Administrator

Administrator

 “--ለአውጉስጢን ታላቅ ክብር ያለው ጥበብ ሃይማኖት ነው፤ የዕውቀቶች ኹሉ መዳረሻ ለሃይማኖት ማገልገል መቻል ነው፤ ፍልስፍና
ከተፈጥሮ ጋር የተናበበችና በምክንያት የምትመራ ስለኾነች ለክርስትና ሃይማኖት መልካም አገልጋይ መኾን ትችላለች፡፡--”

    መግቢያ
ቅኔ ከፍልስፍና ጋር ባለው ግንኙነት ዙሪያ የምናደርገውን ምርመራ በግሪክ ፈላስፎች ዙሪያ ተሽከርክረን፣ ባለፈው ሣምንት የአርስቶትልን ክርከር ዐይተን ነበር ያቆምነው፤ ለዛሬው የቅዱስ አውጉስጢን (St. Augustine) ዕይታ እንቃኛለን፡፡
ቅ. አውጉስጢን የተወለደውና የተማረው በሰሜን አፍሪቃ ነው፤ የኖረበት ዘመን እ.ኤ.አ ከ354- 430 ዓ.ም ነው፡፡ ክርስቲያን ሳይኾን በፊት በሚላን እና በካርቴጅ አስተማሪ እና የት/ቤቶቹ ቀዳሚ ሊቀመንበር ነበር፤ ክርስትናን ከተቀበለ በኋላ ግን ወደ ሰሜን አፍሪቃ ተመልሶ የመኖኮሳት ማኅበርን መሠረተ፡፡ ከዚያም ክህነት ተቀብሎ በሂጶ ጳጳስ ኾነ፡፡ ቅ. አውጉስጢን በተለየ የሚታወቅበት ሥራው የእግዚአብሔር መናገሻ (The City of God) በሚለው መጽሐፉ ነው፡፡
ሊቁ አውጉስጢን ቀድሞ ባለቅኔ ነበር፤ እንዳውም በቅኔው ተወዳድሮ በማሸነፍ እሰከ መሸለም ደርሶ እነደነበር ይነገራል፤ ኋላ ግን ክርስቲያን ሲኾን ያ ኹሉ መውደስ ለባዕድ አምልኮ የሚቀርብ መኾኑን ተረዳ። ስለዚህ ቅኔን ገሸሽ በማድረግ ወደ ማራከስ ዞረ፤ ፍልስፍናንም የክርስትና ሃይማኖት ገረድ አድርጎ በመቅጠር፣ የፕሌቶ የቅኔና የፍልስፍና ንትርክን ቀይሮ፣ በቅኔና በሃይማኖት መካከል የሚደረግ ‹የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ›  ፉክክር አድርጎ ሞገተ፡፡
በአውጉስጢን ላይ ተፅእኖ ያሳደሩ ሦስት ሰዎች አሉ፡- ፕሌቶ፣ ፕሎጢኑስ (Plotinus) እና ማርቆስ ቫሮ (Marcus Varro) ናቸው፡፡ ፕሌቶ ቅኔን በቅጅ ቅጅነትና በተረትነት በመፈረጁ ‹አደገኛ› የሚል ‹ታፔላ› ለጥፎቦታል፤ አውጉስጢንም እንደ ፕሌቶ ቀድሞ የባዕድ አምልኮን አወዳሽ ባለቅኔ ስለነበር፤ ክርስቲያን ከኾነ በኋላ ቅኔን በማንከዋሰስ ከፕሌቶ ጋር ተስማማ፤ በዚህ የተነሣም የፕሌቶ አወዳሽ ለመኾን በቃ፡፡ የThe City of God የሚለው መጽሐፉ የመጀመሪያ ክፍልም ለፕሌቶ ውደሳ ያሽጎደጎደበት ነው፡፡ አውጉስጢን ለፕሌቶ ውዳሴውን በማሽጎድጎድ የቸረው ቅኔን በቅጅ ቅጅነትና በተረትነት አወራርዶ ስላቃለለ እና በአደጋነት ስለፈረጀ ነው፡፡
ሌላው የፕሌቶ አስተምህሮ ፕላቶናዊያንን አስገኝቷል፤ አውጉስጢን ወደ ክርስትና ሲቀየር ሰብዕናውንና አስተሳሰቡን የቀየሩትና ተጽዕኖ ያደረጉበት እነዚህ ፕላቶኒያውያን ሲኾኑ በተለይ ፕሎጢኑስ እና ቫሮ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። የእነዚህ ሐሳቢያን ተፅእኖም በአውጉስጢን የፈጠራና የአስተውሎት ችሎታ እየተሽከረከረ ወደ የቅኔ እና የሃይማኖት ፉክክር አድርሶታል፡፡
የፕሎጢኑስ ተፅእኖ
አውጉስጢን መጀመሪያ ከክርስትና ጋር ሲገናኝ ‹በመጀመሪያ ቃል ነበር፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፤ ቃልም እግዚአብሔር ነው› የሚለው የዮሐንስ ወንጌል ጥቅስ፣ በፕሎጢኑስና በደቀ መዝሙሩ ፖርፊሪ (Porphyry) እየተተረጎመ ተብራርቶ አገኘው። ቃል ደግሞ በፅርዕ (በግሪክ) ሎጎስ ስለሚባል የቃልም ትርጉም አመክንዮ (ምክንያተ ነገር) ማለት መኾኑን ተረዳ፤ የምክንያት ትስስርም ከቅኔ የበለጠ ከሰማያዊ ፍልስፍና ጋር እንደኾነ በማየትም በምክንያት ለምትመራው ፍልስፍና የበለጠ ክብር ሰጠ፡፡
ፕሎጢኑስ የፈላስፎችና የባለቅኔዎች ሥራ በከፍተኛው የማሰላሰል ደረጃ ላይ ሊገናኝ (ሊገጣጠም) ይችላል ይላል፤ ልዩነቱን የሚፈጥረው ማሰላሰልን በዕውቀት (በሥልጠና) የመደገፍ ኹኔታ ስለኾነ ለባለቅኔዎች፣ ለሙዚቀኞችና ለሌሎች የአርት ሰዎች ፊት ለፊት ከሚታየው ክስተት ባለፈ ያለውን መስተጋብር እንዲያስተውሉ፤ እዚያ ማዶ (ከአካባቢያቸው ባለፈ) ያለውን ራዕይ እንዲይዙ ይመክራል፡፡
ስለ ተረት በጥልቅ አስተውሎቱ ፕሌቶን ራሱ ‹የተረት ጸሐፊ ነው› ብሎ ይሞግታል፡- ፕሎጢኑስ፤ ይህ የፕሌቶ ተረትም በማስደነቅ ምሥጢር ይዞ የየትኛውንም አስተሳሰብ ጥልቀትና ስፋት ለመመርመር መነሻ ይኾናል፤ ይህንንም ማወቅና መረዳት የምንችለው ዘይቤያዊ ስልቶችን (በማመሳሰል፣ በማነጻጸር፣ በመወከል፣…) በመጠቀም መኾኑን ሞግቷል፡፡
ፍልስፍናዊ አሰላስሎትም ባለቅኔውን የቅኔን የተፈጥሮ ገላጭነትና ተፈጥሮ የምትፈልገውን መያዝ እንዳለበት እንዲገነዘብ ያደርገዋል ይለናል። ስለዚህ  ቅኔ (አርት) እንደ ፕሌቶ ተፈጥሮን አስመስሎ መቅዳት ብቻ ሳይኾን ከተፈጥሮ ምንጭ ፈልቆ መፍሰስም በመኾኑ፣ ቅኔ ራሱ የህልው (እውን) ነገር ተፈጥሮን መረዳት እስከቻልነው ድረስ መግለጫና መመርመሪያ ጥበብ መኾኑን ሞግቷል፡፡ በሙግቱም ተፈጥሮ በከፍተኛው ደረጃ እውን ነገርን እንድንረዳ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ፍሰቱን ጠብቃ እንደኾነው፤ የአርትን (የቅኔን) ምንነትም በተመሳሳይ መልኩ መረዳት ይገባናል ይላል፡፡
ለፕሎጢኑስ  እውነት በቁስ አካል፣ በነፍስ፣ በአእምሮና በአሐድነት ላይ ያርፋል፤ በዚህም የምትገኝ እውነትም ከመልካምነት ጋር የተዋሐደች ናት፡፡ አሐድነት የኹሉም ምንነት መሠረት ነው፤ አእምሮ ደግሞ የመኾን ኑባሬ እውንነት ነው፡፡ ነፍስም በኹለት ትከፈላለች፡- የዓለም (የኹሉም) ነፍስ  እና የግለሰቦች (ዝርዝር) ነፍስ በሚል፤ እሷም የአካላችን (የሥጋችን) አንቀሳቃሽ ኃይል ናት፤ አካላችን ደግሞ የቁስ አካል ሥሪት ነው፤ ቁስ አካልም ከኹሉም ሥር የሚገኝ ያዥ (ንጣፍ) ነው በማለት ይተነትናል፡፡
በዚያም ላይ ‹እሺ የሕይወት ከፍታው ምንድን ነው?› ብሎ ይጠይቅና  መልሱን ‹አእምሮ› በማለት ይሰጣል፤ አእምሮ እኛን ወደፊት የሚገፋፋንን (የሚያንቀሳቅሰንን) የሰዎችን ነፍስ ጠባያትና የእግዚአብሔርን ሕሊና ጠባያት አዋሕዶ መያዙን ይሞግታል፤ ስለኾነም በከፍተኛ ሕይወት የሚገኝ ትልቁ ሥጦታ የሶቅራጥስ እሰጥ አገባ ነው ይለናል። በዚህ ሥጦታ ነፍስ ኹሉንም ነገር ትመረምራለች፣ ሕሊናም ከአድማሱ ወዲያ ያለውን ኑባሬ ሳይቀር ጠልቆ ያያል፤ ከኹሉም ግን ምርጡ የፍልስፍና ክፍል የእሰጥ አገባ ስልት ነው ይለናል፡- ፕሎጢኑስ።
‹እንዴት ግን በዚህ መልክ ጥልቅ የኾነውን የከፍታ ዕውቀት ገንዘብ ማድረግ ይቻላል?› ሲባል፤ መልሱ በዘይቤ ወይም በምሳሌ ስልት አእምሯችን እየተምዘገዘገ፣ የምሥጢረ ፍጥረትንና የግብረ-ገብን ከፍታን መጥቆና ሰርጎ በመግባት የኑባሬ ምሥጢር፣ የጥልቀት መዳረሻ፣ የንፅሕና ጥግ፣ የኹሉም ነገር መሠረት፣… የኾነውን ነገር መመርመር/መፈተሽ ይችላል ይለናል፡፡  
ደረጃ አውጥቶ ሲያስቀምጥም፤ የከፍታውን ጫፍ መልካምነት አድርጎ ዝቃጩን ሥፍራ ደግሞ ቁስ አካል ያደርገዋል፤ መልካምነት ከመጠበብም የሚበልጥና የኹሉም ነገር ከፍታ ነው ይላል። የፍልስፍና እና የቅኔ መደነቅም ከቁስ አካል ጋር ተያይዞ ከሚገኝ ውበት ጋር ከኾነ ይጠፋል፤ በመልካምነት ተውህቦ ከኾነ ግን ይዘልቃል የሚል ክርክር ነበረው፡- ከታች ወደ መልካምነት ጫፍ ሲያወጣ፡፡ ስለኾነም ቅኔ ከተውህቦ፣ ከዜማና ከጥበብ ንድፍ ይጀምራል፤ ይኽም ቅኔ ከዝቅተኛው ወደ ከፍተኛው ዕይታ መምጠቅ እንዳለበት ይከራከራል፡፡ በአጠቃላይ ግን የፕሎጢኑስ ትልቁ ተፅእኖው፤ አውጉስጢን ወደ ክርስትና እንዲመለስና ፍልስፍናን የሃይማኖት ገረድ ለማድረግ ማስቻሉ ነው፡፡
ማርቆስ ቫሮ
የፕሌቶ ተፅእኖ ብቻ ሳይኾን ቫሮም ያደረገው የአማልክት ምደባም ለአውጉስጢን ትልቅ ግብዓት ኾኖታል፡፡ ቫሮ የሚታወቀው አማልክትን በየግብራቸው መሠረት በመከፋፈል ነው፤ በዚህም 20 (12 ወንዶች እና 8 ሴቶች) አማልክትን ለይቶ አቅርቧል። እነዚህን አማልክትም በሦስት ምደባዎች ጠቅልሎ አስቀምጧቸዋል፡- የሥነ-ተረት፣ የሲቪልና የተፈጥሮ አማልክት በሚል፡፡ የሥነ ተረት አማልክት ከባለቅኔዎች ሥራ ጋር ሲያያዙ፣ የሲቪል ደግሞ ከከተማ ሕዝብ ተግባራት ጋር የተያያዙ ናቸው፤ በሰው ሠራሽ ድርጊቶች (ለምሳሌ በትያትር) ይገለጻሉ፤ የተፈጥሮ አማልክት ደግሞ ከፈላስፎች ተግባራት ጋር የተቆራኙ ሲኾኑ በተፈጥሮ ጠባይ የሚገለጹ ናቸው በሚል ተከራክሯል፡፡
የሰው ሠራሽ ነገሮች የሚገለጹት በአርት ሥራ ሲኾን ከእውነት በጣም የራቁ ወይም ሐሰተኞች ናቸው፤ ቀጥታ ከተፈጥሮ ጋር የሚገናኙት ግን ለእውነትነት በጣም የቀረቡ ናቸው ይላል፡፡ ሰው ደግሞ ከሐሰት ይልቅ እውነትን መምረጥ ስላለበት የተፈጥሮን ጥበብ የሚያጠናው ፍልስፍና ከቅኔ የበለጠ ክብር ሊሠጠው ይገባል ይለናል፤ ስለዚህ በተረትነት ከተፈረጀው ከቅኔ ይልቅ ከተፈጥሮ የሚቀዳው ፍልስፍና የተሻለ እውነት ያለው ነው፡- ለአውጉስጢን፡፡  
ኾኖም አውጉስጢን ቅኔ ስለ አማልክት ተረት በጥልቀት የሚያወራ የሐሳብ ቤት በመኾኑ ይስማማል፤ ግን ደግሞ ሐሰተኛ አማልክትን እንጂ እውነተኛ አምላክን አይገልጽም ባይ ነው፡፡ የዚህን ምክንያት አውጉስጢን ሲገልጽ፤ ቅኔ የሚያቀነቅነው የምድራዊና ሰው ሠራሽ አማልክትን ተግባራት ስለኾነ እና ባለቅኔዎች የሚቀኙት በጋኔን መንፈስ እየተመሩ ስለኾነ፣ ከእውነተኛው አምላክ ጋር አይገናኙም፡፡ ለአውጉስጢን ከተፈጥሮ አማልክት ጋር ስለሚገናኝ ፍልስፍና ለእውነት ከሌሎች የበለጠ ቅርብ ነው፤ አንዱን አምላክ ከሌላው ለመለየትም ትልቅ ሚና ይጫወታል፤ ምድራዊ አማልክቱ ግን እርስ በራሳቸው ስለማይስማሙ ምድራዊ ፍልስፍና እውነተኛውን አምላክ ለማወቅ አያስችልም፤ ትክክለኛው አምላክ የመጨረሻው እውነት መኾን አለበት፤ ይህም የተገለጸው በክርስትና ሃይማኖት ነው ይላል፤ ለእሱ ክርስቲያን የሰማያዊት ከተማ ባለርስት ነው፡፡
የምድራዊ ከተማ ለሐሰተኛ አማልክት ሲያገለግል፣ ሰማያዊ ከተማ ደግሞ የእውነተኛው አምላክ መገለጫ ነው፤ ሐሰተኛ አምላክ በባለቅኔዎች ሲገለጽ እውነተኛው ደግሞ በነቢያት ይገለጻል። የምድራዊ ፈላስፎች ለባለቅኔዎች ምላሽ ሲሰጡ የክርስትና ፈላስፎች ደግሞ ለነቢያት ትንቢት መልስ ይሰጣሉ፤ የምድራዊ ከተማ ፍልስፍናንም ይገነዘባሉ፤ ምክንያቱም እውነተኛው እግዚአብሔር የሚናገረው በነቢያት ነውና ብሎ ሞግቷል፡፡ እውነተኛው አምላክም ኹሉንም ነገር የሠራ፣ የእውነት ገላጭና ደስታን ሰጪ (አዳይ) ስለኾነ ‹እውነተኛ ፈላስፋ የእግዚአብሔር አፍቃሪ ነው› የሚል ክርክር አቅርቧል፡፡ ኾኖም እውነተኛው አምላክም ለዓለሙ የተገለጸው በፈላስፎች፣ በባለቅኔዎች ወይም በሲቪል ሰዎች ሳይኾን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡
በአጠቃላይ
ለአውጉስጢን ታላቅ ክብር ያለው ጥበብ ሃይማኖት ነው፤ የዕውቀቶች ኹሉ መዳረሻ ለሃይማኖት ማገልገል መቻል ነው፤ ፍልስፍና ከተፈጥሮ ጋር የተናበበችና በምክንያት የምትመራ ስለኾነች ለክርስትና ሃይማኖት መልካም አገልጋይ መኾን ትችላለች፡፡ የሥነ ተረት ሥነ መለኮት ግን የባለቅኔዎች የባዕድ አምልኮ ማቀንቀኛ ስለኾነ ከክርስትና ሃይማኖት ጋር አይስማማም፤ ይህም የቅኔን ፉክክር እንደ ፕሌቶ ከፍልስፍና ጋር ሳይኾን ከሃይማኖት ጋር በማድረግ የክርክሩን ዓይነት ቀይሮታል፡፡ አውጉስጢን በዚህ በሥነ-ተረት አስተሳሰቡ በተለይ ከአርስቶትል ጋር አይስማማም፤ ምክንያቱም አርስቶትል ቅኔን በተረትነት አይነቅፍም፤ የተረትን አስፈላጊነትም ይሞግታል። በአጠቃላይ ግን አውጉስጢን ቅኔን ለጣኦት መወድስ የምታወረድ፣ ፍልስፍናንም የሃይማኖት ገረድ አድርጎ ተከራክሯል።
ፍልስፍናም የሥነ መለኮት ዕውቀት አገልጋይ በመሆኗ፣ ቅኔን ከፍልስፍና መለየት/አለመየቱ ዋና ጉዳይ መኾን የለበትም፤ ይልቁንስ ቅኔ የሥነ ተረት መተረኪያ ስለኾነ፣ በውስጡ ያለው የቋንቋ ስህተት ብቻ ሳይኾን የጋኔን (የሠይጣን) መነጋገሪያ ቋንቋ መሆኑም ዋናው ችግር ነው፤ ይኽም ማለት ቅኔ የሥነ ተረት እምነት (አማልክት) መተረኪያ ነው፡፡
 እሱ እንዳለው ከኾነ፡-
የተፈጥሮ ፈላስፎች ሕዝብን ለመጥቀም ይጽፋሉ፤ ባለ ቅኔዎች ደግሞ ሕዝቡን ለማስደሰት ይቀኛሉ፤ ስለዚኽ የባለቅኔዎቹ ትረካዎች ሕዝቦቹና አማልክቱ የሚደሰቱባቸው የእግዚአብሔር ወገን የኾኑ ሰዎች ሊከተሏቸው የማይገቡ የአማልክቱ ወንጀሎች መኾን አለባቸው፡፡ ስለዚኽ ባለቅኔዎች ከማስደሰት ያለፈ ጥቅም የላቸውም፤ የአማልክቱን ትክክልነት ለመተረትና ለሕዝቡ ክብር ለማስገኘት ይጽፋሉና፡፡
በመኾኑም ለአውጉስጢን ቅኔ መጻፍ እጅግ ዝቅተኛ ጠቀሜታ ሲኖረው፣ ለሃይማኖት የሚጠቅም ፍልስፍና መጻፍ ደግሞ በተቃራኒው ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፤ ምክንያቱም ፍልስፍና የሥነ መለኮት ዕውቀት መገልገያ በመኾን ከፍተኛ አገልግሎት ይሠጣልና፤ ቅኔን ግን የአምልኮተ ጣዖት (የባዕድ አምልኮ) ማቀንቀኛ የተረት አካል በማድረግ ይደመድማል፡፡ በመሆኑም ለአውጉስጢን በቅኔና በፍልስፍና መካከል ያለው አለመጣጣም ከፍተኛ ነው፤ በተለይም ፍልስፍና የሃይማኖት አገልጋይ በመኾኗ ፉክክሩን በቅኔና በሃይማኖት መካከል አድርጎ ያጦዘዋል፤ ከእነ ፕሌቶ የሚለየውም የፍልስፍናን ለሥነ መለኮት መመርመሪያ መኾን በማግዘፍ ወይም ለሃይማኖት ከኹሉም የበለጠ ቦታ በማቀዳጀት ነው፡፡

