይ ሰላማዊ አየር እንዲሰፍን ባስተላለፈው ምኞቱ መካከል በተለየ ሁኔታ ስማቸውን ከጠራቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ኤሊ ዊዝል እንባ ባቀረሩ አይኖቹ ታዳሚውን ትክ ብሎ እያየ በእብራይስጥ ቋንቋ ‹‹ከዚያ ሁሉ መአት ያተረፈኝ የእስራኤል አምላክ ይባረክ ›› አለና ጥቂት ፋታ አድርጎ የመጨረሻውን ዓረፍተ ነገር ተናግሮ ከመድረክ ወረደ። ‹‹እነሆ፤ ሁሉም ያልፋል፡፡ ያም ሆኖ ግን በክፉ ሰዎች የተነሳ የደረሰብኝን መራራ ግፍ መቼም መቼም መቼም ቢሆን በፍፁም አልረሳውም!!!››

ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ይባርክልን፡፡ አሜን፡፡

Tuesday, 26 May 2015 08:20

ምሳሌያዊ አባባል

የአዞ ጉልበት በውሃ ውስጥ ነው፡፡

የደቡብ አፍሪካውያን አባባል

ብልህ ወፍ ጎጆዋን በሌሎች ወፎች ላባ ትሰራለች

የዚምባቡዌያውያን አባባል

ሁለት መሪዎች በአንድ ቤት ውስጥ አይጣሉም፡፡

የኡጋንዳውያን አባባል

ደካማ መሪ ጭንቅላቱ ውስጥ ሸክም ያበዛል።

የኡጋንዳውያን አባባል

መሪ ካነከሰ ሌሎችም ማንከስ ይጀምራሉ፡፡

የኬንያውያን አባባል

የመሪ የተሳሳተ እርምጃ ለተከታዮቹ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡

የአፍሪካውያን አባባል

አገር በማስፈራሪያና በስድብ ጨርሶ አትመራም፡፡

የዛምቢያውያን አባባል

መሪ የሌለው ህዝብ ከተማ ያበላሻል፡፡

የጋናውያን አባባል

በዓለም ላይ እጅግ ኃይለኛው መሪ እንኳን በእንቅልፍ ይሸነፋል፡፡

የማላዊያውያን አባባል

አይጥን የሚገድል ዝሆን ጀግና አይባልም፡፡

የካሜሩያውያን አባባል

የመሪ ሃብቱ ህዝቦቹ ናቸው፡፡

የኮንጎአዊያን አባባል

ብቸኛ መሳሪያህ መዶሻ ከሆነ ችግሮችን ሁሉ እንደምስማር ትቆጥራቸዋለህ፡፡

የጋምቢያውያን አባባል

ውይይት ሲበዛ ወደ ፀብ ያመራል፡፡

የአይቮሪኮስት አባባል

አንበሳ ሳር ውስጥ መደበቅ አይችልም፡፡

የኬንያውያን አባባል

ሰው ረዥም ጥርስ ማብቀል ከፈለገ መሸፈኛ ከንፈር ሊኖረው ይገባል፡፡

የናይጄሪያውያን አባባል

አዳነ ግርማ  በብሄራዊ ቡድን 38 ጨዋታዎች በማድረግ 8 ጎሎች አስመዝግቧል

1. ስምንቱ ጎሎች እነዚህ ናቸው

2. በ2008 እኤአ በአዲስ አበባ  በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሞሪታንያ ላይ

3. በ2009 እኤአ በናይሮቢ  በሴካፋ ካፕ ጅቡቲ ላይ

4. በ2011 በአዲስ አበባ ላይ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ማዳጋስካር ላይ

5. በ2011 በዳረሴላም በ2011 ሴካፋ ካፕ በማላዊ ላይ

6. በ2012 በኮተኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ቤኒን ላይ

7. በ2012 በካርቱም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሱዳን ላይ

8. በ2012 በአዲስ አበባ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በሱዳን ላይ

9. በ2013 በኔልስፕሪት ደቡብ አፍሪካ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛምቢያ ላይ

               የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አጥቂ የሆነው አዳነ ግርማ ከዋልያዎቹ አባልነት ጫማ መስቀሉን ባለፈው ሳምንት አስታወቀ፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  ስብስብ ያሳየው የአሸናፊነት መንፈስ መቀጠል እንዳለበት ለስፖርት አድማስ በሰጠው አስተያየት የመከረው አዳነ፤ ዋልያዎቹ ስኬታማ ለመሆን የሚችሉት በአንድነት  እና በትጋት መስራት ከቻሉ ነው ብሏል፡፡ ከዋልያዎቹ ትውልድ በፊት በነበሩት ብሄራዊ ቡድኖች ስንጫወት ማልያችን አያኮራንም ብሎ ያስታወሰው አዳነ፤ ያኔ ተጨዋቾች በተለያዩ ውዝግቦች እርስ በራስ የሚናናቁ፤ በውጤት ማጣት አንገታቸውን የደፉ ነበሩ ይላል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ብሄራዊ ቡድኑ በዋና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በተመራበት ወቅት ግን ሁሉ መቀየሩን ይገልፃል፡፡ ዋልያዎቹ በሚል ስሙ የታወቀው ስብስቡ ከሜዳ ውጭ ወሳኝ ጨዋታዎችን በማሸነፍ፤ በአንድነት እና በፍቅር ተከባብሮ በመስራት እንደተሳካላትም በኩራት አንስቷል፡፡ ዋልያዎቹ በተባለው ትውልድ የተገኙ ስኬቶች እና የተፈጠሩ መነቃቃቶች አሁን ላለው ትውልድ ተምሳሌት ሊሆኑ እንደሚገባ የጠቀሰው አዳነ ግርማ ተጨዋቾች ለአገር ክብርና ውጤት ቅድሚያ ሰጥተው በመግባባት መስራታቸውን እጠብቃለሁ ሲል ለስፖርት አድማስ ተናግሯል፡፡ የእግር ኳስ ህይወቱን በክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቀጠል እንደሚፈልግና አቅሙ እስካለው ድረስ ለመጫወት ማቀዱን የብሄራዊ ቡድን ጫማውን በሰቀለበት ወቅት የተናገረው አዳነ፤ ጎን ለጎን ወደ ኢንቨስትመንት መግባቱ እየተገለፀም ነው፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ታሪክ ፈርቀዳጅ በሆነ መንገድ እስከ  4.5 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ በሃዋሳ ልዩ መዝናኛ ሆቴል ገንብቷል፡፡ ወደ ቢዝነሱ መግባቱ በእግር ኳስ ህይወቱ ላይ ምንም አይነት ጫና እንደማይፈጥርበትም ተናግሯል፡፡

አዳነ ግርማ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ተከታታይ አመታት ለሀዋሳ ከነማ ክለብ የተጫወተ ሲሆን፤ ከዚህ የትውልድ ከተማው ክለብ ጋር ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮና እንዲሁም አንድ የጥሎ ማለፍ በድምሩ  ዋንጫዎችን  ተቀዳጅቷል፡፡   ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ  ደግሞ  ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላለፉት 8 የውድድር ዘመናት ሲጫወት የቆየሲሆን ለ6 ጊዜያት የፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮናነት ክብሮችን እንዲሁም በጥሎ ማለፍ እና በአሸናፊዎች አሸናፊ ሌሎች ዋንጫዎችንም ተጎናፅፏል፡፡ በክለብ ደረጃ ለሃዋሳ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሲጫወት ባለፉት 10 የውድድር ዘመናት በተለያዩ ውድድሮች ከ100 በላይ ጎሎችንም በስሙ ማስመዝገቡ ይገመታል፡፡

አዳነ ግርማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ለስምንት ዓመታት በብሄራዊ ቡድኑ ተጫውቷል፡፡ በተለይም ከ31 አመት በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው ይታወሳል፡፡ በዚሁ ደቡብ አፍሪካው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዳነ ግርማ ከ37 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመዘገበችውን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረውም እሱ ነው፡፡ በ2014 መግቢያ ላይ በዚያው ደቡብ አፍሪካ በተደረገው 3ኛው የቻን ውድድር እንዲሁም በዓለም ዋንጫ ማጣርያ እስከመጨረሻው ማጣርያ በተደረገው ትንቅንቅ ላይም ዋልያዎቹን በማል ሞተርነትና በአምበልነት በመምራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ አዳነ ግርማ በተጨዋችነትዘመኑ መሰለፍ ያልቻለው በግብ ጠባቂነት ስፍራ ብቻ ነው፡፡ አጥቂ፣ አማካይ፣ የመስመር ተመላላሽ ፤የመስመር ተከላካይ፣ መሃል ተከላካይ ሆኖ  በመጫወት ሁለገብ ብቃቱን አሳይቷል፡፡

