Administrator

Administrator

ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የመገናኛ ብዙሃን ሚና የላቀ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ገለፀ። ምክር ቤቱ ከተለያዩ የሚዲያ ባለሞያዎችና የዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር “በሀገራዊ ምክክሩ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን ይመስላል“ በሚለው ጉዳይ ላይ ምክክር አድርጓል።
መገናኛ ብዙሃን ታማኝ፣ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ሙያዊ ሃላፊነት የሚስተናገድበት ተቋም መሆኑን ያነሱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን መገናኛ ብዙኃን ድርሻቸው የጎላ እንደሆነና ለዚህም በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር የምትወጣበት አይነተኛ መንገድ ነው ያሉት የሀገራዊ ምክክሩ ኮሚሽነር ተገኘ ወርቅ ጌቱ (ዶ/ር) ፤ ምክክሩ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ እንዳለና በቀጣይም በአማራና በትግራይ ክልሎች ምክክሩን ለመጀመር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ሀገራዊ ምክክሩን ለመጀመር ከ1 ሺህ 700 በላይ ተባባሪ አካላትን አሰልጥኗልም ብለዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ መገናኛ ብዙኃን ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነው፣ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ማበርከት እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

ሲንቄ ባንክ፤ የሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክን ለማቋቋምና የድርጅት ስትራቴጂን፣ ተግባራዊ ስትራቴጂን እንዲሁም የሂደትና ዳግም የማወቀርያ ድርጅታዊ ዲዛይንን ለማዳበር የሚያግዝ የምክር አገልግሎት ለማግኘት ከዴሎይት ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሒልተን አዲስ ሆቴል መካሄዱ ታውቋል፡፡
የስምምነት ውሉን የተፈራረሙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ነዋይ መገርሳና የአጋር ዴሎይት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ አማካሪ ድርጅት መሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ ሲሆኑ፤ በሥነስርዓቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራር፣ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ ካፒታል ሊድ ዳይሬክተር የሆኑት የዴሎይት ማኔጅመንት ዶ/ር ፖል ኦካቴጅ ተገኝተዋል፡፡
• የቀላቲ ሂውማን ሄር ብራንድ አምባሳደር ሆናለች
• ለቀላቲ ሂውማን ሄር ቆንጆ ዘፈን ሰርቻለሁ
ታዋቂዋ ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ፣ የቀላቲ ሂውማን ሄር አምባሳደር ተደርጋ የተመረጠች ሲሆን፤ ለሁለት ዓመታት የቀላቲ ቢውቲን ምርቶች ታስተዋውቃለች ተብሏል፡፡
በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በቤስት ዌስተርን ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው ሥነስርዓት ላይ የቀላቲ ቢውቲ መሥራችና ባለቤት አቶ ሮቤል ቀላቲ፣ ከድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የቀላቲ ቢውቲ የኦንላይን ሽያጭ መጀመርም በዚሁ ሥነስርዓት ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ ለኦንላይን ግብይቱ በአማርኛና እንግሊዝኛ የተዘጋጀ ዌብሳይትም ተዋውቋል፡፡
ከተመሰረተ 9 ዓመታትን እንዳስቆጠረ የተነገረለት ቀላቲ ቢውቲ፤ የሰው ጸጉር (ሂውማን ሄር)፣ የፊትና የቆዳ ውበት መጠበቂያዎች እንዲሁም የወንድና የሴት ሽቱዎችን ለደንበኞቹ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
በአዲስ አበባና በዱባይ መደብሮች ያሉት ቀላቲ ቢውቲ፤ በቅርቡ ሦስተኛ መደብሩን በሰሜን አሜሪካ እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
”ቀላቲ” በትግርኛ ስጦታ ማለት እንደሆነ ያስረዳው የድርጅቱ መሥራች፤ “አባቴን በጣም ስለምወደው ነው ድርጅቱን በእሱ ስም የሰየምኩት” ብሏል፡፡
ትኩረታችን ውበት ላይ ነው የሚለው አቶ ሮቤል ቀላቲ፤ ለደንበኞቻችን ጥራት ያለው ምርት ስለምናቀርብ አሁን ላይ ድርጅታችን መቶ ፐርሰንት ትርፋማ ነው ብሏል፡፡
የወደፊት ራዕዩንም ሲገልጽ፤ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ እስከ 300 የሚደርሱ የውበት መጠበቂያ መደብር ቅርንጫፎች የመክፈት ዓላማ እንዳለው ይናገራል፡፡ “በአገራችን የመጀመሪያው የውበት ፍራንቻይዝ ለመሆን እንፈልጋለን” ብሏል፤የቀላቲ ቢውቲ መሥራች፡፡
ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ለመንግሥት ተገቢውን ግብር በመክፈል ለአገር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚሻም አቶ ሮቤል ተናግሯል፡፡
