Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Tuesday, 01 November 2011 14:14

ጋዜጣን በፀፀት

የጋዜጣ አንባቢና የውሃ-ሙላት አንድ ነው፡፡ ጋዜጠኛና ለውሃ-ሙላት የዘፈነው አዝማሪም እንደዚያው ተመሳሳይ፡፡ ኧረ እንደውም ተተካኪ ናቸው፡፡ ለጋዜጣ መፃፍ ለውሃ ሙላት እንደመዝፈን ነው፡፡ የሰማው ሲሄድ ያልሰማው ይመጣል፡፡ ቆሞ የሚያዳምጥ ጋዜጣ አንባቢና የውሃ ሙላት የለም፡፡ እየሄደ አዳምጦህ፣ እያዳመጠህ ይሄዳል…

Tuesday, 01 November 2011 14:08

የ11 ዓመት እስር በመጽሐፍ

በ1969 ዓ.ም የሶማሊያ ወረራ ምክንያት ለ11 ዓመታት በእስር ከቆዩት ኢትዮጵያዊያን አንዷ የነበረችው ከበደች ተክለአብ፤ በ1983 ዓ.ም አሳትማ ለአንባቢያን ያቀረበችው መጽሐፍ “የት ነው” የሚል ርዕስ የተሰጠው የግጥም መድበል ሲሆን በሥነ ግጥምም ቢሆን ርዕሰ ጉዳዩን የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ላይ በማድረግ በአገራችን ፈር ቀዳጅ መፅሀፍ እንደሆነ ይነገራል፡፡

አዲሱ ፊልምሽ እንዴት ነው… ጥሩ ፊልም ሠርቻለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? 
በእኔ በኩል ሠርቻለሁ ነው የምለው፤ ሌላውን ደግሞ ሕዝብ ሊያረጋግጥልኝ ይችላል፡፡ ፊልም የአንድ ሰው የምናብ ውጤት ነው፡፡ ተመልካቹን ሁሉ አረካለሁ ማለት ባይቻልም ይኼ የእኔ ፈጠራ ነው ብለህ ስትሰጠው ደስ ካለው ደስ ይልሃል፡፡
ባለፈው ወር “ባለታክሲው” በዲቪዲ ወጥቷል፡፡ ከልፋትና ከገበያ አንፃር በሲኒማ ቤት ማሳየት ይሻላል በዲቪዲ መሸጥ?

ሙሉነት ተሰማኝ፡፡ የመጉድል ፍላጐት በፅኑ አደረብኝ፤ ለመፃፍ ተነሳሁ፡፡ መጉደል ማለት ማጣት አይደለም፡፡ የሀሳብ ደም በመጉደል የሚተካ ነው፡፡ መሆኑ ራሱ የፍቅር ባህርይ አለው፡፡ 
መቶ ቢሊዮን ፀሐዮች በእኛ ጋላክሲ ውስጥ፣ መቶ ቢሊዮን የኒውሮን ህዋሶች ደግሞ በእኔ የራስ ቅል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ምን ያህል የተራራቅን እና የተለያየን ነገሮች እንደሆንን ፀሐይ እና እኔ ወይንም ጋላክሲዋ (ሚልኪ ዌይ) አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ሙሉነት እንደዚህም ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ሙሉነት የተነጣጠሉ ማንነቶችን እና ተቃርኗቸውን በአንድነት የሚሽር ልዕለ ተአምር ነው፡፡ የተአምሩ ስም “ፍቅር” ይባላል፡፡

ጃኪ ኢቫንቾ
ጃኪ ኢቫንቾ የ11 አመት አሜሪካዊ ነች - በአስደናቂ የድምፅ ችሎታ አሜሪካዊያንን ያማለለች፡፡ አምና በ..ጎት ታለንት.. ውድድር ላይ ስትዘፍን፤ በድምጿ የተማረኩ አሜሪካዊያን ልብ ውስጥ ገባች፡፡ ጃኪ ኢቫንቾ፤ በጣም ተወዳጅ የሆነችው በተራ ዘፈን አይደለም - በጣም ከባድ እንደሆነ በሚነገርለት የኦፔራ አዘፋፈን እንጂ፡፡ ምን ልታስቡ እንደምትችሉ ይገባኛል፡፡ ከኢትዮጵያን አይዶል ተወዳዳሪዋ ከሃና ግርማ ጋር ተመሳሳይነታቸው ይገርማል - በእድሜያቸው፣ በኦፔራ አዘፋፈናቸው፣ በአስደናቂ የድምፅ አቅማቸው፣ ከውድድር ባገኙት ተወዳጅነት...፡፡ አጀማመራቸውስ?

በ1955 ዓ.ም በአሜሪካ ኢሊኖይስ ግዛት የተወለደው ቢል ላስዌል የታወቀ ሙዚቃ አቀናባሪ እና ፕሮዱዩሰር ነው፡፡ ለ25 ዓመታት በሙዚቃ ሙያ የዘለቀው አሜሪካዊው አርቲስት፤ ከ700 በላይ አልበሞች ፕሮዲዩስ አድርጓል፡፡ በሙዚቃ ዙሪያ በርካታ ጥናትና ምርምር በማድረግና አዳዲስ አቀራረቦችን በመፍጠር በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ግንባር ቀደም ባለሞያ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ የሬጌን ሙዚቃና የቦብ ማርሌን ሥራዎች ለዓለም በማስተዋወቅ ከሚታወቀው ክሪስ ብላክ ዌል ጋር በመስራት የራሱን አስተዋኦ ያበረከተ አርቲስት ነው፡፡  ይሄ ባለሙያ የታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት ድምፃዊ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ባለቤት ነው፡፡ ቢል ላስዌል በጂጂ ተወዳጅ ሙዚቃዎች ውስጥ በአቀናባሪነትና በፕሮዲዩሰርነት አሻራውን አሳርፏል፡፡ ጳጉሜ 6 ቀን 2003 ዓ.ም ኢትዮጵያን ከመልቀቁ ከሁለት ሰዓት በፊት ካረፈበት የኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ውስጥ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በሙያውና በህይወቱ ዙሪያ አነጋግራዋለች፡፡

