Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ተጫዋችና ቅን እንደሆነ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ይመሰክሩለታል፡፡ ባለፈው ሐሙስ በአዲሱ አልበም ዙሪያ ቃለምልልስ  ሳደርግለት በሳቅና በፈገግታ በሀዘን እየተመላለሰ ነበር ሃሳቡን የገለፀው፡፡ የመጀመሪያ አልበሙ ከወጣ ከሰባት ዓመት በኋላ ሰሞኑን ለአድማጭ ጆሮ የደረሰውን አልበሙን ‹‹ናፍቆትና ፍቅር›› ብሎታል፡፡ በቃለምልልሱ ወቅት ሞባይሉ ስራ አልፈታም፤ ስለ አልበሙ አስተያየት፣ አድናቆት የሚሰጡ አድማጮች ሲደውሉለት ነበር፡፡ ሚካኤል በላይነህ በህይወቱ እና በሙያው ዙሪያ ከጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው

ለቀረበለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሽ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

እንዴት ወደ ሙዚቃ ሕይወት መጣህ?

የተወለድኩት አዲስ አበባ ሲሆን የልጅነት ዘመኔን ያሳለፍኩት ኮተቤ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

Saturday, 29 September 2012 09:53

ሤራዎችን የወለደው “ሤራ”

“አፄ ኃይለሥላሴ በ1953 ዓ.ም. ለተደረገባቸው መፈንቅለ መንግሥት ምክንያቱ ራሳቸው ንጉሡ ናቸው” የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ መጽሐፍ ስላገኘሁ ለዛሬ ዳሰሳና ቅኝት መርጬዋለሁ፡፡ በ2003 ዓ.ም ታትሞ ለአንባቢያን የቀረበው መጽሐፍ “ሤራ! በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት” በሚል ርዕስ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ ልቦለድ መሆኑን ደራሲው ወርቅአፈራሁ ከበደ ገልፀዋል፡፡

“አደራ ሳላቀብል

አልሞትም” ያለች ነፍስ

Saturday, 29 September 2012 09:46

የቤት ስራው

በአ.አ ዩኒቨርስቲ በማታው ክፍለ ጊዜ የሶስተኛ ዓመት የሥነ ጽሁፍ ተማሪ ነኝ፡፡

የመማሪያ ክፍላችን አየር በተማሪዎች የጭንቀት ትንፋሽ ዳምኗል፡፡ ውጥረቱ ከዕለት ወደ ዕለት እያየለ ሄዶ፣ ዛሬ የመጨረሻው ጡዘት ላይ ደርሷል፡፡ ለወትሮው መምህሩ እስኪመጡ የነበረው ድባብ እንዲህ የተቀዛቀዘ አልነበረም፡፡ከቀልደኛነቱ የተነሳ በፍልቅልቅ ሴቶች ተከቦ የሚያመሸውና ወደፊት የተዋጣለት የኮሜዲ ፀሐፊ እንደሚሆን የተማመንንበት ብርሃኑ ግንባሩን አኮማትሮ ከፊቱ የተዘረጋው ወረቀት ላይ አቀርቅሯል፡፡ አይደለም በዚህ ነፃ ጊዜ፤ በትምህርት ሰዓት እንኳ በነዛ ውብ አይኖቿ የምታጫውተኝ ሀና፣ ከነመፈጠሬም ረስታኝ ከዚያች የማትረባ ጓደኛዋ ጋር ወረቀቷን ትናበባለች፡፡

