ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
በኤልያስ አበራ የተዘጋጀውና ‹‹ኤላይጃ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው መሰረታዊ የቻይንኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ነገ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መፅሀፉ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በቻይንኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀ ሲሆን መሰረታዊ የቻይንኛ ቋንቋ መማሪያ ቃላትን፣ የመኪናና የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ ስሞችን፣…
Rate this item
(1 Vote)
ድምፃዊ ሙሉቀን ዳዊት፣ ቃቆ ጌታቸውና ብስራት ሱራፌል በጋራ ያቀነቀኑበት ‹‹መንገደኛ›› የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ ቀረበ፡፡ ግጥምና ዜማው በዓለማየሁ ደመቀ፣ በሙሉቀን ዳዊት፣ በጃሉድና በብስራት ሱራፌል የተሰራ ሲሆን ሙዚቃውን ያቀናበረው ካሙዙ ካሳ ነው ተብሏል፡፡ ‹‹መንገደኛ››ን ጨምሮ 13 ዘፈኖች በአልበሙ መካተታቸውም ታውቋል፡፡…
Rate this item
(1 Vote)
በደራሲና ዳይሬክተር ስንታየሁ አባይ የተሰራውና በአቢሲኒያ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ‹‹ኑርልኝ›› ፊልም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ ለእይታ መብቃቱን አዘጋጆቹ ገለጹ፡፡ የቤተሰብ ድራማ ዘውግ ያለው ፊልሙ፤የወላጆች አለመስማማት የሚያመጣውን ጦስ፣ የቸልተኝነት ውጤትንና የአባትና ልጅን የጠለቀ ፍቅር ያስቃኛል ተብሏል፡፡ በፊልሙ ላይ ሰለሞን ሙሄ፣ ሄኖክ…
Rate this item
(0 votes)
የገጣሚ ሄኖክ ስጦታው ሶስተኛ ስራ የሆነውና ‹‹መንገድ›› የተሰኘው የግጥም መድበል ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ገጣሚው የተለያዩ የህይወት ፍልስፍናዎቹን ያሳየባቸው 64 ያህል ግጥሞች የተካተቱ ሲሆን በመፅሀፉ ጀርባ ‹‹ጠፈጠፍ›› በሚል ርዕስ ገጣሚ አበባ ብርሃኑ በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ግጥሞቿን በጋራ አሳትማለች፡፡ በመቶ ገፅ…
Rate this item
(1 Vote)
የገጣሚ ትዕግስት ማሞ ሶስተኛ ስራ የሆነው ‹‹የጎደሉ ገፆች›› የግጥም መድበል ከነገ ወዲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በማህበራዊ፣ በፍቅርና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 23 ያህል ግጥሞችን የያዘው መፅሐፉ፤87 ገጾች ያሉት ሲሆን በ45 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በምርቃት…
Rate this item
(0 votes)
በምግብ ዝግጅት ባለሙያዋ አዝመራ ካሳሁን የተፃፈውና ከ6 ወር ህፃን፣ ት/ቤት እስከ ሚቋጠር የልጆች ምግብ አዘገጃጀት ያስተምራል የተባለው “ከቤት እስከ ት/ቤት” የተሰኘ የህፃናት ምግብ አዘገጃጀት መፅሐፍ ዛሬ በካሌብ ሆቴል ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ ይመረቃል፡፡ በ51 ገፆች የተቀነበበውና በ50 ብር ለገበያ የቀረበው መፅሀፉ፤…
Page 9 of 186