 በአንድ አገር በአንዲት መንደር ውስጥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰዓሊ ነበር፡፡
በመንደሩ ውስጥ አንድ ሐይቅ አለ፡፡ ሐይቁ ሰዓሊው ከሚኖርበት ቤት ጥቂት ራቅ ይላል፡፡
ያ ሰዓሊ ታላላቅ የተባሉ ስዕሎችን ይሰራና ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይልካል፡፡ በዚህም ታላቅ ስምና ዝናን ያተርፋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የእሱ መንደር ሰው ስለሱ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። እሱ ከማንም አይገጥምም፡፡ ቤቱ ስቱዲዮው ነው፡፡ ከቤቱ ከወጣ ወደ ሐይቁ ሄዶ ቁጭ ብሎ ተፈጥሮን ሲያደንቅ ይውላል፡፡
በዚህ ዓይነት ህይወቱን ሲገፋ ኖሮ፣ አንድ ቀን ታመመ፡፡ ብዙ ማቅቆ ማቅቆ ሞተ፡፡
የዓለም የዜና ማሰራጫ አውታሮች በጠቅላላ የሚያወሩት ስለዚያ ታላቅ ሰዓሊ ሆነ፡፡ የማታ ማታ የመንደሩ ሰው፤ የአገሩ ታላቅ ሰዓሊ መሆኑንና በዓለም ላይ ስመ ጥር ሰው መሆኑን አወቀ፡፡ ስለዚህ በስሙ አንድ ማስታወሻ ማቆም ያስፈልገናል ተባለና መመካከር ጀመሩ፡፡
አንደኛው - ይህ ታላቅ ሰዓሊ ጠባዩ ምን መሳይ ነበረ? በትክክል ገፅታውን ያስተዋለ ሰው አለ?
ሁለተኛው - አመለካከቱስ? ፍልስፍናውስ? ትምህርቱስ ምንድን ነበር?
ሦስተኛው - ይሄንን ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም ማንም አናግሮት የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ስዕሉን እንኳን ዓይተንለት አናውቅም፡፡ ስለዚህ ማንን ጠይቀን መረጃ እናግኝ?
አንደኛው - ማንንም ልንጠይቅ አንችልም፡፡ የሚሻለው ሁልጊዜ ይሄድበት የነበረውን ሐይቅ ሄደን መጠየቅ ነው፡፡
ሁሉም ወደ ሐይቁ ሄዱ፡፡ ከዚያም፤
“ሐይቅ ሆይ! ታላቁ ሰዓሊያችን አርፏል፡፡ እኛ አንድ መታሰቢያ ልናቆምለት አስበናል፡፡ ሆኖም መልኩን እንኳን በቅጡ ማስታወስ የሚችል ሰው ጠፋ፡፡ ስለዚህ ያ ሰዓሊ ምን መሳይ እንደነበር እንድትነግረን ነው ወደ አንተ የመጣነው!”
ሐይቁዉም፤
“አመጣጣችሁ መልካም ነው፡፡ ሆኖም ብዙ የምረዳችሁ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም እናንተ፤ ሰውን በህይወቱ እያለ ከማክበር ይልቅ ሲሞት ክብር የምትሰጡ ሰዎች ናችሁ፡፡ እኔም ብሆን በመጣ ቁጥር ዐይን ዐይኑን ሳይ ነው የከረምኩት፡፡ ስለዚህ ዐይኑ ብርሃን እንዳለው ብቻ ነው የማውቀው፡፡”
*   *   *
ብርሃናማ ሰዎቻችንን ለማወቅ የውጪ ሰው እስኪነግረን አንጠብቅ፡፡ እኛው ብርሃናማ ሰዎቻችንን እንወቅ፡፡ ከየትኛውም ጠባብነት፣ ከየትኛውም ትምክህተኝነት እንለያይ፡፡ የምስራቅንና ምዕራብ ጀርመንን ይከፍል የነበረው “ታላቁ” ግምብ፤ ዛሬም ጀርመናውያን አዕምሮ ውስጥ አለ ይባላል፡፡ ግምብን በአካል ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አገርን የሚያድነው፤ አንድያውን ከአዕምሮ መሰረዝ ነው! ምናልባትም ሥር ነቀል ለውጥ (Radical Transformation) የሚመጣው አላስፈላጊ ጉዳዮችን ከናካቴው ከዕሳቤ በመገላገል ነው! አለበለዚያ “እንደቀንድ - አውጣ ሰንኮፈን፣ እንጭጭ ህሊና ያወጡ” እንዳለው ሎሬት ፀጋዬ፤ በየጊዜው እንጭጭ ህሊና መቀፍቀፍ ይሆናል ዕጣ-ፈንታችን፡፡ ይህን ልብ እንበል፡፡
ሌላው ጉዳያችን፤ ልዩነት ለዘለዓለም ይኑር (viva la difference!) የሚለውን ከልብ መቀበል ነው፡፡ ሆኖም ልዩነት ያለ ጥንቃቄና ያለ ዕውቀት ኪሳራ ነው፡፡ አምላክ አንድ ያደረጋቸውን መለያየት አይቻልም እንደሚባል ሁሉ፤ የለያያቸውንም ማዋሃድ አይቻልም፤ ማለትም ያስኬዳል፡፡ በሁለቱም አባባሎች ውስጥ የኃይል እርምጃ (Coercive measure) እንዳይኖር መጠንቀቅ ነው ዋናው፡፡ የጠረጴዛ ውይይት የሚፈታውን ችግር ጦር ሰብቆ፣ ዘገር ነቅንቆ ካልሆነ፣ አይሆንም ማለት ከግብዝነት የማይተናነስ ጀብደኝነት ነው፡፡ በአንፃሩ በምንም ዓይነት ዘይትና ውሃ መሆኑ የታወቀን ነገር፣ በንግግር ካልፈታሁ ማለት፤
“Poet! Don’t go far a word
When what you all need is a sword
Bile, not the veil, in the war field!”
(“አንት ባለቅኔ ሆይ!
እጦር ሜዳ ገብቶ ጎራዴ ለሚሻው
መፍትሔው ወኔ ነው፣ ቅኔ አይደለም ቋንቋው!
ሀሞትህ ነው እንጂ የሙሽራ ልብስህ
ከባሩድ መካከል፣ ከቶም አያድንህ!”
… እንደማለት ነው፡፡ ሁሉም ነገር አግባብ ባለው ቦታና ሰዓት መደረግ አለበት፡፡ የሹመትና ሥልጣን ሽግግር፤ የለውጥ ዝግጁነትን የሚያስከትል ከሆነ ብቻ ነው፤ ለውጥ የሚገኘው፤ ስለሆነም አመለካከትን መለወጥ ላይ መሰራት አለበት!
ገጣሚው፡-
“በቀን ሦስት ጊዜ እንበላለን ብለን
አንዱም ባንዴ አቃተን!”
እንዳለው እንዳይሆንብን፤ በምግብ ራስን ለመቻል መትጋት ተቀዳሚ መሆን አለበት፡፡ ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልንም መቼም ቢሆን አንዘንጋ!
ሥልጣን የሁልጊዜ ይዞታ አይደለም፡፡ ርስተ - ጉልትም አይደለም፡፡ ወሳኙ ነገር ከህዝብ ጋር እየመከሩ፣ ዘለቄታው ምን ይሁን? የሚረከበንን እንዴት እንምረጥ? እንዴት እንቅረፅ? እኔ እንዴት እዘልቃለሁ ሳይሆን አገር እንዴት ትዘልቃለች? ከትላንት የተሻለች ኢትዮጵያን እንዴት እናምጣት? ማለት ያባት ነው! ምንጣፉን ከእግራችን ሥር የሚጎትቱ ባላንጦች እንዳሉ አንርሳ! ማደግ የሚቻለው የዕድገት ግብአቶችን በትክክል፣ በትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ሰዓት በመጠቀም ነው፡፡ የዚህ ሁሉ መጎናፀፊያው፤ ዕውቀትንና መረጃን መሰረት በማድረግ፣ ዘላቂነትን፤ ረዥም ዕድሜን፤ ከዘለዓለማዊነት ባለማምታታት ነው፡፡
(Not mistaking longevity for eternity)
ዋና ጉዳይ፤ “ሥልጣን ዘለዓለማዊ ቢሆን ኖሮ አንተ ጋ አይደርስም ነበር!” የሚለው የአረቦች ተረት ትርጉም የሚኖረው እዚህ ላይ ነው! ልብና ልቦና ይስጠን!


