ልብ-ወለድ

Tuesday, 28 September 2021 18:47

ምናባዊ ፍቅር

Written by
Rate this item
(7 votes)
..ሦስት ቀን ሲቀረው....በከፊል ሰመመንና በከፊል ንቃት ውስጥ ባለች መስመር ላይ ሰውነቴ ተንጠልጥላ ባፍንጫዬ የምትገባውን የትራስና ብርድልብስ መአዛ በማለዳ አጣጥማለሁ። እንዲሁ በእንዲሁ ሰአት ሁሌም እንደማደርገው፣ አሁንም አሁንም አስባለሁ። ከአልጋው ላይ የሚመጣው የሚሸተኝ ጠረን የፀጉሯ ቅባት ይሆን? ወይስ ሰውነቷን የምትቀባው ሽቶ? ወይስ....…
Monday, 20 September 2021 16:03

መሠንበት

Written by
Rate this item
(6 votes)
 ጠባቧ ክፍል በሲጋራ ጭስ ታፍናለች፡፡ አንገቱን ወደ ኮርኒሱ ቀና አድርጓል፡፡ ዐይኖቹ በኮርኒሱ ርብራብ ሥር ይመላለሳሉ፡፡ ጥልቅ ሐሳብ ይዟል፡፡ጫፍ ላይ የደረሰውን ሲጋራ በኃይል ሲስበው እሳቱ የእጁን ጣቶች መለብለብ ጀምሮ ነበር፡፡ የጽሕፈት ጠረጴዛውን መሳቢያ መዘዘና የሲጋራ ፓኬት አወጣ። ከሲጋራ ሳንዱቁ አንድ ዘንግ…
Saturday, 04 September 2021 17:14

የምርቃናዎች ወግ

Written by
Rate this item
(5 votes)
በጫት ሳቢያ ከሥራ ተባርሬያለሁ፡ የምቅመው ለማንበብ ነው፡፡ ሰሞኑን የሊዮ ቶልስቶይን War and Peace በቶልስቶይ አይነት ተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡የመቃሚያ ብር የለኝም፡፡ እንዳልኩት የምቅመው ለማንበብ ነው፡፡ መቃሚያ ብር ስላልነበረኝ ግን War and Peace ን ሸጬ ወደ ጫት ቤት ሄድኩኝ፡፡እንግዲህ ጫት እዚህ ድረስ…
Rate this item
(4 votes)
...እስከ መቼ? እላለሁ። "እስከ መቼ እንደዚህ የተደጋገመ ጣዕም አልባ ኑሮ እኖራለሁ፤ እንኖራለን? ሰዎች ይወለዳሉ፤ ሰዎች ይወልዳሉ፤ ሰዎች በምቾትና በአግባብ የማያሳድጉትን ልጅ ይወልዳሉ፤ ሰዎች ይበደላሉ፤ ሰዎች ይበድላሉ፣ ጥፋተኞች የወንጀላቸውን ዋጋ አያገኙም። እንዴት ነው ነገሩ? ይሄን ሁላ እየታገስን የምንኖረው እስከ መቼ ነው?’…
Sunday, 22 August 2021 13:12

ቀስቶ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
(የአጭር አጭር ልብወለድ) ቀስቶ በስካር ካልናወዘ፣ እርቃኑን የሆነ ይመስለዋል፡፡ በተለይ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ከብርሌ ጋር ተኳርፎ ብልጧን መጨበጥ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ፤ አዲስ ዓመል አውጥቷል፡፡ ጥቂት ከውሃው ከወሳሰደ፣ ምላሱ እንደ ቀትር እባብ ነው፤ የሚንቀለቀለው፡፡ ስካሩ፣ ትላንቱን እንደ መስታወት ወለል አድርጎ ያሳያዋል።…
Rate this item
(3 votes)
 አልተኛም...ከምወደው እንቅልፌ ከተኳረፍኩ ሰነባብቻለሁ...በርግጥ "ከምወደው እንቅልፌ.." የሚለው ማሽቋለጥ፣ እንቅልፋም መሆኔን የሚመሰክር አይነት በፍፁም አይደለም።ቀድሞም "ሰው ከሙሉ ቀኑ ከስድስት የሚዘለውን ሰዐት ጨፍኖ ማሳለፍ የለበትም... ኪሳራ ነው!" ብዬ ወገቤን ይዤ የምከራከር አይነት ነኝ።ቢሆንም ቢሆንም... ሩብ ቀኔን በሰላም የምተኛው ቆንጆ እንቅልፍ ነበረኝ። እና…