Administrator

Administrator

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር እሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
 
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል ብለዋል።
 
አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ጥረት የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።   
 
ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁሉ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።

እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ገልጸዋል።

" እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ በስፍራው እሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ምንም ሊጠፋ አልቻለም። በስፍራው ላሉ የአደጋ ሰራተኞች ተጨማሪ ቦቴና እገዛ ያስፈልጋል ፤ በውሃ ብቻም የሚሆን አይደለም " ብለዋል።

" በአካባቢው ያሉ እሳቱ ያልደረሰባቸው ሰዎች ንብረታቸውን እያሸሹ ይገኛሉ " ሲሉም አክለዋል።



ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን መገናኛ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት የተገነባው አዲስ ዘመናዊ ስቱዲዮና 50 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ስክሪን ተመርቋል፡፡  

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው "ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር"፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ ባለፈው ቅዳሜ ጠዋት  በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።

አዲሱ ስቱዲዮ አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሟላቱ የተነገረ ሲሆን፤ስቱዲዮው ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለትና የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎችና የግንኙነት ካሜራ የተገጠመለት የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል እንዳለው ታውቋል፡፡

የስቱዲዮ ግንባታው ከ3 ዓመታት በላይ መፍጀቱ  በምረቃው ሥነስርዓት ላይ ተገልጿል።

በምረቃው መርሐግብር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ  የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡


በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መሥራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ፤ ድርጅቱ በሚያሰራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

የቴሌቪዥን ተቋሙ በቅርቡ ከሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ኅብረት በተደረገለት ድጋፍ የቀጥታ ሥርጭት የጀመረ ሲሆን፤ በሣተላይት በኢትዮ ሳት እና በዲኤስ ቲቪ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ ሥርጭቱን ይበልጥ በማሳደግ ላይ ይገኛል ተብሏል።


አንቴክስ ጨርቃጨርቅ ኃ.የተ.የግ.ማ. የ20 ሚ. ብር ውድድር አዘጋጀ

•  በኢኮኖሚና በሰላም ዘርፍ ያሸነፉ 2 ተወዳዳሪዎች በነፍስ ወከፍ 10 ሚ. ብር ይሸለማሉ


•  የሽልማት ሥነስርዓቱ ታህሳስ 17 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ይካሄዳል




ላለፉት 7 ዓመታት በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሰማራው የቻይናው አንቴክስ ጨርቃጨርቅ ኃ.የተ.የግ.ማ፤ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማትና ሰላም የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አወዳድሮ 20 ሚሊዮን ብር ሊሸልም መሆኑ ተገለጸ፡፡


የአንቴክስ ኢትዮጵያ አመራሮችና ዝግጅቱን የሚያስተባብረው በሻቱ ቶለማርያም መልቲሚዲያ፣ ዛሬ ተሲያት በኋላ፣ በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የድርጅቱ አዳራሽ  በሽልማቱ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡


በመግለጫው ላይ እንደተብራራው፣ ድርጅቱ በኢኮኖሚ ልማትና በሰላም ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አወዳድሮ  ያሸነፉ ሁለት ግለሰቦች ወይም ድርጅቶችን ለእያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ብር ይሸልማል፡፡


ለዚህ ሁለት የሽልማት ዘርፎች የሚመረጡ እጩዎች ከመላው ኢትዮጵያ በህዝብ ጥቆማ ታሪካቸው ወይም ሥራቸው እንደሚሰበሰብ የተጠቆመ ሲሆን፤ አሸናፊዎች ለዚህ ውድድር በተመረጡ ዳኞችና በህዝብ ድምጽ ተለይተው የሽልማት ሥነስርዓቱ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ ማዕከል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡



አንቴክስ ኢትዮጵያ ላለፉት 7 ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ በነበረው ቆይታ፣ ያሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጣ ውረዶች በመገንዘብ፣ መፍትሄ የማፈላለግ ሂደት ውስጥ የራሱን ሚና ለመወጣት ባቋቋመው ፉድ ኤንድ ፕላስ የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት በርካታ እርዳታዎች ሲያደርግ መቆየቱ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል፡፡