ሐምሌ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. እዚሁ ጋዜጣ ላይ ..ፖለቲካና የደራሲ ፖለቲከኞች.. በሚል ርዕስ በደራሲ
አለማየሁ ገላጋይ የተጻፈውን ጽሁፍ ””ደራሲW ዋና መሽከርከሪያ ርዕሰ ጉዳያቸው አድርገው የተነሱበት ..የኢትዮጵያ የተገለባባጭ ደራሲ ደሀ አይደለችም... ከጥቂቶቹ ደራሲያን በስተቀር አብዛኞቹ ደራሲያን ጉልበታም የፖለቲካ ወጀብ የሚያስጎነብሳቸው መንፈሰ ድውያን ናቸው.. የሚለው ነው፡፡በተያያዘ ነጥባቸውም ..ፎርመኛ ደራሲዎች አሉን.. ያሏቸውን እነ ብርሀኑ ዘሪሁን፣ ፀጋዬ ገ/መድህንና ሌሎችንም አንስተው ባልተገባ የሀሳብ አካሄድ ወይም ውቅያኖስን በጭልፋ... በሚመስል ቁንጽል ዕይታ ሀሳባቸውን ሲያስነብቡን በዝምታ አለፍን፡፡ እሳቸው ግን ዝምታችንን ..አበጀህ.. እንደመባል ቆጥረውት ቀጥለውበታል፡፡

..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. ሲዳሰስ
ባለፈው ሳምንት ቢሮዬ የመጣልኝ    መሃፍ ለየት ያለ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ ጉጉት የሚፈጥር     ዓይነት ነው፡፡ ..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. ስለሚል ምስጢሮቹ     ምን ይሆኑ በሚል ለንባብ ይገፋፋል፡፡ መሃፉ በዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ተፈራ የተዘጋጀነው፡፡ በርግጥ ደራሲው መጽሐፍ ለማሳተም አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም ያሳተማቸው ስምንት መፃህፍት ያሉት ሲሆን በቅርቡ የሚያሳትማቸውን ሰባት መፃህፍት ዝርዝር በዚህኛው መሃፍ ጀርባ ላይ አስፍሯል፡፡ ቀደም ሲል ካሳተማቸው መካከል ..ክርስቲያናዊ ጋብቻ.. ቁጥር አንድና ሁለት፣ ..እውነተኛ ፆምና መንፈሳዊነት..፣ ..ነቅዕ ገነት (የነፃነት ምን´ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በቅርቡ ከሚያሳትማቸው ውስጥ አንደኛው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሆን |Football and Spiritual life´ ይሰኛል፡፡

Saturday, 10 September 2011 12:14

የመጽሐፍትነገር

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በ2003 ዓ.ም ከመጽሐፍ
ጋር በተያያዘ ስለተፈጠሩ ክስተቶች ጥቂት ነገሮችን ለማንሳት እንጂ በዓመቱስለተከሰተው ነገር ሁሉ የተሟላ ዳሰሳ ለማቅረብ  አይደለም፡፡ ትኩረቴም     ፖለቲካና ታሪክ ነክ በሆኑት ላይ እንጂ፤ እንደ ልብ ወለድ ወይም የሥነልቦና መጻሕፍትን የመሳሰሉትን አላካተተም፡፡ በመጻሕፍቱ አጠቃላይ ኋና ላይ ካልሆነ የመጻሕፍቱን ግምገማንም የሚያካትት አይደለም፡፡
የመጻሕፍት ምርቃት

Saturday, 10 September 2011 12:03

የኔ ቢጤ

እኔ ላንቺ ግጥም
ቃላት ሣጠራቅም
አላዛር ከደዌው
ድኖ አገገመ
ስለዓለም ከንቱነት
ግጥም አሳተመ፡፡
ለውበትሽ ስንኝ
ፊደል አጥቼልሽ
በየመዘክሩ ስንከራተትልሽ
የእዮብ መከራ
ጭንቅ ዘመኑ አለፈ
..መታገስ ነው ደጉ!..
የሚል መጽሐፍ ፃፈ፡፡
እኔ ላንቺ ግጥም
ቃላት ሳጠራቅም
ውዲቷ አገራችን
እጅግ ተራቀቀች
በኤሌትሪክ ሽቦ
ፍቅር አስተላለፈች፡፡
ሰው ባገደመበት
ባለፈበት ስፍራ
ፍቅር አንፀባርቆ
መውደድ በአምፖል ሠራ፡፡
አንድ የተደበቀ
የተቀበረ ቃል
ድንገት ቢኖር ብዬ
ድንጋይ ስፈነቅል
የፍልስጤም ጉብል
ከእስራኤሏ ቆንጆ
ይቅር ተባብለው
ቀለሱልሽ ጐጆ፡፡
ያንቺነትሽን ምስጢር
ቅኔሽን አይቼ
እጽፍልሽ ነገር
እለው ቃል አጥቼ
ቃላት አልሳካ
ከቶ አልሰምር ብሎኝ
የነበረኝ እንኳ
ነጐደልሽ ጥሎኝ
እናም ስለማምላክ
እያልኩ እዞራለሁ
ካገር አገር እያልኩ
ቃል እለምናለሁ፡፡
ምልዕቲ ኪሮስ