ተወዳጇ ድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ በበኩሏ፣ የቀላቲ ሂውማን ሄር ብራንድ አምባሳደር ሆና መመረጧን አስመልክቶ በሰጠችው አስተያየት፤ “ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው፤ በብራንድ አምባሳደርነት ስፈራረም ይሄ የመጀመሪያዬ ነው፤ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፡፡” ብላለች፡፡
ድምጻዊቷ አክላም፣ ከቀላቲ ሂውማን ሄር ጋር ግንኙነት የፈጠረችበትን አጋጣሚ አውስታለች፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው፡፡ ገና ጀማሪ ድምጻዊት ነበረች፤ የታዋቂዎቹን አርቲስቶች ሥራዎች በምሽት ክለቦች የምታቀነቅን፡፡ ቬሮኒካ እንደምትለው፤ የመጀመሪያ የሙዚቃ ሥራዋን ስትሰራ ሂዩማን ሄር ያስፈልጋት ነበር፤ ነገር ግን የመግዛት አቅም አልነበራትም፡፡ በነጻ የሚሰጣት ወይም ስፖንሰር የሚያደርግ መፈለግ ነበረባት፡፡ የመጀመሪያ ሙከራዋ አልተሳካም፡፡ ሁለተኛው ሙከራዋ ያገናኛት ከቀላቲ ሂውማን ሄር ጋር እንደነበር ድምጻዊቷ ታወሳለች፡፡
የቀላቲ ቢውቲ መሥራች አቶ ሮቤል ቀላቲ ባለቤት ጋር ተገናኝታ ችግሯን እንደነገረቻት ትገልጻለች፡፡ “ሳያውቁኝ አምነውኝ ሂውማን ሄር ስፖንሰር አደረጉኝ፤ በነጻ ሰጡኝ፡፡ የመጀመሪያ ሥራዬ ላይ እንደዚያ ፏ ፍንትው ብዬ የምታዩኝ በቀላቲ ሂውማን ሄር ስፖንሰር ተደርጌ ነው፡፡” ስትል ከቀላቲ ሂውማን ሄር ጋር ግንኙነታቸው የተጀመረበትን አጋጣሚ አስረድታለች፡፡
አሁን በብራንድ አምባሳደርነት የተመረጠችው፣ ያኔ ሂውማን ሄር ስፖንሰር ላደረጋት ድርጅት ነው - ለቀላቲ ቢውቲ፡፡
“ዛሬ ታሪክ ተቀይሮ ለብዙ ሴቶች አርአያ ትሆናለሽ ተብዬ የፊት ገጽ በመሆኔ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ያለችው ድምጻዊቷ፤ “በብራንድ አምባሳደርነት ስፈራረም ይሄ የመጀመሪያዬ ነው” ብላለች፡፡
በብራንድ አምባሳደርነት ያላት ሃላፊነት ምን እንደሆነ ከጋዜጠኞች የተጠየቀችው ድምጻዊቷ፤ የፊት ገጽ በመሆን ሂውማን ሄርን ጨምሮ የቀላቲ መዋቢያዎችን ማስተዋወቅ ዋና ሃላፊነቷ መሆኑን ተናግራለች፡፡
ከቀላቲ ቢውቲ ጋር ያላት ግንኙነት እንደ ቤተሰብ ቢሆንም ቅሉ፣ በብራንድ አምባሳደርነት ለመሥራት የተስማማችው ለሁለት ዓመት መሆኑን ገልጻለች፤ቬሮኒካ፡፡
ለብራንድ አምባሳደርነቱ ምን ያህል ተከፈለሽ በሚል ለቀረበላት ጥያቄ፤ ባለፈው የተከፈለኝን ተናግሬ ከደረሰብኝ አንጻር ስለ ክፍያው ባልናገር እመርጣለሁ ያለችው ድምጻዊቷ፤ ነገር ግን የሚመጥነኝን ጥሩ ክፍያ አግኝቻለሁ፤ ስትል መልሳለች፡፡
የቀላቲ ሂውማን ሄርም ሆነ ሌሎች መዋቢያዎች እጅጉን ጥራት ያላቸው መሆናቸውን የመሰከረችው ብራንድ አምባሳደሯ፤ “እኔ ሂውማን ሄርም ሆነ ምንም ዓይነት መዋቢያ ከቀላቲ ነው የምጠቀመው” ስትል ማረጋገጫ ሰጥታለች፡፡
ድምጻዊቷ፤ ለቀላቲ ሂውማን ሄር “ቆንጆ ዘፈን” መሥራቷንም ገልጻለች፡፡
• አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ይበረከትላቸዋል
እናት ባንክ፤ “የዓመቱ ድንቅ እናት” (mother of the year) የተሰኘ ውድድርን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም “ለእናቴ” የተሰኘ አገር አቀፍ የፅሁፍ ውድድርን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ማካሄድ ጀመረ፡፡
እናት ባንክ፤ ሁለት አገር አቀፍ የውድድር መርሐ ግብሮችን በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ይፋ አድርጓል፡፡ አንደኛው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ የእናት ባንክ ድንቅ እናት” የተሰኘ ውድድር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው “ለእናቴ” የተሰኘ የፅሁፍ ውድድር ነው፡፡
ባንኩ፤ ለዘመናት ለሀገርም ሆነ ለቤተሰብ ምሰሶ ለሆኑት የኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ለአንድ ወር የሚቆዩና ሽልማት የሚያስገኙ፣ ሁለት እናት ተኮር ውድድሮችን በይፋ ማስጀመሩን አብስሯል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ የእናት ባንክ ድንቅ እናት” የተሰኘው ውድድር፣ ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች፣ በድምፅና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበት ውድድር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሁፍ ውድድር ደግሞ፣ በዋናነት ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሁፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣ በደብዳቤ ቅርጽ ወዘተ) የሚገልፅበትና “ለእናቴ” የሚልበት መልካም አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡
የዓመቱ የእናት ባንክ ድንቅ እናት ውድድርን አስመልክቶ ተወዳዳሪዎች፣ በፅሁፍ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በቃላቸው፣ በድምጽና በምስል ቀርጸው የሚወዳደሩበትን የዓመቱ ድንቅ እናት (mother of the year) የሚያስመርጡበት ሂደት ነው፡፡ “ለእናቴ” በተሰኘው የፅሁፍ ውድድር ላይም፣ ስለ እናታቸው የሚያጋሩትን ፍቅርና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ይልቁንም ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እንዴት እንደገለፁ፣ ስሜታቸውን ወደ ሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የሚዳኙበት ዐውድ ነው ተብሏል፡፡
