Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

የለሰለሰ ኢትዮጵያዊ መልክና ህብረ ብሔራዊ ዜማ፤ ከዛሬ በላይ ነገ ከነገ ወዲያ ሲሰሙት እያሸተ፤ እየጐመራ ውስጥን በሀሴት እየኮረኮረ የሚሄድ - የቴዲ አዲሱ አልበም!ከዜማው ግጥሙ፣ ከግጥሙ ቅንብሩ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እድሜና ፆታ ሳይለይ የሚያግባባ፣ የሚገባ፣ ታሪክን ከባህል አጣምሮ ከትልቁ የህይወት ክብ ውስጥ ትንሹን ነጥብ መዝዞ” በዚያም ረጅሙን የኢትዮጵያ ታሪክና ባህል በፍቅር የሚተርክ፡፡ ዘላቂ ጭብጦችን (ፍቅር፣ ጥላቻ፣ ፀብ…) ለዛ ባለው ቋንቋ መጥኖ ለጆሮ ያደረሰ “ጥቁር ሰው አልበም”፡፡ “ከሚገባሽ በታች ከምችለው በላይ!” አቤት በእነዚህ ሁለት ሀረጋት መካከል ያለው ርቀት! በብዙ ክንድ ይሰፈራል፡፡ በጣም ወዷትም አልረካ፣ ይህን ያህል ቃትቶም ለእሷ ውበት፣ ስብዕናና ሴትነት አልመጠነለትም…

Saturday, 26 May 2012 13:03

አቦል… ቶና… በረካ

ቅድመ ታሪክ

ከተሞችን ወንዶች ይሠሯቸዋል (ይመሠርቷቸዋል) ሴቶች ይነግሱባቸዋል … አልያም ይገዙባቸዋል፡፡ ወንዶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ በድንጋይ… በጠጠር… በሾህ… በአሸዋ… ሴቶች ያስውቡታል…ቤቶች በሴቶች ይደምቃሉ፤ ቤቶች በሴቶች ይዋባሉ፤ በሸክላ… በሰፌድ… ወንዶች ብረትን ይገዛሉ፤ ሴቶች ብልሃትን ያመጣሉ፤ አንዳንዴ ግን (ለምን አንዳንዴ አብዛኛውን ጊዜ ግን) እንዲህ ይሆናል፡፡ አማራጭ ከጠፋ በኋላ… እንደ እናቷ ከሚወዷት… እንደ እናቷ ከምትወዳቸው ከአክስቷ ጋር በአካለ ሥጋ ከተለያየች በኋላ… ተስፋዋ ከተገደለ በኋላ… ተስፋ የለኝም ስትል… ከሞተው ተስፋዋ በኋላ… ወደ ኋላ ተመልሳ እናቷን ይቅርታ እንዳትጠይቅ… ምን ብላ? ለማያውቁት ላላዩት…የሕይወት ታሪኳ ምን ብለው ይቅርታ ይሏታል… ማንን ጐዳች? መጓዝ የነበረባትን መንገድ ቸል ብላ… ለወንዶች ወሬ… ለፍቅር ስሟ የጠፋ… ማንነቷን እንዴት ማሳየት ትችላለች?

Sunday, 06 May 2012 15:32

ጊዜ

የሌሊቱ ጸጥታ የነፍስን አጥንት ይሰረስር ይመስላል።ብርዱ የዋዛ አይደለም።ከሰዓታት በፊት ስስ ካፊያ ነበር። ከቤቱ ክዳን አሸንዳ የታቆረ የጠፈጠፍ አንኳር ከታዛው ሥር ባለው ጉርድ ጣሳ ውስጥ ‘ጧ! ጧ!’ እያለ ይንከባለላል። የግድግዳው ሠዓት ‘ቀጭ! ቀጭ!’ እያለ ከጠፈጠፉ የጣሳ ድምፅ ጋር አብሯል። ሌሊቱ ይፈጥናል።“ልክ የዛሬ ሳምንት የኢትዮጵያውያን ምዕተ-ዓመት ነው!” አልኩ ለራሴ።“የጊዜ ወሰን የጊዜ ገደብ ከጥጉ ደረሰ። አሁን ደግሞ ሌላ የጊዜ ወሰን ሌላ የጊዜ ገደብ ተቆጥሮ ሊሰጠን ነው።” አልኩ ለራሴ። ሌላ ዕድሜ! ሌላ ዓመት…ሌላ እየተተካካ የሚሔድ ምዕተ-ዓመት፤የትውልድ ዕድሜ፤የታሪክ ዕድሜ፤የግለሰብ ዕድሜ፤የአገር ዕድሜ፤የዕድሜ ዕድሜ…ደነገጥኩ።

በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ዘወትር አርብ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 12 እንዲሁም ቅዳሜ ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ የሚተላለፈውን የ”ጣዕም ልኬት” የተሰኘ ፕሮግራማችንን አስመልክቶ ቃል ኪዳን ይበልጣል የተባሉ አድማጭ በዚህ ጋዜጣ ላይ የሰጡትን አስተያየትተመልክተነዋል፡፡ ይህ ፕሮግራማችን ላለፉት አራት አመታት በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ ሲተላለፍ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬዲዮ ጣቢያ መተላለፍ ጀምሯል፡፡ በዚህ ሁሉ የሥራ ጊዜያችን የፕሮግራማችንን ጠንካራ ጐንም ሆነ ደካማ ጐናችንን አንስቶ እንዲህ በይፋ ለማመስገንም ሆነ ለመወቀስ የቻለ ወገን አልነበረም፡፡ የምንሠራበትን ጣቢያም ጨምሮ ማለታችን ነው፡፡ በእርግጥ ከተለያዩ አድማጮች በስልክ፣ በደብዳቤና በኢሜይል የተለያዩ አስተያየቶች ይደርሱናል፡፡ በዚህም ሲበዛ ደስተኞች ነን፡፡

Saturday, 14 April 2012 13:04

የህፃናት ጥግ

ውድ እግዚአብሔር፡-

በድሮ ጊዜ ብዙ ተዓምራት ሰርተሃል፡፡ አሁን ለምን መስራት ተውክ?

-ፌቨን-

ውድ እግዚአብሔር፡-

ለእረፍት በወጣን ጊዜ ዝናብ ሲዘንብ ስለነበረ አባቴ አብዶ ነበር፡፡ ሰዎች ስላንተ ማለት የማይገባቸውን ነገር ሁሉ ሲልህ ሰምቻለሁ፡፡ ሆኖም ግን እንደማትጐዳው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

(ወዳጅህ ነኝ - ማንነቴን ግን እንዳትጠይቀኝ)

ውድ እግዚአብሔር፡-

የተሻለ እግዚአብሔር ለመሆን የሚችል ማንም ያለ አይመስለኝም፡፡ እንዲህ የምለው ደግሞ አሁን አንተ እግዚአብሔር ስለሆንክ እንዳልሆነ እንድታውቅ እፈልጋለሁ፡፡

-ቻርልስ-

ማንኳኳት… ማንኳኳት… የገነትን በር ማንኳኳት!

ቦብ ዳይላን

(አሜሪካዊ ዘፋኝና የዜማ ደራሲ)

መጪው ዘመን እንደ መንግስተ ሰማያት ነው - ሁሉም ሰው ያወድሰዋል፤ ነገር ግን ማንም እዚያ ለመሄድ አይፈልግም፡፡

ጀምስ ባልድዊን

(አሜካዊ ፀሃፊና የሲቪል መብት አቀንቃኝ)

እግዚአብሄር ሃይማኖት የለውም፡፡

ትኩሳት” ድርሰት ውስጥ ጎልተው የሚታዩት ሴቶች ሶስት ናቸው - አማንዳ፤ ሲልቪ፤ ኒኮል። ያለ ስም የተጠቀሰችውን ሌላኛዋ ሴት እንደ አራተኛ ልንቆጥራት እንችላለን። ስብሃት ገ/እግዚአብሄር፤ የድርሰቱን ምእራፍ ሁለት፤ ይህችን ሴት በመግለፅ ይጀምራል።

“ያን ሰሞን አንዲት ቆንጆ አሜሪካዊት ነበረችኝ። አይኗ ሰማያዊ፤ ፀጉሯ በጣም ንፁህ ቡና አይነት። እጅግ ደስ ትላለች...” (ገፅ19)። ምናልባት፤ የመጀመሪያው አረፍተ ነገር፤ ጎደሎ ነገር ሊመስለን ይችላል። “...ቆንጆ አሜሪካዊት ነበረችኝ”። አሜሪካዊት ምን? አሜሪካዊት ጓደኛ ወይም ፍቅረኛ፤ አሜሪካዊት ሚስት ወይም ውሽማ... በሚል ቢያሟላው ይሻል ይሆናል። ለማንኛውም፤ ፀጉሯ በጣም ንፁህ ቡና አይነት ነው።

