Administrator
Friday, 05 September 2025 16:18
ኢትዮጵያ ከ50 ሚ. በላይ ጎብኚዎች ትጠብቃለች
ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ50 ሚ. በላይ የሃገር ውስጥ ጎብኚዎችን እንደምትጠብቅ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ዘርፉ ለኢኮኖሚው አቅም መሆን እንዲችል ሁሉንም በማሳተፍ እንደሚሠራ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ሲካሄድ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት 1.3 ሚሊዮን የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ሀገሪቱን እንደጎበኙ የተጠቆመ ሲሆን፤ ከ48 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ጉብኝት አድርገዋል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም፣ 228 ኢንቨስተሮችን ወደ ዘርፉ መሳብ እንደተቻለና በ “ቪዚት ኢትዮጵያ” የዲጂታል አሠራር የቱሪዝም ሀብትን የማስተዋወቅ ሥራ መከናወኑን ስፑትኒክ የሚኒስቴር መ/ቤቱን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በበጀት ዓመቱ የሰላም ሁኔታና የሎጀስቲክስ ጉድለት እንዲሁም የሆቴል ደረጃ ምደባ በወቅቱ አለመቅረቡ በተግዳሮነት ተጠቅሰዋል፡፡


See insights and ads
Boost post
All reactions:
1919
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Friday, 05 September 2025 16:16
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ይጀምራሉ፤ ሌሎች መሪዎች ይከተላሉ
• ኢትዮጵያ የአፍሪካ መሪ እየሆነች ነው!!
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግስትንና ብሔራዊ ቤተ መንግስትን በማደስ ከዚህ ቀደም የተደበቀ የህዝብ ንብረትን ለህዝብ ክፍት አድርገዋል። የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የተናገሩትን እነሆ...
- ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የወንዞች ዳር ልማትን ሲጀምሩ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አርአያቸውን ተከትለው የወንዞች ዳር ልማት አስጀምረዋል...
- ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኮሪደር ልማትን ከጀመሩ በኋላ የኬንያ፣ የሶማሊያ፣ የደቡብ አፍሪካና የጋና ፕሬዚዳንቶች እንዲሁ አድርገዋል...
-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አረንጓዴ አሻራቸውን በጀመሩበት ወቅት የኬንያ፣ የሩዋንዳ፣ የኡጋንዳና የናይጄሪያ ፕሬዚዳንቶች ይህንኑ መንገድ ተከትለዋል...
- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ሲገነቡ፣ ቻይና የሳይንስ ሙዚየም ዲዛይን በማድረግ እንድትረዳው ያልጠየቀ አፍሪካዊ መሪ አልነበረም። ምንም እንኳን እስካሁን የተሳካለት አንድም የአፍሪካ መሪ ባይኖርም...
- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የስንዴ እርሻ ጀመሩ፤ ከዚያ በኋላ የስንዴ እርሻ ያልጀመረ አፍሪካዊ መሪ የለም። እስካሁን ውጤት ያስመዘገበ የአፍሪካ መሪ ባይኖርም..
ምንጭ፡- Great Africa



Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 05 September 2025 16:15
ሕብረቱ፣ የአፍሪካን ፍልሰትን ለመግታት 68.3 ቢ. ዶላር መደበ
• ኢትዮጵያም የበጀት ድጋፉ ተጠቃሚ ናት ተብሏል
አውሮፓ ኅብረት፣ ከአፍሪካ የሚነሳ ኢመደበኛ ፍልሰትን ለመግታት፣ ለአፍሪካ 68 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር አዲስ በጀት መያዙ ተጠቆመ፡፡ ኢትዮጵያም የዚሁ የበጀት ድጋፍ ተጠቃሚ እንደምትኾን ተገልጧል።
ኅብረቱ ለአፍሪካ በተለያዩ ድጋፎች መልክ እንዲሠጥ የያዘው በጀት፣ ከአውሮፓዊያኑ 2028 እስከ 2034 ተግባራዊ የሚደረግ ነው።
የገንዘብ ድጋፉ፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት መስፋፋት፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለድህነት ቅነሳ፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለሰላምና መረጋጋት፣ ለግጭት መከላከልና ለድኅረ-ግጭት መልሶ ግንባታ የሚውል መሆኑን ዋዜማ ዘግባለች።
እቅዱ የኢመደበኛ ፍልሰት፣ የግዳጅ መፈናቀልና የአለመረጋጋት መሠረታዊ ምክንያቶችን መቅረፍ ይችላል ተብሎ ታምኖበታል።
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 05 September 2025 16:15
"ለመንግሥት ሠራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል"
