Administrator

Administrator

የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአመት 6,344 ጊጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል፡፡
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኦሞ ወንዝ ታችኛው ተፋሰስ ከጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ 129 ኪሎ ሜትር ርቀት ከኮይሻ መንደር በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።
1800 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ የኃይል ማመንጫ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የኃይል ፍሰት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ነው።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ በአመት 6,344 ጊጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።
ከኃይል አቅርቦት ማስፋፊያነቱ ባሻገር የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ንፁህ፣ አስተማማኝ እና የተጠቃሚዎችን አቅምን ከግምት ያስገባ ታዳሽ ኃይል አቅርቦት የሚያቀርብ ኢትዮጵያም በምስራቅ አፍሪካ የኤሌክትሪክ የውጭ ንግድ ማዕከል ለመሆን ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት የሚደግፍ ነው።
ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ባልፈለጉ አካላት የተነጠቀችውን የባህር በር መጠየቅ መብቷ እንጂ ቅንጦት አይደለም ሲሉ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ አስገነዘቡ።
ለጊዜውም ቢሆን ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችበት ሂደት ሕጋዊ አለመሆኑን አንስተው፤ መንግሥት ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት እንዳለባት አምኖ አጀንዳ ማድረጉ ከሕግም ሆነ ከሞራል አንጻር ትክክል መሆኑን ጠቅሰዋል።
በወቅቱ የነበረው የሽግግር መንግስት እንደ ባሕር በር ያሉ ቁልፍ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሕጋዊ መብት እንደሌለው እያወቀ፤ ኢትዮጵያን ባሕር በር አልባ ማድረጉን አውስተዋል።
ለዓለምና አኅጉር አቀፍ ትላልቅ ተቋማት ምሥረታ ፊታውራሪዋ፤ ከጎረቤቶቿ ጋርም በሰላም ማስከበር፣ በወንዝ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በመሠረተ-ልማት የተቆራኘችው ኢትዮጵያ ከሚናዋ አንጻር የባሕር በር ጥያቄዋ ሊደገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኦሞ ወንዝ ታችኛው ተፋሰስ ከጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ 129 ኪሎ ሜትር ርቀት ከኮይሻ መንደር በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።
1800 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ የኃይል ማመንጫ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የኃይል ፍሰት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ነው።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ በአመት 6,344 ጊጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።
ከኃይል አቅርቦት ማስፋፊያነቱ ባሻገር የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ንፁህ፣ አስተማማኝ እና የተጠቃሚዎችን አቅምን ከግምት ያስገባ ታዳሽ ኃይል አቅርቦት የሚያቀርብ ኢትዮጵያም በምስራቅ አፍሪካ የኤሌክትሪክ የውጭ ንግድ ማዕከል ለመሆን ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት የሚደግፍ ነው።
በሀገር ውስጥም የገጠር ኤሌክትሪክ አቅርቦትን በሚደግፍ መንገድ በመኖሪያ ቤቶች እና በአነስተኛ የንግድ ሥራዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ያሳድጋል።
ይኽም ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማትን የሚያነቃቃ፣ የተሻሻለ የአኗኗር ደረጃን የሚፈጥር ብሎም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ዘላቂ እድገትን የሚደግፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።
Monday, 27 October 2025 06:20