ብሎ እንዲጠይቅ ፈልጌያለሁ”  ድምፃዊ ፀጋዬ ስሜ

በአሁኑ አልበሜ ላይ አንድ ሁለት ቦታ ላይ በጉሮሮ የምጠቀምባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ በኳየር የሚሰሩ ስራዎች ወደ መድረክ ለማምጣት ሲያስቸግር ይታያል፡፡ ለካሴቱ ስራ ኳየር ተጠቅመን ከሆነ በየሄድንበት መድረክ ሁሉ ኳየሩን ይዞ መሄድ የግድ ይሆናል፡፡ ያለበለዚያ ሰው በካሴት የሰማውን የሚመጥን ስራ ማቅረብ አንችልም፡፡ ሙሉ ለሙሉ ባህሉን በጠበቀ መልኩ በከበሮ፣ በእጅ ጭብጨባና በድምፅ /በጉሮሮ ማጀብ ጭምር/ በመጫወት የሚታወቁና በጉራጌ ሰርግ ቤቶች የሚጫወቱ ጎበዝ ልጆች እየታዩ ነው፡፡

በእርግጥ የቀዳሚ እና የተከታይ ደረጃ ለመስጠት ያዳግተኛል፡፡ ይስማዕከ ግን በአማርኛ ልብወለድ ውስጥ ከተለመደው አብራሪነት፣ ገላጭነት፣ (ለምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩም እንደሚተቸው ቀኑ ደመናማ ነው ሰማዩ ብልጭ ድርግም ይላል…) እያልን ከምንወርድበት ዘልማዳዊ ጥንወት መንጭቆ ሊያወጣን ይታትራል፡፡ የ”ዣንቶዣራ” ቁጥር አንድ እምርታ ሁነትን ከማብራራት እና ከመተረክ ይልቅ በገጸ ባሕርያት አማካኝነት የሰላ ትችትን መሰንዘር፣ ጥልቅ ፍልስፍናን መወንጨፍ፣ የሕዝቡን ብሶት ማስተጋባት ወዘተ. ነው፡፡ በህዳሴ እንቅስቀሴአችን ውስጥ ያላየነውን እናይ ዘንድ (ግልብ ስልጣኔአችንን እየገለበ) የሚሞግተው ኪራኮስ በተባለ ገጸ ባሕርይ አማካኝነት ነው፡፡

እርጅና ያልሆነ ሰንፍና ካልተጠናወተኝ በስተቀር አስታውሳለሁ! ከአንድ ድፍን ዓመት በፊት መጽሐፍ እያሳተሙ ከደራሲ ወገን የሚሆኑ ሰዎች እንደመብዛታቸው ፖለቲካችንን እና የአስተዳዳሪዎቻችንን የአስተዳደር ዘይቤ የሚደፍር ትጉህ ብዕረኛ እምብዛም እንደሌለ ጽፌ ነበር፡፡ በዚህኛው ጋዜጣ አልነበረም፡፡ ያኔ በዕውቀቱ ሥዩምን ስለፖለቲካዊ ሽሙጡ፣ ይስማዕከ ወርቁን ስለ የሀገር ፍቅር ቀስቃሽ ጽሑፎቹ መጥቀሴን ግን ኮራሁበት፡፡

Saturday, 15 September 2012 13:13

“አፍሮጋዳ” እና ሌሊሳ ግርማ

ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በጥበቡ፣ በሀብቱና በዕውቀቱ ብዛት የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞንን መወዳደር የሚችል ማንም አልነበረም፤ የለምም ይባላል፡፡ ሁሉ ነገር ሞልቶ የተረፈው ንጉሥ ሰለሞን፤ የምድር ላይ ድካሙን፣ የሕይወትን ፋይዳና ዓለምን ገምግሞ በመጨረሻ የደረሰበት ድምዳሜ “ሁሉም ነገር ከንቱ፤ የከንቱ ከንቱ” የሚል ሆኗል፡፡ እንዲህም ሆኖ በፈጣሪው ላይ ያለው መታመን ግን ጨርሶ አልጠፋም፡፡ ለዚህም ነው በንጉሥ ሰለሞን የተፃፉት መፃሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ሆነው ለዛሬ መድረስ የቻሉት፡፡