          “--አካልን በሚጨቁነው በዚህ ሥልጣኔ ውስጥ ይበልጥ ተጎጅዎች ደግሞ በተፈጥሮ ከአካል ጋር ጥብቅ የሆነ ሥነ
ልቦናዊና ስሜታዊ ትስስር ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ አካልና ስሜትን የሚጨቁን ሥልጣኔ፣ ‹‹የስሜት ምንጭ ናቸው›› ብሎ
የሚፈርጃቸውን ሴቶች የመጨቆኑ ነገር አይቀሬ ነው፡፡ በዚህም ሴቶች ለዘመናት ቂም ይዘው ኖረዋል፡፡--”

           መንፈሳዊነትን በማወደስ ከጥንት ጀምሮ እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ እስኪ ዛሬ ደግሞ የመንፈሳዊነት ሌላኛውን ገፅታ እናንሳ፤ መንፈሳዊነት በተሞገሰ ቁጥር ስለሚንኳሰሰው የሰው ልጅ ‹‹አካል›› እናውራ፡፡ በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ ውስጥ በባህል፣ በሥነምግባር፣ በኪነ ጥበብ፣ በምሁርነትና በመንፈሳዊነት ስም ‹‹አካል›› ላይ ስለሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጥቃት እናነሳለን።
ይሄንን ፅሁፍ በማዘጋጅበት ወቅት አንድ ልብን በጣም የሚያራራ (በያሬድ ‹‹አራራይ›› ዜማ የተሰራ) መዝሙር ከርቀት ይሰማኛል፡፡ መዝሙሩ ‹‹ከንቱ ነኝ! የከንቱ ከንቱ ነኝ!!›› ይላል፡፡ በዚህ አምስት ቃላትን በያዘ አንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ‹‹ከንቱ›› የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ ተደጋግሟል፡፡ በመቶኛ ስናሰላው 60 ፐርሰንት መሆኑ ነው፡፡ ‹‹ከንቱ›› የሚለው ቃል በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ እንደዚህ ታጭቆ ጥቅም ላይ የዋለው ደግሞ ዓለማዊ ህይወትን ለማንቋሸሽና አካልን (የለበስነውን ሥጋ) ለማውገዝ ነው፡፡
በሰው ልጅ ሥልጣኔ ውስጥ ለዘመናት የሰውን ልጅ መከራና ሸክም ከተሸከሙ እንስሳት ውስጥ ዋነኛዋ አህያ ናት፡፡ የሰው ልጅ የሥራ መሳሪያዎቹን ማሻሻል አቅቶት በደነቆረበት ዘመናት ሁሉ የእሱን ድንቁርና የተሸከመችለት አህያ ናት፡፡ አህያ የሰውን ልጅ ድንቁርናውን ብቻ አይደለም የተሸከመችለት፣ ይልቅስ ከድንቁርናው የሚመነጨውን ጭካኔውን ጭምር እንጂ። ድንቁርና ላይ የተመሰረተ ጭካኔ ደግሞ አረመኔነቱ መኖርን ሁሉ ያስመርራል፡፡ አህያ ይሄንን ሁሉ የሰውን ልጅ ዕዳ ተሸክማ ኖራለች፡፡
ከአህያ በላይ የሰውን ልጅ ጭካኔ የተሸከመ አንድ ነገር አለ - እሱም አካል ነው፤ የለበስነው ሥጋ!! አህያ የሰውን ልጅ ጭካኔ ብትሸከም ሳሯን ግጣ፣ ውሃዋን ጠጥታ ነው፡፡ ከስድብ ጋር ዱላ ቢያርፍባት ዱላው እንጂ ስድቡ አይሰማትም፡፡ አካል ግን የእነዚህ ሁሉ ተጠቂ ነው፡፡ ‹‹አካል የመንፈሳዊ ህይወት ፀር ነው›› እየተባለ በርሃብ እንዲጠወልግ፣ በውሃ ጥም እንዲንገበገብ፣ በፍትወት እንዲቃጠል፣ በስድብ እንዲዋረድ ይደረጋል፤ ‹‹ከንቱ ነህ፣ የከንቱ ከንቱ ነህ!!›› ይባላል፡፡
‹‹ከመንፈሳውያኑ አንዱ…›› ይላሉ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌም፤ ‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስ›› በተባለው መፅሐፋቸው ውስጥ በገፅ 33፣
ከመንፈሳውያኑ አንዱ ስለ ፅድቅ የውሃ ጥም ሲያቃጥለው በፅዋ ቀዝቃዛ ውሃ ይሞላና ከፊቱ ያስቀምጣል፤ አእምሮቱ ይባሱኑ ያቃጥለዋል። “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ቢሉት፣ “ዋጋዬ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲበዛልኝ በስቃዬ ላይ ስቃይ መጨመሬ ነው፤” አላቸው፡፡