ፊኒክስ፡ የማይሞተው ወፍ

ፊኒክስ በጥንታዊ ግሪክ አፈታሪክ የሚገኝ ወፍ ሲሆን፣ በውበቱ እና ከሁሉም በላይ በዘላለማዊ የህይወት ዑደቱ የሚታወቅ ነው። ይህ የሚያብረቀርቅ ወፍ በተወሰነ የጊዜ ርዝማኔ መጨረሻ ላይ ራሱን በእሳት አቃጥሎ አመድ ሆኖ፣ ከዚያም እንደገና በወጣትነት እና በታደሰ ጉልበት ከአመዱ ተነስቶ አዲስ ህይወት እንደሚጀምር ይነገራል። ይህ ልዩ ትረካ የሞትና የትንሣኤ ዑደትን፣ ጥፋትን ተከትሎ ዳግም መወለድን፣ እና የማይጠፋ ተስፋን ያመለክታል። የፊኒክስን ታሪክ በማጥናት፣ ምንም ያህል ከባድ ፈተና ቢያጋጥመንም ሁልጊዜም እንደገና የመጀመር እና እራሳችንን የማደስ እድል እንዳለን የሚገልጽ ጠቃሚ ትምህርት መማር እንችላለን።
በሺህ ዓመታት የክብር ህይወት ፍጻሜ ላይ፣ የፊኒክስ ብርሃን ሲደበዝዝ እና ጥንካሬው ሲጠፋ፣ ወፉ መጨረሻው መምጣቱን ተረዳ። ወዲያውም ጥሩ መዓዛ ባላቸው ቅጠሎች ከፍ ያለ ጎጆ በመስራት ራሱን አዘጋጀ። ከዚያም የመጨረሻውን እና እጅግ ውብ የሆነውን ዜማውን ዘፈነና በፀሐይ የመጀመሪያ ብርሃን ራሱን በእሳት ነበልባል አቃጠለ። ይህ ሞት የሚመስለው ድርጊት ግን የዘላለም ፍጻሜ አልነበረም። ሁሉም ነገር ፍጻሜ ደረሰ ብለው ካሰቡ በኋላ፣ አዲሱ እና ታዳሽ የሆነው ፊኒክስ ከዚያው አመድ ውስጥ እንደገና ተወለደ—በወጣትነት ጉልበትና በብሩህ ውበት። ይህ ክስተት ፊኒክስ እሳት ጥፋት ሳይሆን ዳግም መወለድን እንደሚያመጣ የሚያሳይ ምልክት መሆኑን ያመለክታል።
የፊኒክስ ዋና ትምህርት በህይወት የሚያጋጥሙን ውድቀቶችና መቃጠሎች ማብቂያችን እንደማይሆኑ ነው። ልክ እንደ ፊኒክስ፣ ታላቅ ዓላማ በልባችን እስካለ ድረስ፣ የተሰበርንበት አመድ የመጨረሻ መቃብር ሳይሆን፣ ዳግመኛ የምንነሳበት መሠረት ይሆናል። በታሪክ ውስጥ የነበሩ ብዙ ታላላቅ ሥልጣኔዎች ይህን እውነት አሳይተዋል፤ ለምሳሌ ጃፓን፣ ጀርመን እና ሩዋንዳ ከከባድ ውድቀቶች እና ከጥፋት በኋላ እንደገና ተነስተዋል። ይህ የሚያሳየው፣ ሙሉ በሙሉ ስላልወደቁ ሳይሆን፣ ከውድቀታቸው በኋላ ወድቀው ለመቆየት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እና እንደገና ለመገንባት ስለመረጡ፣ ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላም እንኳ እንደገና ለመጀመር እና ከበፊቱ በበለጠ ጠንካራ ለመሆን እንደሚቻል ነው።
ፊኒክስ ተረት ብቻ ሳይሆን፣ ሁላችንም በውስጣችን ያለን የውስጥ ጥንካሬ ነጸብራቅ ነው። ከባድ ውድቀት በደረሰበት ሰው፣ ከተማ ወይም አገር ውስጥ ሁሉ የፊኒክስ መንፈስ አለ፤ ይህም ዳግም የመጀመርን ተስፋ ይዞ ይኖራል። ሁላችንም ምንም ዓይነት አደጋ ሊያጠፋው የማይችል የመቋቋም ብልጭታ በውስጣችን ተሸክመናል። ትልቁ ልዩነት የሚፈጠረው እሳቱ (ፈተናው) እንዲያጠፋን እንፈቅዳለን ወይስ ወደተሻለ ማንነት እንድንለወጥና እንደገና እንድንፈጠር እንፈቅዳለን በሚለው ውሳኔ ላይ ብቻ ነው።
ፊኒክስ ስለ ህይወት እና ሞት ያለውን መሠረታዊ ተቃርኖ ይረዳል። ምህረትን ወይም ሁለተኛ እድልን ከመለመን ይልቅ፣ በራሱ ፍላጎት፣ በክብር ይሞታል እና በከፍተኛ ጥንካሬ ዳግም ይነሳል። ወፉ "በስኬት ለመኖር፣ አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ እንዴት መለወጥ እንዳለበት መማር አለበት" የሚለውን የመጨረሻውን እውነት ያስተምረናል። ስለዚህ፣ ፈተናዎች እና የጨለማ ጊዜያት መጨረሻ የሌላቸው ቢመስሉህም፣ አትርሳ፤ ፊኒክስ አልጠፋም፣ ነገር ግን ለሚቀጥለው ትንሳኤው እና ለሚመጣው አዲስ ንጋት ዝግጅት ላይ ነው። ሲነሳም፣ እውነተኛ ኃያል ነገር ፈጽሞ እንደማያልቅ፣ ነገር ግን አዲስ መልክ እንደሚይዝ ያመለክታል። ይህ የማያቋርጥ ዕድገትና ለውጥ አስፈላጊነትን ያሳያል።
እያንዳንዱ ትውልድ በሕይወት ዘመኑ ውስጥ ተግዳሮቶችን ወይም 'እሳት' ይገጥመዋል። አንዳንድ ሰዎች ይህን ኃይል ያለፈውን ለማጥፋት ቢጠቀሙበትም፣ ሌሎች ግን የወደፊቱን ለማብራት እንደ ብርሃን ይጠቀሙበታል። እሳቱን ተቆጣጥረው ለበጎ የሚጠቀሙ ሰዎች ታሪክ ሲሠሩ፣ ውድቀትን የሚፈሩ ግን ከቦታቸው ፈጽሞ አይነሱም። በመሆኑም፣ አስቸጋሪ ጊዜ ሲመጣ—ሕልምህ ሲፈራርስ፣ አገርህ ስትቸገር፣ ወይም ተስፋ ሲጠፋ—የፊኒክስን ትምህርት አስታውስ፦ ፍጻሜ የሚመስለው ነገር ሁሉ በእርግጥም በጭስ የተሸፈነ አዲስ ጅማሬ ነው። ስለዚህ፣ ተነሳ፣ ፈተናዎችን ተጋፈጥ፣ እና ዳግመኛ ጀምር።
 
