Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

“የፌስቱላ መሰረቱ ዋናው ድህነት ነው፡፡ ድህነት በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም ጭምር ነው፡፡ አንዲት ሴት ገና በህጻንነት እድሜዋ ተለምና ከተገባች በሁዋላ የፌስቱላ ሕመም ሲያጋጥማት ባልዋ ወደቤተሰቦችዋ ይመልሳታል፡፡ ቤተሰቦችዋ ደግሞ በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ ነጠል ያለች መኖሪያ ያመቻቹና በዚያ እንድትቀመጥ ካደረጉ በሁዋላ የሚያገኙዋት ምግብና ውሀ በሚሰጡዋት ወቅት ብቻ ነው፡፡ ታማሚዋ ሽንቱዋን መቆጣጠር ስለማትችል የምትለብሰው... የምትተኛበት እንዲሁም የምትኖርበት ሁሉ ስለ ሚበላሽና ስለሚሸት ውሃ መጠጣትዋን ታቆማለች፡፡ ምግብ መውሰዱዋንም ትቀንሳለች፡፡ በዚህም ሰውነቷ እየደረቀ ይመጣል፡፡ ከዚህም በላይ በውስጧ ያለው ፈሳሽ በሚፈስበት ጊዜ አካባቢዋን እንዳያበላሸው በአቅራቢያዋ ካለ ድንጋይ ተቀምጣ መዋልን ትመርጣለች፡፡ ድንጋይ ስለማይበሰብስና ስለማይርስ ዘመዷ...ጉዋደኛዋ ይሆናል፡፡ ይህች ልጅ በዚህ ሁኔታ ስትቆይ ሰውነቷ የመድረቅ ... የመቀጨጭ ... ጅማቶችዋ የመኮማተር ችግር ስለሚያጋጥማት ለከፍተኛ ሕመም ትጋለጣለች፡፡ በጊዜው እርምጃ ካልተወሰደም ለሕልፈት ልትዳረግ ትችላለች...”

Bonding...  ማለት ቅርበትን መፍጠር/ መተሳሰር/ መጣመር ...ወዘተ ሲሆን በዚህ እትም ለንባብ ያቀረብነው በተለይም በወላጆች እና በልጆች መካከል አያደገ እየተለመደ ሊመጣ የሚገባውን ከፍተኛ የመጣመር/ የመቆራኘት ስሜትን የሚመለከት ነው፡፡ መረጃው Larissa Hirsch ከተባሉ የህክምና ባለሙያ ድህረ ገጽ የተገኘ ነው፡፡

የወላጆችና የልጆች ጥምረት Bonding ... በተለይም ለወላጆች የሚሰጠው ጥቅም ፡-

በከፍተኛ ሁኔታ ፍቅር በተሞላበት እና የእንክብካቤ መጠን ልጆቻቸውን አንዲወዱና እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ፡-

በዚህ አመት ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚሆኑ እናቶች እርግዝና ላይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

ወደ 90.000 የሚሆኑት ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ናቸው ተብሎ ይገመታል፡፡

በዚህ አመት ወደ 14.000 የሚሆኑ ሕጻናት ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናታቸው ይወርሳሉ የሚል ግምት አለ ፡፡

“በአለም ላይ የህጻናትን የኤችአይቪ ስርጭት በሚመለከት ይበልጡን ድርሻ የሚይዘው ከእናት ወደልጅ በሚኖረው መተላለፍ መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡ ቀደም ሲል የወጣ አንድ መረጃ እንደሚጠቁመው በአለም ላይ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ ይያዛሉ፡፡ ሕጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙበት ምክንያትም ይበልጡኑ በእርግዝና ፣በወሊድ ወቅት እና በጡት ማጥባት ጊዜ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት ህጻናት መካከልም አብዛኞቹ የአምስት አመት እድሜያቸውን የልደት በአል ሳያከብሩ ይሞታሉ፡፡

ባለፈው እትም ዘላቂ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን በሚመለከት የወንዶች ተሳትፎ ምን ይመስላል በሚል ለንባብ ያልነውን መሰረት በማድረግ ላንቺና ላንተ በሚለው ድህረገጽ የተወሰኑ ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡ ጥያቄዎቹን ተባባሪ አዘጋጅዋ አዲስ አለም ብርሀኔ ለባለሙያ በማቅረብ እና በተለያዩ የጥናት ወረቀቶች በመታገዝ ለመላው አንባቢ ይድረስ ብላለች፡፡

በታዳጊ አገሮች በአሁኑ ጊዜ የህጻናትና እናቶች ሞት የመቀነስ ሁኔታ እያሳየ ቢሆንም ከሚመዘገቡት የህጻናት የሞት ቁጥሮች 40 ያህሉ ከአምስት አመት በታች ያሉ ሕጻናት ናቸው፡ ከምእተ አመቱ የልማት ግቦች መካከል የእናቶችንና የህጻናቱን ሞት መቀነስ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ይህንንም ለማሳካት አገሮች ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ በአገራችን የተተለመውን እቅድ ለማገዝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን ህዳር 7/2004 የእናቶችና የሚወለዱ ሕጻናትን ጤንነት መረጃ አሰባሰብን በሚመለከት በጋራ አብሮአቸው ከሚሰራባቸው የጤና ተቋማት ተወካዮች ጋር የአንድ ቀን ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ በስብሰባው ላይ ቀርበው ከነበሩ ምስክርነቶች መካከል አንዱን ለንባብ ብለነዋል፡፡

