Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ልብ-ወለድ

Saturday, 17 December 2011 10:52

የካዝና ሰባሪው ንስሃ

Written by
Rate this item
(0 votes)
2011-12-17 “ጂሚ፤ ይቅርታ... ቶሎ አልደረስንለህም” አሉ ማይክ ዳለን። “ስፕሪንፊልድ ውስጥ ተቃውሞ ተነሳብን፤ አገረ ገዢውም እምቢ ሊሉ ትንሽ ነበር የቀራቸው። የምህረት ደብዳቤውን ላለመፈረም አንገራግረው ነበር። ግን አንተ ደህና ነህ... እ?” “ሰላም ነው” አለ ጂሚ። “ቁልፌ አለ?” ቁልፉን ተቀብሎ የፎቅ ደረጃውን እንደወጣ፤…
Saturday, 10 December 2011 09:51

ሰውየው

Written by
Rate this item
(0 votes)
ከእኩለ ሌሊት አንስቶ ምድርን ይረግጣት የጀመረው ኃይለኛ ዝናብ የጥፋት ውሀን ያስታውሳል፡፡ ሌላው ቢቀር ነግቶ እስኪረፍድ እንኳ አላባራም ነበር፡፡ ለወትሮው ሠዎች የሚተራመሱበት አውራ ጎዳና ግራና ቀኝ ካሉት የውሀ መውረጃ ቦዮች ገንፍሎ የወጣው ቀይ ጎርፍ ይገማሸርበታል፡፡ ነጫጭ ጋቢና ነጠላ የደረቡ መንገደኞች ጎርፉን…
Saturday, 10 December 2011 09:50

ጨረታ

Written by
Rate this item
(0 votes)
የሞባይሉ ጥሪ ከአስደሳች እንቅልፉ ቀሰቀሰው፡፡ “የማን ሰዓት አልባ ነው በዚህ ሰዓት የሚደውለው?” እያጉረመረመ ስልኩን አነሣው፡፡ “በጣም ይቅርታ ለአስቸኳይ ጉዳይ ስለሆነ ነው የደወልኩት፤ በጠዋት የተለመደውን አገልግሎትህን ፈልጌ ነው፡፡” የሚያውቀውን ድምፅ ስለሰማ ፊቱ ፈካ፡፡ ከብዙ ደንበኞቹ አንዱ ነው፡፡ ችኮላ የተሞላበትን የደንበኛውን ትዕዛዝ…
Saturday, 03 December 2011 08:27

ግራ እና ቀኝ

Written by
Rate this item
(0 votes)
ታሪኩ ከቁም ሳጥኑ መስታወት ፊት ለፊት ቆሟል፡፡ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ በመስታወቱ ይታየዋል፡፡ መስታወቱን ያያያዘው ማጠፊያ በመገንጠሉ በሚስማር መልሶ ሊጠግን ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን በመስታወቱ ራሱን መመልከት ለምን እንዳስፈለገው አልገባውም፡፡ ሰሞኑን የተጠናወተው አንዳች ውስጣዊ ሃይል ገፋፍቶታል፡፡ የገዛ ሰውነቱን ማዘዝ…
Saturday, 26 November 2011 08:45

ታላቁ ሩጫ

Written by
Rate this item
(0 votes)
ግርማዊነታቸው የሲዳሞን ጠቅላይ ግዛት ጐበኙ፡፡በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች የእርዳታ እህል መከፋፈል ጀመረ፡፡መፈንቅለ መንግስቱ ከሸፈ፡፡ የአብዮትን በአል በማስመልከት ካስትሮ ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡በሻዕቢያ ጦር ላይ ትልቅ ኪሳራ ደረሰ፡፡የህዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት፤ ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጠረ፡፡ ህገ-መንግስቱ ፀደቀ፡፡የአልጀርሱን ስምምነት እንዲያከብሩ…
Saturday, 19 November 2011 14:33

የሰይጣን መኪና

Written by
Rate this item
(1 Vote)
በእንቅልፌ ውስጥ ነቅቼ ነበር፡፡ የተኛሁበትን አልጋም ቤቱንም አላውቀውም፡፡ አንዲት ሴት በሩ አጠገብ ሳጥን ላይ ቁጭ ብላ ጥጥ ታሳሳለች፡፡ እሷንም አላውቃትም፡፡ ድንገት በሩ ተከፈተና አንድ ሰው ገባ፡፡ ቢንያም ነው የመሥሪያ ቤት ባልደረባዬ፡፡ ሴትዬዋን አንዴ በአይኑ ገረፍ አርጐ ወደ እኔ መጣ፡፡ ወደ…