በአሁኑ ወቅት ደግሞ የዚሁ አካል የሆነ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማትና ሰላም የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና የሚሰጥ ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሥራዎች (Best Influencer Work Prize)ሽልማትን ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ከዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ የእጩ ተወዳዳሪዎችን ታሪኮችና ሥራዎች መቀበል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡
 

የBIW Prize ዓላማ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት በተለየ መንገድ ጥረት ለሚያደርጉና በህዝቡ መካከል ሰላማዊ አብሮነትን ለማጎልበት ለሚተጉ፣ በሥራቸውም ለሌሎች አርአያ መሆን የቻሉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ማበረታታትና ሥራቸውንም ማገዝ ነው፤ተብሏል፡፡


አንቴክስ ኢትዮጵያ በአዳማ ኢንዱስትርያል ፓርክ ከ10 በላይ ሼዶች ያሉት ሲሆን፤ ለ4500 ሰራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ ድርጅት መሆኑ ተነግሯል፡፡ አንቴክስ ግሩፕ፤ እ.ኤ.አ በ2003 ዓ.ም በቻይና የተመሰረተ ሲሆን፣ ከቻይና በተጨማሪ በእስያና በአፍሪካ በጨርቃጨርቅና ሌሎች ዘርፎች እየሰራ የሚገኝ  ድርጅት ነው፡፡


በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች፣ ራሳቸው ወይም ጠቋሚዎች፣ በቴሌግራም ቻናል:-@ BIWPrize ወይም በኢሜይል፡ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በመጠቀም ለሰላምና ኢኮኖሚ ያበረከቷቸውን ሥራዎች ከዛሬ ጥቅምት 11 ቀን ጀምሮ ለቀጣይ 15 ቀናት መላክ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

 
             ለዚህ ሽልማት እጩ ለመሆን ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡-

ለኢኮኖሚ ሽልማት ዘርፍ
1.  ከትንሽ ተነስቶ በራሱ ጥረት የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ
2.  ለብዙዎች የሥራ በር የከፈተ
3.  በሥራ ፈጠራ የተካነ
4.  ህዝብና አገርን ለመጥቀም የሚሰራ
5.  ካፈራው ሃብት ማህበራዊ ሃላፊነቱን የሚወጣ
6.  በሥራ ትጋቱ ለብዙዎች ምሳሌ የሚሆን
7.  እውቀቱንና ልምዱን ለትውልድ ለማካፈል የማይሰስት
8.  የአረንጓዴ ልማት አስፈላጊነትን በደንብ የተረዳ
9.  የዲጂታል ኢኮኖሚን ጥቅም የሚያውቅ


ለሰላም ሽልማት ዘርፍ
1.  በአመለካከቱ፣ በንግግሩ፣ በአኗኗሩ ሰላምን ከፍ የሚያደርግ
2.  ለሰብአዊ መብት መከበር ግድ የሚለው
3.  ዋጋ ከፍሎ በህብረተሰብ መካከል እርቅን ለማውረድ የሰራ
4.  ይቅርታን እየኖረ፣ ይቅርታን የሰበከ
5.  የሃይል አማራጭን የማያደፋፍር
6.  ለሃገርና ለወገን ሰላም እንደ ግል ህይወቱ ትኩረት የሚሰጥ
7.  መልካም አስተዳደርን የሚያበረታታና ለድሆች መብት የሚሟገት
8.  ቀና አመለካከትን የሰበከ
9.  የጾታ እኩልነትን ያበሰረና ጥቃትን የሚጸየፍ

“አፍሪካ ቱ ሲልካን ቫሊ” ከአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሰው ሰራሽ አስተውሎት የፈጠራ ስራ ውድድር ተጠናቀቋል። በዚሁ ውድድር ከ4 ሺሕ 900 በላይ ተሳታፊዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የዚህ ውድድር የመዝጊያ ስነ ስርዓት ባሳለፍነው ረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል።

በዚህ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የ”አፍሪካ ቱ ሲልከን ቫሊ” መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤምሬ ቫሮልን ጨምሮ፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች በመገኘት፣ በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተሳታፊዎች ሽልማት አበርክተዋል።

በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት እና ሳይንስ ሙዚየም በተደረገው ውድድር የተሳተፉ እነዚሁ 8 ቡድኖች ከ48 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

“ከ4 ሺሕ 900 በላይ ተወዳዳሪዎች መካከል፣ የተወሰኑት ተመርጠው ሕይወት እና አኗኗርን የሚቀይሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎቻቸውን ለዳኞች ሲያሳዩ ቆይተዋል” ነው የተባለው። በተለያዩ ዘርፎች ለተመረጡት ስምንት ቡድኖች የዋንጫና የ2 ሺሕ 500 ዶላር ሽልማት፤ እንዲሁም ምርጥ አሸናፊ ሆነው አንደኛ ለወጡት 10 ሺሕ ዶላር፣ ሁለተኛ ለወጡት 6 ሺሕ፣ እንዲሁም 3ኛ ለወጡት 4 ሺሕ ዶላር ተበርክቷል።

የአስር ሺሕ ዶላር አሸናፊዎቹ ከቱኒዚያ የመጡ ተሳታፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ፣ ከዚያም በተጨማሪ የ2 ሺሕ 500 ዶላር ሽልማት ሊያሸንፉ ችለዋል።

በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ከተካሄደው መርሃ ግብር በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በዳኞች ከተመረጡት ተሳታፊዎች መካከል፣ ስምንቱ “ምርጥ” የተባሉ ቡድኖች የፈጠራ ስራቸውን በዓውደ ርዕይ መልክ ማሳየታቸው ነው የታወቀው።

“አፍሪካ ቱ ሲልከን ቫሊ” እንደፈረንጆቹ ቀመር፣ ከ2019 ጀምሮ በአፍሪካ ተሰጥኦ ያላቸው እና “አሉ” የሚባሉ ወጣቶችን ከዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት እንደድልድይ ሆኖ ሲሰራ መቆየቱ በውድድሩ የመዝጊያ መርሐግብር ላይ ተገልጿል። ይኸው ተቋም ያፈራቸው ከ20 አገራት የተውጣጡ ከ8 መቶ በላይ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች በአሁኑ ጊዜ በጎግል፣ አማዞን፣ ብሉምበርግ እና በሌሎች ትልልቅ ድርጅቶች ውስጥ ተጽዕኖ እየፈጠሩ “ነው” ተብሏል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ “በዓመት ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ በሕገ ወጥ መንገድ ‘ይወጣል’ ተብሎ ይገመታል” ሲሉ ተናገሩ። በዚሁ “ሕገ ወጥ ንግድ” በጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ውስጥ የተሾሙ አመራሮች ተሳታፊ እንደሆኑም አቶ ጌታቸው አክለው ገልጸዋል።

ትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በበይነ መረብ በተካሄደውና በርካታ በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ተሳታፊ በሆኑበት፣ “ስለትግራይ ዝም አልልም” በተሰኘው የውይይት መርሃ ግብር ተጋባዥ የነበሩት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት፣ ከእነዚሁ ዜጎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ አምሽተዋል። በበርካታ ጊዜያት ሲነሳ ስለቆየው “ሕገ ወጥ” የወርቅ ንግድ ጥያቄ ቀርቦላቸው አቶ ጌታቸው ምላሽ ሲሰጡ፣ “ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽረ እንዳስላሰ ቅርንጫፍ ከተቀበለው የወርቅ መጠን የበለጠ ሶስት እና አራት ዕጥፍ የሚሆነው በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው። በዓመት ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ በሕገ ወጥ መንገድ ከትግራይ ‘ይወጣል’ ተብሎ ይገመታል። እዚያው ሽረ ሄጄ ያነጋገርኳቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ‘አካባቢያችን ዋልድባ ሆኗል። ሁሉም ሽፍታ እየሆነ ነው’ አሉኝ። ከዚህ ሽፍትነት ነጻ ለመውጣት ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። በተለይ በፖለቲካ መዋቅር ውስጥ በርካቶች ይገኛሉ።” ብለዋል።