ከ2 ዓመት በፊት በነበረው የዋልያዎቹ ስኬት አዳነ ግርማ በነበረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ትኩረት ያገኘባቸው ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ በወቅቱ ነዋሪነታቸውን በዱባይ ያደረጉ አምስት ኢትዮጵያዊያን ጓደኛሞች በአፍሪካ ዋንጫላይ ባገባት ጎል ተደንቀው እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሺ ዶላር በማዋጣት በ10ሺ ዶላር  ቶዮታ ኮሎራ ሸልመውታል፡፡ የዋልያዎቹ አፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ ከተጠናቀቀ በኋላ  ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተዘጋጅቶ በነበረው የእራት ግብዣ ለብሶት የነበረው 19 ቁጥር ማሊያ 93,000 ራንድ እስከ 162ሺ ብር ተጫርቷል፡፡

ሌሶቶ እና ሲሸልስ በኮሳፋ ካፕ ተሟሙቀዋል

         አልጄርያ እስከ ኢትዮጵያ ግጥሚያ የወዳጅነት ጨዋታ  የላትም

         ኬንያ የቻን ማጣርያን በሜዳዋ ለመጨረስ ዝግጅቷ ቀጥሏል

                                        ከወር በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ እና በቻን ውድድር የማጣርያ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአስቸኳይ ዝግጅቱን መስራት እንዳለበት ሁኔታዎች እያመለከቱ ነው፡፡ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ  ሆኖ እንዲሰራ በእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተመረጠው  ዮሐንስ ሳህሌ ከ2 ሳምንት በፊት  ስራውን በይፋ  የጀመረ ቢሆንም ብሄራዊ ቡድኑ እስካሁን አልተሰባሰበም፡፡ ከአሰልጣኙ ጋር በሃላፊነቱ ዙርያ የተካሄዱት ተከታታይ ውይይቶች በተሳካ ሁኔታ መደረጋቸውን የገለፀው ፌደሬሽኑ፤ ለብሄራዊ ቡድን የሚያስፈልጉ የተለያዩ ትኩረቶችእና የወዳጅነት ጨዋታዎችን አስመልክቶ ብዙም ተጨባጭ ነገሮችን አላሳወቀም፡፡

በፌደሬሽኑ እና በዮሃንስ ሳህሌ የውል ስምምነት መሰረት በ2017 እኤአ ጋቦን በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ  ዋሊያዎቹ በተደለደሉበት ምድብ 10 በሚያደርጓቸው ስድስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ዋናው ውድደድር ለማለፍ የሚያስላቸውን  ነጥብ ማስመዝገብ እና  በ31ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ  ተሳታፊነታቸውን የማረጋጋጥ ሃላፊነት ተጥሏል፡፡ በቻን 2016 እና በሴካፋ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ  ውድድሮችም አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅባቸው ተማምነዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለ31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካበቁ የስራ ዘመናቸው እስከ ኤፕሪል 2017 ዓ.ም ድረስ እንደጸና ይቆያል ተብሏል፡፡  ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኝ ዮሐንስ  75ሺ ብር  ወርሃዊ ደመወዝ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን ተሽከርካሪ ከሾፌር ጋር እንዲሁም ባለመስመር የሞባይል ስልክና የጤና ኢንሹራንስ ከማሟላት በተጨማሪም  ውጤትን መሰረት ያደረገ ማበረታቻ  እንደሚኖር አስታውቋል፡፡

ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው ለአፍሪካ  ዋንጫ እና  ለቻን የማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለመጀመር ግንቦት 24  ተጫዋቾች በሆቴል እንዲሰባሰቡ ከሳምንት በፊት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ለመጀመሪያ ዙር ምርጫ  44 ተጫዋቾች ጥሪ እንደሚቀርብላቸው ሲገለጽ ስም ዝርዝራቸው ልምምድ ከመጀመሩ ከአንድ ሳምንት በፊት ይፋ እንደሚደረግ፤  ከጥቂት ቀናት ልምምድ በኋላም ከውጭ ሀገር ክለቦች የሚጠሩትን 4 ወይም 5 ተጫዋቾች ጨምሮ  25 ተጫዋቾች  በሁለተኛ ዙር ምርጫ ተለይተው ለወዳጅነት እና ከሌሴቶ ጋር ለሚካሄደው ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ማጣሪያ ጨዋታ ልምምዳቸውን እንደሚቀጥሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችና በሌሎች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች የተገኘውን ልምድና ያጋጠሙ የአሠራር ችግሮችን  በማጤን ለብሔራዊ ቡድኑ ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት ከፍተኛ እገዛ ለማድረግ በፌደሬሽኑ በኩል እቅድ መኖሩን ቡድን መሪው አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የትጥቅ ፣ የሆቴል፣ የልምምድ ሜዳ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የአውሮኘላን ትኬትና የጉዞ ሰነዶችን አስቀድሞ የማዘጋጀትና እንዲሁም የወዳጅነት ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት እና አጠቃላይ የጊዜ ሰሌዳ የመቅረፅና የማስፈፀም ሥራዎች በተጠና እና በተቀናጀ የአሠራር አግባብ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡ ከውድድር፣ ከዳኝነት፣ ከህክምና ፣ከሥልጠና ቡድን አባላት ጋር የሚኖረውን የሥራ ግንኙነትና ከፌዴሬሽኑ የሚጠበቀውን ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ በተመለከተም ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በአገናዘበ መልኩ የዝግጅት መርሀ ግብሩ እንደሚተገበር ታውቋል፡፡  የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ በተሰጣቸው የሥራ ኃላፊነት መሠረት ለብሔራዊ ቡድን በረዳት አሠልጣኝነት እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት የመረጧቸው ፋሲል ተካልኝ እና ዓሊ ረዲን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሰኔ ወር የሚያካሂዳቸው ጨዋታዎች የሚያስተናግዱባቸውን ስታዲየሞች በተመለከተም ከአየር ሁኔታ ትንበያና የተጋጣሚዎችን አጠቃላይ ሁኔታ መሠረት አድርጎ ሰሞኑን ውሳኔ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል፡፡

ሌሶቶ እና   ሲሸልስ በኮሳፋ ካፕ ተሟሙቀዋል

ለ31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረግ የማጣርያ ውድድር ላይ በምድብ 10 የኢትዮጵያ ተጋጣሚዎች የሆኑት ሌሶቶ እና ሲሸልስ በ15ኛው የኮሳፋ ካፕ ላይ በመሳተፍ ዝግጅታቸውን በተጠናከረ ሁኔታ ጀምረዋል። በወርሃዊው የፊፋ የእግር ኳስ ደረጃቸው 127ኛ እና 187ኛ ላይ እንደቅደምተከተላቸው የሚገኙት ሌሶቶ እና ሲሸልስ ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ በታች ቢሆኑም በማጣርያው አስፈላጊውን እድገት እና መነቃቃት ለመፍጠር ትኩረት አድርገዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ አገራት ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች በቀጣይ በአፍሪካ ዋንጫ እና በቻን የማጣርያ ጨዋታዎች ለሚያደርጉት ዝግጅት የውድድር መድረኩን እንደመሟሟቂያ እንደተጠቀሙበት ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ የሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን በኮሳፋ ካፕ በምድብ 2 ከማዳጋስካር፤ ከስዋዚላንድ እና ከታንዛኒያ ጋር ተደልድሎ ተጫውቷል፡፡ ኮሳፋ ካፕ ከመጀመሩ በፊት የሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የአቋም መፈተሻ ግጥሚያውን በሩስተንበርግ አድርጎ 0ለ0 አቻ ተለያይቶ ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካው ሚዲያዎች ግን ከሌሶቶ ጋር የተደረገው የወዳጅነት ጨዋታ በፊፋ እውቅና የማይኖረው እና ወርሃዊው የእግር ኳስ ደረጃ ምንም ነጥብ የማያሰጥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ በምድብ የመጀመርያው ጨዋታቸው ከማዳጋስካር ተገናኝቶ  2ለ1 የተሸነፈ ሲሆን በሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸው ረቡእ እለት ከስዋዚላንድ ተጋጥመው በድጋሚ 2ለ0 ተሸንፏል፡፡ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታውትናንት በውድድሩ ላይ ተጋባዥ ከነበረችው የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ታንዛኒያ ጋር ያደረገው ነው፡፡ ይሄው ግጥሚያ በተለይ የሌሶቶ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር ለሚያደረገው የምድብ የመጀመርያ ጨዋታ ከፍተኛ ልምድ እንደሚገኝበት ለመረዳት ይቻላል። በኮሳፋ ካፕ የተሳተፈው የሌሶቶ ቡድን በወጣቶች እንደተገነባ ለሱፕርስፖርት የገለፁት አሰልጣኙ ሴፋኒ ማቴቴ፤ ቡድናቸው በአፍሪካ ሀ 20 ሻምፒዮንሺፕ በተሳተፉ 6 ወጣት ተጨዋቾች የተገነባ እንደሆነና በኮሳፋ ጥሩ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚያጠናክራቸው ተናግረዋል፡፡ የሌሶቶ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሃላፊዎች ብሄራዊ ቡድናቸው በኮሳፋ ሲሳተፍ እስከፍፃሜ ለመድረስ አቅዶ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡

በሌላ በኩል በምድብ 1 ከደቡብ አፍሪካ፤ ዚምባቡዌ እና ናሚቢያ ጋር የተደለደለው የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን፤ ጥሩ አጀማመር አሳይቶ ነበር፡፡ በምድቡ የመጀመርያ ጨዋታ ከናሚቢያ ጋር 0ለ0 አቻ ተለያየና በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ባለፈው ማክሰኞ ከዚምባቡዌ ጋር ተጋጥሞ ግን 1ለ0 በመሸነፉ ግን ከውድድሩ ውጭ ሆኗል፡፡ በምድባቸው የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከምትመጣጠናቸው ሞውሪሽዬስ ጋር ያደረጉት ለክብር ብቻ ነው፡፡ ዋና አሰልጣኙ ኡልሪች ማቲዮት ቡድናቸው በኮሳፋ ካፕ ሲሳተፍ በምድቡ በከፍተኛ የእግር ኳስ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖችን ቢገጥምም ዋና ዓላማቸው በየትኛው ቡድን ላለመሸነፍ ነው ብለዋል፡፡ የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ላላፉት 2 ሳምንታት ተቀምጦ ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ማቲዩት በተጨማሪ አስተያየታቸው በቡድናቸው የኮሳፋ ካፕ ተሳትፎ አንዳንድ ተጨዋቾች በደቡብ አፍሪካ ክለቦች የሚገቡበትን እድል ከመፍጠሩም በላይ በቀጣይ በሚሳተፉባቸው አህጉራዊ የማጣርያ ውድድሮች የተሰጠውን ዝቅ ያለ ግምት ለማስተካከል ምቹ መድረክ ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡ ሲሸልስ ከኮሳፋ ካፕ የምድብ ጨዋታዎች መሰናበቷ ብዙም የማያስቆጭ እንደነበር የገለፁት ዋና አሰልጣኙ ኡልሪች ማቲዮት፤ ባለፉት አመታት በሻምፒዮናው ሲሳተፉ በሁለት ጨዋታዎች እስከ ስምንት ጎሎች እንደተቆጠረባቸው አስታውሰው ዘንድሮ ግን አንድ ጎል ብቻ እንደተመዘገበበባቸው እና በመከላከል ረገድ ጥሩ ለውጥ ማየታቸው ተስፋ እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል፡፡ የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን በነሐሴ ወር በህንድ ውቅያኖስ ዙርያ በሚገኙ ደሴቶች እና አገራት መካከል በሚደረግ ሻምፒዮናም ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