Wednesday, 04 April 2012 09:54

ቦርጨቅ

-በስብሃት ገብረእግዚአብሔር-

አቶ ዘነበ ሀብትም ሆነ ሹመት ወይም ዝና በምኞታቸው ገብቶ አያውቅም ነበር፡፡ አግብቶ፣ ልጆች ወልዶ አሳድጎ፣ አስተምሮ፣ በስተርጅና ጧሪ ደጋፊ ማግኘት፣ በልጆችና በልጅ ልጆች ተከቦ መድሀኔአለምን ተመስገን እያሉ መሞት፡፡ ይኸ ነበር ያቶ ዘነበ ምኞትና ተስፋ፡፡ ግን እግዜር ሳይለው ቀረና፣ ባንድ መስሪያ ቤት የቢሮ ተላላኪነት ተቀጥረው፣ ካመት አመት ሚስት አገኛለሁ እያሉ ተስፋ ሲያደርጉ፣ በልዩ ልዩ ምክንያት ካመት አመት ሳይሳካላቸው ሲቀር፣ ካመት አመት ጊዜ ትከሻቸው ላይ እድሜ ሲቆልል፣ እድሜው እየከበዳቸው እየጎበጡ ሄዱ፡፡ ተስፋቸው ከወጣትነታቸው እኩል እየመነመነ ሲሄድ፣ መድሀኔአለምን እየተሳለሙ “አንተ አምላክ ሳላውቅ በድዬህ ይሆን? ማረኝ ይቅር በለኝ” እያሉ በልባቸው ሲለምኑ፣ ሲፆሙ ሲፀልዩ ሲሰግዱ፣ እንዲህ ሲሉ ስድሳ አመት ሲሆናቸው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያ ሲያስጎመጃቸው፣ ሲያስጨንቃቸው የነበረ ተስፋ ጥሎአቸው ሲሄድ ጊዜ ቀለል አላቸውና ልባቸው አረፈ፡፡ መድሀኔአለንም እየተሳለሙ “አንተ ታውቃለህ እንጂ እኔ ምን አውቃለሁ? አንተ እንዳልከው ይሁን” ብለው እድላቸውን በሙሉ ልባቸው ተቀበሉ፡፡

ኢትዮጵያዊው ገጣሚ፣ ደራሲና ፀሃፌተውኔት ለምን ሲሳይ በመላው እንግሊዝ ከሚገኙ ዕውቅና ምርጥ ገጣሚዎች በቀዳሚነት ስሙ ይጠቀሳል፡፡ በዓለም አቀፍ ፀሃፊነቱ የሚታወቀው ለምን ሲሳይ፤ አምስት የግጥም መድበሎችን በእንግሊዝኛ ፅፎ አሳትሟል፡፡ የጥቁር እንግሊዛውያን ዘመነኛ ገጣሚዎችን ሥራዎች ያካተተውን “The Fire people” የግጥም መድበል የአርትኦት ስራም እንደሰራ ይናገራል፡፡ ለታዋቂው “Poetry Review” በመደበኛነት ፅሁፎችን የሚያቀርበው ገጣሚ ለምን፤ The Avron Poetry prize የተሰኘውን ውድድር ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የሥነ ፅሁፍ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ሰርቷል፡፡ ቢቢሲን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት ኮሚሽን እየተደረገ በርካታ ግጥሞችን የፃፈው ገጣሚው፤ በማንችስተርና ሌሎች ከተሞች ህንፃዎችና ጐዳናዎች ላይ ግጥሞቹ እንደ መፈክርና ማስታወቂያ የተፃፉለት ገጣሚ ነው፡፡

“ለምግብ የምሰጠው ምንም ዋጋ አልነበረም፤ ከተገኘ እሰየው ከሌለ ግድ አልነበረኝም፤ ያ ነገር ለምዶብኝ ነው መሰለኝ አሁን እራሱ ሆድ መሙላቱ ብዙም ቦታ የምሰጠው አይደለም”

“ጃሉድ” ከቁራን የተገኘ ቃል ነው፡፡ “በሁሉም ነገር ውስጥ መገኘት››የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ የጃሉድ እናት ጎጇቸውን ያደምቅላቸው ዘንድ የወለዱትን የመጀመሪያ ልጅ ለማየት እንኳን አልታደሉም፡፡እንደተወለደ ሕይወቱ አለፈ፡፡ተስፋ አልቆረጡም፤ በድጋሚ ሞከሩ፤ ሁለተኛውም ተመሳሳይ ሆነ፡፡ሦስተኛ ጥረት አደረጉ፤ የመጣው ጽንስ የመወለጃ ጊዜውም ደረሰና ምጡ መጣ፡፡ በፍጥነት እንዲደርስ የተጠራው አምቡላንሱ ድምፁን እያሰማ፣ ነፍሰጡሯን እናት ከቃሊቲ አሳፍሮ በሰላም ለማገላገል መክነፍ ጀመረ፡፡ጎተራ አካበቢ ሲደርስም ምጡ ተፋፋመ፡፡ ሕፃኑ ግን ሆስፒታል መድረስ አልቻለም፡፡  አምቡላንሱ ውስጥ ተወለደ፡፡ እናም ሆስፒታሉ ቀርቶ ጉዞ ወደ ኋላ ሆነ፤ ያን ቀን (የዛሬ 37 ዓመት) የተወለደውና በቅርቡ “ያቺን ነገር” የተሰኘ በሬጌ ስልት የተቀነቀነ አዲስ አልበም የለቀቀው ጃሉድ የተሰኘ ድምፃዊ ነው፡፡