የማወዳደሪያ መስፈርቶች በተመሳሳይ መልኩ የተቃኙ መሆናቸውን የጠቆመው የባንኩ መግለጫ፤ የቅርፅ ጉዳዮች 50 ከመቶ፣ የይዘት ጉዳዮች 50 ከመቶ፣ በድምሩ 100 ነጥብ እንዲይዙ ተደርገው መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡
የእናት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ገነት ሃጎስ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት፤ የውድድሩ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማትና የምስክር ወረቀት የሚበረከትላቸው ሲሆን፤ የገንዘቡን መጠን ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
የዓመቱ ድንቅ እናት ውድድር ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ “ለእናቴ” የጽሁፍ ውድድር ደግሞ ከነገ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 11 ቀን 2047 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር እንደሚቆይ የእናት ባንክ መረጃ ይጠቁማል፡፡
“ተወዳዳሪዎች፣ ስለ እናታቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት በፈለጉት መንገድ የሚገልፁባቸው ሁሉም የ“ለእናቴ” ጽሁፎች ሆኑ የዓመቱ ድንቅ እናትን የማወዳደሪያ ጥቆማዎች የህብረተሰቡን ስነ ምግባር፣ ሀገራዊ መልክና የሃይማኖት ልዩነት ወዘተ ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡” ብሏል፤ መግለጫው፡፡
“ለእናት የጽሁፍ ውድድር” በአዕምሮአዊ ንብረት ተመዝግቦ፣ የእናት ባንክ ንብረት መሆኑን የባንኩ አመራሮች በመግለጫው ላይ አስታውቀዋል፡፡
የዓመቱን ድንቅ እናት ውድድር
ይሄ ውድድር በህይወት ያሉ እናቶች የሚመሰገኑበት የውድድር አይነት ሲሆን ከ “ለእናቴ የፅሁፍ ውድድር” የሚለይባቸው የራሱ መመዘኛዎች አሉት፣ መወዳደሪያ መስፈርቶቹም፡-
* ለውድድር የሚቀርቡት ባታሪኮች በህይወት ያሉ እናቶች መሆን አለባቸው፤
* ታሪካቸው የሚነገርላቸው እናቶች ግዴታ ወላጅ እናተ (የስጋ እናት) መሆን አይጠበቅባቸውም፤
ለምሳሌ አሳዳጊ ወይም ደግሞ በሰፈር አሊያም በጎረቤት ያ እናቶችን ታሪክ ማቅረብ ይቻላል፡፡
* በዚህ ውድድር ላይ ስለ ሚያቀርቡት ታሪክ ከፈለጉ በፅኁፍ አሊያም በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ስዎቻቸውን ቀርፀው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
* ውድድሩ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 14/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
* መወዳደሪያ ስራዎቻችሁን አቅራቢያችሁ በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች ማስረከብ የሚል ሲሆን በቪዲዮና በድምፅ ቅጂ ለምታስገቡ እና ውጭ ሀገር ለምትኖሩ ደግሞ በኢሜል፣ አሊያም በእናት ባንክ ኦፊሻል የፌስቡክ ገፃችን ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
“ለእናቴ” የጽሁፍ ውድድር
የውድድሩ ጽሁፎ መወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
* በሌሎች የህትመት እና የኤሌክቶኒክስ የመገናኛ ብዙሀን ላይ ያልቀረበ ወጥ ፣ አዲስና የተለየ መሆን ይኖርበታል፤
* ጽሁፉ ግልጽ እና ተነባቢ እንዲሆን በኮምፒውተር ተጽፎ፣ በ12 ፎንት የፊደላት መጠን እና በ1.5 የኅዳግ መስመር መቅረብ አለበት፤
* በኤ ፎር ( A4 ) የወረቀት ምጣኔ፣ ከሦስት /3/ ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤
* ለተመረጡ አሸናፊ ጽሁፎች የገንዘብ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ይበረከትላቸዋል፤
* ተወዳዳሪዎች፣ ስማቸውን እና አድራሻቸውን የፅሁፍ ስራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ መፃፍ የለባቸውም፣ ይልቁንም ስራቸውን በሚገያሸ፴ጉት ፖስታ ላይ ብቻ መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
* እናት ባንክ አሸናፊ ጽሁፎን በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡
* የማስረከቢያ ጊዜ ከዛሬ ከታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 11 ቀን 2047 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ይሆናል፡፡
* ተወዳዳሪዎች ጽሁፋቸውን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የውድድሩ መዝጊያ በተመለከተ የተወሰኑ የውድድሩ ተሳታፊዎች፣ የውድድሩ አሸናፊዎች፣ ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች ባሉበት በታላቅ ድምቀት የሚደረግ ሲሆን በእለቱም ለአሸናፊዎች ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁላቸው ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል፡፡
የኢሜል አድራሻ፤ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የሺህ ጋብቻ ኹነትን በማዘጋጀት የሚታወቀው ያሜንት ኃ. የተ.የግ.ማ፤ ሦስተኛውን የሺህ ጋብቻ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በዚህ ኹነት ላይ 1ሺ ኢትዮጵያውያን ጥንዶችና 250 የሚደርሱ ከአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ጥንዶች የሰርግ በዓላቸውን እንደሚያከብሩ ታውቋል፡፡

