ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር፤ ሠዐሊ፣ ቀራፂና ገጣሚ በቀለ መኮንን የቀረፀው ሃውልት፤ ሳር ቤት አካባቢ ባለ አደባባይ የቆመ ሲሆን ኃውልቱ ባለፈው እሁድ ተመርቋል፡፡ የትምህርትን ጠቀሜታ የሚያጎላውንና ሴት ተማሪ ሉል ላይ ቁጭ ብላ ስታነብ የሚያሳየውን ሃውልት በኢትዮጵያ የአሜሪካ…
Rate this item
(2 votes)
በ”ፍትህ” ጋዜጣ መስራችና ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የተዘጋጀው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘ ፖለቲካዊ መፅሃፍ ሰሞኑን ለገበያ ቀረበ፡፡ ፀሃፊው በጋዜጣው ላይ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ፖለቲካዊ ፅሁፎቹን በማሰባሰብ በመፅሃፍ መልክ ተደራጅተው እንደታተሙ በመግቢያው ላይ ጠቅሷል፡፡ በመፅሃፉ ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን፣ ፖለቲከኞችንና…
Rate this item
(0 votes)
የሠዓሊ ጥበበ ተርፋ የሥዕል አውደርእይ ዛሬ እንደሚከፈት ለይላ የሥዕል አዳራሽ አስታወቀ፡፡ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት የሚከፈተው አውደርእይ ለሦስት ሳምንት የሚቆይ ነው፡፡ ሥዕል አድናቂዎች ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከጧቱ አራት ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መመልከት እንደሚችሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኢሮብ አካባቢ ሥነቃል ተሰባስቦ በኢሮብ ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን ይኸው መጽሐፍ ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ተመረቀ፡፡ በመምህር በርሃ ዚግታ የተዘጋጀው ባለ 201 ገጽ መጽሐፍ ዋጋ 50 ብር ነው፡፡
Rate this item
(1 Vote)
ቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ይባል የነበረው ኮከበ ጽባህ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት ዛሬ እና ነገ ያከብራል፡፡ ሰማንያኛ ዓመቱን በማስመልከት ውይይት የሚካሄድና የቀድሞ ተማሪዎቹ የሚዘከሩ ሲሆን በመንገድ ግንባታ ፈርሶ የነበረው የትምህርት ቤቱ አጥር በቀድሞ እና በአሁን…
Rate this item
(1 Vote)
ቶም ክሩዝ የሚተውንበት “ቶፕ ገን 2” ፊልም በቀረፃ ላይ መሆኑን ሎስአንጀለስ ታይምስ ገለፀ፡፡ የፊልሙ የመጀመርያው ክፍል ከ26 ዓመት በፊት ለእይታ መብቃቱን ያስታወሰው ጋዜጣው፤ በአጠቃላይ 354 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ጠቅሷል፡፡ በ”ቶፕ ገን” ፊልም ላይ የአሜሪካ ተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ የሰራው…