“ይህ ሕገ ወጥ ንግድ ከሕዝብ ጥርጣሬ ባለፈ፣ ዓለም አቀፍ ወንጀል ሆኗል። ከቻይና እና ከስዊድን፣ እንዲሁም ከሌሎች አገሮች በመምጣት በዓዲያቦ እና ሌሎች አካባቢዎች ተሰማርተው ሕገ ወጥ የወርቅ ማውጣት ስራ እየሰሩ ነው” ብለዋል፣ አቶ ጌታቸው በማብራሪያቸው።

አያይዘውም፣ “ዓዲያቦ እና ኣስገደ ብትሄዱ፣ በርካታ የወርቅ ዝርፊያ ተግባራት ሲካሄዱ ትመለከታላችሁ። ማዕድን ለማውጣት በሚያገለግል ኬሚካል ምክንያት ሕዝቡ እየተጎዳ ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፣ “ከላይ እስከ ታች በኔትዎርክ ተሳስረዋል” ያሏቸው በርካታ ሰዎች በጠቀሷቸው ተግባራት እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል። ይህንን ዕንቅስቃሴ ለመቆጣጠር “ግዙፍ” ግብረሃይል ተቋቁሞ የማጣራት እና የመለየት ስራ መጀመሩን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

“የሕልውናችን አንደኛው አደጋ ነው። ሰራዊታችንን በግብረሃይሉ ውስጥ አሳትፈን የማጣራት እና የመለየት ስራ እየሰራን ነው። ሲቪል አመራሮችም ተካትተዋል።” ሲሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በተለያዩ ወታደራዊ አዛዦች እና ሲቪል አመራሮች ላይ የሚቀርበውን ነቀፋ “ስም ከማጥፋት የዘለለ አይደለም” በማለት ገልጸውታል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሽረ እንዳስላሰ ቅርንጫፍ ባለፉት ሶስት ወራት ከ13 ኩንታል በላይ ወርቅ ከሕጋዊ የወርቅ አዘዋዋሪዎች መግዛቱን ያስታወቀው ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲሆን፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል “ይፈጸማል” ስላሉት ሕገ ወጥ የወርቅ ንግድ ጥሪዎችን እና መረጃዎችን በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ መቆየታቸው አይዘነጋም።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡

አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ  ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡


መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።


እኔ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በነበርንበት ሰፈር በየግቢው ሀያ ሠላሳ ቤተሰብ ሆነን ነበር የምንኖረው። የቤተሰብ ብዛት ሲታሰብ፤ በአንድ ግቢ ውስጥ መቶ ሁለት መቶ ሰው ይሆናል። አዲስ መኖሪያ ቤት፣ ሁሉም ቤተሰብ የየራሱ መታጠቢያ መጸዳጃ ቤት፣ የየራሱ ማድ-ቤት ሲያገኝ ደስ ይላል።
ዛሬ ደግሞ አይቼ የማላውቀውን አከባበር አይቻለሁ። በ65 ዓመት ዕድሜዬ፣ ከንቲባ በዐይኔ አይቼ አላውቅም። እዚህ መጥተው ሲያበረታቱን፣ ለጥያቄዎችም ጥሩ ምላሽ ሲሰጡን… በጣም ደስ ብሎኛ። በጣም ረክቻለሁ።


=======================


ክብርት ከንቲባ ቤት-ለእንቦሳ ሊሉን መጥተዋል። ባዶ እጃቸውን አልመጡም። ቡና አፍልተን የምንጠጣው ይዘውልን መጥተዋል። ለምግባችንም ሰርተን የምንመገበውን ስጦታ አበርክተውልናል።



====================


ከንቲባዋም እዚህ መጥተው ጠይቀውናል። እንዴት እንዴት እየሆናችሁ ነው ብለው ለመጠየቅና በአካል ለማየት ብለው ነው የመጡት። የሥራ ጊዜያቸውን አብቃቅተው እኛን ለመጠየቅ ስለመጡ ደስ ብሎናል። በጣም እናመሰግናለን።



========================


በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።


=========================


በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።


===========================



ጥራቱን የጠበቀ ቤት ውስጥ ነው የገባነው። መጸዳጃ ቤትም፣ ማድቤትም… ሁሉም ነገር የተሟላ ቤት ነው። ከተጎሳቆለ ጭቃ ቤት ተገላግለናል። ዕድለኛ ነን። ቅር የሚል ነገር የለም። ከዛ ክፉ ችግር ተላቅቄ እዚህ መድረሴ ትልቅ ነገር ነው። ያላሰብነውን ነው ያገኘነው።
እንደዚህ ዐይነት ዕድል ማን ያገኛል? ቦታው ሩቅ አይደለም። መሀል ከተማ ነው። መንገዱ ጭቃ የለው! ምን የለው! ምስጋና ይድረው።  