“...እኔ እድሜዬ ወደ ሀያ አምስት አመት የሚሞላኝ ነኝ ፡፡ የ12ኛ ክፍል ትምህርን ጨርሼ ወደዩኒቨርሲቲ ስገባ ከቤተሰቤ ስለተለየሁ የነበረኝን የጤና ችግር የማዋየው ለጉዋደኞቼ ነበር፡፡ ከማህጸኔ የሚፈሰው ፈሳሽ እጅግ የሚዘገንን ነበር፡፡ መልኩ ደስ አይልም ሽታ አለው፡፡ ጉዋደኞቼ ስነግራቸው ብዙዎቹ እኔም አለብኝ የተፈጥሮ ጉዳይ ነወ የሚሉ ነበሩ፡ እኔ ግን በፍጹም ልታገሰው አልቻልኩም፡፡ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቼ የምሄደው በአመት አንድ ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከርቀት የተነሳ ነው፡፡ ወደ ቤተሰቦቼም ስሄድ ችግሩን ተናግሮ ወደ ሐኪምቤት መሄድ ስላስፈራኝ ዝም ነበር የምለው፡፡ በአጠቃላይም ይህንን ችግር ይዤ ከሁለት አመት በላይ ተሰቃየሁ የሚገርመኝ ነገር እናቴ ስለሁኔታዬ በጭራሽ አትጠይቀኝም ነበር፡፡

“እኔ የ28 አመት ሴት ነኝ፡፡ ከአንድ አመት ወዲህ የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ከጓደኛዬ ጋር መገናኘት በጀመርኩ በስድስት ወር ገደማ አንድ የማያስደስት ነገር ገጠመኝ፡፡ ከማህጸኔ አይቼው በማላውቀው መንገድ ፈሳሽ ይፈሰኝ ጀመር፡፡ የፈሳሹ መልክ የዘንጋዳ ውሀ እንደሚሉት ይመስለኛል፡፡ ጠረኑ ደግሞ ጥሩ አይደለም፡፡ የፈሳሹ መጠን የውስጥ ሱሪዬን ስለሚያረጥብብኝ በአንድ የውስጥ ሱሪ ቀኑን ሙሉ መዋል አልችልም፡፡ የግድ ግማሽ ቀን ላይ ሌላ የውስጥ ሱሪ መለወጥ ይጠበቅብኛል፡፡ ከማህጸኔ በሚፈሰው ፈሳሽ ምክንያትም ከጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ መያዝ አቅቶኛል፡፡ ስለዚህም ጓደኛዬ እንገናኝ በሚለኝ ጊዜ ምክንያት እየፈጠርኩ ቀጠሮውን ስለማዛባ... በቃ... አትወጂኝም ማለት ነው ወደሚል አስተያየት እየመጣ ስለሆነ ከእሱም ልለያይ ነው ማለት ነው፡፡ በእርግጥ እኔም እወደዋለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ችግር ምን ብዬ ልንገረው?... ሁኔታው ስለጨነቀኝ ነው ወደ እናንተ ይህንን መልእክት የላክሁት፡፡ እባካችሁ ባለሙያ አነጋግራችሁ መልሱን ንገሩኝ፡፡”

ሕጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ ከተያዙ እናቶች ከተወለዱ uºL ሊደረግላቸው የሚገባውን የክብካቤና ድጋፍ አገልግሎት ለማመቻቸት አስቀድሞ ሕጻናቱ በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸው በግልጽ መታወቅ አለበት፡፡ Linkage ማለትም በኤችኤቪ ቫይረስ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ሕጻናት የጤና ክትትልን የሚመለከተው አሰራራር በአሁኑ c›ƒ በየሆስፒታሉ በምን መልክ እየተካሄደ ነው? የህክምና ባለሙያዎች እና የህክምና ተቋማቱ አሰራራር እና የህብረተሰቡ ግንዛቤ ምን መምሰል አለበት? የሚለውን በዚህ እትም ለንባብ ብለናል፡፡

አለም በህገወጥ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ምን ያህል ሴቶችን አጥታለች ለሚለው ለጊዜው በእርግጠኝነት ይህን ያህል ማለት ባይቻልም ብዙዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ግን እውን ነው፡፡ እንደ World Health Organization, the Alan Guttmacher Institute, and Family Health International, እማኝነት ከሆነ በአለም Ÿ70,000 - 200,000 የሚሆኑ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም መካከል አፋጣኝ የሆነ እና ሁሉንም አገልግሎት ያካተተ የማህጸን ሕክምና በመላው አገሪቱ ከትላልቅ ሆስፒታሎች ራራቅ ባሉ አካባቢዎች እንዲሰጥ የሚያስችለው (Comprehensive Emergency Obstetric and New Born care)  የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