Administrator
Friday, 24 July 2026 20:02
«የዓለም አቀፍ የሕዝቦች ጉባኤ» በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው
ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በዲፕሎማሲ መዲናዋ አዲስ አበባ «አዲስ ዓለም አፍሪካ የጋራ መፃኢ እድልን በመቅረጽ ረገድ» በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ከ700 በላይ የመንግሥት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የቢዝነስ ባለሀብቶች፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና የሲቪል ማህበራት ተወካዮች ይሳተፋሉ።
ይህ ታላቅ መድረክ በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ ንግድ፣ ዘላቂ ልማትና ሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ላይ ያላትን እየጎለበተ የመጣ ማዕከላዊ ሚና የሚያንፀባርቅ ነው። ጉባኤው በስፖርትና በባህል አማካኝነት ሰዎችን እንደሚያቀራርበው የዓለም ዋንጫ ሁሉ፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላትን በማሰባሰብ ለኢኮኖሚያዊ፣ ቴክኖሎጂያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች የጋራ መፍትሔ ለመፈለግ ያለመ ነው።
የጉባኤው ዋና ማዕከል ከሆኑት ዝግጅቶች አንዱ «አንድነት» (Unity) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን ሲሆን፣ ከ16 የአፍሪካ ሀገራትና ከዳያስፖራው የተውጣጡ ታዋቂ አርቲስቶችን ያሰባስባል። በተጨማሪም «የዛምቤዚ ወንዝ፡ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብ እና መንፈስ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሳይንሳዊ ጥናት የሚቀርብ ሲሆን፣ ጥናቱ ወንዙ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት እድገት ላይ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ በስፋት እንደሚመረምር ተገልጿል።
የጠቅላላው ምክር ቤት ሊቀመንበር አማካሪ ያኒና ዱቤይኮቭስካያ እንደገለጹት፣ ጥበብ ልክ እንደ ስፖርት ሁሉ የሰው ልጅ የጋራ ቋንቋ እና የሕዝብ ዲፕሎማሲ መሣሪያ በመሆኑ ሰዎችን በማቀራረብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
የሰርቭ ግሎባል ምክትል የሀገር ውስጥ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ነጋሽ በበኩላቸው፣ ጉባኤው በንግድ ድርድር ላይ ሳይሆን የእውነተኛ አንድነትን በማሳየት ለሁሉም የዓለም ሕዝቦች የሚሰራ አዲስ ዓለም ለመገንባት መንገድ ይጠርጋል። ይህ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ጉባኤ ዓመቱን ሙሉ የሚቀጥል ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክ አካል ሲሆን፣ ቀጣዩ ዓለም አቀፍ መድረክ በመስከረም ወር በሩሲያ ሞስኮ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል።
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:29
የሊቨርፑሉ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ሀብቱን ለትውልድ መንደሩ እያፈሰሰ ነው
የቀድሞው የሊቨርፑል እና ባየርን ሙኒክ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች ሳዲዮ ማኔ፣ ከስፖርት ህይወቱ ያገኘውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በትውልድ መንደሩ ማህበራዊ እድገት ላይ በማዋል ላይ ይገኛል። ማኔ በተለይም በጤና፣ በትምህርት እና በማህበረሰብ ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የአካባቢውን ህዝብ ህይወት የሚቀይሩ በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን እውን አድርጓል።
በህጻንነቱ የነበረበትን የጤና አገልግሎት እጥረት መሰረት በማድረግ፣ በማህበረሰቡ የህክምና አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ ዘመናዊ ሆስፒታል አስገንብቷል። ከዚህ በተጨማሪም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገንባት፣ ለተማሪዎች ላፕቶፖችን በማቅረብ፣ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት ማበረታቻ በመስጠት እና ወጣት ተማሪዎችን በመደገፍ በትምህርት ዘርፍ ትልቅ አሻራ አሳርፏል።