“ነፍሳችን እንድትድን ሥጋችንን እንጣላት”
የመንፈሳዊነት ማግኛ መንገዳችን በጣም አስገራሚ ነው፡፡ ግብፃዊው አባ እንጦንስ፤ መንፈሳዊ ህይወት የቆመበትን ዋነኛ ምሰሶ ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ፡-
‹‹ከልብ ስንራብ፣ ስንጠማ፣ ስንራቆት፣ ስናዝን፣ በጣር ላይ ስንሆን ለእግዚአብሔር የተገባን እንሆናለን። እግዚአብሔርን እንድናገኘው ሐዘንን እናስቀድማት፣ ነፍሳችን እንድትድን ሥጋችንን እንጣላት፡፡››
በዚህ ሥልጣኔ ውስጥ ‹‹መንፈሳዊነት ያለ አካላዊ ስቃይ አይገኝም›› የሚል ቅቡል የሆነ አስተሳሰብ አለ፡፡ እውነት ታዋቂ የሚሆነው፣ እሴት የሚገኘው፣ መንፈሳዊነት የሚዳብረው በአካላዊ ስቃይ እንደሆነ ሁሉም ተቀብለውታል፡፡ በዚህም አካላዊ ስቃይ ማህበረሰብንና መንፈሳዊ ተቋማትን የማደራጃ መርህ ሆኗል፡፡ ባህል፣ ሥነምግባርና መንፈሳዊነት አካልን በማሰቃየት የሚገኙ ነገሮች ሆነዋል፡፡  
አካል ላይ የሚወርደው ይህ ጭካኔ፣ ውግዘትና ውርደት ደግሞ በረጅሙ የሁዳዴ ፆም ላይ ጠንከር ይላል። ሁዳዴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አካልን የሚያወግዙበት ወር ነው፡፡ አካልን ለማዋረድና ለማዳከም የቀን መቁጠሪያ ላይ ቀጠሮ ይያዝለታል። ምስኪን አካል!!
በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ከዘርዓያዕቆብና ከወልደ ህይወት ሌላ ለአካል ጠበቃ የቆመ አንድም ኢትዮጵያዊ ምሁር እስከ ዛሬ ድረስ አለማግኘታችን ነው። ዘርዓያዕቆብ ለአካል ጠበቃ ሆኖ መገኘቱ ለኢትዮጵያ ፍልስፍና መነሻ ሆኗል፡፡
በጥንት ግሪካውያን ፍልስፍና የተጀመረው እግዜርን ልክ እንደ ሰው አድርጎ የሚያስተምረውን የነሆሜርን ተረት በመቃወም ነው። በኢትዮጵያ ፍልስፍና የተጀመረው ደግሞ በመንፈሳዊነት ስም አካል ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም ነው። ይሄንንም ጥቃት ለመከላከል በነዘርዓያዕቆብ በኩል የቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ፤ የነፍስንና የሥጋን ቅራኔ መፍታት ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ፍልስፍና ይሄንን ቅራኔ የማስታረቅ ፕሮጀክት ነው።
መንፈሳዊ ተቋማት አካል ላይ ብዙ ዓይነት ጥቃት ቢያደርሱም ለአካል ጥብቅና የሚቆም ግን አንድም ተቋም የለም፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አካልን ከሌላ ወገን ከሚመጣ አካላዊ ጥቃት የሚከላከሉ ተቋማት ቢሆኑም፣ በመንፈሳዊ ተቋማት በኩል ለሚመጣ አካላዊ ጥቃት ግን ጥብቅና አይቆሙም፡፡
ይህ ዓለም የአካል ነው፡፡ እግዚአብሔር የራሱን እስትንፋስ አካል (ሥጋ) ካለበሳት በኋላ (አዳም ከሆነ በኋላ) እንድትኖር የላካት ወደ ምድር ነው። በመሆኑም ምድር የአካል መኖሪያ ነች፡፡ ይበልጥ የሚያሳዝነውም አካል በራሱ መኖሪያ ላይ መገፋቱና መዋረዱ ነው። አካል በራሱ ዓለም ላይ በደስታና በፈንጠዝያ መኖር ሲገባው፣ ሥነ ምግባርንና መንፈሳዊነትን ውለድ እየተባለ እንዲሰቃይ ይደረጋል፡፡
በምድር ላይ ስደተኛው ሥጋ ሳይሆን ነፍስ ነች፡፡ በመሆኑም፣ በምድር ላይ ይበልጥ መብትና ተሰሚነት ሊኖረው የሚገባው አካል እንጂ ነፍስ አይደለችም፡፡ በዚህ ምድር ላይ ነፍስ ነች እንጂ ለአካል መታዘዝ ያለባት፣ አካል አይደለም ለነፍስ መታዘዝ ያለበት፡፡ በመሆኑም፣ ስደተኛውን ከቀደምት ነዋሪው የበለጠ መብትና ክብር የሰጠው የሰው ልጅ አስተሳሰብ ኢ-ፍትሐዊ ነው፡፡ እናም በዚህ ኢ-ፍትሐዊነት ውስጥ ስደተኛዋ ነፍስ፣ አካል የሚሰቃይበትን ሲዖል በምድር ላይ ፈጥራለች፡፡ አካል በራሱ ዓለም ላይ እየተሰቃየ ነው፡፡
ይበልጥ የሚያናድደው ደግሞ የእግዜሩ ነው። ገነትን ለአዳምና ለሄዋን በአካል እንዲኖሩበት ከእግዜር የተሰጣቸው ሉዓላዊ ስፍራቸው ነው። እግዜሩ ገነትን በአካል እንዲኖሩበት ከሰጣቸው በኋላ ተደብቆ መከታተልን ምን አመጣው? እግዜር የሰጣቸውን ስፍራ እንደፈለጉ በአካል እንዲኖሩበት ማድረግ ሲገባው፣ ስደተኛዋን ነፍስ በአካላቸው ላይ ሾሞባቸው ሄደ፡፡ ከዚያም አካላቸውን ሲኖሩ ለቅጣት መጣ፡፡
እናም እግዜሩ ሳይቀር ያለ ስፍራው መጥቶ አካልን በራሱ ዓለም ላይ ይቀጣዋል። ‹‹ደም ይፍሰስሽ››፣ ‹‹ምጥሽ ይብዛ›› የሚለው ሄዋን ላይ የተጣለው አካላዊ ቅጣት፣ እግዜር በራሷ በሔዋን ዓለም ላይ መጥቶ የጣለው ኢ-ፍትሀዊ ቅጣት ነው፡፡ ኢ-ፍትሃዊነቱ አልበቃ ብሎት ጭራሽ እንዲፀፀቱም አደረገ፡፡
ይበልጥ የሚያናድደውም ይሄ ‹‹ፀፀት›› የሚባለው ነገር ነው። እግዜሩ በሉዓላዊ መኖሪያቸው ላይ መጥቶ የራሱን እንደራሴ (ነፍስን) በአካላቸው ላይ መሾሙና አዳምና ሄዋን ላይ ያደረሰው አካላዊ ቅጣት አልበቃ ብሎት፣ ጭራሽ ‹‹ፀፀት›› የሚባል ዘላለማዊ የህሊና ስብራት፣ በሉዓላዊው አካላቸው ላይ አትሞባቸው ሄደ። ሉዓላዊ መብታቸው መደፈሩ ሳያንስ ‹‹ፀፀት›› የሚባል ዘላለማዊ (ከልጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ) የህሊና ስብራት ተሸካሚ ተደረጉ። ምስኪን ሔዋን!!
አካል፣ ይሄንን ስቃዩን የሚያቃልሉለት ምሁራን ሊኖሩት ሲገባ፣ ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ ያፈራቻቸው ምሁራን ግን ጭራሽ በተቃራኒው ስቃዩን ደግፈው የሚፅፉትን ነው፡፡ ምሁራዊ ሽፋን እየሰጡ አካልን ከሚያስጠቁ ሰዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ደግሞ ዚግመንድ ፍሮይድ ነው፡፡ ‹‹ይህ ስልጣኔ አካላዊ ስሜትን በመጨቆን የተገነባ ነው፤ ያለ አካላዊ ጭቆና፣ ሥልጣኔን ማምጣት አይቻልም›› የሚለው የፍሮይድ አስተሳሰብ፤ አካልን ማሰቃየት ለሚፈልጉና ‹‹የከንቱ ከንቱ ነህ›› እያሉ ለሚያዋርዱት ሰዎች ምሁራዊ ከለላ ይሰጣል፡፡
ይህ ዓለም፣ “ስሜታችንን ሳንጨቁን ስልጣኔን ማምጣት አንችልም” (Non-repressive civilization is impossible) በሚል በእንደዚህ አይነት ትእቢት በተወጠረ መርህ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በዚህ ትምክህታዊ መርህ ታዲያ ኒቸ እንደሚለው፡-
‹‹ደስታና ድሎትን የምትጠየፍ ፕላኔት፣ ከስሜቱ የተገነጠለና ከተፈጥሮ ስርዓትም ያፈነገጠ፣ ከማህበራዊ ህይወትም ተገልሎ በብቸኝነት የሚሰቃይ፣ ምድራዊ ሕይወትን አምርሮ የሚጠላ፣ ከስቃይ ውስጥም ደስታንና ተስፋን የሚፈልግ ከንቱ የሆነ ማህበረሰብንና ዓለምን ፈጥረናል፡፡››
እስከ ዛሬ ድረስ ዓለም ካፈራቻቸው ምሁራን ውስጥ ለአካል ጥብቅና በመቆም ፍሬድሪክ ኒቸን የሚያክል የለም፡፡ የኒቸ አብዛኛዎቹ ሥራዎቹ ለአካል ጥብቅና የሚቆሙና አካል ላይ የሚሰነዘረውን ምሁራዊና ማህበረሰባዊ ጥቃት የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ ከመንፈሳዊ ተቋማት በኩል አካል ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ፊት ለፊት የሚታይ ቢሆንም፤ በኪነ ጥበብ፣ በፍልስፍናና በፖለቲካ አማካኝነት የሚሰነዘረው ጥቃት ግን ስውር ነው፡፡ ኒቸን ከታላቁ ጀርመናዊ የሙዚቃ ቀማሪ ዋግነር ጋር ያጣላውም ይሄው ነበር -  ‹‹በሙዚቃ ውስጥ ብሕትውናን እያሞገስክ አካል ላይ ጥቃት ትሰነዝራለህ›› በሚል፡፡
ኒቸ፣ ‹‹በፍልስፍና ውስጥ ተደብቀው አካልን ያንቋሽሻሉ›› በማለት ከሚከሳቸው ምሁራን ውስጥ ግንባር ቀደሞቹ ፕሌቶና ካንት ናቸው፡፡ ካንት ‹‹የዚህ ዓለም ነገር ‹‹በህወስታችን›› መታወቅ አይችልም›› የሚለው አባባሉ ፀረ - አካል አቋሙን አሳብቆበታል፡፡
ፕሌቶ ለአካል ያለው ጥላቻ ደግሞ ጭራሽ የባሰ ነው፡፡ የፕሌቶ መሰረታዊ ችግር የሚነሳው ከዲበ አካላዊ (ሜታፊዚካል) ፍልስፍናው ነው፡፡ ገና ከመነሻው፣ ዓለምን ‹‹መለኮታዊና ቁሳዊ›› ብሎ ለሁለት መክፈል ሲጀምር ነው አካል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቆርጦ መነሳቱን ያሳየው። ‹‹በስሜት ህዋሳቶቻችን ተጭበርብረናል››፣ ‹‹ስጋዊ ፍላጎታችንን ከተከተልን አረመኔ እንሆናለን››፣ ‹‹ምድራዊ ሐብትን በሚመኙ ሰዎች ከተመራን እንነቅዛለን›› የሚለው የፕሌቶ ሥነ ዕውቀታዊ (epistemological)፣ ሥነ ምግባራዊና ፖለቲካዊ አስተምህሮው በሙሉ አካልን በማጥላላት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
በመንፈሳዊ ተቋማቱ፣ በኪነ ጥበቡ፣ በፍልስፍናው፣ በፖለቲካው፣ በባህሉ ... በኩል አካል ላይ የሚሰነዘረውን እንደዚህ ዓይነቱን ሁሉን አቀፍ ጥቃት የተመለከተው ኒቸ፤በስተመጨረሻ ‹‹አጠቃላይ ስልጣኔያችን የሰውን ልጅ በማስቃየት የተገነባ (Masochistic civilization) ነው፤›› ወደሚል መደምደሚያ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡
“በማሰቃየት” ብቻ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ በተፈጥሮው ደስታን ፈላጊ ስለሆነ የሚያሰቃየውን ነገር አሽቀንጥሮ ይጥለው ነበር፡፡ ችግሩ ግን ማሰቃየት ውስጥ “ፈቃደኝነትን” እና “ተስፋን” ማስገባታቸው ነው፡፡
ምንም እንኳ አካል ሰብዓዊ ተሟጋች ባይኖረውም አንድ ሁነኛ ጠበቃ ግን አለው - የህመም ስሜት። አካል ጥቃት ሲደርስበት በደሉን የሚያስተጋባለት በህመም ስሜት በኩል ነው። ህመም አካልን የሚከላከለው ሰውየው ላይ ስቃይ በማምጣት ነው። ሆኖም ግን የመንፈሳዊ ተቋማት ‹‹ስቃይ›› የሚባለውን የአካል ተሟጋች የሚያሽመደምዱበት አንድ ዘዴ ዘየዱ- “መታገስና ተስፋ ማድረግ” የሚል፤ ለሚመጣው ዘላለማዊ ህይወት ሲባል አካላዊ ስቃይን መቻልና መታገስ።
ሰው ስቃይን በማስወገድ አካሉን ነፃ እንዳያወጣ፤በዚህ መልኩ ስቃዩን በተስፋ መረዙበት፤ “ይሄንን ስቃይና መከራ ከታገስክ ማርና ወተት ከምታፈልቀው ሰማያዊ መንግስት ውስጥ የዘላለም ህይወት ይኖርኻል፤ እንደ መላዕክትም እያሸበሸብክና አምላክህን እያመሰገንክ በደስታ ትኖራለህ፤” የሚል ተስፋ ሰጡት፡፡ እናም ለዚህ ሰማያዊ ተስፋ ሲል ራሱን በፈቃደኛነት ማሰቃየትን ተያይዞታል፡፡ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ያስቸገራቸው ነገር ይሄ ‹‹በፈቃደኝነት ራስን ማሰቃየት›› የሚባለው ነገር ነው::
አካልን በሚጨቁነው በዚህ ሥልጣኔ ውስጥ ይበልጥ ተጎጅዎች ደግሞ በተፈጥሮ ከአካል ጋር  ጥብቅ የሆነ ሥነ ልቦናዊና ስሜታዊ ትስስር ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ አካልና ስሜትን የሚጨቁን ሥልጣኔ፣ ‹‹የስሜት ምንጭ ናቸው›› ብሎ የሚፈርጃቸውን ሴቶች የመጨቆኑ ነገር አይቀሬ ነው፡፡ በዚህም ሴቶች ለዘመናት ቂም ይዘው ኖረዋል፡፡
ታዲያ ሴቶች በነፃነታቸው ማግስት ያደረጉት ነገር፣ “ያለ አካልና ስሜት ጭቆና ሞራላዊና መንፈሳዊ ዕድገትን ማምጣት አይቻልም፤” የሚለውን የዚህን ሥልጣኔ መርህ፣ ስሜታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ፣ አካላቸውን በማስዋብና ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን በመልበስ መቃወም ነው፡፡
የፍሮይድ ተንታኝ የሆኑት ኤርክ ፍሮምና ማርኩዘም፤ ሴቶች አካላቸውን የደስታና የውበት ምንጭ አድርጎ በመሳል አዲስ ዓይነት ማህበራዊ አስተሳሰብ እያመጡ እንደሆነ እንዲህ በማለት ያስረዳሉ፣
‹‹አሁን ያለው ማህበረሰብ የሚመራበት መርህ፤ ፍሮይዳዊውን አስተሳሰብ የሚፃረር ነው፡፡ ይሄም አዲስ ማህበረሰብ አካልን የሚያየው የሞራልና የመንፈሳዊ እድገቱ ፀር አድርጎ ሳይሆን እንዲያውም ወደ ደስታና ነፃነት የሚወስድ ሃይል አድርጎ ነው፤ ይሄም የሚያመላክተው እስከ ዛሬ ድረስ በአካልና በስሜት ጭቆና ላይ የተመሰረተው ማህበረሰብ መሰረቱ እየፈራረሰ መሆኑን ነው፡፡››
እናም አዲሱ ማህበረሰብ አካልን የደስታ፣ የውበትና የነፃነት ምንጭ አድርጎ በመመልከቱ ውስጥ ‹‹መንፈሳዊነት ያለ አካላዊ ስቃይ አይገኝም›› የሚለውን የቀድሞውን መንፈሳዊ ሥልጣኔ እየተሰናበተ ነው፡፡ ኦሾም ‹‹ሴቷ ይበልጥ ደስተኛ፣ ውብና ጤነኛ እንድትሆን ይበልጥ አካሏ ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት፤ የልስላሴና የአደጋ ተጋላጭነትን የመጨረሻ ከፍታ እየነካች ይበልጥ ስስ፣ ይበልጥ ለስላሳ፣ ይበልጥ ቆንጆ መሆን አለባት!!›› ይላል፡፡
ከአዘጋጁ፡- (ጸሃፊው ‹‹የኢትዮጵያ ፍልስፍና›› መፅሐፍ ደራሲ ነው)