አልጄርያ እስከ ኢትዮጵያ ግጥሚያ የወዳጅነት ጨዋታ  የላትም

የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ፈረንሳዊው ክርስትያን ጉርኩፍ በምድባቸው ጠንካራ ተፎካካሪያቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ ናቸው፡፡ ምድብ 10 ለአልጄርያ ቀላል ነው መባሉን በፍፁም አልቀበልም የሚሉት ጉርኩፍ፤ ለኢትዮጵያ ቡድን የተለየ ትኩረት ቢኖረንም ሌሶቶ እና ሲሸልስንም በቅርበት እንከታተላለን ይላሉ፡፡ ይህን አቋማቸውን በተግባር ለማሳየትም ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው የኮሳፋ ካፕን እየተመለከቱ ናቸው፡፡ በአልጄርያ ሊግ የሚገኙ ምርጥ ተጨዋቾችን በቡድናቸው ስብስብ ለማካተት ከፍተኛ ክትትል እያደረጉ ያሉት አሰልጣኙ ፕሮፌሽናሎቻቸውንም በሁሉም የምድብ ማጣርያዎች በተገቢው ጊዜ አሰባስበው ለመጠቀም እየሰሩ ናቸው፡፡

ለክርስትያን ጉርክፍ ዝግጅት ብቸኛዎቹ እንቅፋቶች በአውሮፓ ክለቦች የሚጫወቱ ተጨዋቾችን ለመሰብሰብ የሚፈጠሩ ውስብስብ ሁኔታዎች እና በተለይ በፊፋ የወዳጅነት ጨዋታዎች መርሃ ግብር መሰረት በመጀመርያዎቹ የምድብ ማጣርያ ሶስት ጨዋታዎች ለሚቀጥሉት ሶስት እና አራት ወራት ተጋጣሚ እንደሌላቸው መገንዘባቸው ነው ተብሏል፡፡ አንዳንድ የአልጄርያ ሚዲያዎች እንደገለፁት አረንጓዴዎቹ 2016 እኤአ እስኪገባ የወዳጅነት ጨዋታ የማያገኙ ሲሆን ምናልባት ግን በአዲሱ የፈረንጆች አመት ዋዜማ ከአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮና ኮትዲቯር ጋር የመያገናኛቸው የፊፋ የወዳጅነት ጨዋታ መርሃ ግብር የመጠቀም እድል እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ኬንያ የቻን ማጣርያን በሜዳዋ ለመጨረስ ዝግጅቷ ቀጥሏል

በሩዋንዳ አዘጋጅነት በ2016 እኤአ ላይ ለሚደረገው 4ኛው የቻን ውድድር የሚደረገውን የመጀመርያ ጨዋታን ኬንያ በሜዳዋ በማስተናገዷ ደስተኛ እንደሆነች ዘገባዎች እያመለከቱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ጠንካራ ተፎካካሪነት በሜዳቸው በሚያስመዘግቡት ውጤት በመጨረስ ለመልሱ ለመዘጋጀት እቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዋና አሰልጣኙ ቦቢ ዊልያምሰን ለዝግጅታቸው ምንም አይነት እንቅፋት መኖር እንደሌለበት እያሳሰቡ ናቸው፡፡ የኬንያ ፕሪሚዬር ሊግ አስተዳዳሪዎች ለብሄራዊ ቡድን በሚለቀቁ ተጨዋቾች ዙርያ ሰሞኑን ያወጡት አዲስ ደንብ ይህን ማሳሰቢያቸውን ያከበረ አይደለም በሚል ተተችቷል፡፡ የፕሪሚዬር ሊጉ ክለቦች ተጨዋቾቻቸውን ለመልቀቅ ቅድመ መስፈርት ማቅረባቸው ከፌደሬሽኑ እና ከሃራምቤ ኮከቦች አሰልጣኝ ጋር ማጋጨት ጀምሯል። የአገሪቱ ክለቦች ለወዳጅነት ጨዋታ  ተጨዋቾቻቸውን የሚለቁት ግጥሚያው 2 ቀን ሲቀረው እንዲሆንና ለአህጉራዊ ውድድር ደግሞ ግጥሚያው 4 እና 5 ቀናት ሲቀረው ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

የኬንያ ብሄራዊ ቡድን ስታርታይምስ በተባለ የቻይና ኩባንያ በ270 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ስፖንሰር ተደርጓል፡፡

Page 5 of 19