Saturday, 15 September 2012 13:32

ጳጉሜ 10

ዛሬ ቀኑ ጳጉሜ “አስር” ነው፡፡ ለኔ፡፡ ለእናንተ መስከረም “አምስት” ሊሆን ይችላል፡፡ መብታችሁ ነው፤ አይመለከተኝም፡፡

ዝናቡ አላቆመም፡፡ ውሸትም አላባራም፡፡ የኑሮ ውድነት ከህመሙ አላገገመም፡፡ ስለዚህ ጳጉሜ ለእኔ ተራዝሟል፡፡ ተስፋዬ ተግባሬ ሲሆን አዲሱ አመት ይጀምራል፡፡ጳጉሜ አስር ለእኔ ቀን መቁጠሪያ ብቻ በቀይ የተፃፈ … በቀይ የተፃፈው አመት በአል መሆኑን ለመግለፅ ስለሆነ… ብቻዬን በአሉን አክብሬ እውላለሁ፡፡ጳጉሜ አስር፡- “የእውነት ቀን” ነው፡፡ ታስቦና ተከብሮ ይውላል፡፡ የውሸት ዝናብ በእውነት ፀሃይ ደርቆ …ውዱ ኑሮም ረክሶ ይውላል፡፡ “ስለ ነገ፤ ራሱ ነገ ይጨነቅ… ዛሬ የራሱ ብዙ ጭንቀቶች አሉበትና” ይላል፤ ክርስቶስ “በተራራ ስብከቱ” ላይ፡፡“የእውነት ቀንን” ለማክበር ከክርስቶስ አስተምሮቶች ትዝታ በላይ የሚያገለግለኝ የለም፡፡ ከክርስቶስ በላይ የክርስቶስ ትምህርቶች ይበልጡብኛል፡፡ ጳጉሜ ላይ በራሴ ቀን መቁጠሪያ ውስጥ ተቆጥሬ ለቀረሁት እኔ፡፡

Monday, 10 September 2012 14:37

የእንቁጣጣሽ ስጦታ

…እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ

አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡

ለምለም አረንጓዴ…

ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት

የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡

በዚሁ ጋዜጣ ላይ አያሌ ሥነጽሑፋዊ ሂሶችን አስነብቦናል፡፡ በልሲለውም ከሥነጽሑፋዊ ሂሶች ወጣ ይልና ማህበራዊ ሂሶችንም ይከትባል፡ ታዲያ ሥነጽሑፋዊም ይሁን ማህበራዊ ሂስ ሲጽፍ ፈራ ተባ እያለ አይደለም፡፡ ጨከን ኮስተር ብሎ ነው፡፡ ልቡ ይመንበት እንጂ ጽሑፉ ከወጣ በኋላ ስለሚፈጠረው ውዝግብ ወይም ስለሚነሳው አቧራ ብዙም አይጨነቅም፡፡ (ወይስ አቧራ ማስነሳቱን ይፈልገው ይሆን;) ለዚህ መልስ ለመስጠት ራሱን ባለቤቱን መሆን ያስፈልጋል - ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ሃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይን፡፡ አሁን ስለማንእየደሰኮርኩላችሁ እንደሆነ አውቃችኋልና በቀጥታ ወደ ጉዳዬ መግባት እችላለሁ፡፡ እንግዲህ በዚህ ጽሑፌ ለመቃኘትም ሆነ ለማስቃኘት የምሞክረው ሃያሲውን ወይም ሁለት ረዥም ልብወለዶች ከምናቡ አምጦ ያበረከተልንን ዓለማየሁ ገላጋይን አይደለም፡፡

Saturday, 01 September 2012 11:45

ንጉሥም እንደ ሰው!

ያው ሰው - ኖሮ ኖሮ

ኑሮን ዞሮ - ዞሮ

ደፈና ሕይወቱን

ወይ ኢምንት ጉልበቱን

በጊዜ እየኖረ - ጊዜውን ጠብቆ - በጊዜ እየሞተ

ስንቱ በሞት ሰፈር - በዛ በረከተ

ሞት ላይሞት ሰው ሞተ

አፈረ - ባከነ - ባዘተ - ቃተተ፡፡