 የስነተዋልዶ ጤና መበቶች በሰብዐዊ መብቶች ላይ የተመሰረቱ እና ለጾታ እና ለስነተዋልዶ የሚያገለግሉ መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች በአራት የተለያዩ ክፍሎች የተጣመሪ ሲሆን፤ ለስነተዋልዶ ጤና መብቶች ስንጠቀምባቸው አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ያላቸው ተዛዶ እጅጉን የጠበቀ ነው፡፡ እነሱ፤
የስነጾታ ጤና፤
የስነጾታ መብት
የስነተዋልዶ ጤና እና
የስነተዋልዶ መብት ናቸው። በስነጾታ፤ እና በስነተዋልዶ ጤና እና መብት ጥናት ውስጥ እነዚህን አራት ሃሳቦች ለያይተን የምንጠቀምባቸው ሲሆን አንዳቸው ከሌላኛው ጋር ያለው ዝምድና ግን እጅጉ ከፍተኛ ነው፡፡
የስነጾታ እና የስነተዋልዶ ጤና በአብዛኛው አንዱ ሌላኛውን እንደሚተኩ አድርገን የምንጠቀምባቸው አገላለጾ ሲሆኑ፤ የስነጾታ እና የስነተዋልዶ መብቶችንም እንዲሁ አንዱ ሌላውን የሚተካ ሃሳብ ተደርጎ መጠቀሙ የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የስነተጾታ መብት በስነጾታ ጤና ውስጥ ተካቶ፤ አሊያ ግልባጩን ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ የተለያዩ የቃላት አጠቃቀሞች በተለያዩ መንግስታዊ ባሆኑ ድርጅቶች መኖቸው ብቻ ሳይሆን፤ በአንድ መንግስታዊ ባሆነ ድርጅት ውስጥም የተለያየ የቃላት አጠቃቀም ይስተዋላል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ አለም አቀፍ የተረዐዶ ድርጅቶች መካከል የአለምአቀፍ የታቀደ ወላጅነት ፌደሬሽን፤ የአለምአቀፍ የስነጾታ ማህበር፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የኤች አይ ቪ አድስ ትብብር ይገኙበታል፡፡
የአለምአቀፌ የጤና ድርጅት የስነጾታ ጤናን እንዲህ ይተረጉመዋል- የስነጾታ ጤና ማለት ከጾታ ጋር በተገናኘ የአካላዊ የስነልቦናዊ እንዲሁም የማህበራዊ ደህንነትን ያመለክታል፡፡ ይህም በመልምነት እና በመከባበር ላይ የተሞላ አመለካከት ለስነጾታ፤ ለጾታዊ ግንኙነቶች እና በማናቸውም ሃይል የተሞላበት ድርጊት ላይ ያልተመረኮዘ የስነጾታ ግንኙነትን መፈለግ ያንንም ለመከነወን መቻልን ያመለክታል፡፡
ከሌሎች ከሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች በተለየ መልኩ የስነጾታ መብት በጾታዊ ግንኙነት መደሰት መቻልን እና ስሜትን በነጻነት መግለጽ መቻል ላይ ያተኩራል፡፡ ይህን መብት ለመታገል የሚደረገው ትግል ከሚደረግባቸው ተጨባጭ መሰረቶች አንዱ የአለምአቀፉ የስነጾታ መብት ማህበር የደነገገው ድንጋጌ ነው፡፡ በ14ኛው በአለምአቀፉ የስነጾታ ኮንግረስ ወቅት ማለትም በሆንግ ኮንግ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1999 አ/ም በተካሄደው፤ ማህበሩ 14 ነጥቦች ያሉት የስነጾታ መብቶችን አውጥቶ አጸድቆ ነበር፡፡ በኋላ ላይ በመጋቢት 2014 ደግሞ ተጨማሪ 14 ነጥቦች አካቶ ስራ ላይ ውሏል። በስተመጨረሻ በጸደረገ ክለሳ አሁን የምንጠቀምባቸው 16 የስነጾታ መብቶች ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የእኩልት እና ከአድሎ ነጻ የመሆን መብት፤
የራስን መብት በራስ የመወሰን መብት
የህይወት፤ የነጻነት እንዲሁም የደህንነት መብት፤
ከሰብዐዊ ካልሆኑ ቅጣቶች ነጻ የመሆን መብት፤
ከማቸውም ጥቃትና አስገዳጅ ሁኔታዎች ነጻ የመሆን መብት፤
 የግለኝነት መብት
ሁኔታዊ የሚፈውደውን የተሻለ የጤና፤ የስነጾታ ጤና አገልግሎትን ጨምሮ የማግኘት፤ ድህንነቱ የተጠበቀ የስነጻታ እርካታን የማግኘት መብት
የሳይንሳዊ ግኝቶችን እና እነሱን ተከትሎ የሚመጡ የጤና አገልግሎት ውጤቶችና ጥቅሞቻቸውን የማግኘት መብት፤
መረጃን የማግኘት መብት
 ለትምህርት እና ለሁሉን አቀፍ የስነጾታ ትምህርት የማግኘት መብት
ትዳርን እና መሰል ግንኙነቶችን የመመስረት፤ ወይም በትክክለኛ መረጃ እና በእኩልነት ላይ በተሰረት መልኩ የማፍረስ መብት
ልጆችን ለማፍራት፤ የሚያፈሩበትን ጊዜ እና ቁጥሩን የመወሰን እና ያንንም ለማድረግ የሚያስችል መረጃን የማግኘት መብት፤
ሃሳብን በነጻነት የማንጸባቅ መብት፤
በማበር የመደራጀት እንዲሁም ሰላማዊ ስብሰባዎችን የማድረግ መብት
በፖለቲካና በማበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የመሳተፍ መብት
ፍትህን፤ እና ይግባኝን የማግኘት መብት
የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህም ድንጋጌውች ቆይተው የዮጋካርታ ድንጋጌ ተብ ለሚጠራው እና በመጋቢት 2007 ለወጣው ድንጋጌ መሰረት ጥለዋል፡፡

  በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የአፄ ቴዎድሮስ ቴያትር ውስጥ ስለ አፄ ቴዎድሮስ መድፍ ስለ ሴቫስቶፖል የተነገረውና የተተወነው ታሪክ በጣም ደማቅ ነው፡፡
አፄ ቴዎድሮስ፤
“ሃያ ሺህ ጎበዝ መልምላችሁ መድፌን ሴቫስቶፖልን መቅደላ አፋፍ ድረስ አምጡልኝ” ብለው ባዘዙት መሰረት፣ መድፉ መጣላቸው፡፡
ያንን ቀጥ ያለ አቀበት፣ እጅግ ክብደት ያለውን መድፍ ይዞ መውጣት በዕውነትም ትልቅ ጉልበት የሚጠይቅ ነበር፡፡ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ መልሶ ወደ ታች ይንሸራተታል፡፡ እንደገና ሽቅብ ይስቡታል፡፡ ደህና ወጥቶ ወጥቶ፣ መልሶ ቁልቁል ይወርዳል፡፡ ሽቅብ ይስቡታል፤ ቁልቁል ይሳባል፡፡ ለአገር አንድነት ሲሳብ፣ እስከ መጨረሻው ተደክሞበታል፡፡
በመከራ አፋፍ ድረስ ተጎትቶ መጥቶ፣ በመጨረሻ ደረሰና ተተኮሰ፡፡ ሆኖም የታሰበው ሳይሆን ያልታሰበው ተከሰተ!
እንደ ሎሬቱ አገላለፅ፤
“ሴቫስቶፖል መድፋችን የኋሊት ፈነዳ!”
ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ቴዎድሮስ
“አየሽ አንቺ እማማ ኢትዮጵያ፣ አየሽ አንቺ እናት ዓለም ቃል የእምነት ዕዳ ነው እንጂ፤ የእናት የአባትኮ አይደለም!” ብለው ቃላቸውን የፈፀሙት!
“… እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ፣ እጅ ተይዞ ሊወሰድ … ምን እጅ አለው የእሳት ሰደድ … አያውቅም ክንዴ እንደሚያነድ!”
የሚሉት እንደ እሳት በሚንቀለቀል ወኔ ነው፡፡ ለሀገራቸው ህይወታቸውን የሰጡት ከዚህ ወዲያ ነው፡፡
“መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ”
የተባለውና የተገጠመው ለዚህ ነበር፡፡
ገጣሚ መንግሥቱ ለማም በ“ባለካባና ባለዳባ” ቴያትራቸው ውስጥ “ቴዎድሮስ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ይሉታል” ብለው የሚያስቡትን እንዲህ ፅፈውታል፡-
“ቀማኛን መቀማት ከሌባ መስረቅ
ለማቅለል ከሆነ የድሆችን ጭንቅ
በእኔ ቤት ፅድቅ ነው አንድ ሰው ይሙት
አንድ መቶ ሺ ሰው ኪኖር በምፅዋት!”
ቀማኛን፣ ሙሰኛን መዋጋታቸው ነው፡፡ ድህነትን መፋለማቸው ነው፡፡ ለደሀ መቆማቸውን ማሳየታቸው ነው!!
*   *   *   *
የህዝብን አደራ መቀበልና ቃልን ማክበር፣ የመልካም መሪ የተቀደሰ ምግባር ነው፡፡ ራስን እስከ መስዋዕትነት ማዘጋጀትም በአርአያነት ተጠቃሽ የሆኑ ታላላቅ መሪዎች መልካም ተምሳሌት ነው፡፡ በተለይ እንደ እኛ አገር ያለች ድህነት ያቆራመዳት፣ አስተዳደር የራባት፣ ወገናዊነት ያጠጣባት፣ ዲሞክራሲ የተራቆተባት፤ ችግር ሲመጣ ብቻ ስብሰባና ግምገማ፣ ግርግርና መዋከብ የሚበዛባት፤ አገር ላይ ሹም መሆን አበሳው ብዙ ነው፡፡ ሥነ ልቦናዊም፣ ፖለቲካዊም፣ ማህበራዊም ዝግጅት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የልዩ አጋዥ ተቋማት መኖር ግድ ነው፡፡ የሲቪክ ማህበራትን መፍጠርና ያሉትንም ማጠናከር ያሻል። ለሀገር የሚበጅ ሀሳብን በአማራጭ እንዲያቀርቡ መንገዱን መጥረግ የጥበብ መጀመሪያ ነው፡፡ ሀሳብን አለመገደብ ልዩ ልዩ የዕድገት አማራጮችን እናይ ዘንድ ያግዘናል፡፡ ምንም ቢሆን ምንም፣ ለተስፋ መቁረጥ ቦታ አለመስጠት የጥንካሬያችን መፍለቂያ ነው፡፡ እፊታችን የተደቀኑ እልህ አስጨራሽ እንቅፋቶች ሊኖሩ መቻላቸው የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ ቀበቶን ጠበቅ አድርጎ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን አጠናክሮ፣ በሆደ - ሰፊነት መስመር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ሀገራችንን ከትናንት ወደተሻለ ነገ ለማሸጋገር ጥረት እናድርግ፡፡ ልዩነት የለም ብለን አናስብ፡፡ ይልቁንም እናጠበዋለን ብለን እንመን! ሁሉም መንገድ ወደ ድል ያደርሰናል ብለን አንገበዝ፡፡
“ህዝብ ያላማከረ ንጉሥ፣ አለአንድ ዓመት አይነግሥ” የሚለውን የአበው ብሂል አንዘንጋ!
“እንግዲህ ንጉሡ ምን እራስ አላቸው
ሁሉ በየአቅጣጫው እያደሙባቸው” የሚለውንም አንርሳ፡፡
ገጣሚው፤
“እንግዲህ ወገኔ ዳሩን እወቅና
መካከሉን ዳኘው በጥበብ ያዝና
አይፈለፈልም ደረቁ ባቄላ
እሳት አይገባውም፣ ርሶ ካልተበላ
አለቀ እምንለው ሰው አላቂ አይሆንም
ተሳፋሪው እንጂ አሳፋሪ አይወርድም!” የሚለውንም አንዘንጋ!
ከሁሉም በላይ ግን ረግጠን የመጣነውን መንገድ ሳንረሳ፣ የመሄጃችንን አውራ ጎዳናውንና መጋቢ - መንገዱን እንለይ! እንደ ጥንቱ ሚሲዮናውያን የኋሊት የሚፈነዳ መድፍ ሊሰሩልን የሚመኙትን ታላላቅ መንግሥታት በዐይነ - ቁራኛ እንይ!! ደግ - አሳቢ ነው ያልነው መቼ ክፉ - አሳቢ እንደሚሆን አይታወቅምና በተጠንቀቅ መጠበቅ ብልህነት ነው፡፡ ዮሐንስ ቤል እንዳለው፤ የሀገራችን ደወል “ፍርሃት … ብልሃት … ብልሃት … ፍርሃት …” እንደሚል ማዳመጥ መታደል ነው! “ሽቅብ መሳብ፣ ቁልቁል መሳብ፤ ለአገር አንድነት ሲባል” የሚለው እሳቤ ግን መቼም የማይሞት ነው! እያንዳንዱ ድል የራሱን መስዋዕትነት ይጠይቃልና!!    

