Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

“...እኔ እድሜዬ ወደ ሀያ አምስት አመት የሚሞላኝ ነኝ ፡፡ የ12ኛ ክፍል ትምህርን ጨርሼ ወደዩኒቨርሲቲ ስገባ ከቤተሰቤ ስለተለየሁ የነበረኝን የጤና ችግር የማዋየው ለጉዋደኞቼ ነበር፡፡ ከማህጸኔ የሚፈሰው ፈሳሽ እጅግ የሚዘገንን ነበር፡፡ መልኩ ደስ አይልም ሽታ አለው፡፡ ጉዋደኞቼ ስነግራቸው ብዙዎቹ እኔም አለብኝ የተፈጥሮ ጉዳይ ነወ የሚሉ ነበሩ፡ እኔ ግን በፍጹም ልታገሰው አልቻልኩም፡፡ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቼ የምሄደው በአመት አንድ ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከርቀት የተነሳ ነው፡፡ ወደ ቤተሰቦቼም ስሄድ ችግሩን ተናግሮ ወደ ሐኪምቤት መሄድ ስላስፈራኝ ዝም ነበር የምለው፡፡ በአጠቃላይም ይህንን ችግር ይዤ ከሁለት አመት በላይ ተሰቃየሁ የሚገርመኝ ነገር እናቴ ስለሁኔታዬ በጭራሽ አትጠይቀኝም ነበር፡፡

አዲሱ ፊልምሽ እንዴት ነው… ጥሩ ፊልም ሠርቻለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? 
በእኔ በኩል ሠርቻለሁ ነው የምለው፤ ሌላውን ደግሞ ሕዝብ ሊያረጋግጥልኝ ይችላል፡፡ ፊልም የአንድ ሰው የምናብ ውጤት ነው፡፡ ተመልካቹን ሁሉ አረካለሁ ማለት ባይቻልም ይኼ የእኔ ፈጠራ ነው ብለህ ስትሰጠው ደስ ካለው ደስ ይልሃል፡፡
ባለፈው ወር “ባለታክሲው” በዲቪዲ ወጥቷል፡፡ ከልፋትና ከገበያ አንፃር በሲኒማ ቤት ማሳየት ይሻላል በዲቪዲ መሸጥ?

Saturday, 22 October 2011 11:53

“ሲኒማ ሴፍ” ሥራ ጀመረ

በሁለት ወጣት ባለሐብቶች በቡራዩ ከተማ የተቋቋመው “ሲኒማ ሴፍ” ባለፈው እሁድ “ፔንዱለም” የአማርኛ ፊልምን በማሳየት ሥራ ጀመረ፡፡ አቶ ገዛኸኝ በልስቲ እና አቶ ታምራት አበበ በሚባሉ ባለሀብቶች የተከፈተው አዲስ ሲኒማ ቤት 380 መቀመጫዎች አሉት፡፡“ፀናፅል ሃላፊነቱ የተወሠነ የግል ማህበር” የሚያንቀሳቅሰውን “ሲኒማ ሴፍ” አስመልክቶ አቶ ገዛኸኝ በልስቲ ለዝግጅት ክፍላችን ሲናገሩ የአማርኛ ፊልሞች በማሳየት ሥራ የጀመረው ድርጅታቸው ለወደፊት የውጭ ሀገር ፊልሞችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማሳየት ማቀዱንም አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመርያው እንደሆነ የሚነገርለት ደብረዳሞ ገዳም “ሕዳሴ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ” በሚል መሪ ቃል ሰሞኑን እንደሚያከብር ገለፀ፡፡ የገዳሙ ልማት ኮሚቴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በአካባቢው ለ1469 ዓመት የተቀመጡ ቅርሶች የሚቀመጡበት ቤተመዘክር ይገነባል፡፡ የኮሚቴው ፀሀፊ አቶ ተወልደብርሃን ታደሰ እንደገለፁት የገዳሙ መንፈሳዊ እሴቶች፣ እና ታሪካዊና ሐይማኖታዊ ቅርሶች ተጠብቀው ምዕመናን እንዲሁም የሐገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚተሙበት ኢትዮጵያዊ መስሕብ ይደረጋል፡፡ ከቅርሶቹ መሃል የአቡነ አረጋዊ 1469 ዓመት ያስቆጠረ ቆብ እና የብራና መፃሕፍት ይገኙበታል፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ላይ በተቃጡ የውጭ ወረራዎች እና የርስ በርስ ጦርነቶች እንዲሁም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሳይደርሱበት እስካሁን የዘለቀ ብቸኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳም ደብረዳሞ ነው፡፡

