ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
ራዕይ የህፃናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር፣ከዱባይ ንግድ ምክር ቤት 60 ሺህ ብር ደደማ የሚያወጡ መጻህፍትና ደብተሮች ተበረከተለት፡፡ ባለፈው ረቡዕ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት፤ የዱባይ ንግድ ምክር ቤት፣የኢትዮጵያተወካይ አምባሳደር ተክለአብ አረጋዊ በተገኙበት የርክክብ ስነስርዓቱ ተካሂዷል፡፡ በምክር ቤቱ የተበረከቱት መፅሀፍትና ደብተሮች ማህበሩ በነፃ ለሚደግፋቸውና…
Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ቪዥዋል አርቲስቶች ማህበር ከ60 በላይ አባላት የተሳተፉበትና የተለያዩ የስዕል አሳሳል ዘይቤዎች የተንፀባረቁበት ‹‹አርትፌር” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ ባለፈው ረቡዕ በብሄራዊ ሙዚየም አቀረበ፡፡ የፊታችን ማክሰኞ ድረስ ለዕይታ ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የተለያዩ የአሳሳል ቴክኒኮች የሚታዩባቸው እጅግ በርካታ…
Rate this item
(0 votes)
 የደራሲ፣ አርታኢና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ልብ ወለድ ‹‹በፍቅር ስም›› የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡ 30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ፣ ቴዎድሮስ አጥላውና አሸናፊ መለሰ በመፅሐፉ ላይ ዳሠሳ የሚያቀርቡ ሲሆን በሀይሉ ገ/እግዚአብሔር - ወግ፤ ገጣሚ ኤፍሬም…
Rate this item
(1 Vote)
 የፊዚክስ መምህሩ ወጣት ወስናቸው አጥናፌ (ቦንጋ) አዲስ የከፍኛ የሙዚቃ አልበም ያወጣ ሲሆን ነገ በሚያስተምርበት የድል በር ት/ቤት አዳራሽ ይመረቃል ተብሏል፡፡ ‹‹ሀማሂኔ›› የሚል መጠሪያ የተሠጠው አልበሙ፤ ሙሉ በሙሉ ቪሲዲ ሲሆን 585 ሺ ብር እንደወጣበት ድምፃዊው ተናግሯል፡፡ አልበሙ የከፋ ማህበረሰብን ቋንቋ፣ ባህል፣…
Rate this item
(1 Vote)
ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ፣ በአበበ አካ በተጻፈው ‹‹የቤልሆር ሹመኞች›› የተሰኘ መፅሐፍ ላይ ውይይት ያካሂዳል። ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የቋንቋ መምህሩ አቶ ይድነቃቸው አለሙ ናቸው ተብሏል። ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፣ ፍላጎት ያለው ሁሉ በፕሮግራሙ…
Rate this item
(0 votes)
 የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር “የሂስ ጥበብ ሂደት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ ዛሬከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ያቀርባል፡፡ በጥናቱ ላይ በርካታ የስነ ፅሁፍ ባለሙያዎች፣ ደራሲያንና አንባብያን ተገኝተው ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል፡፡ በውይይቱ ፍላጎት ያለው ሁሉ እንዲገኝና ሀሳብ እንዲያዋጣ ደራሲያን ማህበር ጥሪ…
Page 2 of 190