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያገለግለውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ለማዘጋጀት “ኬፒኤምጂ ኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ኩባንያ ጋር ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ቦሌ ደንበል ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡
የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አስፈፃሚዎችና የኬፒኤምጂ ተወካዮች በተገኙበት በተፈፀመው የውል ስምምነት ሥነ - ሥርዓት ላይ የባንኩ ፕሬዚንት አቶ ብሩክ ፎንጃ እና የኬፒኤምጂ ኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ኩባንያ ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ሌሂ ፊርማውን ፈፅመዋል፡፡
ስትራቴጂክ እቅዱን ለማሰራት ባንኩ ጨረታ ካወጣ በኋላ ለመወዳደር ጨረታውን ከወሰዱት 23 ድርጅቶች መካከል ስምንቱ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች መሆናቸውን በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የተገለፀ ሲሆን በተደረገው የቴክኒክ ምርመራ ኬፒኤምጂ ኢስት አፍሪካ ሊሚትድ የተሻለ ውጤት በማግኘት፣ ጨረታውን አሸንፎ ለስምምነት መብቃቱም በዕለቱ ተገልጿል፡፡
ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ የባንኩን ድርጅታዊ አወቃቀር ከዘመኑ ጋር እንዲዘምን በማድረግ ለሰራተኛውም ሆነ ለተገልጋዩ የተቀላጠፈ አሰራርና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ በአሁኑ ወቅት 25 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ሲሆን ተቀማጩ 20 ቢ. ብር፣ በብድር የተሰጠ 13 ቢ. ብር፣ እንደደረሰ ጠቁሟል፡፡ 209 ቅርንጫፎችና እንዲሁም ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉትና ከቀዳሚ የግል ባንኮች አንዱ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

Saturday, 07 April 2018 00:00

የከረመለታ!...

አረዱለት ጥጃ
ጋረዱለት ግምጃ፣
የከረመለታ…
ጎደ’ላሉት ጎታ
ከለከሉት ኩታ!
(መኮንን ተሾመ ቶሌራ - ዘ ገዳም ሰፈር)

Saturday, 07 April 2018 00:00

የተራራው ላይ ዛፎች ምኞት!

ካልጠፋ ሁሉ ከምድር
እንዴት ይገዟል የገባር ፣
በሔዋንማ በናታችሁ
ግንደ በል ነበራችሁ፡፡ (ዘፍጥ 3፣6) (… ወዳጄ ልቤና ሌሎችም … ገጽ 36 … ዛፍ በልታችሁ እንደሞታችሁ … በዛፍ ደግሞ ዳናችሁ! … ሲሉ አስተማሩን!)
*   *   *
በተራራው አናት ያሉ 3 ዛፎች ገና እንደተተከሉ፣ በችግኝ ዘመናቸው ሲወያዩ…. ተስፋቸውንና ህልማቸውን ሲነጋገሩ ለሰማቸው በጣም ይገርሙ ነበር፡፡ ከበታቻቸው ባለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ካሉት ዘመዶቻቸው በተለየ መልኩ የተለየ ህልምና ምኞት ነበራቸው …  
*   *   *
የመጀመሪያ ዛፍ ችግኝ እንዲህ አለ … ‹‹.. እንግዲህ የሆነ ቀን አድጌ ስቆረጥ የከበሩ ዕቃዎች ማስቀመጫ እንዲሰሩብኝ እመኛለሁ፡፡ ዘናጭና ምርጥ በዓለም ካሉት ነገሮች ሁሉ የከበረ ነገር ማስቀመጫ ሳጥን መሆን ምኞቴ ነው፡፡ ይህ ካልተሳካልኝ ምኑን ኖርኩት … እኔ በተስማሚ ሁኔታ ለማደግ እሞክራለሁ … ቀሪውን ተካይና ተንከባካቢያችን ይጨነቅበት…››
ሁለተኛው ችግኝ እንዲህ አለ ‹‹…እኔ ግን ወደፊት የሆነ ግዜ ታላቅ መርከብ እንዲሰራብኝ እመኛለሁ፡፡ ምርጥና ውብ እንዲሁም ጠንካራ መርከብ ሆኜና ከንጉሶች ሁሉ ታላቅ የሆነውን ንጉስ ጭኜ በዓለም ዙሪያ መዞር … በእኔ ጥንካሬ ሰዎች ሁሉ እንዲተማመኑብኝና በእኔም መልካም ነገር እንዲሰሩብኝ እመኛለሁ …››
ሶስተኛው ዛፍ እንዲህ ሲል ምኞቱን አስቀመጠ ‹‹… እኔ የምመኘው በጣም ትልቅ፣ ረጅምና መለሎ ሆኜ ማደግ ነው፡፡ ሰዎች ሲመጡ ገና ከሩቁ ያዩኝና ይህስ ወደ መንግስተ ሰማያት ሊደርስ ምን ቀረው! እያሉ ያደንቁኛል፡፡ ከዛፎቹ ሁሉ ድንቅ እሆናለሁ፣ እናም ሰዎች በድንቅነቴ ያስታውሱኛል … ሲያስታውሱኝም … ‹… ያ! ዛፍ የሰማይ መክፈቻ ቁልፍ ቢኖረው ከፍቶ በገባ ነበር … ዳመናዎችን ወሽሟል … ዝናብን ይስማል …› …. ይሉኛል …››
ለምኞታቸው መሳካትም በየዕለቱ መትጋት ጀመሩ …
*   *   *
ከአመታት ጸሎት በኋላ ህልሞቻቸው እውን የሚሆንበት ወቅት መጣ፡፡ እነሆ በአንድ የጸደይ ማለዳ ጥቂት ዛፍ ቆራጮች ተሰብስበው ወደ ተራራው መጡ፡፡ አንደኛውም ወደ መጀመሪያው ዛፍ እየተጠጋና ግንዱን እየደባበሰው እንዲህ አለ …
‹‹ይህ ጠንካራ ዛፍ ይመስላል ስለዚህ ለአናጺው ወዳጃችን እንሸጥለታለን፡፡ እርሱም ሳጥን ይሰራበት ይሆናል…›› እናም መጥረቢያውን ይዞ ይቆርጠው ጀመር፡፡ ዛፉም እየተቆረጠ … ደስ አለው፡፡ ትክክል! እንደ ምኞቴና ህልሜ አናጺው የከበሩ ዕቃዎች ማስቀመጫ ሳጥን አድርጎ ይሰራኛል ሲል አሰበ፡፡
ሁለተኛውን ዛፍ እየደባበሰ ሌላው ዛፍ ቆራጩ እንዲህ አለ … ‹‹ይህም ጠንካራ ዛፍ ይመስላል፤ ይህንን ደግሞ ለመርከብ ሰሪው እሸጠዋለሁ… ጥሩ መርከብ የሚገነባበት ይመስለኛል …›› ሁለተኛውም ዛፍ እጅግ ደስ ብሎት ነበር፡፡ እነሆ ታላቅ መርከብ ሊገነባብኝና በመጨረሻም ህልሜ እውን ሊሆን ነው ሲል አሰበ፡፡
ወደ ሶስተኛው ዛፍ ሲመጡ ዛፉ በድንጋጤ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ቁመቴ ገና ሁሉን የሚበልጥ እጅግ ግዙፍ አልሆንኩምና አሁን ከቆረጡኝ ህልሜ አይሳክልኝም ሲል አስቦ ነበር፡፡ ከዛፍ ቆራጮቹ አንዱ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከዚህ ዛፍ ምንም የተለየ ነገር አላየሁበትም፤ ሆኖም ቆርጬ ልውሰደው… መቼም ለሆነ ነገር ማገልገሉ አይቀርም…!›› አለና ቆረጠው፡፡
እነሆ ዛፎቻችን ተቆረጡ፤ ተጫኑ፤ ወደ ሰፈሩም ተጋዙ፡፡
የመጀመሪያውም ለአናጺው ተሰጠ፡፡ በእርግጥም አናጺው ሳጥን ሰራበት፡፡ ሆኖም ሳጥኑ የተሸጠው ለከበሩ ዕቃዎች ማስቀመጫ እንዲያገለግል ሳይሆን በበረት ውስጥ ለበጎች መመገቢያ ነበር፡፡ ዛፉም… ለዚህ አልነበረም የጸለይኩት ሲል አሰበና አዘነ፡፡
በሁለተኛውም ዛፍ የመርከብ ሰሪው ትንሽዬ የአሳ አስጋሪዎች የሚጠቀሙበት ታንኳ ሰራበት። ታላቅ መርከብ የመሆን ምኞቱ ድቅቅ አለ፡፡ ሆኖም ምን ይደረጋል! ሲል አሰበ፡፡ መርከብ መሆኔ ቢቀር … ታንኳም ቢሆን ሆኜ ልኑር የወደፊቱ አይታወቅምና…  ሲል ተቀበለው፡፡
ሶስተኛው ዛፍ ግን በረጃጅሙ እንደተቆረጠና ጥቂት እንደተስተካከለ ምንም ነገር ሳይሰራበት ከቆራጩ ዕቃ ቤት ተቀመጠ፡፡ እነሆ ወደ ጨለማው ዕቃ ቤት ተጣለና አቧራውን እየለበሰ … አዝኖ ቁጭ አለ፡፡ ተፀፀተ…
‹ምነው ጥቂት ጊዜ ቢተውኝ ኖሮ … ሁሉንም በልጬ አድግ ነበር!› ሲል አሰበ….
አመታት ነጎዱ፡፡ ዛፎቹም ህልማቸውን ዘንግተውና ረስተው መኖር ጀመሩ፡፡ ጸጥ ብለው ስራቸውን ይሰሩ ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን አንዲት ሴትና አንድ ሰውዬ ወደዚያ የበጎች በረት መጡ፡፡ ሴትየዋም በምጥ ተይዛ ነበር፡፡ ቆይታም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ህጻኑንም ከመጀመሪያው ዛፍ በተሰራው በበጎቹ የመመገቢያ ሳጥን ውስጥ አስተኙት፡፡ እነሆም የመጀመሪያው ዛፍ ከዓለም ድንቅ ነገሮች ሁሉ የላቀው ድንቅ ማረፊያ ሆነ። በቤተልሄም ከተማ የከብቶች ግርግም የኖረ ቢሆንም፣ የዓለምን ታላቅ ስጦታ አቀፈ፡፡ አማኑኤልን፡፡
(የማቴዎስ ወንጌል 2፣ 1 -)
*ከሌላ ዓመታት በኋላ በሁለተኛው ዛፍ በተሰራው ታንኳ ሆነው ባህሩን ያቋርጡ ዘንድ ሰዎች ነበሩ … በባህሩ ላይ ታላቅ መናወጥ ሆነ፣ ታላቅ ማዕበልም ተነስቶ ታንኳይቱን ያንገላታት ያዘ፡፡  ያቺ ትንሽ ታንኳ ታላቁን ወጀብ ተቋቁማ ሳትሰባበር ታገለች፡፡ ከመካከላቸውም አንዱ ተነስቶ ‹‹ሰላም ይሁን!›› ብሎ ወጀቡንና ንፋሱን ገስፆ እስኪያቆመው ድረስ ያቺ ታንኳ ታላቅ ስራ ሰራች። ያ የተሸከመችውና ወጀቡን የገሰፀው ሰውም የንጉሶች ሁሉ ንጉስ የሆነው መሆኑን ባወቀች ግዜ ተደሰተች፡፡ እኛም የሁለተኛው ዛፍ ምኞት መሳካቱን አወቅን ….
(የማቴዎስ ወንጌል 8፣ 23 -)
*በመጨረሻም ከሶስተኛው ዛፍ ተቆርጦ ወደተቀመጠበት ጭለማ ክፍል አንድ ሰው መጣ፡፡ እነዚያን ቀጥ ያሉ የሶስተኛው ዛፍ ግንዶች አወጡ … መስቀልያ ሰርተውም ካጣመሯቸው በኋላ ለአንድ ምስኪን ሰው አሸክመው ያንገላቱት ጀመር፡፡ ስምኦን የተባለው የቀሬና ሰው ሲመጣ በእርሱ አህያ ጭነው ከዚያ የወጀብና የማዕበል አዛዥ ኋላ አስከትለው አስጓዙት፡፡ዋይ ዋይ የሚሉ እናቶች በሞሉበት መንገድ አቋርጠው ሲሄዱ ሰውየው ‹ለራሳችሁ አልቅሱ!› እያለ ይመክራቸው ነበር … ሰውየው በደም አበላ ታጥቦና በስቃይ ውስጥ ሆኖ ይጓዝም ነበር … ከቀራንዮ ተራሮች ላይ አወጡና በመስቀሉ ላይ ከሁለት ወንጀለኞች መሃል  ቸነከሩት፡፡
(የሉቃስ ወንጌል 23፣ 25 -)
ሶስተኛውም ዛፍ አለ ‹‹ … እነሆም በመጨረሻው በታላቁ ተራራ ላይ ታላቁን የሰማየ ሰማያት ልጅ ተሸከምኩ!... ምኞቴም ልክ መጣ … የሰማያትን ሁሉ መክፈቻ ቁልፍ በእኔ ላይ አኑረዋልና … ›› ሲል አሰበ፡፡
*   *   *
እንግዲህ የህልማችንን መፈቻ ወቅት መጠበቅ ግድ ነው … ለህልማችንም መሳካት መስራትና ቀሪውን ለተተኪያችን መተው ይገባል፡፡ የተመኘሁት አልተሰጠኝም፣  በወቅቱም አላገኘሁትም ልትል ትችላለህ፡፡  እመነኝ ላንተ የተባለ ዘግይቶም ቢሆን ወዳንተ ይመጣል፡፡
ዘግይቶም ቢሆን ግን በጣም ይፈጥናልና አይዘገይም፡፡
በርትቼ ብነሳ አውርጄም ባየው
ለካ ምግብ ኖሯል የተሰቀለው … (የሉቃስ ወንጌል 22፣ 19) (…ወዳጄ ልቤና ሌሎችም … ገጽ 69)
*   *   *
 (…የሃሳቡ አመንጪና እውነተኛ ፀሃፊው ያልታወቀ ሰው፡፡ ተሻሽሎ የተተረጎመ የ3ቱ ዛፎች ታሪክ …)
መልካም የትንሳኤ በዓል!