የማኔ በጎ አድራጎት በትውልድ ስፍራው ባምባሊ እንደ ማዶ ጋዝ ማደያ፣ የፖስታ ቤት፣ የ4ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት እና ታዳጊ ተጫዋቾችን የሚያበቁ የእግር ኳስ ቁሳቁሶችን በማቅረብ መሰረታዊ ልማቶች እንዲሟሉ አስችሏል። ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ለአካባቢው ቤተሰቦች የወርሃዊ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲወጡ ያግዛቸዋል። ለማኔ ስኬት ማለት የግል ውጤታማነት ብቻ ሳይሆን እሱን ለፈጠረው ማህበረሰብ ምላሽ መስጠት ነው።
Great Africa-
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:25
የኢራን የድሮን ጥቃት የሩሲያ እጅ እንዳለበት ጥርጣሬ አስነሳ
ኢራን በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የሲአይኤ ተቋማት ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት ላይ ሩሲያ የመረጃ ወይም የቴክኖሎጂ ድጋፍ አድርጋለች በሚል ምርመራ ሊደረግበት እንደሚገባ የአሜሪካ የደኅንነት ባልደረቦች ገለጹ። እንደ ሪያድ እና ምስራቃዊ ኢራቅ ባሉ ስፍራዎች በተፈጸሙት በእነዚህ ጥቃቶች ላይ የሩሲያ ቀጥተኛ ተሳትፎ ስለመኖሩ ገና ሙሉ ድምዳሜ ላይ ያልተደረሰ ቢሆንም፣ የጥቃቶቹ ዒላማቸውን የጠበቁ እና እጅግ ውጤታማ መሆን የደኅንነት ተቋማቱን ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ጥሏቸዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሩሲያ ለኢራን የምታደርገውን ሰፊ የቴክኒክ ድጋፍ የሚያውቁ ሲሆን፣ ይህም ለጥርጣሬው በቂ ምክንያት ሆኗል። በመጋቢት ወር ከተፈጸሙት ጥቃቶች በተጨማሪ ሌሎች የሲአይኤ ተቋማትም ጥቃት እንደደረሰባቸው ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን፣ የሩሲያ የመረጃ አገልግሎት ወይም የተሻሻለ የድሮን ቴክኖሎጂ አቅርቦት ለዚህ ድርጊት ሽፋን ሰጥቶ እንደሆነ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:24
የሁቲዎችን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ አሻቀበ
በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የየመኑ ሁቲዎች በባብ ኤል መንደብ ወሽመጥ ሁለት የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ መርከቦችን መትተዋል። ሁቲዎች ይህንን አስፈላጊ የባህር መስመር እንደሚዘጉና ወደ ሳዑዲ የሚሄዱ መርከቦችን እንደሚመቱ ያስጠነቀቁት፣ ባለፈው ሳምንት የሳዑዲ ጦር በሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ድብደባ ካደረገ በኋላ ነው።
በሌላ በኩል ሳዑዲ አረቢያ፣ አሜሪካና ወዳጆቻቸው፡ «የሁቲዎች እርምጃ ከእነሱ ጋር ውጥረት ውስጥ ለምትገኘው ኢራን ድጋፍ ለመስጠት የተደረገ ሴራ ነው» ሲሉ ይከሷቸዋል። የጥቃቱ ዜና እንደተሰማ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በአንዴ በ6 በመቶ በመጨመር አንድ በርሚል ነዳጅ 100 ዶላር ገብቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በሁቲዎችና በኢራን ላይ የሚያደርገውን የአየር ድብደባ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዝተዋል።
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:22
የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎች ባካችሁ ይዘት ላይ ሥሩ!
የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎች 'ይሻሻላሉ፣ ገና ጅምር ላይ ናቸው፣ ብዬ በተስፈኝነት ጠበቅሁ። እኔን ብሎ ተስፈኛ! እነርሱ ግን እያደር የጳጳሳት_ዲያሪ ሆነው ቁጭ!
"ብፁዕነታቸው መሠረት ጣሉ፣ ጎበኙ፣ ከፈቱ፣ ተጓዙ...።" non sense! የሚዲያ ይዘት እንዲህም ይሞታል እንዴ?! ኃፍረት ወዝንጓጔ ማለት ለእናንተ! እያደር ማዘቅዘቅ! እንደ ተዘዋዋሪ ሰባኪ በየንግሡ ለአበል ሩጫ ብቻ! ያሳዝናል! ሚዲያችን contentwise ክፉኛ፣ ያውም ፀዋግ ሞት እየሞተ ነው።
ኅሡ ርእሰክሙ አኃው።
ቤተ ክህነቱን እንደ መደብ ጀርባው እንደሚቆጥር ደብተራ ባላችሁ ይዘትም ሆነ አቀራረብ ኃዘንም ኃፍረትም ይሰማኛል።
የላዕላይ መዋቅሩ የዕለት ተዕለት ውሎ ዘጋቢ ሆናችሁ እየቀራችሁ ነው። ሁሌ "የሙከራ ስርጭት" ላይ ያላችሁ መስላችሁ መታየት ደስ አይልም። አዘጋገባችሁ ቤተ ክርሰቲያን ማለት "ጳጳሳት/መምሪያዎች ብቻ" ያስመስላል።
ባካችሁ ይዘት ላይ ሥሩ፣ የካህኑና የምዕመኑ እንዲሁም የአጥቢያዎች ድምፅ ለመሆንም ሞክሩ። የይዘት ሳይሆን የአደባባይ ተርእዮ መድረክ እየሆናችሁ ነው።
በአማን ነጸረ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:19
ጄነራል ታደሰ ወረደ ወዴት ተሰወሩ?