ባለፈው ወር አጋማሽ የወጣው የታዋቂው ጉራጊኛ ድምፃዊ ኃይሉ ፈረጃ “ትኩሰለ” አዲስ አልበም በአንደኝነት እየተደመጠ መሆኑን ድምፃዊዉ ገለፀ፡፡ ድምፃዊው የሙዚቃ ቤት ምንጮችን ጠቅሶ እንደነገረን አዲሱ አልበም ዘንድሮ ከወጡ ዘጠኝ የጉራጊኛ አልበሞች በሽያጭና በመደመጥ እየመራ ነው፡፡ ግጥምና ዜማውን ራሱ ኃይሉ ፈረጃ በሰራው እና አስር ዘፈኖች በያዘው አልበም መሃመድ ኑርሁሴን፣ ከድር ሁሴን፣ አሸናፊ ከበደ፣ እድሪስና ዘሪሁን በሙዚቃኝነት ተሳትፈውበታል፡፡ ኃይሉ ፈረጃ ለካሁን ቀደም “ቃሳ ቃሳ” በሚለው አልበሙ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ድምፃዊ ሃይሉ ፈረጃ እና ድምፃዊት ሄለን በርሄ በቅርቡ በውጭ ሀገራት የሙዚቃ ድግስ በአዲካ አማካኝነት ሊያቀርቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያንን የአስራ አንድ ዓመታት የሶማሊያ እስር ቤቶች ህይወት በመዳሰስ እውነተኛ ታሪኮች ያካተተው “ሀበሻ በሶማሊያ እስር ቤቶች” መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በአቶ ጥላሁን አትሬሶ የተዘጋጀው መፅሐፍ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሲወጡ የነበሩ መጣጥፎችንና ሌሎች አዳዲስ ፅሁፎችን አካቷል፡፡ 267 ገፆች ያሉት ይህ መፅሐፍ በ40 ብር ዋጋ ለገበያ ቀርቧል፡፡
ይኸው መፅሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓመተ ምህረት ከቀኑ 10፡30 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የታሪክ ምሁራን፤ ደራስያን፤ እና በሶማሊያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የኪነጥበብ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ይመረቃል፡፡

በደመና ፕሮሞሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው “አንፋታም” አዲስ ትያትር በመጪው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ አንተነህ ኪዳኔ የደረሰው ይህ ትያትር በምስጋና አጥናፉ ተዘጋጅቷል፡፡ ወይንሸት በላቸው፣ ሄለን ቸርነት፣ ዝናሽ ጌትነት፣ ራሄል ብርሃኑ፣ ኢሳያስ ጥላሁን፣ ልዕልት ሉሉ፣ አንተነህ ኪዳኔ እና ምስጋና አጥናፉ ይተውኑበታል ትያትሩ ዘወትር ማክሰኞ በተመሳሳይ ስፍራ ለሕዝብ እንደሚቀርብም ማወቅ ተችሏል፡፡ ደራሲው ካሁን ቀደም “ዕድል 20”፣ “አይዳ”፣ “ደም”፣ በተሰኙ ትያትሮቹና ጥቁር በለስ በተሰኘ ፊልሙ ይታወቃል፡፡

ክብደት መጨመርና መቀነስ ለሚፈልጉ እንዲሁም በጤና እክል ሐኪም ያዘዘላቸው ደንበኞች የሚመገቡበት ምግብ ቤት (ዳይት ሀውስ) ቦሌ መድሐኔአለም አካባቢ ተከፈተ፡፡ የምግብ ቤቱ ባለቤት ወ/ሮ መሳይ ባዬ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት ለወደፊት የኤሮቢክስ ማዕከል የሚኖረውን ምግብ ቤት እንዲከፍቱ ያነሳሳቸው በተለይ ሕመምተኞች የሚስማማቸውን ምግብ ለማግኘት ሲቸገሩ በማየታቸው መሆኑን ነግረውናል፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚያካሄዳቸው ዘመቻዎች በበጎ ፈቃድ መልእክተኝነት እየሰሩ ያሉ ሁለት አርቲስቶች ሜዳሊያ ተሸልመው “የጤና ጀግና” የምስክር ወረቀት ተሰጣቸው፡፡ ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ከተማ በተደረገ ሥነ ሥርዓት የተሸለሙት አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያምና ወጣት አርቲስት ሜሮን ጌትነት ናቸው፡፡ በእሁዱ ሥነሥርዓት ከአርቲስቶቹ ሌላ አራት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በመሠል አስተዋፅኦ ለሽልማት በቅተዋል፡፡

የካቶሊኩን ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ ናዚ ስትል የጠቀሰችው የፊልም ተዋናይቷ ሱዛን ሳራንደን በካቶሊክና አይሁድ ቡድኖች ተቃውሞ ገጠማት፡፡
የካቶሊክ ሊግ የተባለ ተቋም የሱዛን ሳራንደንን ንግግር “ነውር” በሚል የተቸ ሲሆን የፀረ ስም ማጉደፍ ሊግ የሌሎችን እምነት በሚዳፈር አሳፋሪ ተግባሯ ይቅርታ እንድትጠይቅ አሳስቧል፡፡ በርካታ ሃያሲዎች እንደተናገሩት፤ የፊልም ተዋናይቷ አፀያፊ የተባለውን ንግግር የተናገረችው የታሪክ ዕውቀቷ አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ሳራንደን በ1995 ዓ.ም በሰራችው የሞት ፍርድን በሚቃወመው “ዴድ ማን ዎኪንግ” የተሰኘ ፊልሟ ኦስካር መሸለሟ ይታወቃል፡፡ ተዋናይቷ በካቶሊክና አይሁድ ቡድኖች ተቃውሞ የገጠመውን አስተያየቷን ሃምፕተን የፊልም ፌስቲቫል ላይ ባደረገችው ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገረች ተገልጿል፡፡ ሳረንደን የጀርመን ትውልድ ያለው ጳጳስ የናዚ ደም አያጣም በሚል አስተሳሰብ መናገሯ ውግዘቱን አስከትሎባታል፡፡