 “ማንነታችን እንዳንለያይ ሆኖ የተሰናሰነ፣ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ፣ የተዋደደና የተዋሃደ ነው”

     የኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ንግግር፤ ሁሉን ያስደነቀ በአንጻሩ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጉጉትና ተስፋ ሰንቀው በአንክሮ፣ እንዲከታተላቸው ያደረገ ነው፡፡ በበዓለ ሲመታቸው ቀን ያደረጉት ንግግርና የአቀራረብ ሰብዕና፤ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኙት መሪዎች ተርታ ያሰልፋቸዋል ለማለት ያስደፍራል፡፡ በመጀመሪያ የዳሰሷቸውን ሀሳቦችና ያሄሷቸውን ርዕሰ ጉዳዮች አንድ በእንድ እየነቀሱ ማየት ተገቢ ነው፡፡ ብዙዎች እንደሚያስታውሱት፤ ዶ/ር አብይ በጨው የተቀመመ፣ የሰውን ልብ የገዛ፣ የተስፋ ‹‹ገበታ›› ነው በንግግራቸው ያቀረቡት፡፡ የኢትዮጵያ ገበታ ሰፊ ነው እንዳሉት፣ እሳቸው ሰፊውን ገበታ ነው ለኢትዮጵያ እነሆ ያሉት፡፡
የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ንግግር፤ ብዙዎችን የሳበበት ትልቁ ምክንያት የንግግሩ ማጠንጠኛ  የተቋጠረበት የትንታኔ ፍሰት ነው፡፡ የንግግራቸው ጅረት የተቀዳው ከተለያዩ ምልከታዎች በመሆኑ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ የሕዝቡን፣ የፓርቲውንና የጊዜውን እንዲሁም የወጣቱንና የጥቅል ማሕበረሰቡን የፍላጎት አውድ መሰረት አድርጎ የተነሳ በመሆኑም አድናቆት አትርፏል፡፡
 1ኛ. ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናቸው የሚክስ ነው
በንግግራቸው ውስጥ ያቀረቡት የታሪክ ትንታኔያቸው፤ ለኢትዮጵያውያን ካሳ የከፈሉበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክና ማህበራዊ ስሪት ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር አቆራኝተው መግለጻቸው፣ አንድ የንግግራቸው ጥንካሬ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊነትን  ትልቅ ቦታ ሰጥተው፣ ዋጋ የከፈሉ አባቶችን እውቅና መስጠታቸው ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ትልቅ ካሣ የከፈሉበት ንግግር ነው፡፡ ከልዩነት አንድነትን አስቀድመው፣ በዚያው ደግሞ አንድነት፤ አንድ ዓይነትነት አይደለም ሲሉ የተደመጡበት ንግግራቸው መሳጭ ነበር፡፡ የሚፈልጉትን ሃሳብ  የገለጹበት ሞገስና  ትህትና፣ ንግግራቸውን አጣፍጦላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያንና የሕዝቦቿን ጥምረት ሲገልጡ፤ ‹‹ማንነታችን እንዳንለያይ ሆኖ የተሰናሰነ፣ እንደይነጣጠል ሆኖ የተገመደ፣ የተዋደደና የተዋሃደ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን፤ “I have a dream” ዓይነት ንግግር ይመስላል፡፡ መተማን፣ ካራማራን፣ ባድመንና አድዋን ሲያነሱ፤ ሉተር ሚሲሲፒን፣ ጆርጂያን፣ ቴኔሲንና የመሳሰሉትን እየጠቀሱ የተናገሩትን ይመስላል፡፡
2ኛ. አሳታፊ የሆነ የፖለቲካ ፍልስፍናቸው
ጥሪ ደማቅ ነበር
 ይህ ፍልስፍናቸው የሚቀዳው ምናልባትም ስለ ኢትዮጵያ ካላቸው እውቀት፣ የስራ ልምድ እንዲሁም ወጣትነታቸው ካቀበላቸው ስንቅ ሊሆን ይችላል። በመጀመሪያ ቁስል እንዳለብን ተገንዝበው የቁስል መፈወሻ ቃል ማቀበላቸው ያስደንቃል፡፡ ተቃዋሚ የሚለውን ተፎካካሪ፣ “ህገ መንግስቱን ለመናድ” የሚል ቅጥያ ስም የወጣላቸውን፣ ለሃገራችን በጎ ርዕይ ያላቸው ወንድሞቻችን፣ ጽንፈኛ ዲያስፖራ የሚለውን፣ ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚዞሩ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ሲሉ ቁስሉን ሽረውታል፡፡ በተዘዋዋሪ ነፍጥ አንስተው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሲዋደቁ የኖሩትን አርበኞች እውቅና መስጠታቸው ያስደንቃቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ፤ ከኢህአዴግም ሆነ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች በላይ መሆኗንም ተናግረዋል - ‹‹ኢትዮጵያ ከፖለቲካ አመለካከት በላይ ነች›› በማለት። ይህ ምን ማለት ነው? “ኦህዴድ ወይም የፖለቲካ መስመሩ ከኢትዮጵያ አይበልጥብኝም” እንደ ማለት  ነው፡፡ ይህ ነው አዲሱ መንገዳችን የሚሉም ይመስላል፡፡ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ እውነትና “የኔ ብቻነት” የተላቀቁ መሆናቸውን ንግግራቸው ይጠቁማል፡፡ ድርጅቱንም ወደዚህ ጠርዝ ፈቀቅ ያደርጉታል ብሎ መገመት ይቻላል።
3ኛ. ዴሞክራሲንና ፍትህን ከነጻነት
ጋር አንስተው ያሄሱበት ንግግር ይለያል
በንግግራቸው ውስጥ የዴሞክራሲን አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊነቱን ፈትሸዋል፡፡ አገሪቱ በተስፋና በስጋት ውስጥ ናት ሲሉ ከተናገሩ በኋላ ምክንያቱን ሲዘረዝሩ፤ የዴሞክራሲ እጥረት ነው ብለዋል፡፡ ግለሰቦች ነጻነታቸው ተገድቧል ሲሉ በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በአጭሩ የዲሞክራሲ ሥርዓቱን የተቸ የሰላ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ ነጻነት የተፈጥሮ ጸጋ እንጂ የመንግስት ሥጦታ አይደለም ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩ፡፡ በዚህም ከቡድን  ነጻነት ይልቅ ለግለሰብ ነጻነት ቅድሚያ (ትኩረት) መስጠታቸውን መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ይህም ኢህአዴግን ወደ አዲስ መንገድ  ይመሩታል የሚል ሃሳብ ያጭራል፡፡አዲሱ ጠ/ሚኒስትር፣ ማልኮም ኤክስ እንዳለው፤ “we haven’t benefited from America’s democracy, we suffered from America’s hypocrisy” (ከአሜሪካ ዴሞራሲ እየተጠቀምን ሳይሆን በግብዝነቱ እየተሰቃየን ነው) የሚለውን ዓይነት ሃሳብ ማንጸባረቃቸው ያስደምማል፡፡
4ኛ. የተዘነጉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በተገቢ ሁኔታ ያስታወሰ ንግግር
የተዘነጉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለፖለቲካ ትርፍ ሳይሆን ለተጠቃሚነታቸው መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ የወጣቱን ክፍል ሃሳብ፣ጥያቄና ትግል እውቅና ሰጥተዋል፡፡ ተግባር ሲጨመርበት ደግሞ የግሩም ግሩም ይሆናል፡፡ ሌላው ያነሱት የሴቶችን ትግል አስፈላጊነት ነው፡፡ የሴቶች ትግል በትክክል ሊወከል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር አብይ በንግግራቸው መደምደሚያ ላይ የእናታቸውን፣ የሚስታቸውንና የሌሎች እናቶችን ሚና በሚገባ ማንሳታቸው፣ ቁርጠኛ የሴቶች መብት ተሟጋች ያደርጋቸዋል፡፡ ምናልባትም የእናታቸውን ውለታ እያዩ አድገው፣ የኢትዮጵያውያንን እናቶች ጭቆና አስተውለውና የወለዷቸው ሦስት ሴት ልጆች ዕጣ ፈንታን ተገንዝበው ትኩረት የሰጡት ጉዳይ ስለሚመስለኝ፣ ከንግግራቸው ትልቁን ቦታ የሚይዝ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ “Which side of America are you living in” እንደተባለው፤ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የአኗኗር ሁናቴ አጢነው፣ በዚህ አቅጣጫ ለውጥ ለማምጣት የፈለጉ ይመስላሉ፡፡ ድሃ አደጉን አይተውታል፡፡ የእናቶችን፣ የባልቴቶችንና ሕጻናትን ሁኔታ ያውቁታል፡፡
4ኛ. የማህበራዊ ፈውስ (ሶሻል ቴራፒ) ፈጣን መርሃቸው ይመስላል
የንግግራቸው አንኳር ማጠንጠኛው፤ ማሕበራዊ ፈውስ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ያላቸውን የተሳሳተና የተንጋደደ አስተሳሰብ በተመለከተ እርምት ሰጥተዋል፡፡ ጨለምተኛነትንና ጠባብነትን እንዲሁም የታጋይ ግብዝነትን ተችተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊት አገር ናት ሲል ደምድሞ የተነሳውን ድርጅታቸውንም ቢሆን  ሞግተውታል፡፡ በመጀመሪያ ለሰብአዊ መብት ሲሟገቱ፣ ህይወታቸውን ለተነጠቁ  ግለሰቦች ይቅርታን ጠይቀዋል፡፡ ይህ ትልቅነት ነው። ፈውስ ያመጣል፡፡ ይህን በማለታቸው ጠ/ሚኒስትሩ ከድርጀታቸው ያፈነገጡ የሚመስላቸው አይጠፉም። ግን አፈንግጠው አይደለም፡፡ ብዙዎቹም የድርጅቱ አባላትም ይህን ይጋሯቸዋል፡፡
የሙሰኞችን የበረታ እጅ አንስተው ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንደሌለ አስምረውበታል፡፡ አንዱ ዘርፎ አንዱ ሰርቶ የሚኖርባት አገር ማየት አንፈልግም ብለዋል። ‹‹የልዩ ተጠቃሚ ነን” ኃይሎችንና ወደፊት አዳዲስ ጎሳን ወይም ሌላ የጥገኝነት መስመር ዘርግተው፣ ለዘረፋ የተዘጋጁ ተስፈኞችን፤ ድርጅታቸውንና ሰፊውን ሕዝባቸውን ይዘው እንደሚታገሏቸው መግለጻቸው ያስደንቃል። የማሕበራዊ ማለትም የፖለቲካ ተጽዕኖ፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛና በአዲስ መልክ የተገለጸውን ዘረፋና ማሕበራዊ ውርደት (ሶሻል ዲግሬዲሽን) አውግዘዋል፡፡ ወደፊት እንደማይከሰትም ተስፋ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰርቆ አደሮች››፣ በሰርቶ አደሮች ይሸነፋሉ ማለታቸው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ዕድገት አላሳየችም የሚሉትንም ጨለማ አንጋሾች በሥነ አመክንዮ ሞግተዋል፡፡በአንጻሩ ሰዎች በኢትዮጵያ ተስፋ እንዲሞሉ፣ ”ኢትዮጵያ ማሕጸነ ለምለም ናት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ተስፋ ነው፡፡ የትምህርት ጥራቱን አንስተው ሲናገሩም፤ “ጥራት የለም” ከሚሉ ብዙ ተችዎች ጋር አቀራርቧቸዋል። ይህም ማህበረሰቡን  የማድመጥ ችሎታቸውን ያሳያል። ጠ/ሚኒስትሩ ለትምህርት የሰጡት ቦታ ትልቅ ነው፡፡ ትምህርት ለነጻነት ያለውን አስተዋጽኦ ታላቁ የጥቁሮች ታጋይ ፍሬደሪክ ዳግላስ አጽኖት እንደሰጠው መሆኑ ነው፡፡
ይቅርታንና ፍቅርን ማንሳታቸው አንዱ የማህበራዊ ፈውስ ፈላጊነታቸውን ማሳያ ነው፡፡ አንዳንዶች ብሔራዊ እርቅ ሲሉት ሌሎች ብሔራዊ መግባባት ይሉታል። እሳቸው ግን ሦስተኛውን መንገድ መርጠዋል፡፡ ይቅርታ እና ፍቅር፡፡ ይቅርታ ሲሉ፤ በዳይና ተበዳይ አለ ማለታቸው ነው፡፡ ፍቅርን ሲያነሱ፤ ጠብ ወይም ቁርሾ አለ ማለታቸው በመሆኑ የቃላት ንትርኩን ትተው፣ የይቅርታ እና የፍቅር አስፈላጊነትን  ነው ያነሱት፡፡ በሌላ አነጋገር፤ ጠ/ሚኒስትሩ ተግባሩ ላይ ነው ትኩረት ያደረጉ የሚመስሉት፡፡ ለፍቅር ያላቸው ሃሳብ፣ ከደቡብ አፍሪካው ኔልሰን ማንዴላ ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡”እምዬ ምኒልክ” እንዲሉ፣ “እምዬ ፍቅር” እንላቸው ይሆናል፤ማን ያውቃል!?
5ኛ. ተስፈኛነትና እራስን ማግኘትን
ያንጸባረቀ ንግግር   
ድርጅታቸውን ኢህአዴግን እንደሚወዱት ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ባይሆን ኖሮ ይህን ያህል ጊዜ በድርጅቱ ውስጥ አይቆዩም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለድርጅቱ ያላቸው ፍቅር፤ በድርጀቱ አስተሳሰብ  ሙሉ በሙሉ የሟሙ አላደረጋቸውም፡፡ ማልኮም ኤክስ፤ ‹‹እኔ አሁንም የእስልምና እምነት ተከታይ ነኝ፤ ከዚሁ ጋር የጥቁሮች ብሔርተኛ መሪ ነኝ፡፡ የኔ ሐይማኖታዊ ፍልስፍና እስልምና ነው፡፡ ለነብዩ መሐመድ ትልቅ ቦታ አለኝ፡፡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍልስፍናዬ፣ የጥቁር ብሔርተኝነት ነው፡፡›› እንዳለው ነው፡፡ ዶ/ር አብይ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማሕበራዊ ፍልስፍናቸው፤የኢህአዴግ ዓይነት ቢሆንም ከአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፍልስፍና ሌላ የሃይማኖት ፍልስፍናቸው በግልጽ ነጥሮ የወጣበት ንግግር ነው ያቀረቡት፡፡
ለዚህ አንዱ ምስክር፤ እኔ ብቻ ወይም ለእኔ ብቻ ወይም ፓን ሰልፊዝም አያስፈልግም ብለዋል፡፡ ቃል በቃል ለማስቀመጥ፤ ‹‹የኔ ሃሳብ ብቻ ካላሸነፈ ሞቼ እገኛለሁ›› ማለትን ተችተዋል፡፡ የሪፐብሊካኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶ/ር ካርሰን፤ የሪፐብሊካንን እና የዴሞክራትን “የኔ ይሻል፣ የኔ ይሻል” ደረቅ ሙግትን ሲተቹ፤  “My way or the Highway” ማለት አያስፈልግም እንዳሉት ማለት ነው፡፡ የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ፍልስፍና፤ መደማመጥ፤ መመካከር ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ”ይህ ወይም ያኛው ፖሊሲ ወይም አዋጅ የሚለወጠው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ነው” የሚለውን ግትር አቋም አሂሴው ነው ያለፉት - በንግግራቸው፡፡
ሌላው  የፈጣሪን ስም  ማንሳታቸው ካለፉት ሁለት ጠ/ሚኒስትሮች ይለያቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የፈሪሃ እግዚአብሔርን አስተሳሰብና የማሕበረሰቡ የሞራል መሪ ምስረታ ላይ ገንቢ ሚና ይኖረዋል፡፡ “ለምመራው ሕዝብ ስል የማምንበትን እምነት አልናገርም” ሲሉን እንደነበሩት መሪዎች፤ አብይ (ዶ/ር) ድብቅ አልሆኑም። የአዲሱ ትውልድ ትሩፋት ይህ ነው፡፡ ግልጽነት!!! የተግባር ፈፋውን ይሻገሩት ይሆን? እግዚአብሔር ይርዳቸው፤ ሰውም ይስጣቸው፡፡ የኦሮሞው ታሪክ ፀሃፊ ዓፅመ ጊዮርጊስ፤ “አቤቱ እባክህ ጌታዬ፤ ምኒልክን ከክፉ …ጠብቃቸው” እንዳለው፤ እኔም “አቤቱ  ጌታዬ፤ እባክህ አዲሱን ጠ/ሚኒስትር ከእንቅፋቶች ሁሉ ጠብቃቸው፣ መከናወንንም እንደ ታላላቆቹ መሪዎቻችን ስጣቸው፣ የታላላቆቹን መሪዎች ድካምንስ አርቅላቸው። ኢትዮጵያውያን እፎይ ብለው ይኖሩ ዘንድ!!” እላለሁ፡፡