የሺህ ጋብቻ ትልቁ ዓላማ፣ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት፣ አዲስ አበባን “የሃኒሙን ማዕከል” ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

የኹነቱ አዘጋጆች ሦስተኛውን የሺህ ጋብቻ አስመልክቶ ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሃርመኒ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዘንድሮ በሚካሄደው የሺህ ጋብቻ በተቻለ መጠን ከሁሉም ብሔርና ብሔረሰቦች የተውጣጡ ጥንዶች የሚሳተፉበት እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንና ሙሽሮች ለሠርጋቸው የሚያወጡት ምንም ዓይነት ወጪ እንደማይኖር በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል፡፡

የሺህ ጋብቻ የሠርግ ሥነሥርዓትና ባህላዊ ካርኒቫል፤ ከሠርግ ድግስ ጋር የተያያዙ፣ ለዘመናት የቆዩና ሥር የሰደዱ ጎጂ ማኅበራዊ አመለካከቶችን ለማስወገድና ወደ ለውጥ የሚያመራ ማኅበረሰባዊ ውይይት ለማንሳት እንደሚረዳ የተነገረ ሲሆን፤ ቤተሰብ በማህበረሰብ ግንባታ ውስጥ ያለውን ፋይዳ በማጉላት፣ ለበጎ አስተሳሰብ መጎልበት መሠረት መሆኑን ለማሳወቅ እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡

የሺህ ጋብቻ፤ የውጭ አገር ጎብኚዎችን በመሳብ ከቱሪስት ፍሰት የውጭ ምንዛሪ ግኝትን መፍጠር፣ የባህል ልውውጥ መድረክ በመፍጠር ሃገሪቱ ለህዝቦች አንድነት መጠናከር እንዲሁም ለሰላምና ለባህሎች ዕድገት የምታደርገውን ጥረት መደገፍ አላማው ነው ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ያሜንት ኃ. የተ.የግ.ማህበር ኹነቱን በተሻለ መንገድ ለማስተዋወቅ፣ አርቲስት ተስፋዓለም ታምራትና ባለቤቱን ቃልኪዳን አበራ እንዲሁም አርቲስት ይገረም ደጀኔና ባለቤቱን ፅዮን ዮሴፍን የየሺ ጋብቻ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል፡፡

ለዚህ ኹነት ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው አጠቃላይ በጀት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

”ቤተሰብን መመስረት አገርን መገንባት ነው" የሚል መሪ ቃል ያለው ያሜንት፤ የመጀመሪያውን የሺ ጋብቻ ኹነት በ2005 ዓ.ም 500 ጥንዶችን በመዳር ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

ድርጅቱ በመጀመሪያው ዙር ለተጋቡ ጥንድ ሙሽሮች የ10ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን በሸራተን አዲስ ያከበረላቸው ሲሆን፤ ለሁለተኛው ዙር ሙሽሮች የመልስ ጥሪ በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ ተደርጎላቸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ከአዲስ አበባ ፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል፡፡
በዚህ አውደርዕይ ታዋቂ ባለሙያዎች አንቶኒዮ ፍዮሬንቴ፣ ሙሉጌታ አየነ፣ ማኅደር ኃይለሥላሴ፣ ናሆም ተስፋዬና ሚካኤል ጸጋዬ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
አውደርዕዩ ቅዳሜ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም 10፡00 ላይ በአካዳሚው ሙዚየም በይፋ ይከፈታል፡፡ መግቢያው በነጻ ሲኾን እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል፡፡
ከፒያሳ ወደ ውንጌት መስመር በሚወስደው ጎዳና - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ -
በተለምዶ ወረዳ ስምንት ተብሎ በሚጠራው ቀጭን መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ወይንም ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል

የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሕወሓት አዳዲስ ተዋጊዎችን በመመልመልና ነባሮችን በመቀስቀስ ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው ሲሉ ከሰዋል።
የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ ባይቶና እና ዓረና ፓርቲ ትላንት በሰጡት መግለጫ፤ ሕወሓት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብ ተመራጭ ሹሞች ላይ ማስፈራሪያ እየፈጸመ ይገኛል በማለትም ወንጅለዋል።
የትግራይ የፖለቲካና የጸጥታ ኃይል አመራሮች በሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በመርዛማ ኬሚካሎች በመታገዝ ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን ዝርፊያ እየፈጸሙና የአካባቢ ብክለት እያደረሱ እንደኾነም ፓርቲዎቹ ጠቁመዋል፡፡
ተቃዋሚዎቹ በሰጡት መግለጫ፤ የክልሉን ችግር ለመቅረፍ ሁሉን አካታች የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም በድጋሚ ጠይቀዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መከላከል ዓላማ ያደረገ ሕገ-ደንብ አጽድቆ ወደ ትግበራ ሊያስገባ ነው።
በሕገ-ደንቡ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ የሚመክር የኢጋድ ከፍተኛ ቀጣናዊ ፎረም ዛሬ በኬንያ ሞምባሳ መካሄድ ጀምሯል። የጅቡቲ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር እና የኢጋድ የአምባሳደሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ መሐመድ ዓሊ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ስብሰባ በይፋ አስጀምረዋል።
ፎረሙ ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚያስችለው ረቂቅ ሕገ-ደንብ ላይ በመምከር እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤ ሕገ-ደንቡ ጸድቆ ወደ ሥራ ይገባል የሚል እምነት እንዳላቸው በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
(ኢዜአ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት አፀደቀ። ምክር ቤቱ በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል።
በዚሁ ጊዜ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግና ለምጣኔ ሀብት ዕድገቱ ቀጣይነት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል። የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ሥራ መሰማራታቸው የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ከማምጣት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ለማሳደግ ያግዛልም ተብሏል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት የአገር ውስጥ ባንኮችን አቅም ሳያሳድጉ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ ይዞት ሊመጣ የሚችል አሉታዊ ተፅዕኖ የለም ወይ የሚል ጥያቄ አንስተዋል። የምክር ቤቱ አባላት ከብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅም፣ ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦት ጋር ሊያጋጥሙ ይችላሉ ያሏቸውን ስጋቶች አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ በሰጡት ምላሽ፤ ረቂቅ አዋጁ የባንክ ዘርፉ ለውጭ ባንኮች ክፍት የሚሆንበትን ስርዓት የሚያስቀምጥ ነው ብለዋል። የፋይናንስ ዘርፉን ክፍት ማድረግ የአገር ውስጥ ባንኮችን አቅም የሚያጠናክር እንጂ የሚያጠፋ አለመሆኑንም አብራርተዋል።
አሰራሩ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ተቀጥላ ኩባንያ እንዲከፍቱና ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር በሽርክና እንዲሰሩ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።
ዘርፉ ለውጭ ባንኮች ክፍት መደረጉ የአገር ውስጥ ባንኮችን የበለጠ በማጠናከር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ ያስችለዋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። ምክር ቤቱ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን በሦስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

 


- ቃል ገብተዋል፤ በተግባር ፈጽመዋል!

 • በሁለት ወር የተገነቡ ትምህርት ቤቶች፣ የዳቦና የእንጀራ ፋብሪካዎች፣

አስፋልት መንገድና መናፈሻዎች፣ ሱቆችና የስፖርት ማዘውተሪያዎች…

 ከሁለት ወር በፊት ነበር የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ “የጎደለውን ሁሉ እናሟላለን” ብለው ቃል የገቡት።

ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት የተነሡ ነዋሪዎች ወደ ገላን ጉራ የገቡበት ሰሞን ነበር - ጊዜው። ከ60 ዓመት በላይ ያለማሻሻያና ያለ እድሳት በእርጅና የተጎሳቆሉና የተፋፈጉ የቀበሌ ቤቶች ውስጥ ነበር ኑሯቸው።
ለልማት ተነሺ ነዋሪዎች በገላን ጉራ የተዘጋጁት ቤቶች ግን፣ አዳዲስ የኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ናቸው። ቤቶቹ ስፋት አላቸው። የግንባታቸው የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ነው። የድሮውና የዛሬው አይገናኝም ይላሉ - ለ52 ዓመታት በካዛንቺስ እንደኖሩ የነገሩን ወ/ሮ እታገኘሁ አመሜ።
በእርግጥም በገላን ጉራ አዲስ ኑሮ የጀመሩ 1200 ቤተሰቦች ዕድለኞች ነን ይላሉ። ቤቶቹ ያምራሉ። ነገር ግን…
የልጆች ትምህርት ቤትስ? እስከ መኖሪያ መንደራቸው የሚወስደው ኮሮኮንች መንገድስ? የትራንስፖርት አገልግሎትስ? ብዙ ጥያቄዎች ነበሯቸው።
ከመደበኛ የስራ ቦታ ከገበያ ጋር የተራራቁ ሰዎች እንዴት ይሆናሉ? ቀድሞውኑ ቋሚ የመተዳደሪያ ስራ ያልነበራቸውስ?
የካዛንቺስ ነዋሪ እንደነበረ የገለጸልን ጥላሁን ደለለኝ፣ በረዳትነት እና የተገኘውን ነገር እሰራ ነበር፤ አንዳንዴ ስራ ይኖራል፣ አንዳንዴ አይኖርም ይላል። በገላን ጉራ የተሠጠን ቤትና ሰፈሩ ያስደስታል፤ ነገር ግን መጀመሪያ ላይ የመሠረተ ልማትና የሥራ ዕድል ችግሮች ነበሩብን በማለት ያስታውሳል።
ከካዛንቺስ ተነሥተው ወደ አዲሱ መኖሪያቸው ሲገቡ፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ከጠበቁት በላይ ድጋፍ እንዳደረገላቸው አይደብቁም። ከነባር ሰፈር ወደ አዲስ ሲዛወሩ የሚፈጠርባቸውን የስነልቦና ጫና ለመቋቋም የሚረዳ የማካካሻ ገንዘብ በፍጥነት እንደደረሰላቸው ይገልጻሉ። የዕቃ ማጓጓዣ ድጋፍ በነጻ ማግኘታቸው ከብዙ ጭንቀት እንዳዳናቸው ይናገራሉ። በገላን ጉራ መኖሪያ ቤቶችና በአካባቢው ገጽታ ደስተኛ ናቸው።
ቢሆንም ግን ነዋሪዎቹን የሚያሳስቡ ጉዳዮችም አጋጥመዋቸዋል - የዛሬ ሁለት ወር። በትራንስፖርት፣ በትምህርት ቤት፣ በስራ እጦት እንቸገራለን የሚል ነበር ሐሳባቸው።
ካዛንቺስ የመናኸሪያ አካባቢ ነዋሪ እንደነበረች የገለጸችልን ወ/ሮ ቤቴል ከበደ፣ ወደ ገላን ጉራ የገባችው መስከረም 30 እንደሆነ ታስታውሳለች። የተሰጠን መኖሪያ ቤት ደስ ይላል፤ ሌሎች ነገሮች አልነበሩም ማለት ይቻላል። ጅምር ሥራዎች ብቻ ነበር ትላለች። እዚህ የገባን ሰሞን፣ ክብርት ከንቲባችን አዳነች አበቤ እዚህ ሊጠይቁን መጥተው አነጋግረውናል በማለት ታስታውሳለች።
ቀጠሮ የተያዘለት የተስፋ ቃል የት ደረሰ?
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ የገላን ጉራ አዲስ ነዋሪዎችን ለመጠየቅ፣ ጊዜያዊ የዱቄት፣ የዘይትና የቡና ድጋፍ እንዲሁም የመማሪያ ቁሳቁስ ይዘው ነበር የሄዱት። ከነዋሪዎች ጋር ተነጋገሩ። ጥያቄዎችን ሰሙ። ቀድሞውኑ የከተማው አስተዳደር ያሰበባቸው ጉዳዮች ናቸው በአብዛኛው። እናም…
የጎደለውን ሁሉ እናሟላለን ብለው ለነዋሪዎች ቃል ገቡ - ከንቲባ አዳነች አበቤ።
በደፈናው አይደለም።
“ሁሉንም ነገር አመቻቻለሁ። የመንገድ ግንባታ በፍጥነት ጨርሰን፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እናቀርባለን” ብለውን ነበር ትላለች ወ/ሮ ቤቴል። “በቀድሞ የስራ ልምዳችሁና ይዛችሁት በመጣችሁትን ሙያ እንድትቀጥሉ ዘዴ እንፈጥራለን። ተጨማሪ የስራ ዕድሎችን፣ የስራ ቦታዎችንና የገበያ አማራጮችን እናሟላለን” ብለው ከንቲባችን ቃል ገብተውልን ነበር በማለትም ታስታውሳለች።
ከንቲባ አዳነች ዕቅዳቸውን በሙሉ በነዋሪዎች ሁሉ ነው በይፋ የተናገሩት።
ዋናውን መንገድ እስከ መኖሪያ መንደር የሚያገናኝ አስፋልት መንገድ ለመገንባት ቃል ገብተዋል። የአውቶቡስ ማዞሪያ ተሰርቶ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚመቻችም ተናግረው ነበር።
የሕፃናት ማቆያ እንዲሁም የቅድመ መደበኛ ትምህርት መዋዕለ ሕፃናት እናዘጋጃለን። ለአንደኛና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ አዲስ የትምህርት ቤት ሕንጻ እንገነባለን ብለውም ቃል ገብተዋል።