 
ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ከ 20 አመት በታች የአለም ዋንጫ አርጀንቲናን 2 ለ 0 በመርታት የአለም ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችላለች።
ለሞሮኮ ያሲር ዛብሪ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ሀገሩን አሸናፊ አድርጓል።
ይህ እንዲሳካ በተለያዩ መንገዶች ላገዛችሁኝ፤ ረቂቁን በማንበብ ላበረታታችሁኝ፣ በ”የዳግማዊ ገፆች” ተስፋ ጥላችሁ በአዲስ ስራ እንድመጣ ናፍቃችሁ የገፋፋችሁኝ …….. ሁሉ ምስጋናችሁን ውሠዱ!
በ“የጨቀየ ጥለት” ፍቅር፣ ፖለቲካ፣ ማሕበረሠብ፣ ስነልቡና፣ ጥበብ፣ እውነት፣ ፍልስፍና ……. ብዙ ብዙ ርዕሠጉዳዮችን አንስቼበታለሁ፡፡
ሐሳብ ጠጥሮ እንዳያነቅፋችሁ፣ ጨዋታ ላልቶ እንዳያሠለቻችሁ፣ እናንተንም እኔንም እንዲመጥን እጅግ ብዙ ደክሜበታለሁ!
ጥቅምት 24 ድርብ በዓላችን ይሆናል!
Thursday, 16 October 2025 00:00

ቀይ አንበሳ

ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም (ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ)
ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!
ነገረ መጻሕፍት
ተጋባዥ ጸሐፊ:-
ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ (ዶ/ር) /ተርጓሚ
የተመረጠው መጽሐፍ:-
ቀይ አንበሳ
“ለአቢሲኒያ ህይወቴን እሰጣታለሁ እንጂ አልሸጥላትም…” ኮ/ል አልኸንድሮ ዴል ባዬ (1928)
አዘጋጅና አቅራቢ:- እንዳለጌታ ከበደ
አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ
የዝግጅት ቦታ:- FSS. አዳራሽ
(አድራሻ:- ቀበና፣ የካቶሊክ ኪዳነምሕረት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት፣ ባማ ሕንጻ አጠገብ፣ FSS አዳራሽ)
የአድራሻችን Google Map link:-
ለበለጠ መረጃ:- 0976066720
0900651010
በቴሌግራም ቻናላችንም ቤተሰብ ይሁኑን:-
ከዚህ ቀደም የተደረጉ ፕሮግራሞችን ለመከታተል:-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልፃለች፡፡
ቤተ-ክርስቲያኗ ባስተላለፈችው የሀዘን መግለጫ፤ የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ዜና እረፍት የሰማነው በታላቅ ኀዘን ነው፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የሰላም የፍቅር፣ የአንድነት ተምሳሌት አባት ነበሩ ስትል ገልጻለች።
በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተወደዱና የተከበሩ የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ፤ በመላው ኢትዮጵያን ዘንድ በመልካም ስብእናቸውና በርሕራሔያቸው በታሪክ ሲታወሱ እንደሚኖሩም አመልክታለች።
ቤተ-ክርስቲያኗ በእኒህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት በነበሩት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዕረፍት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልጻ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን ተመኝታለች፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ኀዘን ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ ባስተላለፈው የሀዘን መግለጫ፤ የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ ሄደዋል ብሏል::
ሀገራችን ታላቅ አባት አጥታለች ያለው ምክር ቤቱ፤ ሀዘናችን መሪር ቢሆንም የአላህን ውሳኔ ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም ሲል የሀዘን መግለጫ መልእክቱን አስተላልፏል::
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል።
ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን።
ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ።
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Page 4 of 790