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ለመንግሥት ሠራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል ማለቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከአዲሱ በጀቱ አምስት በመቶውን ለውዝፍ ደመወዝ ክፍያ ለማዋል ማቀዱን መናገሩንም ዘገባው ጠቅሷል።
ፕሬዝዳንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ አስተዳደራቸው የክልሉ መምህራን ባነሱት የውዝፍ ደሞዝ ጥያቄ አሉታዊ ምላሽ እንደማይሰጥም ዛሬ መቀሌ ውስጥ በትምህርት ዙሪያ በተካሄደ ምክክር ላይ ገልጸዋል ያለው ዘገባው፣ ሆኖም በቅድሚያ ስምምነት ሊደረስባቸው የሚገቡ አንዳንድ የፋይናንስ ጉዳዮች መኖራቸውን መጠቆማቸውን ጠቅሷል።
-ዋዜማ-
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 05 September 2025 10:25
ግብፅና ሱዳን የሕዳሴው ግድብ "ዘላቂ ስጋት" ደቅኖብናል አሉ
ግድቡ ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ ከሰዋል
ግብፅና ሱዳን ኢትዮጵያ የገነባችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በምሥራቅ የናይልተፋሰስ አገራት ላይ ዘላቂ ስጋት ደቅኗል አሉ።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ አጠናቅቃ ለምረቃ እየተዘጋጀች ባለችብት ጊዜ፣ የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይና የመስኖ ሚኒስትሮች በካይሮ ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ባወጡት መግለጫ ነው ስጋታቸውን የገለጹት።
ሚኒስትሮቹ ትላንት ረቡዕ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ግድቡ "በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ መረጋጋት ላይ ቀጣይነት ያለው ስጋት" መደቀኑን አመልክተዋል።
የሁለቱ አገራት ሚኒስትሮች በካይሮ ባደረጉት በዚህ ስብሰባ ላይ፣ ግድቡ ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰና በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር መሆኑን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ ለመሙላት የወሰደችውን የተናጠል እርምጃ የተቃወሙት አገራቱ፤ የውሃ ደኅንነታቸው ጉዳይ አንድና የማይነጣጠል መሆኑን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
አክለውም፤ "ኢትዮጵያ ትብብርን ዳግም ለማጠናከር በምሥራቃዊ የናይል ተፋሰስ አገራት ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ መቀየር አለባት" ብለዋል።
ግብፅና ሱዳን በዚህ መግለጫቸው፣ ሌሎች የናይል ተፋሰስ አገራትን ተሳትፎ ውድቅ አድርገው፣ ጉዳዩ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና ሱዳን መካከል ብቻ መታየት እንዳለበት አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ ሀብታሙ ኢተፋ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለመነጋገር አሁንም ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል። ነገር ግን ግብፅና ሱዳን የግድቡን ውሃ ሙሌትና ቀጣይ ሥራን በሚመለከት የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነትን መሠረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ይፈልጋሉ ብለዋል።
በኢትዮጵያ በኩል ግን ይህ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና ሁሉንም የተፋሰሱ አገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት እንዲደረስ እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 04 September 2025 11:18
"ወይ አዲስ አበባ"ን በአዲስ ዓመት ዋዜማ
“ወይ አዲስ አበባ” መጽሔት .. በኅትመት ዋጋ መናር ምክንያት ከተቋረጠች በኋላ በአዲስ ዓመት ዋዜማ፣ የፊታችን ቅዳሜ .. ዳግም ለኅትመት በቅታ ከእጃችሁ ትገባለች።
"ምነው ጠፋችሁ?!" የሚለው ጥያቄ ላለፉት ዓመታት ከብዙ አንባቢዎቻችን ለዝግጅት ክፍላችን የቀረበ ጥያቄ ነበር። "ተመለሱ" ያሉንም ብዙዎች ናቸው። .. እነሆ ለቀረቡልን የ"ተመለሱ" ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያደረግናቸው ጥረቶች ተሳክተው በአዲስ መንገድ፣ በአዲስ መንፈስ፣ ከቀደመው በተሻለ ጥራት መጥተናል። ከአሁን በኋላም በየሁለት ወሩ እየታተመች ለንባብ ትበቃለች።
"ወይ አዲስ አበባ"ን በአዲስ ዓመት ዋዜማ! ...
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Thursday, 04 September 2025 10:51
ግጥም ሲጥም በብሔራዊ ቤተመንግስት AHOC
'እንዲህ ያለም የለ!' የተሰኘ ጥዑም የግጥም ስብስብ መጽሐፉን እንዘክራለን።
በሰዓቱ ተገኙና በሀብታሙና በጓደኞቹ በሚቀርቡ ጥዑም ግጥሞች ሰላምን ሸምቱ፤ ጎበዝ ገጣሚያንን ተዋወቁ!