የሥራ ዕድሎችን በስፋት ለመፍጠርም፣ የወፍጮ አገልግሎትን ጨምሮ የእንጀራና የዳቦ ፋብሪካዎችን እንገነባለን። የስራና ቦታዎችና ሱቆችን እናሟላለን ሲሉም ተናግረው ነበር።
የስፖርት ማዘውተሪያዎችንና መናፈሻዎችንም ሰርተን እናስረክባችኋለን በማለት በርካታ ዕቅዶችን በዝርዝር ለነዋሪዎች ገልጸው ነበር። ብዙ ነገር ለመሥራትና ለማሟላት ነው ቃል የገቡት።
ለዚያውም፣ “ወደፊት እንሰራዋለን፤ በሂደት እናሟላዋለን” አላሉም።
በሁለት ወር ውስጥ ገንብተን እናጠናቅቃለን፤ በሥርዓት አዘጋጅተን እናስረክባለን በማለት ነበር የቀን ቀጠሮ ለነዋሪዎች የሰጧቸው።
በደፈናው ሳይሆን፣ ዕቅዶችን በዝርዝር መግለጽና ቀን ቆርጦ ቃል መግባት አንድ ቁም ነገር ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘንድ እየተለመደ ቢሄድ ለአገር መልካም ነው።
ነገር ግን፣ ቃል የተገባው በተግባር ይፈጸማል ወይ የሚል ነው ዋናው ጥያቄ።
በተግባር ሥራው ቢጀመር እንኳ፣ በተያዘለት ጊዜ በፍጥነት ተገንብቶ ይጠናቀቃል ወይ?
ግንባታዎቹ በፍጥነት ተጀምረዋል። ነገር ግን፣ የግንባታ ሥራ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ቁፋሮውና ጥድፊያው ይታያል እንጂ፣ ወዲያውኑ ዓይን የሚገባ በግልጽ የሚታይ መልክ አይኖረውም። እንዲያውም ከሥራው ብዛት የተነሣ፣ ግንባታው የሚጠናቀቅ፣ ለውጤት የሚበቃ፣ አገልግሎት የሚጀምር፣ ለወግ ለማዕርግ የሚደርስ አይመስልም። “ይሄ ሁሉ ሥራ አንድ ላይ ተጀምሮ በጊዜ ያልቅ ይሆን?” የሚል ጥርጣሬ መፍጠሩ አይቀሬ ነው።
ደግሞም ከባድ ነው። በኃላፊነት ስሜት ካልበረቱ፣ ቃልን አክብረው የመተግበር፣ የታቀደውን የመፈጸም የዕለት ተዕለት ትጋትና ክትትል ካልታከለበት አይሳካም።
ቃል በተግባር ሲፈጸም አላየንም ማለት ግን አይደለም። በአዲስ አበባ፣ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ግንባታ ጀምሮ እስከ አንደኛው ዙር የኮሪደር ልማት ድረስ፣ በርካታ ፕሮጀክቶች ለውጤት በቅተዋል። ቃልን በተግባር የመፈጸም፣ የተጀመሩ ግንባታዎችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ጠንካራ የሥራ ባህል ሲፈጠር አይተናል።
ቢሆንም ግን፣ ወደፊትስ ይቀጥል ይሆን? እዚህኛው ፕሮጀክትስ ይሳካ ይሆን? ብለን መጠየቃችን አይቀርም።
በሁለት ወር ገንብተን ሁሉንም እናሟላለን የሚለው የከንቲባ አዳነች አበቤ የተስፋ ቃልም በዚሁ ዓይን ልናየው እንችላለን? ለገላን ጉራ ነዋሪዎች የገቡት ቃል በተግባር ይፈጸም ይሆን?
ጊዜው ደርሷል። ሁለት ወር ሞልቶታል - ቃል በተግባር።
እውነትም፣ ግንባታዎቹ በፍጥነት ተጠናቅቀዋል። አገልግሎት መጀመራቸውን ለማብሰርና ከነዋሪዎች ጋር ሆነው ፕሮጀክቶቹን ለማስመረቅ ከንቲባ አዳነች አበቤ ሰሞኑን በገላን ጉራ ተገኝተዋል።
የሕጻናት ማቆያ እንዲሁም የቅድመ መደበኛ ትምህርት መዋዕለ ሕጻናት ተገንብተው በቁሳቁስ ተሰናድተዋል።
የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አዲስ በተገነባ ባለ አምስት ፎቅ ሕንጻ ውስጥ ትምህርት ጀምረዋል - የትምህርት የደንብ ልብስ እንዲሁም የመማሪያ ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው።
ከዋናው መንገድ ጋር የመኖሪያ መንደሩን የሚያገናኝ 1.6 ኪሎ ሜትር አዲስ የአስፋልት መንገድም አስቸጋሪ ነው ተብሎ ቢገመትም፣ በፍጥነት ተገንብቶ ተጠናቅቋል
20 አውቶቡሶችን የሚያስተናግድ ማዞሪያ በሰፊው ተገንብቷል።
በርካታ ሱቆችና የስራ ቦታዎችም ለነዋሪዎች ተላልፈዋል።
የእንጀራ ማዘጋጃ ማዕከልም አመቺ አዳራሽ ተገንብቶለት፣ ደረጃቸውን በጠበቁ ቁሳቁሶች ተደራጅቶ ለአገልግሎት ተዘጋጅቷል። በሦስት ፈረቃ ለ270 እናቶች የሥራ ዕድልና የመተዳደሪያ ገቢ ያስገኝላቸዋል።
በቀን 60 ሺ ዳቦ ማምረት የሚችል የዳቦ ፋብሪካም ተከፍቷል።
ምርጥ ዳቦ እያመረትን ነው ይላል - ጥላሁን ደለለኝ። መጀመሪያ ላይ የነበሩብን የመሠረተ ልማት ችግሮች አሁን ተስተካክለው፣ ወደ ስራ ገብተናል ብሏል ጥላሁን።