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅና በጥበቃ ተሽከርካሪዎች የተከበበ የነበረ ቢሆንም፣ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ግን አብረዋቸው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል።
ጄነራሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌደራል መንግሥት ዳግም በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሚታወስ ነው። ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊትም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር።
በአሁኑ ወቅት በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት በጨመረበት ሁኔታ፣ የጄነራሉ ከአካባቢው መሰወር በትግራይ ክልል አዲስ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:15
100 እንቁላል በ1 ብር!
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ገጼን ሳይ Zerihun Gultie የ1955 ጋዜጣ ለጥፏል። ጋዜጣው ከሚያወሳቸው አንዱ ዜና 785,275 ኪሎ ግራም በቆሎ በ78,267 ብር ለሱማሊያና ለየመን እንደተሸጠ ይገልጻል።
ይህ ሽያጭ እስከ አሰብ የተጓጓዘው በኛ ትራንስፖርት ከሆነ በኩንታል ከብር 30.00 በታች መሆኑ ነው። ያኔ የሀገር ውስጥ ዋጋ በኪሎ ከ0.25 ሳንቲም አይበልጥም ነበር። እንቁላልም በኪሎ ከ1.00 በታች እንደሆነና በ2058 ብር ልዩ ልዩ የተሻለ ዝርያ ያላቸው ከብቶችን ከውጭ አገር ማስገባታችንንና አሜሪካ 225 ግመሎች ማጓጓዣውን ጨምሮ በ5060 ብር መግዛቷን ጋዜጣው ያወሳል።
የብርም ዋጋ ከዶላር በላይ ነበር። ባልሳሳት ያኔ 3USD 1EthD ነበር። ለማንኛውም በቆሎ ለውጭ የተሸጠው በ12 እጥፍ ሲሆ፣ እኔ ሳውቅ በአንድ ብር 100 እንቁላል ስለነበር ብዙ እጥፍ መሆኑ ነው። የምርጥ ከብቶቹንና የግመሎቹን ስሌት ለናንተ ልተወው። በአሁኑ ጊዜ ግን ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ከሀገር ቤት ባነሰ ይመስለኛል።
ጋዜጣውን ለለጠፈው ወዳጄ ምስጋና አቀርባለሁ።
Teshome Berhanu Kemal
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ማራኪ አንቀፅ
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:14
የትራምፕ አስተዳደር በማሊ በሚገኙ አማፂያን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለማድረስ እያሰበ ነው
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በማሊ ከሚንቀሳቀሰውና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ካለው አማፂ ቡድን ጋር በተያያዘ ወታደራዊ ጥቃት ለማድረስ እያሰበ መሆኑን የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ይህ ውሳኔ ከጸደቀ ማሊ በትራምፕ ሁለተኛ የፕሬዝዳንትነት ዘመን አሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት የፈጸመችባት 8ኛዋ ሀገር ትሆናለች፤ ይህም አሜሪካ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያሰፋው ይሆናል። እስካሁን ድረስ የተላለፈ የመጨረሻ ውሳኔ የሌለ ሲሆን በጉዳዩ ላይ በአስተዳደሩ ውስጥ ውይይቶች አሁንም ቀጥለዋል።
Published in
ከአለም ዙሪያ
Tagged under
Thursday, 23 July 2026 18:11
የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት መስራችና ሊቀመንበር ሰር ቶኒ ብሌየር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የጎበኙ ሲሆን፣ ከአመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ወቅት ሰር ቶኒ ብሌየር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ረገድ ያለውን ከፍተኛ ሚና አጉልተው በመናገር፣ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለመደገፍ እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል። ሁለቱ ተቋማት በቀጣይም በኢትዮጵያ የኤ.አይ (AI) ቴክኖሎጂ ልማትን እና ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ በጋራ እና በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተመላክቷል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 22 July 2026 00:00
እስራኤል የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አወደሰች
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ እድገት በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ አድናቆታቸውን ለግሰዋል።
ይህ የእስራኤል ድጋፍ የመጣው የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ግድቡን በብቸኝነት እያንቀሳቀሰች ነው ሲሉ ከከሰሱ በኋላ ሲሆን፣ አምባሳደሩ በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በእርሻ፣ በጠብታ መስኖና በዓሣ ሀብት ልማት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በካይሮና በአዲስ አበባ መካከል ያለው የቃላት ልውውጥ እና ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት እየጨመረ መጥቷል። ግብፅና ሱዳን ያለ ህጋዊ ስምምነት ግድቡን መሙላትና ማካሄድ የውሃ ደህንነታችንን ይጎዳል ሲሉ ሲቃወሙ፣ ኢትዮጵያ በበኩሏ የ4 ቢሊዮን ዶላሩ ግድብ በታችኞቹ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጎጂ ተጽዕኖ እንደማያደርስና ለሀገሪቱ የኃይል ፍላጎት ወሳኝ መሆኑን አጥብቃ ትገልጻለች።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under