=======================


አዲሱ ሰፈራችን ጥሩ ነው። የነበርንበት ሰፈር፣ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ችግር ነበር። ወረፋ ነው። ፍሳሽም አለ። የወዲህኛው ቤት ደህና ቢሆን፣ ከወዲያኛው ወይም ከጓሮ በኩል ፍሳሽ ይመጣል። በጣም ይረብሻል። ብቻ… ብዙ ችግር ነበር። ወደ አዲሱ ሰፈራችን ስንገባ አስተዳደሩ ጥሩ ድጋፍና አቀባበል አድርጎልናል። የዕቃ ለማጓጓዝ የከተማው አስተዳደር የጭነት መኪኖችን በነፃ ሰጥቶናል። የጫኝ የአውራጅ ወጪም አልነበረብንም። በከተማው አስተዳደር ድጋፍ በነፃ ነው።
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ነገር፣ የመኖሪያ ቤት አመዳደብ ነው። አካል ጉዳተኞችና በዕድሜ የገፉ አዛውንት፣ በመኖሪያ ሕንጻው እንዳይቸገሩ የታችኛው ፎቅ ላይ ተስማሚ ቤት አግኝተዋል። ጥሩ አስበውበታል። የሚመሰገን ተግባር ነው።






የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።


እኔ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በነበርንበት ሰፈር በየግቢው ሀያ ሠላሳ ቤተሰብ ሆነን ነበር የምንኖረው። የቤተሰብ ብዛት ሲታሰብ፤ በአንድ ግቢ ውስጥ መቶ ሁለት መቶ ሰው ይሆናል። አዲስ መኖሪያ ቤት፣ ሁሉም ቤተሰብ የየራሱ መታጠቢያ መጸዳጃ ቤት፣ የየራሱ ማድ-ቤት ሲያገኝ ደስ ይላል።
ዛሬ ደግሞ አይቼ የማላውቀውን አከባበር አይቻለሁ። በ65 ዓመት ዕድሜዬ፣ ከንቲባ በዐይኔ አይቼ አላውቅም። እዚህ መጥተው ሲያበረታቱን፣ ለጥያቄዎችም ጥሩ ምላሽ ሲሰጡን… በጣም ደስ ብሎኛ። በጣም ረክቻለሁ።


=======================


ክብርት ከንቲባ ቤት-ለእንቦሳ ሊሉን መጥተዋል። ባዶ እጃቸውን አልመጡም። ቡና አፍልተን የምንጠጣው ይዘውልን መጥተዋል። ለምግባችንም ሰርተን የምንመገበውን ስጦታ አበርክተውልናል።



====================


ከንቲባዋም እዚህ መጥተው ጠይቀውናል። እንዴት እንዴት እየሆናችሁ ነው ብለው ለመጠየቅና በአካል ለማየት ብለው ነው የመጡት። የሥራ ጊዜያቸውን አብቃቅተው እኛን ለመጠየቅ ስለመጡ ደስ ብሎናል። በጣም እናመሰግናለን።



========================


በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።


=========================


በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።


===========================



ጥራቱን የጠበቀ ቤት ውስጥ ነው የገባነው። መጸዳጃ ቤትም፣ ማድቤትም… ሁሉም ነገር የተሟላ ቤት ነው። ከተጎሳቆለ ጭቃ ቤት ተገላግለናል። ዕድለኛ ነን። ቅር የሚል ነገር የለም። ከዛ ክፉ ችግር ተላቅቄ እዚህ መድረሴ ትልቅ ነገር ነው። ያላሰብነውን ነው ያገኘነው።
እንደዚህ ዐይነት ዕድል ማን ያገኛል? ቦታው ሩቅ አይደለም። መሀል ከተማ ነው። መንገዱ ጭቃ የለው! ምን የለው! ምስጋና ይድረው።  