ቦታው ሰፊ ስለሆነ፣ ሥራችንን ለማስፋፋት ማሽኖች ይጨመራሉ። በብዛት ገዝተው ለሚሸጡ ሰዎች ቅናሽ እናደርጋለን፤ የ10 ብር ዳቦ በ7 ብር እናስረክባቸዋለን፤ እኛም ግን ተጨማሪ የመሸጫና የማከፋፈያ ቦታዎችንም ለማዘጋጀትም እያሰብን ነው በማለት ዕቅዳቸውንና ተስፋቸውን ገልጾልናል - ጥላሁን።
ለ20 ሰዎች የሥራ እድል እንደከፈተላቸውና በሰዓት 5 ሺ ዳቦ የማምረት ዓቅም እንዳለው ጥላሁን ተናግሯል።
ወፍጮዎች ተተክለዋል - 50 ኩንታል ጤፍ ለመነሻ ተሰጥቶናል።
የእህልና የበርበሬ ወፍጮች አመቺ የስራ ቦታ ተገንብቶላቸው ተተክለዋል። የካዛንቺስ ነዋሪ እንደነበረና አሸዋ ሜዳ አካባቢ ወፍጮ ቤት ይሠራ እንደነበር የነገረን አደም መሐመድ፣ አሁን በገላን ጉራ የተተከለው ወፍጮ ቤት 10 ሆነን ሥራ ለመጀመር ተዘጋጅተናል ብሏል።
በራችንን አንኳኩቶ የመጣ ዕድል ነው፤ የእህል እና የበርበሬ ወፍጮዎች ተተክለው የኤሌክትሪክ መስመር ተዘርግቶላቸዋል፤ ለመነሻም 50 ኩንታል ጤፍ በመኪና አምጥተው አቅርበውልናል በማለት በአዲስ አበባ አስተዳደርንና ከንቲባ አዳነች አበቤን ያመሰግናል።
ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳይኖረን ሁሉንም ነገር እያሟሉልን ነው።
ሱቅ ለማግኘት ፈልጌ ነበር ያለችን ቤቴል ከበደ፣ የዕድል ጉዳይ ሆኖ እንዳሰብኩት አልሆነም፤ ፍትሐዊ እንዲሆን በዕጣ ነው የተደረገው ትላለች። አሁን የእንጀራ ማዘጋጃ ማዕከል ውስጥ ገብታለች። የሙከራ ሥራ አጠናቅቀው መደበኛ ምርት ለመጀመር እንደተዘጋጁም ገልጻልናለች።
“10 ሳንቲም አላወጣንበትም። በልማት ተነሺዎች ስለሆንን ሥራ የለንም። የሥራ ቦታው ተገንብቷል። ምጣዶችና የኤሌክትሪክ መስመር ተሟልተውልናል። የገቢ ምንጭና የስራ መነሻ ገንዘብ ስለሌለን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሥራ መነሻ ድጋፍም ሰጥቶናል” ትላለት - ቤቴል።
“ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳይኖረን፣ መጀመሪያ ለመሞከሪያ የሚሆን የተወሰነ ጤፍ ገብቶልናል። ከዚያም የሥራ መነሻ 50 ኩንታል ጤፍ ገብቶልናል” በማለትም ታመሰግናለች።
“ሰርተን እንለወጥ እያልን ነው። በርትተን ከሰራን... ወደፊት እንለወጣለን” በማለትም፣ የብርታታችንን ያህል ውጤት እናገኝበታለን ብለው እንደሚያስቡ ገልጻለች።
የተጋገረ እንጀራ፣ ገዢ እና ተመጋቢ አያጣም ለማለት ይሆን? ገበያ ያገኙ ይሆን? በእርግጥ ገበያው ሰፊ ነው።
ትምህርት ቤቶች በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ያቀርባሉ። ብዙ እንጀራ ይፈልጋሉ። በገላን ጉራ ለ500 አረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የምገባ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመውን አዲስ ማዕከልን ጨምሮ፣ በአዲስ አበባ በርካታ ተመሳሳይ ማዕከላት በየቀኑ እንጀራ የሚያቀርብላቸው ይፈልጋሉ። ፖሊስ ጣቢያዎችም እንዲሁ። ሆቴሎችም አሉ።
ገበያተኛው ብዙ እንደሆነ የገለጸችልን ቤቴል፣ “የአዲስ አበባ መስተዳድር የገበያ ትስስር እንደሚፈጥርልን በተደጋጋሚ ነግሮናል። አትጨነቁ… እናንተ አምርቱ እንጂ፣ እኛ የገበያ ትስስሩን እንፈጥራለን ብለውናል” ትላለች።
ከሩቅ የሚጣሩ ውብ የስፖርት ስፍራዎች
በጣም የሚያምሩ ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም ተሠርተዋል። የሕጻናት መጫወቻ ለብቻው አለ። የወላዶች መመልከቻ ስፍራ የተዘጋጀለት ነው። የእግር ኳስ ሜዳም በዙሪያው ምቹ የመመልከቻ ወንበሮች ተሟልተውለታል።
በአሸዋማ ቦታ እግር ኳስ ሲለማመዱ የነበሩ ታዳጊዎች፣ አሁን ደረጃውን የጠበቀ “አርቴፊሻል” ሜዳ አግኝተዋል። ለዚያው ሙያተኛ አሰልጣኝ ጭምር።
የእግር ኳስ አሠልጣኝ ሽዋንግዛው ጸጋዬ እንደሚለው ከሆነ፣ ሜዳው ለልጆች ጤንነት ተስማሚ ነው። ቢወድቁ የመላላጥ ጉዳት አይደርስባቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሜዳው በጥራት ስለተሰራ፣ የቴክኒክና የታክቲክ ስልጠናዎችን በተሟላ መንገድ ለመስጠት ያመቻል ብሏል - አሠልጣኝ ሽዋንግዛው።

Page 10 of 752