Saturday, 10 February 2024 10:14

ለ32 ዓመታት ሞትን ያስኮረፈው ግርማ በየነ!

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በግርማ ሙዚቃዎች ውስጥ ሁሉ ያለችው ሴት አንድ ናት፡፡ የሚወዳት የሚያኮርፋት፣ የሚቀርባት የሚርቃት እሷን ብቻ ነው - እጸገነትን፡፡ እጸገነት ገብረሥላሴ የልጅነቱ ናት፤ የልጁም እናት፡፡ በንጹሕ ልቡ የወደዳት፤

የምትወደው፡፡ “ሴት አላምንም” ፣ “ትወጅኝ እንደሁ”፣”ቁርጡን ንገሪኝ” እና “ፍቅር እንደክራር”ብሎ ያዜመላት፡፡ “ይበቃናል” ብሎ ያንጎራጎረውም ለእጸገነት ነው- የራቀችው ቢመስለው፡፡ ግን አይሆንለትም፡፡

“ጥሩልኝ ቶሎ” ይላል፡፡
አቃተኝ ፍፁም መለየት
እሷን ከመሰለ ወጣት
ጥሩልኝ ቶሎ በፍጥነት
ትድረስ በነፍሴ ሳልሞት
ፍፁም ፍፁም አልተዋትም
ካለሁ በሕይወት አረሳትም...
“ጥሩልኝ ቶሎ” የግርማ የአፍላነት ዜማ ነበር፡፡ ኋላ ግን የአሳዛኝ ሕይወቱ ማጀቢያ ሙዚቃ ሆነ፡፡ በፍቅራቸው ሰሞን ስትጠፋበት “ጥሩልኝ ቶሎ” ብሎ ያንጎራጎረላት እጸገነት፤ በጎልማሳነቱ ዘመን ጥላው ሔደች -

ወደ አምላኳ፡፡ ግርማ ከዚያ በኋላ ሙዚቃን ፈራ፡፡ በብዙ ጉትጎታ ተመልሶ ሲመጣም ከእጸገነት መራቅ ተሳነው፡፡ “Mistakes on purpose” ብሎ በሰየመው የሙዚቃ አልበሙ ላይም “በመልክሽ

አይደለም” በተሰኘ ዜማው፤ የልጅነት ፍቅሩን ዘከረ፡፡ በካንሰር ሕመም ካለፈች 32 ዓመታት ቢሞላትም፣ ዛሬም ፎቶዋን አቅፎ እንደሚተኛ አንጎራጎረ፡፡
እስኪመሽ እናፍቃለሁ፤ እስክተኛም እጓጓለሁ፤ ምክንያቱም ጸጊን ስለማገኛት አለ፡፡ ግርማ ዕድሜውን ሙሉ የዘፈነላት ሴት አሁንም አብራው እንዳለች ያስባል፡፡ በጊዜ ቤቱ ገብቶ ከፎቶዋ ጋር ሲጫወት ያመሻል፡፡ እኔም

ተራው ደርሶኝ በድጋሚ እስካገኛት እያለ፡፡...!

Read 1330 times