=======================


አዲሱ ሰፈራችን ጥሩ ነው። የነበርንበት ሰፈር፣ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ችግር ነበር። ወረፋ ነው። ፍሳሽም አለ። የወዲህኛው ቤት ደህና ቢሆን፣ ከወዲያኛው ወይም ከጓሮ በኩል ፍሳሽ ይመጣል። በጣም ይረብሻል። ብቻ… ብዙ ችግር ነበር። ወደ አዲሱ ሰፈራችን ስንገባ አስተዳደሩ ጥሩ ድጋፍና አቀባበል አድርጎልናል። የዕቃ ለማጓጓዝ የከተማው አስተዳደር የጭነት መኪኖችን በነፃ ሰጥቶናል። የጫኝ የአውራጅ ወጪም አልነበረብንም። በከተማው አስተዳደር ድጋፍ በነፃ ነው።
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ነገር፣ የመኖሪያ ቤት አመዳደብ ነው። አካል ጉዳተኞችና በዕድሜ የገፉ አዛውንት፣ በመኖሪያ ሕንጻው እንዳይቸገሩ የታችኛው ፎቅ ላይ ተስማሚ ቤት አግኝተዋል። ጥሩ አስበውበታል። የሚመሰገን ተግባር ነው።






“ከንቲባዋ ስጦታ ይዘው፣ በአካል መጥተው ጠይቀውናል፤ “ቤት ለእንቦሳ” ብለውናል!”… ወደ አዲስ ቤታቸው የገቡ የልማት ተነሺዎች።
“የካዛንችስ ነዋሪዎች ለከተማችን ልማት ባለውለታዎች ናቸው፤ በትዕግሥትና በአስተዋይነት ድጋፋቸውን ሰጥተውናል”… ከንቲባ አዳነች አበቤ።
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች፣ ስለ ቀድሞው አኗኗራቸው፣ ስለ አዲሱ ቤታቸውና ስለ ከከተማ አስተዳደሩ ምን ይላሉ?
የአዲስ አበባ ከንቲባ፣ “እንዴት እየሆናችሁ ነው?” ብለው ነዋሪዎችን ለመጠየቅ በየቦታው ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

አዲሱ ቤታቸውን መልክ እያስያዙ ከአዲሱ ሰፈራቸው ጋር መላመድ የጀመሩት የልማት ተነሺዎች፣ የከተማዋ ከንቲባ እነሱን ለመጠየቅና ለመጎብኘት ይመጣሉ የሚል ግምት አልነበራቸውም። ለዚያውም ገና አንድ ቀን ሁለት ቀን ሳይሞላቸው ነው ለጥየቃ የመጡት።
ደግሞም፣ ከነባር የመኖሪያ ሰፈር ወደ መኖሪያ ቦታ የሚሄዱ የልማት ተነሺዎች፣ ወዲያውኑ ጠያቂና ጎብኚ ቢያገኙ ነው የሚጠቅማቸው። ከትንሽ ጊዜ በኋላማ፣ አዲሱን ሰፈራቸውን ይላመዱታል።
መንፈሳቸውን የሚያረጋጋና የሚያበረታታ ሰው የሚያስፈልጋቸው በመጀመሪያዎቹ ቀናት ነው። ከንቲባዋ ትክክለኛውን ጊዜ አውቀው በአካል እነሱን ለመጠየቅ መምጣታቸውን በማየት ብቻ የልማት ተነሺዎቹ ልብ ተነክቷል።
“በዚያ ላይ፣ ባዶ እጃቸውን አይደሉም የመጡት” በማለት ነዋሪዎቹ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ታዲያ፣ ምስጋናው ከአንድ አቅጣጫ ብቻ የተሰነዘረ አይደለም።
ከንቲባ አዳነች አበቤም የልማት ተነሺዎቹን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋል።