በፍል ውሃ በኩል ባለው የብሔራዊ ቤተመንግስት መግቢያ (5ኛ በር) ቢገቡ አዲስ ሃውስ ኦፍ ካልቸርን በቀላሉ ያገኙታል።
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Thursday, 04 September 2025 10:45
"የብሌን አንዳች
''የብሌን አንዳች'' የተሰኘው የጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ መጽሐፍ አርብ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ይመረቃል።
ቦታ፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ፣ አራት ኪሎ፣ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
ሰዓት፡ ከቀኑ 10 ሰዓት
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:37
1500ኛው የነቢዩ መሐመድ መውሊድ (ልደት) ነገ ይከበራል
ነገ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባልና የወጣቶችና ሴቶች ዘርፍ ተጠሪ ሼህ አብድልሃሚድ አህመድ፤ መውሊድ ሲከበር የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የታላቁ አንዋር መስጊድ ኢማም ሼህ ጠሃ መሐመድ ሃሩን በበኩላቸው፤ " ነቢዩ መሐመድ ለዓለም ሰላምና ለሰው ልጆች እዝነት የተላኩና የሰሩ በመሆናቸው ሙስሊሙ ማህበረሰቡ አርዓያነታቸውን ሊከተል ይገባል" ብለዋል።
በመውሊድ በዓል አከባበር ወቅት የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱና በዓሉ የእስልምና አስተምህሮን ለእምነቱ ተከታዮች ለማስረፅ እንደሚረዳም ገልጸዋል፡፡
በዓሉ ነገ ሐሙስ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር ሲሆን፤ በአዲስ አበባም በታላቁ አንዋር መስጊድ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም ተጠቁሟል፡፡


See insights and ads
Boost post
All reactions:
1010
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 03 September 2025 18:30
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ከሃላፊነታቸው ለቀቁ
"ለምንወዳት ሀገራችን ማገልገል ትልቅ እርካታ የሚሰጥ ነገር ነው"
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 10ኛው ገዥ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ፣ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
አቶ ማሞ ምህረቱ፣ ለሰባት ዓመታት ያገለገሉበትን የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት መልቀቃቸውን በዛሬው ዕለት በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡
"ከ7 ዓመታት የሕዝብ አገልግሎት በኋላ ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን ከመንግሥት ኃላፊነት ለመልቀቅ ወስኛለሁ" ያሉት አቶ ማሞ፤ "ለምንወዳት ሀገራችን ማገልገል ትልቅ እርካታ የሚሰጥ ነገር ነው" ብለዋል፡፡
በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት የቤት-አስተዳደር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ውስጥ በመስራታቸው እንዲሁም፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን በገዥነት በመምራታቸው ከፍተኛ እርካታ ማግኘታቸውን በመግለጽ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አክለውም፤ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እንደመሆኔ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ከ50 ዓመታት ወዲህ ትልቁ የሚባለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርቻለሁ" ብሏል፡፡
"በእነዚህ ማሻሻያዎች ምክንያት የውጭ ምንዛሪ ከሦስት እጥፍ በላይ ጨምሯል፤ ይህም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል" ያሉት አቶ ማሞ፤ የዋጋ ግሽበት በሰባት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን እንዲሁም የዲጂታል ክፍያዎች ከ10 እጥፍ በላይ መጨመራቸውን አስረድተዋል፡፡
አክለውም፤ "የብሔራዊ ባንክ ቡድንና የሥራ ባልደረቦቻችን ወደር ለሌለው ሙያዊ ብቃትና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የሥራ ሥነ ምግባር ምስጋና ይግባውና፤ በዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ወደ ገበያ ተኮር የምንዛሪ ተመን ሥርዓት በመሸጋገር የባንኩን የራስ ገዝ አስተዳደር በአዲስ ሕግ እንዲቋቋም አግዘናል" ብለዋል፡፡
የፋይናንስ ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ በመስፋፋቱ ከ5 ትሪሊየን በላይ ሀብት መድረሱን በመግለጽ፤ እነዚህና ሌሎችም የመንግሥት ታሪካዊ ክንዋኔዎች አስደናቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
አቶ ማሞ በመጨረሻም፤ "ዛሬ ብሔራዊ ባንክን ለቅቄ ስወጣ የዘመናዊ ማዕከላዊ ባንክ ዓላማና ራዕይ ሊደረስበት እንደሚችል እርግጠኛ በመሆን ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