 ተወዳጁ ሸገር 102.1 ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ፤ “ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር” የሚለውን ቃል እንደ መፈክር በማስተጋባት ይታወቃል። ከመፈክርም በላይ ግን የጣቢያው መሪ ቃል ሆኗል፡፡ የሬዲዮ ጣቢያው የፕሮግራሞች መክፈቻና መዝጊያ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የሸገር ሬዲዮ ሌላ ስሙ እስከ መሆን ደርሷል - “ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር”!! በሚያስገርም ሁኔታ ግን ሸገር ይሄን ቃል መጠቀሙ የማያስደስታቸው ወገኖች እንዳሉ የጣቢያው ሃላፊዎች ይናገራሉ። “የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች” ለሚል ፍረጃም ዳርጓቸዋል፡፡ “ይሄን ቃል ለምን እንደማይወዱት ግን አናውቅም” ይላሉ - ሃላፊዎቹ፡፡
እንዲያም ሆኖ ይህ በሸገር ለዓመታት ሲዘመር የዘለቀው “ኢትየጵያ ለዘለዓለም ትኑር” የሚል የመልካም ምኞት ቃል፣ በሬዲዮ ጣቢያው ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎች የሚያዜሙት ቃል እየሆነ መጥቷል። አዲሱ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትርም ታሪካዊውን ንግግራቸውን የቋጩት በዚህ ቃል ነው፡፡ ሸገሮች ምን ተሰምቷቸው ይሆን? ለመሆኑ ቃሉን ለጣቢያቸው የመጠቀም ሃሳብ ከየት መነጨ? ምን ተግዳሮትስ ገጠማቸው? የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ ሸገር ሬዲዮን ከመሰረቱትና ከሚመሩት አንዱ የሆነውን አርቲስት ተፈሪ ዓለሙን በዚህ ዙሪያ አነጋግሮታል፡፡
             

    “ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር” የሚለውን መሪ ቃል መጠቀም የጀመራችሁት እንዴት ነው?
 ከዛሬ 19 ዓመት በፊት በኤፍኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ላይ የ”ጨዋታ” ፕሮግራምን በጀመርን ወቅት ፕሮግራማችንን ስናስተዋውቅ፣ ”ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር” እንል ነበር፡፡ በመጀመሪያ የ”ጨዋታ” ፕሮግራምን ስናዘጋጅ ዝም ብለን ጀመርነው፡፡ ከዚያ በኋላ የፕሮግራማችን መሪ ቃል (Moto) አደረግነው፡፡
ጣቢያው ውስጥ ተነጋግራችሁበትና ተመካክራችሁበት ነው የጀመራችሁት?
አይደለም፡፡ ስለ ሀገር ጉዳይ በምናነሳ ወቅት በማሳረጊያችን በልማድ “ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር” እንል ነበር፡፡ በኋላ ግን ለምን የፕሮግራማችን መክፈቺያና መዝጊያ አይሆንም ብለን ሲጀመርም ሲጠናቀቅም ቃሉን ወደ መጠቀም ገባን፡፡ በዚህ ሁኔታ እየተለመደ መጣና አጠናክረን ቀጠልንበት። በኋላ እንደውም ያልተገባ ትርጉም ሲሰጠው፣ እኛ አጠናክረን ነው  የቀጠልንበት፡፡ አሁን ግን ሸገር ላይ የምንጠቀምበት አውቀን፣ ሆን ብለን መሪ ቃላችን (Moto) በማድረግ ነው፡፡  
መሪ ቃሉን መጠቀም ከጀመራችሁ በኋላ የገጠማችሁ ተግዳሮት ነበር?
ብዙ ጊዜ ቃሉ እንዲባል አይፈለግም ነበር። በወቅቱ እንደውም አንድ የጣቢያው ኃላፊ፤ ”ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር የምትሉት የምን መፈክር ነው? በመፈክር ሃገር አያድግም” ብለው አነጋግረውን ነበር። በወቅቱ እኔም፤ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ብትኖር ምን ችግር አለው?” ብዬ ለመመለስ ሞክሬ ነበር፡፡ እሳቸው ግን “አይ ተፈሪ፤ ልክ እናንተ ቃሉን ስትሉት፣ ሀገሪቷ ላይ ችግር ያለ ይመስላል” ብለውኛል፡፡ ከዚህ ውጭ ሌሎች ለምን ቃሉን እንደማይወዱት አይገባኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ደስ አይላቸውም ነበር፡፡ “የትኛዋ ኢትዮጵያ…?” ምናምን በሚል ለማጣጣል ነው የሚሞከረው፡፡ መቼም “የዚህኛው የዚያኛው መንግሥት ኢትዮጵያ” ማለት አይቻልም፡፡ ግን ቃሉ አይወደድም ነበር፡፡
ኃላፊዎች ከማነጋገር ባለፈ የወሰዱት እርምጃ የለም?
የለም፡፡ ዝም ብለው “ለምንድን ነው የምትጠቀሙት” ነበር የሚሉት፡፡ እኛም ክርክራችን፤ “ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ብትኖር ችግሩ ምንድን ነው?” የሚል ነበር። ምናልባት እነሱ ድሮ የሚባል ነገር ስለሆነ እንዲሁ ቃሉ ከብዷቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ሃገር መውደድ ድሮም ነበር፤ አሁንም አለ፡፡ ለሃገር ጥሩ መመኘት ድሮ ኖሮ፣ አሁንም ብትመኝ ምን ችግር አለው? ብዙ ጊዜ ተፅዕኖ ነበር እንጂ ሌላ እርምጃ ውስጥ አልተገባም። አሁን በሸገር ላይ ያሉ ፕሮግራሞች በሙሉ ቃሉን ይጠቀሙበታል። በዚች ቃል ምክንያት “የድሮ ስርአት ናፋቂዎች” የሚሉ ፍረጃዎች መስፋፋት ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም “ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች መንገዳቸውን ይቀጥላሉ” እንደሚባለው እኛም ቀጥለንበታል፡፡
ግን በታሪክ ይህን ቃል መጠቀም የተጀመረው መቼ ነው? ማንስ ጀመረው?
ድሮ ከአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ጀምሮ በንግግሮች ማብቂያ ላይ የሚባል ልማዳዊ ንግግር ነው። ረጅም እድሜ ለንጉሡ ወይም ለጳጳሱ ማለት የተለመደ ነበር። በመጨረሻ ላይም ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር! ይሉ ነበር፡፡ በጣም ጎልቶ መባል የተጀመረው እንደውም ከፋሽስት ወረራ በኋላ ነበር። ምክንያቱም ሃገር ያለመኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በወቅቱ አይታወቅም፡፡ ከወረራው በኋላ ግን በብዙ ንግግር ውስጥ ይገባ ነበር፡፡ እኛም ያንኑ ነው የተጠቀምነው፡፡ ስለ ታሪክ፣ ስለ ማንነት እየተናገርን፣ በዚያው መጠን መደምደሚያችን ይሄ ቃል ነበር፡፡ አሜሪካኖቹም እኮ የራሳቸው የሚሉት፣ ስለ ሀገራቸው የሚግባቡበት የጋራ ቃል አላቸው፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ፤ ይሄን ቃል ባልተለመደ መልኩ ተጠቅመውበታል …
ከአሁን በፊት የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ እዚህ መጥተው ንግግር ሲያደርጉ፣ ሁልጊዜ  ቃሉን ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአማርኛ ነበር ቃሉን የሚሉት፡፡ የቀድሞ ጠ/ሚ ያረፉ ሰሞንም፤ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር የሚለው ቃል፣ ከፎቶግራፋቸው  ጋር ተደርጎ  ይሸጥ ነበር፡፡
ዶ/ር አብይ በንግግራቸው መዝጊያ ላይ  ይሄን ቃል በመጠቀማቸው ምን ተሰማህ?
ለኛማ ደስ ነው የሚለን፡፡ ሁሉም ሰው ቢያስተጋባው መልካም ነው፡፡ ሁሉም እየተቀበለው ሲሄድ፣ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር መባሉ ልክ እንደነበርን ያረጋግጥልናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ሰው ቢለው ደስ ይለኛል፡፡ የዕለት ፀሎታችን ቢሆን ደስ ይለናል። ለሀገራችን ያለንን ምኞት የምንገልፅበት ስለሆነ ቃሉ መልካም ነው፡፡