ድሮና ዘንድሮ፤ ያረጁ ቤቶችን አዲስ በተገነቡ ቤቶች መተካት
ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት የተነሱ ነዋሪዎች፣ በከተማዋ አስተዳደር ወደ ተሰጣቸው አዲስ መኖሪያ ቤት የተዛወሩት በዚህ ሳምንት ነው። በአብዛኛው፣ ለ50 ዓመታት ምንም ጥገናም ሆነ እድሳት ያልተደረገላቸው የቀበሌ የኪራይ ቤቶች ውስጥ ነበር የሚኖሩት።
ቤቶቹ አርጅተው የተጎሳቆሉ የጭቃ ቤቶች ናቸው። ግድግዳቸው ተቦርቡሮ በቆርቆሮ የተለጣጠፉ ናቸው - አብዛኞቹ። ጣሪያቸው በዕድሜ ብዛት እየዛገ፣ እየተበሳ ውኃ ያፈስሳል። አብዛኛው ጣሪያ የላስቲ ሸራ ተነጥፎበታል። በነፋስ እየተገነጣጠለ ተነቃቅሎ ለመብረር በትንሽ ሽውታ እየተወራጨ እንቅልፍ ይነሳል፤ ያስጨንቃል። ጣሪያ ላይ ብዙ ትልልቅ ድንጋዮች የሚታዩትም የዛገውን ቆርቆሮ ከነፋስ ለማስጣል ነው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀጥላ ቤቶች በቆርቆሮ እየተጨመሩበት ከሕዝብ ብዛት ጋር የቀድሞ መኖሪያ ሰፈሮች ተጨናንቀዋል። የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ መንገዶቹ ጠባብ ናቸው።
ብዙዎቹም የሰፈር ውስጥ መንገዶች፣ ለመኪና የሚታሰቡ አይደሉም። ከአንድ ከሁለት ሰው በላይ አያሳልፉም። በዚያ ላይ ፍሳሽ አለ። መጸዳጃ ቤትም፣ ብዙ ቤተሰብ በወረፋ የሚጠቀምበት ሲሆን ደግሞ፣ ለኑሮም ለጤናም የዕለት ተዕለት ፈተና ይሆናል።
ቢሆንም ግን፣ ያደጉበት ሰፈር፣ የኖሩበት ቤት ከነችግሩም ቢሆን፣ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው። የሚያናንቁት ነገር አይደለም። የተሻለ ሰፈርና መኖሪያ ቤት ካልተገኘም፣ “ይቅርብኝ” ብለው የሚያጣጥሉት አይሆንም።
ደግነቱ፣ ለልማት ተነሺዎች የተዘጋጁ መኖሪያ ቤቶች፣ ከቀድሞ መኖሪያ ቤቶች የተሻሉ ብቻ አይደሉም።


አዲስ ናቸው። የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ማድቤት፣ መታጠቢያ፣ መጸዳጃ የተሟላላቸው ባለፎቅ መኖሪያ ቤቶች ናቸው።
የመኖሪያ ቤት አመዳደብ የተካሄደውም በዘፈቀደ አይደለም። የቀድሞ ጎረቤታሞችና የሰፈር ሰዎች ማኅበራዊ ግንኙነታቸው እንዳይበጠስና እንዳይበተን ታስቦበታል።
አንድ ሰፈር ላይ የነበሩ የልማት ተነሺዎች፣ ወደ አንድ አካባቢ እንዲዛወሩ ነው የተደረገው። ገሚሶቹ በአቃቂ ገላን ጉራ ወደተገነቡ መኖሪያ ቤቶች፣ ገሚሶቹ ደግሞ በቦሌ አራብሳ ወደተሠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ገብተዋል።
ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ነው ማለት አይደለም።

እንዴት እየሆናችሁ ነው? ብሎ የሚጠይቅና የሚያበረታታ ያስፈልጋል።
ምንም እንኳ፣ አዲሱ መኖሪያቸው በአሠራሩና በጥራቱ ከቀድሞው እጅግ የተሻለ ቢሆንም፣ ከነባር ቦታ በአንዴ መልቀቅ… ለጊዜውም ቢሆን መንፈስን ይረብሻል። ወደ አዲስ ሰፈር መግባትና መላመድ ለጊዜው ስሜትን ይፈታተናል። ሊያስጨንቅም ይችላል።
ለዚህም ነው፣ ከንቲባ አዳነች አበቤ “ይዋል-ይደር” ሳይሉ የልማት ተነሺዎችን በአካል ለማየትና ለመጠየቅ መምጣታቸው፣ ለነዋሪዎቹ ልዩ ትርጉም የነበረው።
ከንቲባ አዳነች አበቤ ወደ አቃቂ ገላን ጉራ ሄደው ነዋሪዎችን ጠይቀዋል። ወደ ቦሌ አራብሳ ሄደውም ጎብኝተዋል። ወደ ነዋሪዎች ቤት ጎራ እያሉ ከነዋሪው ጋር ቁጭ ብለው ተነጋግረዋል።
ቡና፣ የምግብ ዘይት፣ የዳቦ ዱቄት፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ ይዘው ነው የልማት ተነሺዎችን ለመጠየቅ የሄዱት። ብዙ ነዋሪዎች ይህን እናያለን ብለው አልጠበቁም።
በከንቲባዋ ጉብኝት መደነቃቸውን የገለጹ ነዋሪዎች፣ በዚያ ላይ ስጦታ ይዘውልን ነው የመጡት ሲሉ ተናግረዋል።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ከንቲባዋ እነሱን በማሰብ በቦታው ተገኝተው እነሱን ለማየት መምጣቸው ነው ነዋሪዎቹን ያስደሰታቸው።
ሐሳባችንን የሚረዳልን፣ ስሜታችንን የሚያውቅልን አገኘን የሚል መንፈስ ያደረባቸው ነዋሪዎች ከንቲባዋን ማመስገናቸው ለዚህ ነው።
ከንቲባዋም ግን የልማት ተነሺዎችን አመስግነዋል። የካዛንችስ ነዋሪዎች በትዕግሥትና በአስተዋይነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር በትብብር ሠርተዋል ሲሉ ከንቲባዋ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ፤ ለከተማችን ልማት በበጎ መንፈስ ለሰጣችሁን ድጋፍ ከልብ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ ብለዋል - ከንቲባዋ።
የልማት ተነሺዎች፣ ለኑሮ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው ንጹህ መኖሪያ ቤቶችን ማግኘታቸው መልካም ነው። መሆንም አለበት።
ለተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት፣ ለነዋሪዎች የጤና ተቋማትና ፋርማሲ፣ የሸማቾች ሱቆች ተዘጋጅተዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ ለእናቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚከፍቱ ሼዶች ተገንብተዋል። ውሃና መብራት ገብቶላቸዋል።
ችግሮች የሉም ማለት ግን አይደለም። በገላን ጉራ መኖሪያ ሕንጻዎች ላይ፣ መንደርን ከመንደር እንዲሁም ከዋና መስመር ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ወደ አስፋልት ደረጃ አልተሻሻሉም። የትራንስፖርት ችግርም አለ።
ከንቲባ አዳነች አበቤ የገቡት ቃል
አስፋልት በፍጥነት ተሠርቶ የአውቶቡስ አገልግሎት እንደሚጀመር ለነዋሪዎች ገልጸዋል - ከንቲባዋ።
የተማሪዎች የክፍል ጥበት በማጋጠሙም አዲስ ትምህርት ቤት እንገነባለን ብለዋል። በደፈናው እንገነባለን አላሉም። ረዥም ቀጠሮ አልሰጡም።
አዲሱ ትምህርት ቤት 2 ወር ይጠናቀቃል ብለዋል።
ሴቶችን ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንዲያገኙና በባለቤትነት ስሜት ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ፣ እንጀራ ማምረቻ ማእከል ግንባታ አስጀምረናል ሲሉም ለልማት ተነሺዎች ተናግረዋል።
በአዲሱ መኖሪያ ቤት፣ በከንቲባዋ ጉብኝትና በተቻለ ዐቅም ችግሮችን በፍጥነት ለማቃለል ቃል መግባታቸውን ሁሉ በመጥቀስ የልማት ተነሺዎች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በበኩላቸው፣ “በፍትሃዊነት እንሰራለን። ጊዜያዊ ችግሮችን ጨከንብለን በትብብር ሰርተን በፍጥነት እናልፋቸዋለን። ለከተማችን ልማት በሙሉ ልባችሁ እየደገፋችሁ ከጎናችን ሆናችሁ ስላበረታታችሁን አክብሮት እየገለጽኩ ከልብ አመሰግናለሁ” ብለዋል።






Page 1 of 731